by ባለ-ሱቅ » Thu Aug 30, 2018 5:46 am
ሙከራ አንድ ሁለት አንድ ሁለት
ዋርካ የድሮ ስሜን ወስዶ አልሰጥ ቢለኝ በአዲስ ስም ብቅ አልኩኝ
ባለ-ሱቅ እባላለሁ
በቀደም ለታ ነው... ከአንድ የክብረመንግስት (አዶላ) ልጅ ጋር ቁጭ ብለን ስናወራ.... እንዴት እንደሆነ ባላስታወስኩት አጋጣሚ ስለሰርግ ተነሳ...
አዶላ ውስጥ ስንት ሰርግ ትዝ ይልሃል ብሎ ጠየቀኝ፡፡እኔም ትዝ የሚለኝን ቆጥሬ ነገርኩት ... ለኔ ትዝ የሚለኝ እራት ነበር....
1ኛ የሃጂ-ሃሰን ልጅ ስታገባ (ከድጃ ይመስለኛል.... ምንም ህፃን ብሆንም ትዝ ይለኛል.... የዚያን ጊዘ ወጣቶች ሰርግ ቤት ሲዘፍኑ..... አስኪ እንመካከር ... እርስ በራሳችን.... ዘር መለየት ይቅር ... አንድ ነው ደማችን.... እያሉ ሲዘፍኑ ትዝ ይለኛል....
2ኛ.. የመድኔ ልጅ ያገባች ግዜ.... ማስታውሰውእአስናቀ ገ/የስ ሰርጉን አድምቆ ሲመሻሽ እና መድረኩን ጥሎልኝ ሲሄድ... እኔ በአብዮት ዘፈን ተራዬን ማደምቀው እና መሳቂያ ምሆነው
3ኛ... ከለምለም ቤት በላይ ያለው የወለዬዎቹ ቤት ውስጥ የነበረው ሰርግ.... የማስታውሰው ደሞ... እነ-ፍቃዱ እቦምሳ የሚያዘፍኑኝ ዘፈን
በናፍቆት አለንጋ ጨክነሽ.. ልቤን የቀጣሽው
እቱ የምወድሽ ናፍቆቴ ነይ የት ነበር ያለሽው
የምች መዳኒት ስሙ ዳማከሴ
መሃረብ አይደለሽ አልከትሽ በኪሴ
ማታ በሁለት ሰእት እጠብቅሻለሁ
ኮሮንቲ ሲጠፋ ጉብ እልብሻለሁ....
የምትል ከየት እንደመጣች የማላቃት ግጥም እሱዋን ስል የሚሳቀው ሳቅ...እአይረሳኝም
በ4ኛ ደረጃ ማስታውሰው... የጋሽ በቀለ ልጅ ስታገባ.... ታደሰ ሚባል ይመስለኛል ባሉዋ... 02ቀበሌ.... አማረች ወይም ምናምን ጠጅ ቤት እካባቢ... ያለ ቤታቸው
እዛ ትዝ የሚለኝ.... በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ በራሴ ላይ ኤክስፐርመንት የሰራሁበት ስለሆነ.... ምክንያቱም.... ልጆች ሆነን ሲነገረን ያደግነው የክርስቲያን ስጋ ከበላህ ትሞታለህ .. ነው.... እኔ ደሞ... መሞት እንዴት እንደሆነ ... ቼክ ያደረኩበት ስለሆነ.... በፍፁም አይረሳኝም
እያልኩ ስቀድ ለግዋደኛዬ.... ተገርሞ አየኝና...
እኔ ግን አዶላ ውስጥ ያለ-አንድ ሰርጋ አላቅም አለኝ....
የማንን ስለው.... የጋሽ አሰጋኽኝ ቤት ሰርግ ብሎ ልቤን አቆመብኝ..... እኔ ካገር ከወጣሁ በሁዋላ ሆነ እንጂ እያመልጠኝም ነበር፡፡ ራስብሩ ና እኔ እንተዋወቃለን... ለምን ልቤ እንደቆመ
እና ስኪ ንገረኝ እልኩት የሚያውቀውን
ሳስበው ሳስበው... ብሎ ጀመረ
ሳስበው ሳስበው ያኔ እኔና ጌቱእአድማሱ ኩሽኔታ ለመንዳት መድሃኒያለም ዳገት ስንወጣ.... እንዲት ቆንጅዬ ልጅ.... ቀ----ይ ቆንጆ.... የአዶላ ፀሃይ ነክቶዋት የማያቅ ምትመስል ውብ የሆነች ልጅ... ከአንድ ማንነቱን ካማላቀው የ01 ልጅ ይመስለኛል... ከሱ ጋር ሆነው......
ይሄ መብራት ሃይል ጊቢው አለ እይደል.... እሱ ጋር ካለው ሳር ላይ ቁጭ ይሉና.... ይሉና...... ይሉና
እኛ ደሞ ተደብቀን እናያቸው ነበር... እኔና ጌቱ
አቤት ደስ ሲሉ ብታያቸው
ታውቃቸዋለህ ግን?... ብሎ ድንገት ሲጠይቀኝ... ከንዴት እለም ትካዜ ውስጥ ድንገት መንጥቆ አወጣኝ....
እያየሁዋቸው ነበር... እነዚያን ሁለት ውብ ልጆች.... ከመዳህኒያለም ጫካ ውስጥ ወጥተው... መብራት ሃይሉ ሜዳ ላይ ቁጭ ብለው... ሲጎነጫጩ
ወይኔ እኔ ብሆን ያኔ... በድንጋይይ አላስተርፋቸውም ነበር
ብዬ በጣም ቆጨኝ
ይሰማል ራስብሩ
እዎን በጣም ቆጨኝ... ጌቱን ወይም ጉዋደናዬን ባደረገኝ ብዬ... ቁጭትትትትት
ቆጨኝ የሚለውን የትእግስት ወዪሶን ዘፈን ጋብዤሃለሁ
አሃሃሃሃሃ
A Thing of beauty is a joy Forever