ክቡራን wrote:ምክሩ አንተ ሾካካ!! :D እየነካካህ ታናግረኛለህ..አይደል..አንተ የምትፈልገው በሰንበት ክፉ ተናግሬ ሀጢያት እንድገባልህ ነው እይደለም?? !! እኔ ደሞ ዝም!! እንኴን ቡድናችን አልተሰለፈ አልልም:: :lol: በነገራችን ላይ ያለምን ዋንጫ ጀርመን ያነሳል:: አላህ ገለጸልኝ:: ክቡራን ምን አለ በል ..! ጀርመኖች የኴስ ጥበብ ወይም እኛ ድሮ ሜዳ ላይ እንደምናደርገው አብዶ የላቸውም:: አብዶ መስራት ለቲፎዞ ወይም ለተመልካች እንጂ ለቡድን የሚያመጣው ቡዙም አስተዋጾኦ የለውም:: ሜሲ አብዶ ያበዛል:: ግን ሲለው ፍትፍት የሆነ ኴስ እየፈተፈተም ያቀባላል:: እኔ በስድስት ቦታ አንዳንዴም በዘጠኝ ቦታ ሆኘ ሳከፋፍል የነበረውን ትዝታዬን ይቀሰስቅስብኛል ይሄ ሜሲ!! ዔጭ! :lol: ግን እኔ በቀኝ እንጂ በግራ እግሬ እንደሱ መጫወት አልችልም:: ቡዙ ተጫዋች ወይም ተከላካይ በቀኝ እግሩ ስለሚጫወት በቀኝ በኩል ባለው አእምሮው የሚያስብ ይመስለኛል ለዚህ ነው እንደ ሜሲ ያሉ አጥቂዎች ለተከለካይ የሚያቃጥል ሚጥሚጣ የሆኑት:: በግራ ኴስ ይዞ ለሚመጣባቸው አእምሯቸው ዝግጁ አይደለም::
... እንዳልኩት ጀርመኖች ጋ አብዶ የለም...ለውጤት የሚያበቃ ከብረት የጠነከረ የኴስ ዲሲፕሊን ግን እነሆ ጀርመኖች ጋ አለ....
ክቡራን ነኝ:: ከፍቅሩ ኪዳኔ የስፖርት ዘገባ ስር ሆኜ የብራዚልን ሜዳ ከሚቃኙ ወገኖች ተርታ..ከሀሳዊ መሲሁ ጋዜጠኛው ዲጎኔ ወዲያ ማዶ:: :lol:
መልካም ሮመዳን ይሁንልህ::
ክቡሻ ሮመዳን እግር ጥሎህ እንግዳዬ ብትሆን የፈጥርን ሥርዓት በተምርና ሳምቡሳ በሾርባና ሸፉት ታጣጥመው ነበር:: ሙክክ ያለ የኢስላም ሥጋ: በሽትኒ: በዝግኒ ...ሁለተኛ ቴረሪስት የሚባል ነገር ካፍህ ሲወጣ ትን እንዲልህ አድርጌ :D :D :D
ዋንጫዉን ጀርመን አይወስድም:: ከአርጀንቲና ና ብራዚል አንዱ ያነሳል:: ጀርመኖች ለመጨረሻው ማጣሪያ በመድረስ ሪከርድ የሚስተካከላቸው የለም:: ዘንድሮ ግን አልታዩኝም እልሃለው::
እኔ ምልህ ቂቂቂ ስድስትና ዘጠኝ ቁጥር ነበርክ እንዴ? ክቡሻ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፎቶግራፍህ ላይ የለበስከው ማልያ ሁለት ቁጥር ቁልጭ ብሎ ይታያል:: ምንድነውሱ? ወይስ ፎቶግራፈሩ አድሃሪ ነበር ልትል ነው? :D :D :D .....ሠላም ሁን::