ግራ የገባው ለቅሶ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ግራ የገባው ለቅሶ

Postby እቴጌይት » Fri May 23, 2014 5:36 am

በድንቁርና ጥማድ
በጽልመት ከመኖሩ
ማይምነት አውሮት
ፊደል ካለመቁጠሩ
ባልተከፈተ አስኳላ
አማርኛ መማሩ
ላስመረረው ወገኔ
ላልቅስ ወይስ ለ'እኔ'?

ዛሬ በቀነበር ጠምዶ
በአፈ ሙዝ አስገድዶ
ከቀዬው አፈናቅሎ
ቢያሻው ዘብ-ጥያ ጥሎ
ቢያሻው በጅምላ ገሎ
ከሚገዛው ሹም ይልቅ
. 'ሀውልት' ሠላሙን ነስቶት
'ጥቁር ሰው" አስቆጥቶት
ለተሰልፈው በአንባ
ለተጨቋኙ ላልቅስ
ወይስ ለራሴ ላንባ?

ለባዕዳን ሲታደል
ቅርጫ ድንግል መሬቱ
ከእልፍኙ ነቅነቅ ሳይል
አንቀላፍቶ ማጀቱ
ቃሊትና ሱሉሉታ
ለገጣፉ ሰበታ
ሸገር መጠቅለላቸው
አስቆጥቶት በሆታ
አሰልፎት በእንቢታ
በመተረየስ እርሙታ
ግንባሩን ለተመታ
ለደመ-ከልቡ ላልቅስ
ወይስ- ለራሴ ደረት ልምታ?
እቴጌይት
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 656
Joined: Sun Sep 23, 2007 10:38 pm

Re: ግራ የገባው ለቅሶ

Postby ፉኚዶ ተራራ » Sat May 24, 2014 7:33 pm

እቴጌይት wrote:በድንቁርና ጥማድ

በጽልመት ከመኖሩ

ማይምነት አውሮት

ፊደል ካለመቁጠሩ

ባልተከፈተ አስኳላ

አማርኛ መማሩ

ላስመረረው ወገኔ

ላልቅስ ወይስ ለ'እኔ'?ዛሬ በቀነበር ጠምዶ

በአፈ ሙዝ አስገድዶ

ከቀዬው አፈናቅሎ

ቢያሻው ዘብ-ጥያ ጥሎ

ቢያሻው በጅምላ ገሎ

ከሚገዛው ሹም ይልቅ

. 'ሀውልት' ሠላሙን ነስቶት

'ጥቁር ሰው" አስቆጥቶት

ለተሰልፈው በአንባ

ለተጨቋኙ ላልቅስ

ወይስ ለራሴ ላንባ?ለባዕዳን ሲታደል

ቅርጫ ድንግል መሬቱ

ከእልፍኙ ነቅነቅ ሳይል

አንቀላፍቶ ማጀቱ

ቃሊትና ሱሉሉታ

ለገጣፉ ሰበታ

ሸገር መጠቅለላቸው

አስቆጥቶት በሆታ

አሰልፎት በእንቢታ

በመተረየስ እርሙታ

ግንባሩን ለተመታ

ለደመ-ከልቡ ላልቅስ

ወይስ- ለራሴ ደረት ልምታ?
አዬ እተጌይቱ

ግራ የገባቲቱ

አልሰማሽም እንዴ?

ልቅሶ እንደቀረ ዱሮ

ዛሬማ............

የልማት ጮራ በያቅጣጫው ፈንጥቆ

ቁጭ ብሎ ለማልቀስስ-

መች ጊዜ ተገኝቶ

እዚህ ጋ- አባቢያ ህንጻ

እዛ ጋ ወረድ ብሎ- ያሲን ሁለገብ ሞል

መንገዱን ተሻግሮ ደግሞ- በረደድ ሾፒንግ ሴንተር

አለፍ ብለን ኮርነሩ ላይ- ገብራይ ሆስፒታል

እዛች ጋ ደግሞ- ፎርሲዶ ሆቴል

በየአቅጣጫው ስንገነባ

እየለመለምን ስናለማ

ለልቅሶ

ጭራሽ ጊዜ መች ተገኝቶ

ግና---አንቺ ግን

ገና በጨቅላነቱ እያለ ለሞተው- ለHR2003ሽ

ብትንትኑ ለወጣው- ለቅንጅትሽ

ባዶ ለቀረው- ህልምሽ

በምቀኝነት ለጨቀየው ነፍስሽ

እንደተመቸሽ- ግራም ቀኝም እየተገላበጥሽ

ይውጣልሽ- በደንብ አልቅሽ
ፉኚዶ ተራራ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 99
Joined: Wed Jul 17, 2013 6:34 pm
Location: americas

Re: ግራ የገባው ለቅሶ

Postby ዲጎኔ » Tue May 27, 2014 5:27 pm

ሰላም ይሁንልሽ እቴጌዋ
የአጼውን ኒክ ተጠቃሚዋ
በፊት በሳል የዋርካ ጨዋ
ግን ዛሬ ግራ ያጋባኝ ግጥሟን
ማለፍ አልፈልም ጉልህ ስህተቷን
በገባሮቹ ልጆች ትግል መሳለቅዋን
የህዝቦች ፍልሚያን ግራ ማለቷን
የኦሮሞ ልጆች ጥያቄ መናቁዋን
እስቲ አስትውይ እቴጌያቸው
እኒያ ፊውዳል ያፈናቀሉዋቸው
መቻራ/መታራን መቀማታቸው
ያለህዝቦች ፈቃድ በስልጣናቸው
ከዚያ ደርጉ በተራ የፈጃቸው
ዛሬ ወያኔው የሚነግድባቸው
አንድ ገዥ ቁብ ያልሰጣቸው
የዋህ ምስኪን ወገኖቼ ናቸው
አንቺ እዚህ የተሳለቅሽባቸው
ልጆቻቸው በሰልፍ የጮሁላቸው
ወደሸገር መጠቃለል ብለሽ የቀባባሽ
አንቺ በገባሮቹ መሬት ምን አገባሽ
ማንነት ባህል ሲጨፈለቅ የት ነበርሽ
እነደክሀራራ /እርቅ ቦታ ያልተረዳሽ
የድሮ ጨለማ ንጉሳዊን ናፋቂ ነሽ
አታገኝውም እንዳማረሽ ትቀሪያለሽ
የህዝቦች ፈደራል ዲሞክራሲ ያልገባሽ
ዘመኑ ወደሁውላ ይመለስልኝ ባይ ነሽ
እኛ ግን እንባችን ይታበሳል
ወደብርቱ ትግል ይለወጣል
ፊውዳልና ወያኔን ያስወግዳል
ህዝቦችን በቀያቸው ያሳድጋል
የሁሉንም ማንነት ያስከብራል
የታጋይ ልጆቻቸው ደም ይለመልማል
ደመከልብ ሳይሆን የአቤል ደም ይሆናል
እልፍ አእላፋትን ከየጎራ ለትግል ያስነሳል

እቴጌይት wrote:በድንቁርና ጥማድ
በጽልመት ከመኖሩ
ማይምነት አውሮት
ፊደል ካለመቁጠሩ
ባልተከፈተ አስኳላ
አማርኛ መማሩ
ላስመረረው ወገኔ
ላልቅስ ወይስ ለ'እኔ'?

ዛሬ በቀነበር ጠምዶ
በአፈ ሙዝ አስገድዶ
ከቀዬው አፈናቅሎ
ቢያሻው ዘብ-ጥያ ጥሎ
ቢያሻው በጅምላ ገሎ
ከሚገዛው ሹም ይልቅ
. 'ሀውልት' ሠላሙን ነስቶት
'ጥቁር ሰው" አስቆጥቶት
ለተሰልፈው በአንባ
ለተጨቋኙ ላልቅስ
ወይስ ለራሴ ላንባ?

ለባዕዳን ሲታደል
ቅርጫ ድንግል መሬቱ
ከእልፍኙ ነቅነቅ ሳይል
አንቀላፍቶ ማጀቱ
ቃሊትና ሱሉሉታ
ለገጣፉ ሰበታ
ሸገር መጠቅለላቸው
አስቆጥቶት በሆታ
አሰልፎት በእንቢታ
በመተረየስ እርሙታ
ግንባሩን ለተመታ
ለደመ-ከልቡ ላልቅስ
ወይስ- ለራሴ ደረት ልምታ?
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby እቴጌይት » Tue Jun 03, 2014 1:53 am

ሠላም ወንድም ዲጎኔ
ጎራ ስል ግጥምህን አየሁና ወዳጄ ሀሳቤ አልገባውም ብዬ በስድ ንባብ ልሞክርህ ተነሳሁ:-

የግጥሙን ጽንሰ ሀሳብ በእርጋታ ብታነበው እንደ እኔ የግለሰብ ነጻነትን ማዕከል ያደረገ ዘመናዊ ስርዓትን የምትደግፍ ፕሮግረሲቭ ... 'የፊውዳል ስርዓት ናፋቂ ናት' ወደ ሚል ትልቅ መሳት አትግባም ነበር:: ጭብጡ እንዲህ ነው አለቃ:-

ትልቅ ደን እየተቃጠለ ስለ አንድ ባህር ዛፍ ቅርንጫፍ የሚውተረተር ግራ ያጋባል:: የቤቱ መሠረት እና ምሰሶ እየተናደ ስለ ትንጥዬ የመኝታ ክፍሉ የግርግዳ ቀለም የሚባክን ያስገርማል:: ንጽጽሩን እናፍታታው:-


ወደ 70 በመቶ የሚጠጋው ለአቅመ ሄዋን የደረሰ ሴት ማንበብና መጻፍ የማይችልባት ሀገር ውስጥ ከድንቁርናው ብሶት ይልቅ.... ጥቂት የመማር እድል ያገኙት....በቋንቋ ውርስም ሆነ በባህል ምንም ትስስር በሌለው የነጭ ቅኝ ገዢ ሆሄ ለምን አልጻፉም ብሎ የሚብከነከን ተጨቋኝን ሳይ ያስገርመኛል:: Bilinguialismን ( ኦሮሚኛ እና አማርኛ ከተጠቃሚው ብዛትና ታሪክዊ ድርሻው አንጻር ብሄራዊ ቋንቋችን እንዲሆን) ወይም በቋንቋው መገልገልን በስክነት ከመፈለግ ይልቅ... የግዕዝ ፊደልን አልይ ብሎ በታሪክም ሆነ በውርርስ የማይዛመደውን የፈረንጅ ቅኝ ገዢን ሆሄ ፍለጋ የሚሄድ 'ተጨቋኝ' ልበለው 'ቂመኛ"
ሳይ የነጻነቴን ርቀት አስቤ ለራሴ ልዘን 'ለተጨቋኙ" ልዘን ብዬ ግራ ቢገባኝ "ፊውዳሊዝምን መናፈቅ' በምንም ስሌት ይሆናል ትላለህ?

ዛሬ በዘመነ ነጻነትና አኩልነት... በጅምላ የሚያስረውና የሚገለው ነፍሰ በላ ስርዓት ከዙፋኑ ይውረድ ብሎ በቁጣ ሳይነሳ.... የዛሬ መቶ አመት ባርነትና ጭቆና 'ኖርም' በነበረበት ሌላ ዘመን አስተሳሰብ የኖርና የሞተው ሚኒሊክ... ሀውልቱ ይውረድ ብሎ በቁጣ የሚሰለፍ ተጨቋኝ ስታይ መጸቱ ግራ አያጋባህም? እነ ማርቲን ሉተር ስለ ዘመናቸው ሰግሪጌሽን እና የጥቁር ጭቆና ከመታገል ይልቅ ባሪያ እንደ ንብረት የነበረው "የጆርጅ ዋሽንገትን' ወይም የጥቁሮችን ሰግሪጌሽን ያራምድ የነበረው' የአብርሀም ሊንከን ሀውልት ይወረድልን ብለው ሲስለፉ አስበው እስቲ?.....

ዛሬ የሕዝባቸውን ድምጽና ሚድያቸውን አፍኖ የሚገዛ ስርዓት ላይ በቁጣ ከመነሳት ይልቅ አንድ ግለሰብ ስለ "ጥቁር ሰው" ለምን ዘፈነ ብለው ለአድማ የሚነሱ የዛሬ ተጨቋኞች የነገ አምባገነንነታቸው አይታይህም?

በሁለት ዓመት ውስጥ ብቻ የእስራኤልን ግዛት የሚያክል መሬታቸው በውዳቂ ሊዝ ለእነ ሳውዲ ሲቸበቸብ ፀጥ ለጥ ብለው እየተማሩ....ለገጣፉና ሱሉሉታ አዲስ አበባ አስተዳደር ውስጥ ተጠቀለለ ብለው በከፍተኛ ቁጣ ስለፍ የሚወጡ ተማሪዎች ግራ እንዴት አያገቡህም? እርሱ አርዶ ላይበላው የጌታው ዶሮ ጓሮ ታሰረ ፊትለፊት ከጌታው ጋር የሚጣላ አሽከር እኔ ያስገርመኛል? ሰበታ ፊኒፊኔ ሆነ ኦሮሚያ ከወያኔ የብዝበዛ እና የጭቆና መዳፍ ይወጣል? በተለይ በተለይ ፊደል የቆጠሩ ወጣቶች አስተዋይ ታጋዮች ሳይሆን አሳዝኝ ቂመኞች ሲሆን ሳይ ለነጻነት ገና ስንት ዘመን እንደቀረን ይታየኛል::

እና ወንድም ዲጎኔ እስቲ ረጋ ብለህ አስበው::
መልካም ቆይታ ይሁንልህ::
እቴጌይት
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 656
Joined: Sun Sep 23, 2007 10:38 pm

Postby ዲጎኔ » Tue Jun 03, 2014 5:25 pm

ሰላም ለሁላችን
ውድ እቴጌ የህዝቦችን ትግል ግራ የገባው(confused) ሰማእታቱ ደመ ከልብ/የውሻ ደም ብለሽ በግጥም ስትዘልፊ መልስ ስሰጥ በስድ ንባብ ከተመለሽ ምላሼ እነሆ:_
በመሰረቱ የጦቢያን ህዝቦች ትክክለኛ ችግር ያልተረዳና ያንን ችግር ከመሰረቱ ለማስወገድ የማይደረግ ትግል ስልጣን ሰራቂ ደርግና ወያኔን ማፍራቱ ያየሁ ነኝ::
የሰሞኑ የተማሪዎች እንቅስቃሴና የተሰጣቸው ኢፍትሀዊና ኢሰብአዊ ምላሽ በጎ ህሊና ያለው ሰው ለምን እንዴት መቸ ብሎ መጠየቅ እንጂ በትግሉ መሳለቅ አይገባም::ያልሽው በኦሮሞ ተማሪዎችና በሌሎቹ የተነሱ ጥቂት ጥያቄዎች በጽንፈኞች ግፊት የተሰነዘሩ ሲሆን በነዚያ ጥያቄዎች ምክንያት አጠቃላይ እንቅስቃሴው ግራ የገባው ሰማእታቱን ደመከልብ ማለት በጣም ያሳዝናል ከማን ጋር በህብረት ይህን ግፈኛ አገዛዝ እንደምናስወግድ ለገባሮቹ ልጆች እንቆቅልሽ ሆኗል::ከ100 አመታት በፊት የነበሩ ታሪኮች የዛሬ አጀንዳ ማድረጉን ባልደግፍም ያኔ የተፈናቀሉ ቁዋንጃና ጡት የተቆረጡ ማስታወሱ ለነእንቶኔ ባይጥም ለእኛ ታሪካችን ነው ይወሳል::መጽሀፍ ልጋብዝሽ ሀገርቤት ትንሽ ተርጉሜ ያውም ቤ/ክ ያልተሰራጨ በገባሮቹ ላይ ምን ያህል ግፍ እንደተፈጸመ ያሳያል Evangelical pioneers II by Gustav Aren published in Sweden Lunden publishing

ጥቁሮች ከሰው በታች ይቆጠሩባት በነበረውና ዛሬም ያ አመለካከት ባንዳንዶች ባሉባት አሜሪካ Black History day ስናከብር ለብዙ ነጮች በጎ አደለም::እንደአንቺና መሰሎችሽ አመለካከት የጥቁሮች የግፍ ታሪክ መወሳት የለበትም ይህ ደግሞ ያልተነካ ግልግል አያውቅም ነው ተረቱ ወይም በሰው ቁስል እንጨት ስደድ ነው::ከአፍሪካ የመጣን ከነጭ ኮሎኒያሊስት በላይ የራሳችን ጉዶች የጎዱን ሚዛን ስለደፋ ብዙዎች በአሉን አይፈልጉትም::አንዳንድ ጥቁሮች ደግሞ አናሳ ቁጥር እንዳለን በመዘንጋት ለነጻነቱ ነጮች ከጎናችን እንደነበሩ በመርሳት በአሉን ሲያበላሹ አይቻለሁ::ወበአሉ መጀመሪያ ጊዜ የወሰደኝ ነጭ ፓስተር የጥቁር አንበሳ የመጀመሪያ የጦቢያአየር ሀይል ሰማእታትን ታሪክ ያወሳኝ ሲሆን ባለቤቱ ጥቁሮችን ማታ ማታ እየደበቁ ከባርያ ስቴቶች ወደ ነጻዎቹ የሚያጉዋጉዙ አቦሊሽኒስቶችን ታሪክ Under ground railway የጻፈች ነች::እዚያ ቤ/ክን Indiana ሄጄ ከጥቁሮቹ ትውልዶች ጋር የነጻነቱን ጌታ በእንባ አምልኬያለሁ!
የኦሮሞ መሬት ድሮ በአጼው ከዚያ በደርጉ አሁን በወያኔ ሲቸበቸብ ገባሮቹ አንዳች ሳይተርፍላቸው ሲፈናቀሉ ባንዳ ተለጣፊ እንደአስማ እየበላ እንደውሻ በበላበት ሲጮህ ያን ግፍ መቃወም ምኑ ነው ጥፋቱ?ማስተር ፕላን ተማሪዎቹ ማስተር ገዳይ ያሉት የኦሮሞን መሬት የሚነጥቅ የዘመኑ ነፍጠኛ ደባ ስለሆነ ነው ልጆቹ የተቃወሙት::ደግሞም ስለኦሮሞው ኦሮሞ ይናገር ነውና በአሁኑ ሰአት ለኦሮሞ ህዝብ ሲተገል ወህኒ የወረደ በቀለ ገርባ ድርጅት ኦፌዲን ከአንችና ከወያኔ የአዞ እንባ ይልቅ በጣም ይመቸናል::
በእውነት በጦቢያ ዲሞክራቲክ ሁሉን እኩል የምትቀበል ሀገር እንድትኖር ከተፈለገ የመጀመሪያው ነገር የብዙሀኑ ህዝቦች በተለይ የኦሮሞና ደቡቦች ጥያቄ ባግባቡ ሲመለስ የስልጣን ውክልና በእውነተኛ ዲሞክራቲክ ፈደራል ሲደራጅ ብቻነው አሊያ ጦቢያ በግፍና በድህነት ሁሌም ትኖራለች::
ዲጎኔ ሞረቴው ሀቀኛ ህዝባዊት ፈደራላዊት ዲሞክራቲክ ጦቢያን ናፋቂ
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby እቴጌይት » Wed Jun 04, 2014 12:26 am

ዲጎኔ
የሕዝቦች የዲሞክራሲና የእድገት ጥያቄ ለመመለስ የሚደረገው ትግል ቴዲ አፍሮ ለምን ስለጥቁር ሰው ዘፈነ ብሎ ለአድማ በመነሳት ነው ብለህ ከተሟገትክ ብዙም የምልህ ነገር የለኝም:: አዎ...ለገጣፉ አዲስ አበባ ሆነ ኦሮሚያ ለተጨቋኙ የሚፈይድለት ነገር እንደሌለ መረዳት ከከበደህና ሕይወትን የሚያክል ነገር በእንደዚህ ዓይነት ትርጉም የለሽ ጉዳይ መገበር አግባብነት ያለው የትግል ስልት ነው ብለህ የምታምን ከሆነ "ግራ የገባው ለቅሶህን" እንድትቀጥል ከመተው ሌላ ምን እልሀለሁ? የቀድሞ የግፍ ታሪክን እንደመማሪያ መጠቀም ማለት "የሚኒሊክ ሀውልት ይውረድልን' ብሎ መሠለፍ ነው ብለህ ካመንክ እና አዎ....የጥቁር መብት አክቲቪስቶች (የምታወድሰው ዶ/ር ኪንግን ጨመሮ) "የሊንከን ወይም ዋሽንገተን" ሀውልት ይወርድልን..ወይም መሠል ኢምንት ጉዳዮች ላይ ያለመባከናቸውን ምሳሌ መረዳት ከከበደህ....ነጋቲ ቡላ እንጂ ምን እልሀለሁኝ:: የጊዜ ትርጉም ያልገባው....ትልቁን ራዕይ በማይመጥን ኢሚንት ጉዳይ የሚዋጥ ተጨቋኝ ነጻነትን ያገኛል ብሎ ማለም አይቻልም::

ሠላም ክረም
እቴጌይት
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 656
Joined: Sun Sep 23, 2007 10:38 pm

Postby ዲጎኔ » Wed Jun 04, 2014 1:25 pm

ሰላም ለሁላችን
ክብርት እቴጌይቱ ምንድነው የከፈትሽውን አጀንዳና ዋና ሀሳብ የምታስቀይሽ?አዎን ለእቴጌ አያልቅባት ስህተትን መቀበል እርም ሆኖባቸው በስተርጅና ድንግል ካለገባሁ ብለው እንደጣሩ ፊታውራርሪ እንደሻውና ልጄን የፊውዳል ደም ለሌለው አልድርም እንዳሉት ፊታውራርሪ አሰጌ(ፍቅር እስከመቃብር) ህዝቦች ለሰደብሽ ይቅርታ ትጠይቂያለሽ ብዬ አልጠብቅም ርእስ ጠብቆ መወያየት የግድ ነውና ከርእሱ አትውጭ::ያን አትችይም በበቃኝ ድምጽ ሳታሰሚ ውልቅ ወይም አምዱን ዝጊ::እስኪ የትነው የልቅአፍ ቴዲ አፍሮ አባባል ተማሪውና ዲጎኔ ያነሳን?የሚኒሊክ ሀውልት ይፍረስ በዚህ ትግል ተነስቷል ወይስ ለማምታታ የቆጥ አወርድ ስትይ የብብት መጣልሽ ነው ቅቅ ጥቁርሰው የጥቁር ድል ማዜሙ ማን ተቃወመ? የተቃወምን ለኢኮኖሚና ፖለቲካ ጥቅም የመስቀል ጦርነት እያሉ ህዝብ የፈጁበትን ቅዱስ እንዳሉት የአርሲና የባሌ ህዝቦች ቁዋንጃ የተቆረጠበትን ወረራ ቅዱስ ሲል ነው ነገር ያበላሸ::ምን አለ ድሀ ብለው ንቀውት ጉድ ያረጋቸው መይሳው ካሳ?ሽመል ይገባዋል የአዝማሪ ቀልማዳ ቅቅቅ የዋርካው ለማ እባክህ ለፓ/ር ዳንኤል ያልክ ሽመል ለዚህ ማስተዋል ለጎደለው አዝማሪ አርገው ቅቅ ደግሞ ወዴት ከፍ አልሽ? ባርነት ይቅር ስላለ የተሰዋ አብርሀም ሊንከን አዋጅ ሲያወጣ ኦሮሞ/ባሪያ ይሁን ሰው አትግደሉ ካለው ንጉስ ጋር ታስተካክይ?በይ አንቺ ግራ የገባሽ ሳትሆኝ ግራነት የገባብሽ አምላክ ቀኙን ሀሳብ ያስገባብሽ::
ዲጎኔ ሞረቴ ከእቴጌ አያልቅባት ሩቅማዶ ባልቻ አባነፍሶ አደባባይ

እቴጌይት wrote:ዲጎኔ
የሕዝቦች የዲሞክራሲና የእድገት ጥያቄ ለመመለስ የሚደረገው ትግል ቴዲ አፍሮ ለምን ስለጥቁር ሰው ዘፈነ ብሎ ለአድማ በመነሳት ነው ብለህ ከተሟገትክ ብዙም የምልህ ነገር የለኝም:: አዎ...ለገጣፉ አዲስ አበባ ሆነ ኦሮሚያ ለተጨቋኙ የሚፈይድለት ነገር እንደሌለ መረዳት ከከበደህና ሕይወትን የሚያክል ነገር በእንደዚህ ዓይነት ትርጉም የለሽ ጉዳይ መገበር አግባብነት ያለው የትግል ስልት ነው ብለህ የምታምን ከሆነ "ግራ የገባው ለቅሶህን" እንድትቀጥል ከመተው ሌላ ምን እልሀለሁ? የቀድሞ የግፍ ታሪክን እንደመማሪያ መጠቀም ማለት "የሚኒሊክ ሀውልት ይውረድልን' ብሎ መሠለፍ ነው ብለህ ካመንክ እና አዎ....የጥቁር መብት አክቲቪስቶች (የምታወድሰው ዶ/ር ኪንግን ጨመሮ) "የሊንከን ወይም ዋሽንገተን" ሀውልት ይወርድልን..ወይም መሠል ኢምንት ጉዳዮች ላይ ያለመባከናቸውን ምሳሌ መረዳት ከከበደህ....ነጋቲ ቡላ እንጂ ምን እልሀለሁኝ:: የጊዜ ትርጉም ያልገባው....ትልቁን ራዕይ በማይመጥን ኢሚንት ጉዳይ የሚዋጥ ተጨቋኝ ነጻነትን ያገኛል ብሎ ማለም አይቻልም::

ሠላም ክረም
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby ገልብጤ » Wed Jun 04, 2014 3:38 pm

ወይዘሮ እቴጌይት
ወደ ኍላ ከሚያስብ ሰው ጋር ምን ቢያዳርቅሽ ነው .. ያለፈ አፈ ታሪክ ሲያቃዥው መናፍቅ ጋር አተካራውን ከምታራግቢ እሱን ንቀሽ የመሰለሽን ብትከትቢ ጥሩ ይመስለኝል
ምክኒያቱም መናፍቁ መጭውን ትውልድ አስቦበት አያውቅምና ..ንቀሽ ተይው ወይ በቃሪያ ጥፊ ብለሽ አጋድሚው
ያልበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ
የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል
James freeman clarke
ገልብጤ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1680
Joined: Sat Jun 26, 2010 11:24 pm

Postby ጌታ » Wed Jun 04, 2014 4:09 pm

እቴጌ

ከስምሽ ውጪ ብዙም አንብቤሽ አላውቅም:: እዚህ ቤት ላየሁት አስተሳሰብሽ የቋንቋሽ ውበት እና ፍሰት እጅ ነስቻለሁ::
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3029
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby ዲጎኔ » Wed Jun 04, 2014 5:20 pm

ሰላም
አይ የዋርካው ጌታ ዲፕሎማሲውን ታቅበታለህ ቅቅቅ
የዲጎን የግጥም መድበል ማሰባሰብ አትርሳ ያን ስታደርግም ለእትጌይቱ ምላሽ የሰጠሁትን አይነት በደንብ አንብበህ ስታምንበት ብቻ ይሁን::
ዲጎኔ ሞረቴው ከቅድስት ማሪያም የተወለደውን ጌታ ብቻ የሚያምን የዋርካው ጌታ የልብ ወዳጅ

ጌታ wrote:እቴጌ
ከስምሽ ውጪ ብዙም አንብቤሽ አላውቅም:: እዚህ ቤት ላየሁት አስተሳሰብሽ የቋንቋሽ ውበት እና ፍሰት እጅ ነስቻለሁ::
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby ጌታ » Wed Jun 04, 2014 5:35 pm

ዲጎኔ wrote:ሰላም
አይ የዋርካው ጌታ ዲፕሎማሲውን ታቅበታለህ ቅቅቅ
የዲጎን የግጥም መድበል ማሰባሰብ አትርሳ ያን ስታደርግም ለእትጌይቱ ምላሽ የሰጠሁትን አይነት በደንብ አንብበህ ስታምንበት ብቻ ይሁን::


ዲጎ

ግጥሞችህን ሳሰባስብ እኮ 'ዲጎኔ ግጥም አይችልም' የሚሉህን ለማሳፈር እንጂ ግጥምህ ውስጥ ያለውን ኃሳብ መደገፌ አይደለም::
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3029
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby ዲጎኔ » Wed Jun 04, 2014 5:54 pm

በሳሉ ጌታ አሁን ሀሳብህ በደንብ ገባኝ!እንዲህ አይናቸው ተከፍቶ በፖለቲካ በእምነት በብሄር የተለያቸውን ሰው ጥሩ ነገር መስካሪ ያብዛልን!እኔም እንዳቅሚቲ ይችኑ ከነስሟ የአባቶቻቻን ፊውዳል አሰጋባሪዎች ኒክ የወሰደችና የዘመኑ ነፍጠኛ ወያኔ አባላትና ደጋፊ ስልኪን አውሎነፋስና አሁን ደግሞ ዳግማዊን ጥሩ ነገር አደንቃለሁ::

ጌታ wrote:
ዲጎኔ wrote:ሰላም
አይ የዋርካው ጌታ ዲፕሎማሲውን ታቅበታለህ ቅቅቅ
የዲጎን የግጥም መድበል ማሰባሰብ አትርሳ ያን ስታደርግም ለእትጌይቱ ምላሽ የሰጠሁትን አይነት በደንብ አንብበህ ስታምንበት ብቻ ይሁን::


ዲጎ

ግጥሞችህን ሳሰባስብ እኮ 'ዲጎኔ ግጥም አይችልም' የሚሉህን ለማሳፈር እንጂ ግጥምህ ውስጥ ያለውን ኃሳብ መደገፌ አይደለም::
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby ፕላዞግ » Thu Oct 02, 2014 8:52 am

እቴጌይት:
እኛም እንደ ጌታ ላጻጻፍሽ ውበት እና ምቾት...ቺርስ!
ስትጽፊ ግን ትንሽ ቀለል አርጊው...ማለት ቋንቋውን አታከባብጂብን:: ብዙ ያላነበብን ያልተፈላሰፍን ተማሪዎች አለንና!
ግጥሙ ፖለቲካ ምናምን ቢሆንም አጻጻፉ ይመቻል:: ይመችሽ::
ፕላዞግ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 38
Joined: Sat Dec 06, 2008 7:21 pm


Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: Google Adsense [Bot] and 3 guests