ይልማ ሃብተየስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ይልማ ሃብተየስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡

Postby ዘርዐይ ደረስ » Tue Apr 18, 2017 10:42 pm

በኢትዮጵያ ሥነ ፅሑፍ ታሪክ የወንጀል ነክ ልብወለድ ፈር ቀዳጅ ከነበሩት ደራሲያን አንዱና ዝነኛው ደራሲ ይልማ ሃብተየስ በትላንትናው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡ከማስታውሳቸው መፃሕፍቱ መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡ሌሎቻችሁ የቀረውን እንደምትጨምሩበትና ስለ ዝነኛውና አንጋፋው ደራሲ የምታውቁትን እንደምታካፍሉን ተስፋ አደርጋለሁ፡፡በተራ ቁጥር 3፣4፣5፣6 የተጠቀሱት በድርማ መልክ ተሠርተው በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ቀርበው እንደነበር ይታወሳል፡፡
1እሱን ተይው 2)እትዬ ላድርስ 3)ደስ ያለው ሐዘንተኛ 4)ከቀብር መልስ 5)ደም የነካው እጅ( 6)ያልተከፈለ ዕዳ7)ያልታደለች በሰው ሠርግ ተዳረች
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1096
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: ይልማ ሃብተየስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡

Postby humaidi » Wed Apr 19, 2017 10:01 am

ሂወቱን ይማረው
humaidi
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1741
Joined: Tue Jan 03, 2006 11:50 am

Re: ይልማ ሃብተየስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡

Postby እሰፋ ማሩ » Wed Apr 19, 2017 11:52 am

April 18, 2017 – ቆንጅት ስጦታው
እውቁ የወንጀል ምርመራ ልቦለድ ደራሲ ይልማ ሃብተየስ በ79 ዓመታቸው አረፉ፡፡
ይልማ ሀብተየስ ማን ናቸው?
በአዲስ አበባ ከተማ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን አካባቢ ከራስ ዳምጠው ሆስፒታል ጀርባ ልዩ ስሙ ነጋዴ ሰፈር በ1930 ዓ.ም ተወለዱ፡፡በቄስ ትምህርት ቤት ዳዊት የደገሙ ሲሆን ከ1940ዓ.ም አስከ 1947ዓ.ም መጨረሻ ድረስ በሊሴ ገ/ማርያም ት/ቤት ተምረዋል፡፡
ከ1948 ዓ.ም ጀምሮ በፓስተር ኢንሲቲትዩት ውስጥ የተሰጠውን የላቦራቶሪ ቴክኒሺያንነት ኮርስ በመውሰድ እስከ 1949ዓ.ም መጨረሻ ድረስ በራስ ደስታ ሆስፒታል የስራ ልምምድ ሲያደርጉ ቆዩ፡፡
ከ1950 ዓ.ም እሰከ 1952ዓ.ም በጎንደር ጤና ጥበቃ ኮሌጅና ማስልጠኛ ማዕከል የሜዲካል ላቦራቶሪ ስልጠና ተከታትለዋል፡፡
በ1953 ዓ.ም ኢትዮ ስዊዲሽ ፔዲያትሪክ ክሊኒክ በቴክኒሺያንንት ተቀጠሩ፡፡
ከ1957ዓ.ም -1958ዓ.ም ለሁለት አመታት ሲዊዲን ሀገር በሚገኘው የኡፕሳላ ዩኒቨርስቲ አካል በሆነው ሜዳካል ኬሚስትሪ ኢንስቲትዩት የሚሠጠውን የምግብ ኬሚስትሪ ( food analysis ) አጥንተዋል፡፤
ከ1959ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ ምግብ ጥናት ኢንስቲትዩት( Ethiopian Nutrition Institute ) በመቀጠር ጡረታ እስከወጡበት 1986 ዓ.ም ድረስ አገልግለዋል፡፡
የድርሰት ስራዎቻቸው፦
ከ1955ዓ.ም -1964 ዓ. ም በግላቸው ያሳተሟቸው፦
1.ያልታደለች በሰው ሰርግ ተዳረች
2. እትዬ ላድርስ
3.ለወጉ ለአርባ ስምንት ሰዓት ተጋቡ
4.አርሱን ተይው
5.ከቀብር መልስ
6.ሳይናገር ሞተ
7. ደስ ያለው ሀዘንተኛ
የኢትዮጵያ መጽሐፍ ድርጀት ያሳተማቸው( ከ1978 -1981)
1.ያልተከፈለ እዳ ( 20 000 ኮፒ )
2.አጋጣሚ (20 000 ኮፒ)
3.የአበቄለሽ ኑዛዜ( 10 000 ኮፒ )
4.ሶስተኛው ሰው( 15 000 ኮፒ)
5.ደላላው (15 000 ኮፒ)
6.ሌላው እጅ (15 000 ኮፒ)
7.ወዳጅ በወዳጁ 15 000 ኮፒ)
በጋሽ ክብሩ መጽሐፍት መደብር የታተሙ
1.ደም የነካው አጅ (3 000 ኮፒ)
2.ሞት ፈረዱ (3 000 ኮፒ)
3.የቤቱ መዘዝ (3 000 ኮፒ)
የቴሌቪዢን ድራማዎች፦
በ1968 ዓ.ም ደም የነካው እጅ ፤
በ1969 ዓ.ም ቁጭ ብለው አይሞቱም
በ1974 ዓ.ም ያልተከፈለ እዳ
በ1975ዓ.ም የአበቄሌሽ ኑዛዜ
በ1975ዓ.ም ሞት ፍለጋ ሄደች
በ1976ዓ.ም አስታራቂ
በሜጋ የኪነጥበብ ማዕከል በ1990 ዓ.ም ” አጋጣሚ ” በፊልም ተቀርፆ ለህዝብ ቀርቧል፡፡ደረሲ ይልማ በወንጀል ምርመራ ታሪክ ላይ ባተኮሩ ልቦለዶችና የቴሌቪዢን ድራማዎችን በማስተዋወቅ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሱ ሲሆኑ ከ50 ዓመታት በላይ በሙያው ላይ ቆይተዋል፡፡
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1550
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm

Re: ይልማ ሃብተየስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡

Postby ክቡራን » Thu Apr 20, 2017 6:07 am

ደራሲ ይልማን ነፍሳቸውን ይማር!! እሰፋ ማሩ እረ ያንተስ ጉዳይ እንዴት ነው ? መቼ ነው?? መሬት እኮ ዋይ ዋይ አለች ጮሃች...ከዚህ በላይ የመሸከም አቅም የለኝም አለች እኮ ቻይ ናት የምትባለዋ መሬት..ሎል
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8026
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Re: ይልማ ሃብተየስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡

Postby እሰፋ ማሩ » Thu Apr 20, 2017 7:44 pm

ያ ከይሲ ሙት መሪህ የቅንጅቱ መሪዎችን በግፍ ሲያስር በትእቢት "ስላረጁ ውጭ ሆነው በህመም እንዳይሞቱ ነው ያስረናቸው" ብሎ ሲቀልድ እራሱ ቀድሞ ፍግም እንዳለ ቀድመህኝ ትደፋለህ! ደማቸው በዘመዶችህ የፈሰሰው የየዋሆቹና ቅኖቹ ወገኖቻችን አምላክ ይጥረግህ!ከነፍሰገዳዮች በቀር የስጋ ሞት ለማንም የዘላለም ሞት ደግሞ ለሁሉም ስለማልመኝ ከመሞትህ በፊት ለኑዛዜህ እንድትጠራኝ ፈጣሪ ያብቃህ!
የይልማ ሃብተየስን ፈለግ የሚከተል እውነትን ብቻ የሚዘግብ ደራሲ ፈጣሪ ይስጠን አሜን!

በሞት መላእክት የሚነዳው wrote:ያንተስ ጉዳይ እንዴት ነው ? መቼ ነው??
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1550
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm

Re: ይልማ ሃብተየስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡

Postby ክቡራን » Fri Apr 21, 2017 4:06 am

እሰፋ ማሩ/ዲጎኔ/እርኩስ መንፈስ wrote:ያ ከይሲ ሙት መሪህ የቅንጅቱ መሪዎችን በግፍ ሲያስር በትእቢት "ስላረጁ ውጭ ሆነው በህመም እንዳይሞቱ ነው ያስረናቸው" ብሎ ሲቀልድ እራሱ ቀድሞ ፍግም እንዳለ ቀድመህኝ ትደፋለህ! ደማቸው በዘመዶችህ የፈሰሰው የየዋሆቹና ቅኖቹ ወገኖቻችን አምላክ ይጥረግህ!ከነፍሰገዳዮች በቀር የስጋ ሞት ለማንም የዘላለም ሞት ደግሞ ለሁሉም ስለማልመኝ ከመሞትህ በፊት ለኑዛዜህ እንድትጠራኝ ፈጣሪ ያብቃህ!
የይልማ ሃብተየስን ፈለግ የሚከተል እውነትን ብቻ የሚዘግብ ደራሲ ፈጣሪ ይስጠን አሜን!

በሞት መላእክት የሚነዳው wrote:ያንተስ ጉዳይ እንዴት ነው ? መቼ ነው??


ቀና የሆነውን አምላክ ክፉ ነገር እንዲያመጣና እንዲሰራ አትገፋፋ !! አይባልም፡፡ ባክ ፋየር አድርጎ እንዳያስተኛህ..ሎል... ደሞ ምክር ነው መጥፎ ተመኘልኝ ብለህ አትንጨርጨር!! እኔ የመሬትን ቁዋንቁዋ ስለምሰማ ያለችውን አምጥቼ እንጂ ከራሴ የጨመርኩት ምንም ነገር የለም..ጉድ እኮ ነው ዘንድሮ!! ይሄ ሁሉ ውርጅብኝ በኔ ላይ ...ሎል
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8026
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Re: ይልማ ሃብተየስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡

Postby ክቡራን » Fri Apr 21, 2017 10:03 pm

እሰፋ ማሩ wrote:ያ ከይሲ ሙት መሪህ የቅንጅቱ መሪዎችን በግፍ ሲያስር በትእቢት "ስላረጁ ውጭ ሆነው በህመም እንዳይሞቱ ነው ያስረናቸው" ብሎ ሲቀልድ እራሱ ቀድሞ ፍግም እንዳለ ቀድመህኝ ትደፋለህ! ደማቸው በዘመዶችህ የፈሰሰው የየዋሆቹና ቅኖቹ ወገኖቻችን አምላክ ይጥረግህ!

በሞት መላእክት የሚነዳው wrote:ያንተስ ጉዳይ እንዴት ነው ? መቼ ነው??

ወይ ጉድ ምን ክፉ ነገር ተናግሬ ነው ግን ይሄ ሁሉ ውርጅብኝና እርግማን እንዲህ የሚወርድብኝ ? መሬት ዋይ ዋይ!! አለች ብዬ የመሬትን ብሶት ባስተጋባሁ ይሄ ሁሉ ስድብ በኔ ላይ ይደርሳል?? እንድው ግን ምን አይ ነት ዘመን ላይ ደረስን ጃል!? እስኪ ይሁን...." ጦር ሲያነሱባችሁ በፍቅር መልሱ" ይላል መጽሃፍ፡፡ ትቸዋለሁ እሰፋ ማሩ aka ዲጎኔ ሎል..
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8026
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Re: ይልማ ሃብተየስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡

Postby ዘርዐይ ደረስ » Sat Apr 22, 2017 5:36 pm

ሰላም እሰፋ ማሩ:-
አንተ ያቀረብከው መረጃ የተሟላ ይመስላል::መረጃውን ላሰባሰበውና አንተም ወደዚህ ስላመጣኸው አመሰግናለሁ::ይልማ ሃብተየስ እንዳሁኑ ሳይሆን መጽሐፍ ማሳተም ብርቅ በነበረበት ወቅት በርካታ መጽሐፍትን (ያውም በአገራችን ባልተለመደ የሥነጽሑፍ ዘርፍ) ማበርከት መቻሉ ዘመን ያልሻረው አሻራ ትቶ ለማለፍ አስቸሎታል::
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1096
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: ይልማ ሃብተየስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡

Postby እሰፋ ማሩ » Wed May 03, 2017 8:21 pm

ዘርዐይ ደረስ
ደራሲ ይልማ በዚያን ዘመን የማሳተም ችግር ሳይበግረው ማሳተሙ ይደነቃል፡፡በአሁኑ ወቅት ደግሞ ባለው የፕሬስ አፈና ማተሚያቤቶች ፖለቲካ ነክ ለማሳተም አይፈልጉም በየምክንያቱ ደራሲዎች ለእስርና ለስደት ለሞትም በቅተዋል፡፡የበለጠ የማደንቀው በዚህ ሁኔታ ያሉ ደራሲያንና አሳታሚዎችን ነው፡፡የፕሬስ መብት ተሟጋቹ CPJ ችግሩን ያብራራል፡-
Ethiopia's independent publishers may face another hurdle
By A CPJ Guest Blogger
Text Size Print
Share
Newspapers are significant in Ethiopia because there are no other independent media sources in the country. (Ethiopia Forums)
Newspapers are significant in Ethiopia because there are no other independent media sources in the country. (Ethiopia Forums)
In what appears to be one of a collection of measures to silence the press ahead of 2015 elections, Ethiopian authorities in the Communications Ministry are preparing a new system to control the distribution of print media. Privately owned newspapers and magazines, possibly the only remaining independent news sources in the country, would face more state control if the proposal is set into motion.
Originally proposed in February, the new measures are still at a draft stage. They aim to ensure that private newspapers and magazines are distributed through one company with links to the ruling party, according to local journalists.
The proposal, entitled "A Draft Document for Making the Print Media Accessible," claims that supporters of the opposition are mainly in control of the current newsprint distribution system, according to the draft proposal in my possession.
Members of the media and some observers have sharply criticized the government's move to hand over circulation to a single company. The step comes after the anti-terrorist law of 2009, which criminalized reporting on opposition groups and has intimidated many journalists into self-censorship. Since 2011, 11 journalists have been given harsh prison terms under Ethiopia's anti-terrorism law, and five are currently serving sentences under this legislation.
While the reach of independent newspapers is negligible, with roughly 90,000 copies a week circulating in a population of 90 million, the papers are significant because there are no other independent media sources in Ethiopia. The state controls the only television station, and out of five privately-operated radio stations, three are wholly pro-government while the rest toe the state line.
"I am suspicious of this move," said freelance journalist Betre Yacob. "These enterprises are created by the government to push their own political agendas and interests. I am sure this particular case will be similar--where the distribution company is used to ensure only positive government news is distributed." Betre is president of the independent Ethiopian Journalists Forum, a contributor to several Ethiopian news sites, and a former political columnist for the now-defunct local magazine Ebony.
Currently, publishers of newspapers and magazines either distribute directly to retailers across the country, or contract trusted private distributors to do so for them. Under the new proposal, a company with direct government links would take copies from the printers and control distribution. Local journalists fear that the new company would block distribution if the government deems a publication too critical.
According to the draft proposal, print media suffers from the lack of a legal framework governing the current distribution system. The proposal claims most distributors do not have designated areas in which to circulate or proper identification. It also suggests that giving the distribution work to a company with some information about the media will help the industry as well as create jobs for youth.
However, independent journalists argue that the biggest challenge for Ethiopia's media industry is not the print distribution system but government intervention and suppression of the flow of free information. "The government should take its hands off the media. Giving the distribution of newspapers and magazines to a politically motivated enterprise does not solve the problem," Betre said. "Instead it just adds fuel to a fire."
Another bad sign for publishers is a study conducted this year by the pro-government Ethiopian Press Agency, a state-controlled news wire, analyzing the editorial content of certain magazines. Published in February, the study claimed that seven magazines were responsible for inciting violence and terrorist acts and upholding opposition viewpoints, according to local news reports.
Local journalists working for these publications fear that the study will be used as a pretext to censor them. "Magazines are some of the few independent publications left in circulation here," said one local journalist based in the capital, Addis Ababa, who did not wish to be identified for safety reasons. Betre concurs, saying, "The release of this research could indicate that the government is preparing to silence these magazines."
The prohibitive cost of printing in Ethiopia also serves as a barrier to media freedom. Because of a fear of censorship from the state printer, independent publications prefer to use private printers, even though they often lack the capacity to produce sufficient copies. At times, security agents infiltrate these private printing companies, local journalists said. "It is very challenging to find a printing house willing to publish independent publications," Betre said. "Sometimes agents warn printing houses not to print a particular publication and so they fear any association with the private press."
These challenges, along with high taxation, are already having a detrimental effect on independent publications. While newspapers pay a reasonable publishing tax of two percent of their sales after printing each edition, annual taxes can sometimes equal a months' total sales revenue, if not more. After six years in circulation, the local Ebony magazine closed in April due to the high annual income tax and printing costs, according to a local news report. Authorities recently demanded business income tax of 143,000 birr (US$7,300) from the independent newspaper Ethio-Midhar, an amount equivalent to their annual gross revenue, the same report said.
Unlike overt political interference such as the recent jailing of nine journalists, which has drawn a local and international outcry, these economic measures have the potential to undermine an alternative Ethiopian narrative without drawing public attention. If adopted, the new distribution system would subtly but effectively silence any critical publication ahead of May 2015 elections.
The author is an Ethiopian journalist in exile. He chooses not to be identified for his security.
ዘርዐይ ደረስ wrote:ሰላም እሰፋ ማሩ:-
አንተ ያቀረብከው መረጃ የተሟላ ይመስላል::መረጃውን ላሰባሰበውና አንተም ወደዚህ ስላመጣኸው አመሰግናለሁ::ይልማ ሃብተየስ እንዳሁኑ ሳይሆን መጽሐፍ ማሳተም ብርቅ በነበረበት ወቅት በርካታ መጽሐፍትን (ያውም በአገራችን ባልተለመደ የሥነጽሑፍ ዘርፍ) ማበርከት መቻሉ ዘመን ያልሻረው አሻራ ትቶ ለማለፍ አስቸሎታል::
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1550
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm


Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest