ETHIOPIAN FUN & ( .) ( .)

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

Re: :-)

Postby ደጉ » Sat Jan 04, 2014 5:29 pm

ጌታ wrote:ደግሻ - የማያድግ ሕዝብ ከመቶ ዓመት በፊት በተደረገው ወይም ባልተደረገው ይናጫል ብሏል ታላቁ ሌኒን:: ከሁሉም የሚገርመው ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ዓለም በ10 ዓመት ውስጥ የምታደርገው ዕድገት በጥንት ጊዜ በ1000ም አይደረግም ነበር:: እና እኛ የዚህ ዘመን ሰዎች ከመቶ ዓመት በፊት የነበሩን ሰዎች ለመማሪያ ከመጠቀም ውጪ እንዴት እንደዘመኑ ሰው አላሰቡም ብለን ጀጅ እናደርጋለን?

ከላይ ለጠየቅኸው ጥያቄ ስለ እስራኤል አገር ባላውቅም እኔ በግሌ መርሰዲስ እና BMWን ቦይኮት ያደረኩት ሳልወለድ ጀምሮ ነው - ዋናው ምክንያቴ ድህነት ሲሆን ሁለተኛው ያቅም ማነስ ነው ቂቂቂቂቂቂ

...ጌታ ወንድማችን አሽቃባጭ ሆዳሙን ተውና ...ቁም ነገሩን በጥሩ መልክ መልሰህዋል አመሰግናለሁ.. :D
... ወደ ሪች ልመለስ ...እኔ አዎ አዝማሪዎችም ሆኑ ማንም ሰው በነጻ ህሳቡን የምግለጽ መብት አለው ብዬ አምናለሁ....ህሳቡን ሲሰጥ ማሰብ ያለበት ህሳቡን እሚሰጠው ሰው እንጂ እኔ ወይም አንቺ አይድለሽም...ብዙ ጊዜ በየ ዌብ ሳይቱ እሚሽከረከረው ይሄ ወሬ መስመሩን እየለቀቀ እየሄደ ነው ....እኔ ሚኒሊክ በ ኦሮሞ ላይ ፈጸሙት ለሚባለው ሆሊ ዋር ነው እሚል የትም አንብቤ ወይም ከማንም ባለ ታሪክ ሰምቼ አላውቅም...ሚኒሊክ ሆሊ ዋር አድርገው ቢሆንና እስላም እሚባልን ህብረተሰብ ድራሹን አጥፍተው ቢሆን እኔ አንደኛ ደጋፊያቸው ነበርኩ....ግን የሰማሁት አድዋ ላይ ጊዮርጊስን ይዘው ወተዋል እሚባል ነው...እሱም በወቅቱ የመሳሪያ እጥረት ስለነበራቸው እና ጊዮርጊስ የያዘው ጦር ተጨማሪ እንዲሆን በማሰብ ይመስለኛል...ስለ ጦርነቱ የታሪክ እውቀት ባይኖረኝም...:-)
...ከዛ ውጪ በሌላ መገናኛም እንደ ተወያየነው ቴዲ አፍሮ (ጆሮ) በ እሱ ፐርሰናሊቲ ላይ እኔ ምንም ጥላቻ የለኝም ከድሮም...ሆኖም ግን ድምጹ አይመቸኝም ..ከዛ ውጪ በግል ምንም በድሎኝ አይደለም... ልጁ ኢንተርቪው ላይ ሰጠ ለተባለው መልስ ..እሱን እሚመለከት እና የ ኦሮሞ ህዝብ የሱን ኮነስርት እንዳያይ ወይም አልቡን እንዳይገዛ ቦይ ኮት ማድረግ ሲቻል ...በደሌ አጥጠጡ ብሎ የበደሌ ቢራ ቀጥሮ እሚያሰራቸውን ከ እነ ቤተሰቦቻቸው ስራ እንዲያጡ ለማድረግ መሞከር ትክክል ነው እሚለኝ ካለ 1 አለቀበለውም በዛ ላይ አስተሳሰብ የጎደለው ነው ብዬ አምናለሁ...
....አሁንም እኔ በበኩሌ ሚኒሊክን እምቃወምበት ምንም ምክንያት የለኝም ....በሚኒሊክ ጊዜ አልነበርኩም..አባቴም አልነበረም ...:) ታሪክም ስማር መንግስት ያወጣውን የታሪክ መጽህፍ ነው የተማርኩት...ታሪካችንም በ አብዛኛው በ ውጪ ዜጎች የተጻፈ ነው...እስከማውቀው ደርስ ሚኒሊክ እንዲህ አደረጉ እንዲህ አላደረጉም እሚል ነገር አጋጥሞኝ አንብቤ አላውቅም... ስራዬ ብዬ ስለ ታሪክ ተጨንቄ እማነብ ሰው አይደለሁም ግን ማወቅ ያለብኝን ያክል ለማወቅ እሞክራለሁ...:)
.....ሚኒሊክ ዘር ለይተው ገድለው ከሆነም ዛሬ ላይ ሆኔ አልፈርድባቸም....ምክንያቱም እኔ ዛሬ በማስብበት ጭንቅላት ሚኒሊክ ማሰብ ነበረባቸው ማለት አልችልም...አይደሉም ሚኒሊክ ..ደርግ 1 ጄኔሪሽን የጨረሰው....ወያኔም አላስፈላጊ በሆነ ጦርነትና የፖለቲካ ተቃዋሚዎችን በተለያየ መንገድ በመግደል እዚህ እንደ ደረስን እያየን ነው...ዛሬ እሚያደርጉትን ነው ማስቆም እንጂ ሚኒሊክ በወቅቱ ማድረግ አለብኝ ብለው ያመኑትን አደርገው አልፈው ለዛሬ ደርሰናል....በወቅቱ አልገዛ ያለውን ይገድሉ ነበር ግዞት ይልኩ ነበር ከታሪክ ነው እምንሰማው.....ከዛ ውጪ ግን ወሬ እና ነገር አራጋቢዎች ያራግቡ....እኛ ያው ሲፈጥረን የተሰራውን ጥሩ ነገር ትተን ትንሽም ብትሆን መጥፎዋን ማጋነን እንወዳለን እንጂ...ስለ ሰሩት ጥሩ ስራም እሚያከብራቸው ህዝብ ከየትኛውም ዘር ከፈለገ የሳቸውን 100ኛም ይሁን 200ኛ ቢያከብር በበኩሌ ምንም እምቃወመው ነገር የለም....እኚህ ሰው በ ውጪ ወራሪ እንዳንገዛም ተዋግተዋል...:) ኦሮሞም ሆነ ሌላው ከሚኒልክ ጋ ተዋግቶ በጅግንነት ያለፈ ካለም ...ተዋግቶ ያለፈ ጀግና ተብሎ ሊከበርለትም ይችላል...መታሰቢያ እንጂ :)
.....ለሁሉም ወደ ሁዋላ እየሄድሽ በህሳብ ከማለም ቀኑ እንዳይመሽብሽ ትናንት ዛሬ አይደለም ብሎ ዘፍኑዋል ዘፋኙ....እና ስለ ትናት ሳይሆን ስለ ነገ እናስብ ...: :D
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4527
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

Postby ወርቅነች » Sun Jan 05, 2014 3:14 am

ቅቅቅቅ....በሰው መልከ የተፈጠረ ከታላቁ የዋርካ ---- አህያ ዛሬም ሆነ ነገ ምንም አይነት መሻሻል አይጠበቅም...እሚመገበው ሳር ሰለሆነ ታላቁ የዋርካ ---- አህያ የሚሰለጥነው ፋንዲያ ቾክሌት ሲህን ነው ትላለች ጀሚላ ከቸርል ጎዳና :lol: :lol: :lol: :lol:
ወርቅነች
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 967
Joined: Sun Oct 03, 2010 10:05 am

:-)

Postby ደጉ » Fri Jan 10, 2014 3:58 pm

....አምስቱ ቡችሎች...

....አምስት እሚሆኑ ቡችሎች ያሉት አንድ ሰው ነበር....እሱ ከሞተ በሁዋላ ቡችሎቹ ቤቱንና ንብረቱ የነበረውን ሁሉ ለሚቆጣጠሩለት ሰዎች በሞት ምክንያት አሳልፎ ሰጠ....
...ያሰማራቸውንም ውሾች የ እሱን ቤት ያያዙት ባልቤቶች ትሽ እያበሉዋቸው ከቀድሞው ባልቤታቸው የበለጠ ብዙ ያስጮሁዋቸው ጀመር...
....ቡችሎቹ የተለያየ ቀለምና የ እድሜ ልዩነት ያላቸው ቢሆኑም...በ ውሻ እድሜ ግን ሊሞቱ ሩብ ጉዳይ የቀራቸው ናቸው...እሚያሳዝነው ግን ቡችላ እንደ ሆኑ ውሻ ደረጃ ሳይደርሱ ለሞት መቃረባቸው ነው...
...አልፎ አልፎ ባንድ ሁለቱ ላይ የውሻ በሽታ (ውሻን) እሚያስብድ አይንነት እንደ ያዛቸው ምንም ጥርጣሬ የለኝም...ግን የ እንስሳት ክሊኒክ ወስዶ እሚያሳክማቸው ባለምኖሩ በ እብደት ይሞታሉ ብዬ አስባለሁ..አለዛም ሰው ቀጥቅጦ ይገላቸዋል...
....እርግጥ ትንሽ እሚበላ እየተጣለላቸው ከሚጮሁ ቡችሎች ሰው ማሰብ እሚባል ነገር ባይጠብቅም....ቡችሎች ከቡችላነት ጊዜ ጀምሮ ውሻ እስከምሆን ሲደርሱ በተለያየ አገር ስልጠና እየወሰዱ ከተራ ፖሊስነት እስከ ባለ ማእረግ የደረሱ አሉ...የፊል አክተርም ሆነው እሚኖሩ አሉ...
...እኔ እማውቃቸው እነዚህ 5 እሚሆኑ ቡችሎች ግን አልታደሉም..ያልታደሉት ለማስልጠን ሳይሞከር ቀርቶ አይደለም....ችግሩ ግን ከመብላት እና በየቦታው በሚመለከታቸውም በማይመለከታቸውም ከመጮህ ሌላ መስልጠን አልቻሉም....ከዚህ በሁዋላም በዚሁ ይሞታሉ እንጂ ስልጣኔ እና እነሱ በምድር ሳይገናኙ ነው እሚያልፉት....
...አንድ ውሻ ሆነ ሌላ እንስሳ እሚነከስ ቦታ ለይቶ ይነክሳል...ቡችላ ግን ሁሉ እሚነከስ ሰለሚመስለው ሁሉ ላይ ይጮህል ...ሊነክስምይሞክራል...ችግሩ ግን ከመጮህ ሌላ ጥርሱ ሰው አይጎዳም...ከ አለቆቻቸው እሚሰጣቸውንም ጥርስ ስለማይኖራቸው በፈሳሽ መልክ ነው እሚበሉት....ባልቤቶቻቸው እንዲያገለግሉዋቸው የፈለጉትም በ ጩህታቸው ብቻ እንጂ ከዚህ በሁዋላ ምንም እንድማያመጡላቸው ያውቁታል...:)
....በጣም ደስ እሚለው ግን ቡችሎቹም አላቃቸውን መርጠው አለቃቸውን እየተከተሉ እሱ የጮህበት ሁሉ እየሄዱ ይጮህሉ.. :lol:
...እስካሁን ባለው አንዱ ቡችላ ሊሞት ነው መእለኝ ትንሽ ተዳክሙዋል...ሌሎቹም ቢሆኑ ጭንቀት የቀን ተቀን ችግራቸው ሆኑዋል....የ አለቆቻቸውን የግለት ቴምፕሬቸር በ ቡችሎቹ መለካት ብቻ ሆኑዋል ጊዜ ሲኖረኝ ስራዬ.. :lol:
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4527
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

Postby ጌታ » Fri Jan 10, 2014 7:52 pm

ደጉ እኔ የእንስሶች ነገር እንደማይሆንልኝ እያወቅህ እንዲህ ዓይነት አሳዛኝ ታሪክ መለጠፍህ አሁን ደግ ነው?
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3083
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby ደጉ » Mon Jan 13, 2014 2:16 pm

ጌታ wrote:ደጉ እኔ የእንስሶች ነገር እንደማይሆንልኝ እያወቅህ እንዲህ ዓይነት አሳዛኝ ታሪክ መለጠፍህ አሁን ደግ ነው?

ቅቅቅቅ...ቡችሎቹ የግባቸው ቀን ይገድሉህል መቼም.. :lol:
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4527
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

:-)

Postby ደጉ » Tue Jan 14, 2014 3:00 pm

... :D ይቅርታ ገና ልጽፍ ሳስብ ሳቄ መጥቶ ነው:: ...ሰሞኑን የነበረው ጸር አፄ ሚኒሊክ ቱል ቱላ ጋብ ያለ ይመስላል በ ፋናቲክ እስላም ኦሮሞዎች አካባቢ....ይልቅ እኛ ፍየ በገር ገር እናትውን...እንድሚባለው እኛም በግርግር ስለ ንጉስ አጼ ሚኒሊክ የበለጠ ለማወቅ ቻልን....
...ሚኒሊክ 6 ሚሊዬን የኦሮሞን ህዝብ ፈጁ እያሉ አፋቸው እንደ ጣቃ ሲቀደድ የነበሩት ...ኢትዮጵያ በወቅቱ ከነበራት 7ሚሊየን ህዝብ ጋ ያለቀው አለመመጣተኑ እነሱ ያው ግባ ያለው በ አርባ ቀን አትግባ ያለው በ አርባ አመትም አይገባውም እንደሚባለው በአርባ አመት ከገባቸው ነው..ኦ! ይቅርታ ለካ ከመቶ አመት በሁዋላም ሳገባቸው ቀርቶ እስከዛሬ ይጨቃጨቁ የለም.. :lol:
...እነሱ ታላቁ ንጉስ ሚኒሊክ ጡት ቆረጡ በሚሉበት ወቅት...እሳቸው አሜሪካን አገር ኢንቬስት ያደርጉ ነበር ተብሎ ጋዜጣ አሳዩን.. :lol:
....በነገራችን ላይ አይድለም ሲዳሞ..ኦሮሞ...አሩሲ ..የነሱ ጡት እና ብልት ሊቆረጥ ቀርቶ ዋናዎቹ ጡትና የወንድ ብልት ሰላቢዎች እነሱ ነበሩ:: ደርግ በ አጉል በህል ማስወገድ በሚል ዘመቻ ባብዛኛው የተቀነሰ ሲሆን ...አሁን አሁን አልፎ አልፎ ሳይኖር እንድማይቀር እገምታለሁ...ሚኒሊክ ጦርነት ማድረጋቸው እና አልገብር ያለውን ማስገበራቸው ግን ወቅቱ እሚጠይቀው ግዴታቸው ነበር ..በሚገባ ተወጥተዋል.. :D
....ሚኒሊክ አገር ሸጡ እየተባሉም ይታማሉ ...አቅም በማጣት አገር መሸጥ እና ዛሬ እንደምናየው አቅም እያለው በፍርህት እና ለሌሎች አገሮች ሎሌ በመሆን አገር መሸጥ ይለያያሉ...;) ሚኒሊክ አቅማቸውን እሚያውቁ ብልህ መሪ እንደነበሩ ማንም እማይክደው ነው...አይደለም በዛን ጊዜ ከዚህ በሁዋላ እሚመጣ ምንም እሚተካቸው አይኖርም::
....ትናትና በስልክ ከ ጄኖሳይድ ሚኒሊክ. ምናምን ከሚል ሩም ...አጼ ሚኒልክን ለቀቅ አድርገው ..አበበ በቂላ ላይ መግባታቸውን ሰማሁ...ቅቅቅቅ አበበ ቢቂላ በባዶ እግሩ ሮጦ ያገሩን ባንዲራ በኦሎምፒክ እንዲውለበለብ ያደረገ የ ኦሎምፒክ ጀግና ነበር ..በክብርም ያረፈ ነው::
...አሁን እነሱ እንድሚሉት ..አማራ አበበ በባዶ እግሩ ሮጠ እያሉን ጫማ እንዳንገዛ ያደረጉን እነሱ ናቸው...እነሱ ጫማ አድርገው የኛ ዘመዶች እስካሁን በቦቲ ናቸው ብለው ማማረር ጀምረዋል.. :D
....ውድ የ ያልገባችሁ ወይም የማይገባችሁ የ ኦሮሞ ልጆች ...አበበ በወቅቱ ፌዴሬሽኑ ጫማ ሰጥቶ ነበር...አቤ ግን የሰጡት ጫማ ፍጹም አልተመቸውም ...ለዛም ሩጫውን ከማቆም ብሎ ያን አዲስ ጫማውን አውልቆ በ እግሩ ሮጠው...ታሪኩ ይሄ ነው...ጫማ ላለማድረጋችሁ አማራ ምንም ተጠያቂ እሚያደርገው ነገር የለም....ሌላ ምክንያት ፈልጉና ደግሞ እንስማው...

ውድ ወንድማችሁ ደጉ .

ፊርማ :D
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4527
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

:-)

Postby ደጉ » Fri Mar 21, 2014 7:03 pm

ሰላም አባሎች :)

......በደንባራ በቅሎ ቃጭል ተጨምሮ እሚል ነገር ትዝ ብሎኝ ነው... :D አዘር ባጃን ሰለነበርኩ ዋርካ ዝር ማለት አልቻልኩም ነበር ...ግን ደስ እሚለው ማንም የት ጠፋህ ብሎ የጠየቀ የለም ...ልክ እኔም እንደ ዘጋሁዋችሁ... :D
.... በመህል የተለያዩ የአለም ወሬዎች እየስማን አልፈናል....የ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ኮ-ፓይለት የአየር መንገዱን አይሮፕላን ጠለፈ ሲባል የተገረመ ብዙ ሰው ነበር ..እናነትን አላልኩም በ አካል እማውቃቸውን ማለቴ ነው...ስለ እናንተ አያገባኝም....:) ፓይለቱ ተዘጋጅቶበት ያን እንዳደረገ ምንም ጥያቄ የለውም....ያደረገበት ምክንያት ደግሞ ጥገኝነት ሰለፈለገ ብቻ አይደለም...አገር መርጦ በ እግሩ መግባት ይችላል...ያን ለምን አደረገ ደግሞ ሌላ ጥይቄ ነው....መልሱ ግን በ አየር መንገድ ውስጥ ያለው የበከተ አሰራር ውጪ አይሆንም..... አገር ውስጥ ያያችሁ ካላችሁ ህግ የለም ..መንግስትም የለም ...መንግስት ከድሮም እንደ አጀማመራቸው ወንበዴዎች ናቸው...ልዩነቱ ድሮ ጭካ ሆነው በውንብድና ነበር እሚዘርፉት ..አሁን ግን በመንግስትነት ስም ..ስም ነው ያልኩት ..እሚዘርፉት....አሳ እሚገማው ከጭንቅላቱ ነው እንድሚባለው ጭንቃልቱ የሸተትው አሳ ሌላውንም አግምቶ ሁሉም በአቅሙ ዘራፊ ሆኑዋል....በቃ በቀላሉ መቀማማት ነው...ብዙ ጊዜ እሚገርመኝ ነገር ከ አንድም ሶስት አራት ሰዎች አጋጥመውኛል የተሸጠላቸውን መሬት እንደ ገና ለሌላ የተሸጠባቸው አሉ....ማንንም መክሰስ እና ለፍርድ ማቅረብ አይቻልም...ሁሉም ሌባ ስለሆነ ይተባብራል... ከ 5ችወር በፊት እዛ እያለሁ ያየሁትና የታዘብኩት በጣም ብዙ ነገሮች ናቸው....አገር አለኝ ለማለት እሚያሳፍር ነግር ነው እሚታየው...
....አንድ ጊዜ በአይኔ ያየሁትን ላጫውታችሁ ...ይሄ የሆነው ውጪ ጉዳይ ሚንስትር ቢሮ ነው....ከአንድ ጉዋደኛዬ ጋ ለጉዳይ ነበር የሄድነው...እናም ሰልፍ ላይ እያለን ..የሆኑ ነጮች መጡ ...እዛ ያለው ወያኔ የመደበው ዘበኛ ከፊት የነበረውን እድሜው በግምት ወደ ህምሳዎች የሆነን ሰው...ከሁኔታው ውጪ የተምማረና እሚኖር እሚመስል ሸሚዙን ከትከሻው ይዞ አንስቶት ካለበት አንስቶ ነጮቹን እሱ ቦታ ከፊት አስቀመጣቸው....አያሳፍርም...? እስኪ እናንተ እዛ ቦታ ብትሆኑ ምን የስማችሁዋል...? ያ ደንቆሮ ዘበኛ ያልገባው ነጮቹ እሱን እንደማያመሰግኑትና ጭራሽ የራሱን ዜጋ እንደዛ በማድረጉ ይታዘቡታል..? ትክክለኛ የሆነ አገልግሎት አይሰጣቸው አይደለም...ግን እንደ አመጣጣቸው...የጣLኢያን ባንዳ የነበሩ አብቶቻቸው ይሄን ነው ያስተማሩዋቸው ...? :D
....ከዛ ብዙም ሳንቆይ ደግሞ በሌላ ቀጠሮ እዛው ሄደን ነበር ...መቼም ጉድ እይ ብሎ መሆን አለበት ቡድህ :) የዛን ቀን ደግሞ አንዱን ተገልጋይ ይዘው ዘበኞቹ ይደበድቡታል...ሰውየው በህግ አምላክ እያለ ይጮህል ያ ሁሉ ባለ ስልጣን ያለበት ቢሮ አንድ ሰው እንኩዋን ወጥቶ እሚያስቆማቸው የለም....ይሄ ነው ነው ያለው መንግስት:: እንግዲህ ይሄ በአይን ያየነው ነው ያላየነው ስንት ነገር ይኖራል...
...አንድ ጊዜ ደግሞ ቦሌ መንገድ መንገድ እሚያቁዋርጡ ህጻናት ነበሩ ..እናም እዛ የነበረው ትርፊክ ፖሊስ መኪኖቹን አስቁሞ ልጆቹን ሲያሳልፍ ...አንድ ሮቨር አይነት መኪና የቤተ መንግስት ታርጋ ያለው ግን ሳያቆም ልጆቹን ሊያገኛቸው ጥቂት ነበር የቀረው...ይሄ ነው እንግዲህ ስልጣኔውም መኪና መንዳትም ወይ ህግ ማክበር ህጉ ለወጣለት ህዝብ እንጂ ስልጣን ላይ አሉትን ከ እነሹፌሮቻቸው እንደማይመለከታቸው ነው...:)
....አንድ መጽህፍ ሰው ገዝቶ ሰጥቶኝ ነበር ...በሙት መንፈስ አገር ሲታመስ እሚል...ፈልጋችሁ አንብቡት ሁሉንም በግልጽ ቆንጆ አድርጎ የተጻፈ እና ምን እየተካሄደ እንዳለ ሊያስረዳችሁ ይችላል....መጽህፍዋ እንደ ትንሽነትዋ ሳሆን ብዙ ነግሮችን የያዘች ነች ...:)
...ያን ስታነቡ አዎ ኖሮ ህይወት ያለው ሰው ስለሌለ ነው ለካ አገሪቱ በሙት መንፈስ እምትመራው ትላላችሁ....ለነገሩ ስልጣን ላይ ያሉት እኮ በበረህ ኑሮ የነፈዙ ናቸው በምን ተአምር አገር መምራት ይችላሉ...መማር ቢችሉ 21 አመት አይደለም 2 አመት በቂ ነበር... :D
...ሶርያ ውስጥ ባላፈው አንድ ሪፖርት ሳይ....ሶርያ ውስጥ ያሉት ህጻናት ጉዳይ ዩኒሴፍን ጨምሮ ብዙ ያሳሰባቸው ድርጅቶች አና ዜጎች ነበሩ....በዚህ ወቅት ያሉት ህጻናት ትምህርት መማር አልቻሉም በዛም ምክንያት የወድፊትዋ ሶሪያን እሚረከብ የተማረ ትውልድ አይኖርም እሚል በጣም እያሳሰባቸው ነው....ስለ ሶሪያ እንድታውቁ ፈልጌ አይደለም ..ግን ወደ እኛ አገር ስንመጣ .... መንግስት ነኝ እሚለው ቡድን እያለ ወጣት ተማሪዎች በከተማና ክፍለ ህገር ለ ሴክስ ገበያ መቅረባቸው ነው ...አንድ ጊዜ በደርግ ወቅት ፒያሳ አካባቢ አንድ አበሻ ወንድ እና ሶስት ስቶች አብሯቸው ደግሞ 1 ነጭ አብረው ይሄዱ ነበር ቀን 10ሰአት አካባቢ ነበር እና ፖሊስ ያዛቸው...ለምን እንደተያዙ ስንጠይቀው ፖሊሱ ወንዱን ከነጭ ጋ እንደ አገናኝ አድርጎ ስለጠረጥረው ነበር ..ነገሩ ግን እንድዛ ሳይሆን ሁሉም አብረው እሚሰሩ ለ ቡና አንድ ላይ ወጥተው ነበር...በአጋጣሚ ደግሞ አንዱዋ አባትዋ ኮለኔል የነበሩ ነበሩ ...ፖሊሱም ይቅርታ ጠይቆ ተዋቸው...ያ ፖሊስ ትክክለኛ ነገር ነው ያደረገው ..ዛሬ እንደዛ አይነት ነገር የለም:: ወዴት እያመራን ነው ለሚለው እንኩዋን በ ወያኔዎቹ ጭንቅላት የተማሩትም መመለስ እሚችሉ አይመስለኝም..መስተካከል አለበት እንድምትሉ አምናለሁ ...ሰዎቹ በ ወጉ ገና አገር መምራት እንኩዋን አልቻሉም . :D እየተደናበሩ ነው ቅቅቅቅ
...እስኪ ትንሽ ልረፍ ደግሞ ....:)
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4527
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

Postby ጌታ » Fri Mar 21, 2014 7:22 pm

ደግ ሰው አልተናገርኩም እንጂ መጥፋትህስ አሳስቦኝ ነበር:: እንኳን በሰላም ተመለስክ::

ስለአዘርባጃን አሪፍ ኦብሰርቬሽን ነው ይዘህልን የመጣኸው:: እስቲ አረፍ በልና ጨመርመር አድርግልን...........
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3083
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

:-)

Postby ደጉ » Fri Apr 04, 2014 1:14 pm

ጌታ wrote:ደግ ሰው አልተናገርኩም እንጂ መጥፋትህስ አሳስቦኝ ነበር:: እንኳን በሰላም ተመለስክ::

ስለአዘርባጃን አሪፍ ኦብሰርቬሽን ነው ይዘህልን የመጣኸው:: እስቲ አረፍ በልና ጨመርመር አድርግልን...........

... :D ሰላም ጌታ ቃላትክሮባትህን (የቃላት አክሮባትህን) ተረድጀዋለው ...ስለ አዘር ባጃን ባወራህ ደስ ይለኝ ነበር ..ግን የነበርኩበት በረህ ስለነበር እሚወራ ነገር የለውም ...ሊወራ እሚችለውም ነገር እንኩዋን ሚስጥር ነው ... :D
....ለነገሩ ወደ ኢትዮጵያ ከመሄድ አዘር ባጃን በጣም ሳይሻል አይቀርም ....ኢትዮጵያ ውስጥ እንደ ስርአቱ ህግና መስመር እማይጠብቅ የትራፊክ ችግር አታይም ..ከምር ያዲስ አበባን የትራፊክ ሁኔታ አይተህ ..መንግስት ነኝ እሚለውን ስታይ አንዱን ካንዱ ምንም እሚለየው የለም...ሳይሻሻሉበት ያለፉት 21 አመታት እዚህ አንድ ልጅ ተወልዶ ዮንቨርሲቲ የመጨረሻ መዳረሻው ነው....ማ ምን እንድሚሰራ አያውቅም ...ነጋዴው ዋጋ እንደ ፈለገ ይጨምራል ...ለምሳሌ በፊት ቡና በወተት ብትጠጣ በውህ ብርጭቆ 60 ሳንቲም ወይ ብር ክህያ ልትከፍል ትችል ይሆናል ብንል ..ዛሬ ብርጭቆው ያው ሆኖ 15 ብር ብትከፍል አግባብ ነው ልትል ትችላለህ እሱም አግባብ ባይሆንም...ግን በፊት ሻይ በምትጠጣበት ስኒ 15ብር ሲሸጡልህ መንግስት ነኝ እሚለው ክፍል ቁጭ ብሎ ያይልህል...ከዛም ብሶ ቫት ትጠየቃለህ...አያስቅም..? እንዳያስለቅስህ ደግሞ አንተ እኮ ሆደ ባሻ ሆነህል...:)
....እስኪ ለሁሉም አትጥፋ እኔም አፍጋኒስታን ከመሄዴ በፊት ብቅ ማለቴ አይቀርም...
.....አንዱ ባለ ትዳር ጉዋደኛውን ሊጠይቅ ይሄሄድና እዛው ሲጫወት አምሽቶ ወደ ቤቱ ሊሄድ መኪናውን ሊያስነሳ ቢሞክር መኪንው አልነሳ ትላለች ...ሁሉንም ቢሞክሩ እምቢ አለች...ስልክ ለመካኒክ እንዳይደውሉ ቀኑ እሁድ ምሽት ሁሉም ነገር ዝግ ነው....መጨረሻ ላይ ባለ ትዳሩ ..እነሱ ጋ እንዲያድር ጠየቀውና ምንም አማራጭ ስለልለው ተስማማ....ቤት ውስጥ ምንም ለመኝታ እሚሆን አልጋም ሆነ ሶፋ የለም...ያለው አማራጭ አብረው 3ቱም አንድ ላይ መተኛት ነበር ...
....ሁሉም እንደ ተኙ ባልን በቅድሚያ እንቅልፍ ይወስደዋል ...ይህን እንዳየች ሚስቱ የጉዋደኛውን ትከሻ መታ መታ አድርጋው ለሴክስ ትጋብዘዋለች ...እሱም አይሆንም ይላታል..እሱዋም ግድ የለም ና አትፍራ ትለዋለች...እሱም ኖ መፍራት አይደለም እሱ እኮ በጣም የቅርብ ጉዋደኛዬ ነው አይሆናም ይላታል....በዚህ ላይ ቢነቃስ ያላታል እሱዋ አይዞህ ለሱ እንደሆን አንዴ ከተኛ በአለም ላይ ካሉት ነገሮች ሁሉ ማናቸውም ሊቀሰቅሱት አይችለም...ካላመንከኝ ከ ቂጡ ላይ ጸጉርን ንቀልና እይ ትለዋለች...እሱም እንዳለችው አደረገ ባልየው አልነቃም ..እሱም ተሻግሮት ሄዶ ስድ ነገር አደርጎ ቦታው ተመለሰ...አሁንም ትንሽ ቆይታ ትከሻውን መታ መታ አደረገችው...እሱም ኖ አሁንስ ይነቃል አላት ..ሞክረው ስትለው አሁንም ከቂጡ ላይ ጸጉር ነቀለ..ባል አልነቃም....እንደገና ስድ ነገር አድርገው ቦታው ተመለሰ....ትከሽውን እየመታች እሱም መተኛቱን ለማረጋገጥ የባልዋን ጸጉር ከቂጡ እየነቀለ 8 ጊዜ እሚሆን ካደረጉ በሁዋላ በዘጠነኛው ላይ አሁንም ትከሻውን መታ መታ ስታደርገው ...ተይ አሁን ይብቃን ይላታል...እሱዋም የመጨረሻ ስትለው ...ከባላዋ ቂጥ ጸጉር ሲነቅል ..ብላዋ ይነቃል ...ወድ ጉዋደኛዬ ሚስቴን እንደ ፈለክ ንጫት ..በፈጣሪህ! የኔን ቂጥ ግን ነጥብ መያዣ ሰሌዳ አታድርገው..:)
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4527
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

Postby ለማ12 » Mon Apr 07, 2014 4:15 pmበዘጠነኛው ላይ አሁንም ትከሻውን መታ መታ ስታደርገው ...ተይ አሁን ይብቃን ይላታል ...እሱዋም የመጨረሻ ስትለው ...ከባላዋ ቂጥ ጸጉር ሲነቅል ..ብላዋ ይነቃል ...ወድ ጉዋደኛዬ ሚስቴን እንደ ፈለክ ንጫት ..በፈጣሪህ ! የኔን ቂጥ ግን ነጥብ መያዣ ሰሌዳ አታድርገው


ቁቅቅቅቅቅቅቅ
የኔ ደግ እንዴት ያለች ጨዋታ አመጣህ:

እኔ ወንድምህ ድሮ ንጉሱ ወደቤቱ ይሂድ ብለን በምንጨፍርበት ጊዜ በወጣትነት ዘመኔ ጎበዝ ነበርኩ እያልኩ ስፎክር ጉድ አደረከኝሳ
ያኔ እኔ ጎበዙ 7 ነጥብ ነበር ባንድ ሌሊት ያስያዝኩት ታዲያ ይህን የሚሽር ጎበዝ የለም እያልኩ ስዘፍን 9 ጊዜ የሚዘልቅ ጎበዝ ተገኘ::
ይህንማ ጎበዝ እንኩአን ባንድ ሌሊት በ9 ሌሊትስ መች እደርስበታለሁ::

ቁቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1147
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Postby ጌታ » Tue Apr 08, 2014 3:19 pm

ደግሰው

ያገራችንን የዋጋ ንረት ሁኔታ ሳስተውለው አንዳንዴ ሕዝቡም እራሱ ሁኔታውን የሚያበረታታ ይመስለኛል:: ኢኮኖሚስቶች ዋጋ ሲጨምር ፍላጎት ይቀንሳል ይላሉ:: ይሕ ደግሞ በተለይ ኔሰሲቲ ባልሆኑ ዕቃዎች ላይ በደንብ መንጸባረቅ አለበት:: ጤፍ እና ሽሮ መግዛት የግድ ስለሆነ ቢወደድም ተፈላጊነቱ ባይቀንስ አይገርመኝም:: ነገር ግን የነማኪያቶ እና ሻይ ዋጋ የፈለገ ሰማይ ቢወጣ ሕዝባችን ኬክ ቤቶችን ማጨናነቁን አያቆምም:: ይሄንን ዛሬ አይደለም ድሮም በሳንቲም ደረጃም በሚጨምርበት ጊዜ ያስተዋልኩት ነገር ነው::

መንግስት ዋጋን የመቆጣጠር ኃላፊነት ቢኖርበትም ሕዝቡም ነጋዴው ላይ አቅሙን ማሳየት ቢችል ጥሩ ነበር:: ይህንን ለማድረግ ደግሞ ንቃት ያስፈልገዋል:: ጋዜጠኞቹ አርሰናል ተሸነፈ ኦፕራ ወፈረች እያሉ ሕዝቡን ከሚያደነቁሩ እንዲህ ዓይነት ነገሮችን ቢያስተምሩ ደግ ነበር::

ባጭሩ ድሕነትንም ሆነ ማንኛውንም ማኅበራዊ ቀውስ ለማስወገድ ሕዝብ መንቃት አለበት!! በየአቅጣጫው የተማረ ያልተማረን ያስተምር!

የጸጉር መንጨቱ ጆክ አልገባኝም:: እስቲ ለሚቾ አብራራልኝ -:)
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3083
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby ደጉ » Thu Apr 17, 2014 7:49 pm

ለማ ቅቅቅቅ እንዴ እረ ተው በዘጠኝ ለሊትማ ካልደረስክበት የማቆሚያ እገዛ ነገሮች ሊያስፈልጉህ ነው ማለት ነው....ዙሩ ቀርቶብህ ለነጥብ ብትሄድ ይሻላል...ድሮ በሞኝነት ያጠፋህው ጉልበት ያን ግዜ ድንችና ካሮት ´ጉዋሮህ ተከልህበት ቢሆን ዛሬ ቢጠሩት እማይሰማ ህብታም ትሆን ነበር ...:)
ጌታ wrote:ደግሰው

ያገራችንን የዋጋ ንረት ሁኔታ ሳስተውለው አንዳንዴ ሕዝቡም እራሱ ሁኔታውን የሚያበረታታ ይመስለኛል:: ኢኮኖሚስቶች ዋጋ ሲጨምር ፍላጎት ይቀንሳል ይላሉ::

...ጌታ አባባልህ ትክክል ነው ነው ግን ህዝቡ ስትል ወደ 90 ሚሊዮን እሚሆነውን መሆን አለበት...እሚገርምህ ወደ 3000 እሚሆን ዜጋ ነው አገሪቱ ውስጥ የንግዳል ግብር ይከፍላል ተብሎ እሚነገረው...አስበው 90 ሚሊየን ህዝብ ባለበት አገር 3000 ሰው...?? ከተማ ውስጥ አብዛኛው ጫት እና ሸሻ ሲያጨስ እሚውለውም ቢሆን ትናንሽ ንግድ ያለው እና እያምታታ እምኖር ደላላ ብቻ ነው ማለት ትችላለህ...:)
ይሕ ደግሞ በተለይ ኔሰሲቲ ባልሆኑ ዕቃዎች ላይ በደንብ መንጸባረቅ አለበት:: ጤፍ እና ሽሮ መግዛት የግድ ስለሆነ ቢወደድም ተፈላጊነቱ ባይቀንስ አይገርመኝም::

....ልክ ነህ እዛ እምታየው ነገር ግን ፍጹም የተምታታ ነው...ጦፍ እማ ነው ህዝቡን የያዘው መንግስት አይደለም...ቅቅቅቅ
ነገር ግን የነማኪያቶ እና ሻይ ዋጋ የፈለገ ሰማይ ቢወጣ ሕዝባችን ኬክ ቤቶችን ማጨናነቁን አያቆምም:: ይሄንን ዛሬ አይደለም ድሮም በሳንቲም ደረጃም በሚጨምርበት ጊዜ ያስተዋልኩት ነገር ነው::

...ድሮ ብዙም እኮ እንዲህ አይጨምረም እርግጠኛ ነኝ መንግስትም ይቆጣጠር ነበር ...ብዙ ጊዜ አስተውስ ነበር ዳቦ ከግራም አሳንሰው ሸጡ የተባሉ ነጋዴዎች ሲቀጡ...አሁን እንድዛ የለም መንግስት ሌባ የነበረ ነው ...ህዝቡንም ለ እንደ እሱ ላለ ሌባ ነጋዴ አሳልፎ የሰጠ ነው...
መንግስት ዋጋን የመቆጣጠር ኃላፊነት ቢኖርበትም ሕዝቡም ነጋዴው ላይ አቅሙን ማሳየት ቢችል ጥሩ ነበር:: ይህንን ለማድረግ ደግሞ ንቃት ያስፈልገዋል:: ጋዜጠኞቹ አርሰናል ተሸነፈ ኦፕራ ወፈረች እያሉ ሕዝቡን ከሚያደነቁሩ እንዲህ ዓይነት ነገሮችን ቢያስተምሩ ደግ ነበር::

....መንግስት እንዲዘርፍ ከቆመለት ነጋዴ ጋ ህዝብ ማታገል ፌር አይመስለኝም....;)
...እሚገርምህ የሚዲያው ነው ደግሞ ...የራስዋ እያረረባት የሰው ታማስላለች ይባል ነበር ...:)

ባጭሩ ድሕነትንም ሆነ ማንኛውንም ማኅበራዊ ቀውስ ለማስወገድ ሕዝብ መንቃት አለበት!! በየአቅጣጫው የተማረ ያልተማረን ያስተምር!

....አይ ጌታ የተማረ እሚባል ነገር እዛ አገር አይሰራም...ይልቅ አንድ በቅርብ የሆነ ታሪክ የሰማሁትን አስታወስከኝ...ምንጭ ካልከኝ የገዛ ጆሮዬ ....አንድ የፌድራል ደንና አካባቢ ጥበቃ ሚንስቴር ምናምን እሚል መንግስታዊ ድርጅት 5 ሰው በዳይሬክተርነት ለመቅጠር ይፈልግና ከ 15 አመት በላይ በሙያው የሰራና PHD or Masters ያላቸው እንዲወዳደሩ ይጋብዛል....በዛም መሰረት 30 እሚሆኑ ተወዳዳሪዎች ይወዳደሩና 20 እሚሆኑ ጥያቄዎችን ይፈተናሉ....ውጤቱ ሲወጣ 30 ዎቻጩም ወድቃችሁዋል ይባላሉ...አስበው እዛ ውስጥ የሙያ ብቃት ክ አንድም 2 ፒ ኤች ዲም ሆነ ማስተርስ ያላቸው ናቸው...;) ከዚህ ሁሉ ሰው 5 ይቅር 2 ወይ ሶስት ማለፍ አይችልም..? አስበው ..ያ ማለት እኮ የሙያ ሰው ጭራሽ በአገሩ የለም ማለት ነው...ነገሩ ግን በግልጽ እሚያሳየው ማስታወቂያ የወጣው ለይስሙላ እንጂ በሙያው ብቃት የሌላቸው ሰዎች ቦታውን እንዲይዙ መደረጉ ግልጽ ነው ...ይሄ ነው እንግዲህ ልማታዊ መንግስት ነኝ እያለ እሚያወራው ጥፋታዊ መንግስት ..:) አሁንም በ ሞተ ሰው ራእይ እንጂ ህይወት ባላቸው ሰዎች እማይመራ ድርጅት ነው...:) ከምር ያስቃል በቁሙ እያለ መምራት ያልቻለን መሪ እንደ ገና ሞቶ ሲመራ...ቅቅቅቅ አንድ ጊዜ አንድ መለስ ዜናዊ አህያ ተሸክሞ በጽሁፍ በአህያ ላይ አህያ እሚል ፎቶ ከፌስ ቡክ ላይ አግኝቶ ሰው ልኮልኝ ነበር ...አሁን ሳስብ የነበረው አህያዋን የተሸከመው አህያ ሲሞት...የቀረው የተሸከመው አህያ መሆኑን ሳይ ከምር ሳቄ መጣ... :lol: እዚህ ሳንቲም እየተሰጣቸው ወይ በድል አጥበኝነት አልቃሾችን ስታይ የግማው አናታቸው ከየት እንደጀምረ ታውቃለህ...;)

የጸጉር መንጨቱ ጆክ አልገባኝም:: እስቲ ለሚቾ አብራራልኝ -:)

...ጸጉር ያልው ሰው ይዘህ ከመጣህ እኔ አሳይህለሁ... :D
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4527
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

Postby ለማ12 » Tue Apr 22, 2014 11:20 am

ቁቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
እረገይ
የኔ ደግ ምንካህ ያንጊዜማ የሚአልቅ ይመስለኝ ነበር እንጂ እኔን የሚጨርሰኝ ይመስለኝ ነበር??
እሱንማ ባውቅ ኖሮ ካሮት ቀርቶ ደንጋይ ለማብቀል እሞክር ነበር:

ቁቅቅቅቅቅቅቅቅ
የሚረዳ ነገር አለ ነው የምትለው እባክህ መንገዱን ጠቁመኝ
አመት ባል በሰላም አለፈ?
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1147
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Postby ደጉ » Sun Aug 10, 2014 10:57 pm

ለማ12 wrote:ቁቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
እረገይ
የኔ ደግ ምንካህ ያንጊዜማ የሚአልቅ ይመስለኝ ነበር እንጂ እኔን የሚጨርሰኝ ይመስለኝ ነበር??
እሱንማ ባውቅ ኖሮ ካሮት ቀርቶ ደንጋይ ለማብቀል እሞክር ነበር:

ቁቅቅቅቅቅቅቅቅ
የሚረዳ ነገር አለ ነው የምትለው እባክህ መንገዱን ጠቁመኝ
አመት ባል በሰላም አለፈ?

...ለማ ሰላም ነህ ለጥያቄህ በፍጥነት ስለደረስኩ ይቅርታ...ያው በጊዜ ጉዳይ እንደሆነ ትረዳለህ መቼም...ካሮት ማብቀሉ ይሻልህል የሚል ግምት አለኝ ..ተቀራራቢነት ስላለው...አይመስልህም...ድንጋይማ ድንጋይ ነው እዚህ እንድሚጮሁት :lol:
እስኪ ይሄን ቀልድ በ አዲስ መልክ. :D ....አንድ ወጣት ያለ ግዜው ይሞትና መንግስተ ሰማይ መግባት ሲገባው ቅዱስ ጴጥሮስ ገህነም እንዲገባ ያደርገዋል ለጊዜው ...ልጁ እዛ እንደገባ የቀድሞ ጠ|ሚ መለስ ዜናዊን ያገኛል...ልጁ በመገረም...እንዴ! እርስዎ ምን ያደርጋሉ ይላቸዋል...እሳቸውም ቶሎ አሉና እረ ዝም በል! አቡነ ጳውሎስም እዚህ አሉ አሉት.... :wink: :)
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4527
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

Postby ሞጥሟጢት » Mon Aug 11, 2014 3:18 am

መጣና ..........., ፓስዋርዴን አለመርሳቴ አይገርማችሁም ?
ሞጥሟጢት
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 56
Joined: Mon Feb 28, 2005 3:37 am
Location: united states

PreviousNext

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests