ሰው...

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ሰው...

Postby ክቡራን » Sat Feb 18, 2017 1:46 pm

ሰው
✿ ካላገባህ መቼ ነው የምታገባው ?
✿ ካገባህ መቼ ነው ልጅ የምትወልደው ?
✿ ሁለት ልጅ ካለህ መቼ ነው ሶስተኛ የምትደግመው
✿ ትዳርህ ጥሩ ካልሆነ ፍቺ እያለ ለምን እንዲህ ትሆናለህ
✿ ከትዳር አጋርህ ስትፋታ ምነው ትንሽ ታግሰህ በነበረ
✿ ጥብቅ ሰው ከሆንክ ምነው ከሰው አትቀላቀልም
✿ ከሰዎች ተቀላቅለህ ስትጨዋወት ምነው ወሬ አበዛህ
✿ ቁምነገረኛ ሰው ከሆንክ ምን አይነት ሻካራ ሰው ነህ
✿ በጥቂቱ ቀልደኛ ከሆንክ ቁምነገር የለህም
✿ አንዳንዴ ቁምነገረኛ አንዳንዴ ቀልደኛ ስትሆን የምትጨበጥ ሰው አይደለህም
በቃ ሁሌም ማውራት ነው!
♥ ስትወፍር → ያወራሉ
♥ ስትከሳም → ያወራሉ
♥ ረዥም ከሆንክ → ያወራሉ
♥ አጭር ከሆንክ → ያወራሉ
♥ መካከለኛ ከሆንክ → ያወራሉ
♥ ---- ከሆንክ → ያወራሉ
♥ ጎበዝ ከሆንክ → ያወራሉ
♥ ድሃ ከሆንክ → ያሾፉብሃል
♥ ሃብታም ከሆንክ → ይቀኑብሃል
♥ ስራ ከሌለህ → ይንቁሃል
♥ ስራ ስትሰራ → ያሙሃል
ፌስ ቡክ ወይንም ሶሻል ሚዲያ ላይ..
☞ ረዥም ስትፅፍ → «አሳጥረው»
☞ አጭር ስትፅፍ → «አብራራው»
☞ ምንም ካልፃፍክ → «ዳዕዋ አድርግ እንጂ?»
☞ ዝም ስትል → « ምከረን እንጂ»
☞ ሐቅ ስትፅፍ → « ለምን ፃፍከው!»
☞ ከተሳሳትክ → «ድሮም‘ኮ ..»
☞ ክረምት ሲሆን → «ወየው ብርዱ»
☞ በጋ ሲሆን → «አረረ ሙቀቱ»
☞ ሰዎች ሁሌም ሙሉ በሙሉ እርካታ አይሰማቸውም!
ሰውን እርሳውና ፈጣሪህን አስደስት!
ምንጭ ፌስ ቡክ፡፡
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7944
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 3 guests

cron