እናቶች፣ “ሶሻል ሚዲያ”ና ህወሃት/ኢህአዴግ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

እናቶች፣ “ሶሻል ሚዲያ”ና ህወሃት/ኢህአዴግ

Postby ደሊል » Thu Oct 06, 2016 4:34 pm

" አዲስ አበባ የሰፈር ሴቶችን ሰብስበው መግለጫ ስለ social media አጠቃቀም ስጡ ተብለው የሰጡት መግለጫ እና ከመግለጫው በኋላ ለእናቶች የተደረገ ኢንተርቪው።
ዜና FBC ፦

“መንግስት በሶሻል ሚዲያው ላይ ህዝብ የሚቀሰቅሱትን ጸረ-ሰላም ሃይሎች ከሚኖሩበት አገር ጋር በመመካከር ለህግ ማቅረብ አለበት!” ሲሉ ነዋሪነታቸው በቀበሌ 07 ልደታ ክከ የሆነ እናቶች ተናገሩ …
↩ ከዜናው በኋላ የእናቶች ኢንተርቪው፦

☞ የመጀመሪያዋ ተጠያቂ እናት (በግምት ከ 60 – 65 አመት እድሜ)፦

ጋዜጠኛ፦ እናት ለቃለ መጠይቅ ፈቃደኛ ስለሆኑ አመሰግናለሁ
እናት፦ እኔም አመሰግናለሁ እልልልልል …

ጋዜጠኛ፦ ምነው እናት? እልልታው ምንድነው??
እናት፦ የገደሉት ለህግ ይቅረቡ አይደለም እንዴ ሲባል የነበረው???

ጋዜጠኛ (በድንጋጤ ክው ብሎ)፦ የለም የለም እናቴ ሶሻል ሚዲያ ነው የተባለው፣
እናት፦ (ዝም ይላሉ ግራ ተጋብተው)

ጋዜጠኛው (ቀጠለ)፦ እናቴ ሶሻል ሚዲያ ማለት ምን ማለት ነው??social-media
እናት፦ ምን አውቃለሁ እኔ ቶታል ሚዳ ሲሉ ነው የዋሉት ያው ቶታል እኔ ማውቀው ነዳጅ ማደያ ነው፣ እንግዲ ስጠረጥር ነዳጅ ሊወደድ ነው መሰለኝ፣ ልጄ ባጃጅ አለችው ገዝቶ በጄሪካን እንዲያስቀምጥ መስማቴ ጥሩ ነው።

ጋዜጠኛ (ግርም ብሎት)፦ ከዚህ ስብሰባ እንዲያው ምን አገኙ??
እናት፣ አቤት ምሳ በላነው! ምሳው ግሩም ነው! በዛ ላይ እነዛ ከይሲወች ነዳጅ ሊያስወድዱ ነው ተብሏል እንግዲህ ይሄን ነው ከዚህ ስብሰባ የተረዳሁት።


ሁለተኛዋ ተጠያቂ፦ የ 65 አመት እናት

ጋዜጠኛ፦ እናቴ ለቃለ መጠይቅ ፈቃደኛ ስለሆኑ አመሰግናለሁ፣
እናት፦ እሺ

ጋዜጠኛ፦ እናቴ ሶሻል ሚዲያ ምን ማለት ነው??
እናት፦ እኔ ምን አውቃለሁ ሶሻሜዳ ሶሻሜዳ፣ ሶሻሜዳ፣ ይላሉ ያው እንግዲህ ሽሮሜዳ ብጥብጥ ተነስቶ ይሆናላ ልጄ።

ጋዜጠኛ፦ እንዲያው ከዚህ ስብሰባ ምን ተማሩ??
እናት፦ በመጀመሪያ የበላነው ምሳ ወደር የለውም፣ አይ ሙያ! አይ ሙያ! በመቀጠል ደግሞ ይቺ ኤርትራ እያቃጠረች በሽሮሜዳ ብጥብጥ ማስነሳቷ አዝኛለሁ።

ጋዜጠኛ፦ ውድ የሬዲዮ አድማጮቻችን እንደሰማችሁት ስብሰባው የታቀደለትን አላማ ያሳካ እንደነበር ለመገንዘብ ችለናል። "
ደሊል
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 154
Joined: Mon Dec 22, 2003 9:00 pm

Re: እናቶች፣ “ሶሻል ሚዲያ”ና ህወሃት/ኢህአዴግ

Postby ክቡራን » Thu Oct 06, 2016 6:16 pm

ቅቅቅቅቅቅ..ውይ አምላኬ ወደው እይስቁ ከምር ስቄም አላቅም ነበር ሰሞኑን ....በጣም ነው ያሳቀኝ ይሄ ቃለ ምልልስ...ቅቅቅቅ ! እስኪ ይሁን፡፡
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7990
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm


Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 0 guests