ዋርካችን አንኳን በሠላም ተመለስሽ?

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ዋርካችን አንኳን በሠላም ተመለስሽ?

Postby ዋናው » Mon Aug 29, 2016 10:09 am

የድሮዉን ሠው ሁሉ ማሰባሰብ ቢቻል ምንኛ ደስ ይል ነበር ?
'ስቲ የተቻለንን ሁሉ እንሞክር፣ በፌስቡክ ግድግዳችን ላይ የክተት አዋጅ እንለጥፍ፣

ዋናው
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2801
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Re: ዋርካችን አንኳን በሠላም ተመለስሽ?

Postby ደጉ » Wed Aug 31, 2016 10:16 am

ዋናው wrote:.... በፌስቡክ ግድግዳችን ላይ የክተት አዋጅ እንለጥፍ፣

ዋናው

ቅቅቅቅቅ የክተት አዋጅ አሪፍ እባባል ነው ... ርግጠኛ ነኝ ያሉት እንደሚመጡ ተስፋ እለኝ ... አሁን ትንሽ በ አስተሳሰብ ሳናድግ እነቀርም ...፡)
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4423
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

Re: ዋርካችን አንኳን በሠላም ተመለስሽ?

Postby ሾተል » Thu Sep 01, 2016 10:07 am

ዋናው wrote:የድሮዉን ሠው ሁሉ ማሰባሰብ ቢቻል ምንኛ ደስ ይል ነበር ?
'ስቲ የተቻለንን ሁሉ እንሞክር፣ በፌስቡክ ግድግዳችን ላይ የክተት አዋጅ እንለጥፍ፣

ዋናው


ሰላም ጤና ይስጥልን ወንድም ዋናው!!

እንደምን ከረምክ?
እኛ ደህና ነን።ምነው ግን ቂም ይዘህብን ነው ሙሉ ስማችንን እያወቅክ ዋርካ ስትዘጋ በፌስ ቡክ የመፈለግያ ማሽን ስሜን መፈለግያው ማሽን ውስጥ ዱለህ ፌስ ቡክ ላይ አግኝተህ ጉዋደኝነት ያልጠየቅከኝ።

እኔ ላፈላልግህ ሞክሬ ነበር…እውነተኛው ስምህን ባለማወቄ እቅዴ ከንቱ ቀረ።

እስቲ ለብእር ውበትና እድገት ስንል የተጋጨናችሁ ካላች ሁ የብ እ ር አምላክ ይቅር እንዲለን ይቅር እንባባልና እንማማር።ስንተችና ስንተች የማይከፋን ሆደ ሰፊዎች ሆነን ቂም በደልን አስወግደን ወደ ሁዋላ እንደግመል ሽንት የተጉዋዘው ስነጽሁፋችንን እንታደግ ዘንዳ በግልም በቡድንም እንረባረብ።ቂም ተያይዞ እድገት የለም።መቼም ካለፉት አመታቶች በመኖር ብቻ ሳንበስል አልቀረንም።እንደገና የህይወት ልምድ ትምህርት ብዙ ማየትና ማንበብ ደግሞ ከመብሰል አልፎ አገንትሮናል ብዬ አስባለሁ።

እንደመጻፍና ማንበብ የመሰለ የሚጥም ነገር በህይወቴ አላስተዋልኩም።ስለዚህ ይሄንን የህይወት ያንጎል ማር እናጣጥመው…ለበታቾቻችን እናስተምር…ከበላዮቻችንም ከበታቾቻንም እንማር።

የሚተቹ ነገሮች ሲኖሩ ብትንትን አድርገን እንተቻቸው።እነ ፓስዎርድም የጀመሩትን ስንቱን ያስተማረ ጽሁፍን የመተቸት ጥበብና እውቀት እንደኔ ያለው ይቅሰም...ስጽፍ ለመተቸት እራሴን ላቅርብ…የጻፈም ካለ ከማመስገን ይልቅ እዚህ ጋር ጠንካራ ነው እዚህ ጋር ላልቶዋል ይሄ ይስተካከል ይሄ እንዳለ ይሁን እዚህ ጋር እንደዚህ ነው እዛ ጋር ወንዳታ እንባባል።

አይመስልህም ወንድማችን ዋናው?


ስላየንህ ደስ ብሎናል

ሾተል ነንል
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9647
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Re: ዋርካችን አንኳን በሠላም ተመለስሽ?

Postby ራስ አሉላ1 » Fri Sep 02, 2016 2:53 pm

ጤና ይስጥልኝ ብለናል፡፡
እልልልልል ነው የሚያስብለው፡ 2 አመት እካባቢ የተጠፋፋን ሰው ማፋለጉ ይሄን ያህል የሚከብድ ባይሆንም፤ የድሮውን አይነት ሞራል ይዞ ይመጣል ወይ ነው ጥያቄው፡፡
ለማንኛውም እንካን ደስ አለን፡፡

ዋናው wrote:የድሮዉን ሠው ሁሉ ማሰባሰብ ቢቻል ምንኛ ደስ ይል ነበር ?
'ስቲ የተቻለንን ሁሉ እንሞክር፣ በፌስቡክ ግድግዳችን ላይ የክተት አዋጅ እንለጥፍ፣

ዋናው
ራስ አሉላ1
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 44
Joined: Wed Mar 23, 2005 7:26 pm
Location: ethiopia

Re: ዋርካችን አንኳን በሠላም ተመለስሽ?

Postby ጌታ » Sat Sep 03, 2016 4:57 pm

ዋንቾ ሰላም ነው?

እማርኛ መፃፍ እየተለማመድኩ ነው እንዳዲስ፡፡ እነ ዲጎኔ ሲመጡ ቤቱ ሞቅ ይላል...............
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3029
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Re: ዋርካችን አንኳን በሠላም ተመለስሽ?

Postby password » Sat Sep 03, 2016 7:04 pm

አሮጌው ዓመት አልፎ አዲሱ ሳይተካ
የዘመኑ ስራችን በቅጡ ሳይለካ
ታየች ሳይበር ላይ መድረካችን ዋርካ!

ሰላምታ ለዋርካዊያን ሁሉ. . ." ዋናው" ስምህን ሳየው በጊዜ ወደኋላ ሄጄ ብዙዎቻችሁን ኣሰብኳቹ፣ ዋርካን የሳይበር ዩኒቨርሲቲ አድርጋችኋት የነበራችሁን ሁሉ። ግጥሙ፥ ልቦለዱ፥ ሂሱ ሁሉ ትዝ አለኝ። የቀድሞው ተሳትፎ ከቀጠለ አሁንም መወያያና መማማሪያ ትሆናለች።

ፓስ
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 314
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Africa

Re: ዋርካችን አንኳን በሠላም ተመለስሽ?

Postby ዋናው » Sun Sep 04, 2016 1:01 pm

ሠላም ሠላም ውድ ዋርካዊያን/ያት
ሾተል የሆነ ቦታ ፖስት ያደረገውን አይቼ በረሳዉት ትልቅ ነገር ራሴን ስውቅስ ነበር እሁንም አልረፈደም ለነገሩ... አዎ የሳይበር ኢትዮጵያ ባለቤቶች ዋርካችንን ምንም ዕቃ ሳይጎል ድጋሚ አምጥተው ስላስረከቡን እጅግ የላቀ ምስጋናና አድናቆት ይገባቸዋል፡፡

ሾተል እንዴት ነህ? እንክዋን ለመተያየት አበቃን፤ ስለቂም ብለህ በፃፍከው ነገር ላይ (በነገራችን ላይ [ፀ]ን ፍለጋ ያልደነቆልኩት የኪቦርድ ቁልፍ የለም) እናም ሾተል በመሃል የነበሩት ዓመታት ጥቂቶች አልነበሩም'ኮ በዛ ዘመን ምንዘባዘበው ሁሉ የሆነ እንድ ኮሌጅ ውስጥ ሆነን የምንበሻሸቅ ዓይነት ስሜት ብቻ ነበር የሚመስለኝ በበኩሌ፡፡ መቼም ዋርካ መስኮት ሰርታ ድንጋይ ተወራውረን አተፈነካክተንም ሁሉም ትዝታዎች 'ንዳሉ ሆነው እሁንም ድረስ ደስ የሚሉ ናቸው፡፡

ደጉሻ ልክ ብለሃል መቼም በነበርንበት ፖዝ አናደርግም እድሜ ደጉ ብዙ ነገር ያስተምራል ብዬ አስባለሁ፤ አሉላ የዋርካ ሞራል ድሮም ቢሆን ብልጭ ድርግም የሚል ስሜት ነበረው እሁንም አዳዲስ ዋርካዊያን ተፈጥረው ጥሩና አዲስ ሞራል ይዘው ይመጣሉ የሚል እምነት አለኝ፡፡

ጌት'ሽ ሰላም ነው? የታይፑን ነገር አታንሳ ያማርኛ መተየቢያ ዴቬለፖሮቹ ባንድነት ከመስራት ይልቅ ሁሉም ለየራሱ ስልሚሰራ በየጊዜው አንዱ ካንዱ የሚሳከር ነገር ይፈጠራል በነገራችን ላይ ጉግልም ግራ የሆነበት ነገር ይህ ነው ለማንኛዉም እየተኮላተፍክም ቢሆን ፃፍና ተቀላቀል

ፓስ 'ንዴት ነህ? ስላየሁ ደስቦኛል አስተማሪ ብሕርህ ከቆመበት 'ንደሞቀጥል ተስፋ አለኝ፡፡

'ስቲ ባካችሁ አያ ዳሞት ዋኖስን በሕይወት መኖር የምታውቁ ጠቁሙኝ አንድ ወቅት መፀሐፈፊት ላይ በደምብ 'ንገናኝ ነበር የሆነ ጊዜ በዛው 'ልም አለብኝ ባለበት ሰላም 'ንደሚሆን ተስፋ አልኝ

መልካም ሰንበት
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2801
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Re: ዋርካችን አንኳን በሠላም ተመለስሽ?

Postby ሾተል » Wed Sep 07, 2016 8:05 am

ዋናው
ሠላም ሠላም ውድ ዋርካዊያን/ያት

ሰላም ዋናው?ጤና ይስጥልን

ሾተል የሆነ ቦታ ፖስት ያደረገውን አይቼ በረሳዉት ትልቅ ነገር ራሴን ስውቅስ ነበር እሁንም አልረፈደም ለነገሩ... አዎ የሳይበር ኢትዮጵያ ባለቤቶች ዋርካችንን ምንም ዕቃ ሳይጎል ድጋሚ አምጥተው ስላስረከቡን እጅግ የላቀ ምስጋናና አድናቆት ይገባቸዋል፡፡

ዋናው-በረሳውት ያልካት በሰራሁት ለማለት ነው?የሆነ ቦታ ላይ ዋርካ ቫይረስ በቫይረስ ሆና ነበር ብዬ ጽፌያለሁ።እና እራሴን ስወቅስ ነበር ብለህ የጻፍከውን ሳነብ እንዴ በሰራሁት ሊል ፈልጎ ይሆን ?ካለ ደግሞ ምን ቢሰራ ነው እራሱን ያስወቀሰው?ይሄ የኮምፒውተርና የስ እል ሊቅ የኮምፒውተር ሊቅነቱን ፈተሽ ለማድረግ ከ 3ዲ አልፎ 7 ዲ አድርጎ በኛ ላይ ሙድ ለመያዝና ለቤተ ሙከራ ተጠቅሞ ቫይረሶቹን ፈጥሮዋቸው ሲያበቃ ኮምፒውተራችን ላይ ቼዝ እንዲጫወቱ ዋርካ ሜዳ ላይ ደግሞ ዳንግላሳ እየጋለቡ አንዴ በኮቴያቸው ሲላቸውም ደግሞ በግንባራቸው ካላቸውም ደግሞ በአንዳች የፈረስ ጉልበታቸው ነፍስና ስጋችንን እየለያዩ መከራ ፍዳችንን እንዲያበሉን ያደረገው እሱ ይሆን እንዴ ብዬ እንድጠረጥር ባያደርገኝም እንደአጻጻፍህ ግን ወደዛ ስለሚያስጠረጥርህ ብሮ ለጨዋታ ያመጣሁትን በተወዳጅዋ ስንቶቻችንን ባዝናናች ባስተማረች ባፋቀረች ባጣላች ባጋባች ባለያየች በሳይበር ዋርካ ላይ እንደዛ ታደርጋለህ ብዬ ባልጠረጥርም እንደአጻጻፍህ እኔ የጻፍኩትን ጽሁፍ ያነበበ እንደዛ ሊጠረጥርህ ስለሚችል ለምን እራስህን የወቀስከው ከዋርካ መዘጋትና ከነበራት ችግር ጋር የተያያዘ ከሆነ ንገረን ።

ሾተል እንዴት ነህ?

እግዚያብሄር ይመስገን በጣሙን ደህና ነኝ።ያው ሳይበር ዋርካ ከተዘጋች ጊዜ ጀምሮ ብዙም አልጻፍኩም እንጂ ደህና ነኝ።ሰው ሁሉ እድሜ ለዘመነኛው ፌስ ቡክ ሁሉም ቪድዮ ለቃቂና ጸሃፊ በሆነበት ዘመን ለምን እንደሆነ አንዳንዴ ሸንቆጥ የሚያደርጉኝ ካልተላተሙኝ በስተቀር እሱም እዚህ አንድ አገር አብረናቸው የምንኖረው መናገር መጻፍ ሳይችሉ ጸሃፊ ባንሆንም ልክ ልክ ተናጋሪዎቹን ሸንቆጥ ሲያደርጉን መኖር እስኪደብራቸው ድረስ አንድ አንዴ ለመከላከል ስል አልሜ ከመተኮስ በስተቀር ምኑም የፌስ ቡክ ነገር ሙዴ ስላልሆነ መጻፍ እያማረኝ እንዲሁ ከመሆናችን በስተቀር በጣሙን ደህና ነኝ።የሁሉም የዲሞክራሲ መብቱ ቢሆንም ግን ጽሁፍን ሲያረክሱ ፈጠራን ክብሩን ሲያሳጡ ክርክርን ወይም ውይይትን መላ ሲያሳጡት ካሜራ ፊት ለፊት ምድረ የአይምሮ ገርዳሜዎች ማንንም ሊያሳምን የማይችል ያልበሰለ እዚህ ግባ የማይሉት ነገር እራሳቸውን ቀርጸው ሲለቁና ሲሞጋገሱ ሳይ ድብርት ውስጥ እያስገባኝ ስላየሁትና አንዳቸውም በምትሰጠው ኮሜንትስ የሚደግፍህ ያላንዳችን ማብራርያና ለምን አስተያየትህን እንደደገፈ እንኩዋን ሳያብራራልህ ይደግፍሃል…የሚቃወምህ እኛ ያቆምነውን ስድብ ሊሰድብህ ይሞክራል።ቆይ እስቲ እኔን የስድብ ማስተርስ ያለኝን ማን ነው ሰድቦ የሚያበሽቀኝ?እዚህ ሳይበር ዋርካ ላይ ቀኑን ሙሉ ቁም ነገር ሳልጽፍ ስ ሳደብ እንደ ማንጆ ስጋ ገንችሬ የማልታኘክ የእንጨት ሽበት እንዳልሆንኩ ሁሉ ተሰድቦ ተሙቶ በግል ሳጥኔ ሳይቀር ስድብ ይልኩልኛል።ከዛ መልሼ እንዳላጫውታቸው ፈሪዎች ስለነበሩ ፕራይቬታቸውን ቅርቅር።ስለዚህ ፌስቡክን የተለያዩ የዜና አውታሮችን የስነድሁፍ አምዶችን ወዘተ ላይክ ስላደረኩ የሚለቁትን የሚመቸኝን በሙሉ ሳነብ ነው የምውለው።አንዳንዴም ደግሞ እንደ አጋሰሱ ብርሃኑ ጋግርታም የግም ቦቲ 7 የሞኞች አለቃ ጸጉሬ ጎፈሬ ከመሆኑ በፊት የተነሳሁዋቸውን አንዳንድ ፎቶዎች ለቅቄ ላይክ ስጠብቅ ምን አልባት ያንን የመሰለ አሳሳቄን መልክና ቁመናዬን አረማመዴን ያዩ አንድ አንድ ሄዋኖች በፕራይቬት እንዴት ነው ትኬት ቆርጠንልህ ትመጣ ይሉኝ ይሆን እያልኩ አንጋጥጬ ስጠብቅ እውላለሁ።መቼም አንድ ቀን ጉድ ሳልሆን አልቀርም።የዛኒው የ 47 እመት ጉብልን ፎቶ ሲያዩና ሲያዩኝ የማሳሳና ሁለመናዬ በእንስቶች አይን የታየ ጊዜና ይሄንን እንኮይ እንብላው ወይስ ይሄንን ማንጎ እንጉመጠው በሚሉኝ ሰአት የተነሳሁትን ፎቶ ለጥፌ ነው ቢቀናኝ ብዬ እየጠበቅኩ ያለሁትና ያ የድሮ አይናማነቴን አይተው በአለም አንደኛ በአፍሪካ ስድስተኛ የሆነን የአውሮፕላን ትኬት ወይም የባቡርም ይሆናል ካለም የመርከብ ትኬት ቆርጠውልኝ ሄጄ ስገናኛቸው ፎቶውና እኔ አንጃና ግራንጃ ሆእነንባቸው በዛው አሸልበው ለወቀጣ የአለም የሱፐርማርኬት ላስቲክ ይጄበት በሄድኩት ሻንጣዬ ሃብታቸውን ወርሼ ከሼህ አላሙዲን ተርታ ተሰልፌ እንዳላርፈው ነው የፈራሁት እንጂ ወንድምዬ ምን እሆናለሁ ብለህ ነው?እምቢ አላረጅም ብዬ ይሄው ቁልጭ ቁልጭ ብዬ ባንዲት ሙጫ ቤት ውስጥ ከነ አሳንቴና ኦባማ ጋር እየተዳረቅኩ አለሁ።

አንተስ እንዴት ነህ?አገራችሁ ጀምራችሁት የነበረው የትያትር ፕሮጀክትስ እንዴት ሆነ?በዛው ቀጠላችሁበት ወይስ ?ልናየው የሆነ ቦታ ለጥፋችሁት ከሆነ እባክህ ወዲህ በለን።

በኮምፒውተር የምትስላቸው እነዛ አስገራሚ ሰሎችህስ ከምን ደረሱ?እስቲ በወንድምነት ደፈረኝ አትበለኝና አንድ ቀን ምናለ በካርቶን ፊት አይጠ መጎጥ አድርገህ ጆሮዬን እንደ አንቶኖቭ ክንፍ አፍንጫዬን ሁለት ነጥብ አድርገህ እዚህ ጋር አፍንጫ መኖር ነበረበት ነገር ግን ያፍንጫው ባለቤት አፍንጫ ሳይሆን ሁለት ቀዳዶች ነው ያሉበት ብለህ ጽፈህ ቅጥነት ድሮ ቀረ ይሄንን የፈረንጅ አሳማ ውጬ ውጬ እርጉዝ ሴት ምስጋን ትጣ አይነት አድርገህ ለምንድነው የማትስለኝና በስጦታ መልክ ሰጥተሀኝ ለምንድነው ግርግዳዬን የምድረ የማላውቃቸው የፈረንጅ ቺኮችን ለጥፌ ይቺን ነበር ወይ ነዶ እያልኩ ከምመኝ የራሴን ፎቶ ግርግዳው ላይ አሳፍቼ ገርግጄ እራሴን እያየሁ ስፈራ እንድውልና እንዳድር እንዲሁም ቤቴን ፈርቼ እነ አሳንቴና ኦባማን ፊት ለፊት እያደረኩ ከዋልኩበት እቤተ እንድገባ አታደርግም?

መጣን

ሾተል ነን
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9647
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Re: ዋርካችን አንኳን በሠላም ተመለስሽ?

Postby ቆቁ » Tue Sep 13, 2016 8:52 pm

ሾተል ነፍሱ ትኖራለህ ጤናህ ይጠበቃል ?

ስማ ማሰባሰብ ትወዳለህ መሰብሰግ ግን ደስ እይልህም

ስማ ከላይ የዘከዘክው ምንድነው ነፍሱ?

ሰላምና ጤና ከቀልድና ከጨዋታ ጋር ይመኛል ፈላስማው ቆቁ
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4069
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states


Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests