ጫት ብዙ ዶላር ስለሚያስገኝ በአደንዛዥነት አልተቆጠረም

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ጫት ብዙ ዶላር ስለሚያስገኝ በአደንዛዥነት አልተቆጠረም

Postby እሰፋ ማሩ » Wed May 17, 2017 3:32 am

ጫት በአለም ጤና ድርጅት በአደንዛዥ ሱስ አስያዥነት የተመዘገበ ቢሆንም በሃገራችን ብዙ ዶላር ስለሚያስገባ በአደንዛኝነት ሊታወቅ አልቻለም፡፡ፕሮፌሰር ህዝቅያስ ገቢሳ አንድ ሰሞን ሪፖርተር ጋዜጣ ላይ አደንዛዥ አይደለም ስላሉ ተገቢ የሙያ ተቃውሞ ቀርቦላቸው ነበር፡፡ በአሁኑ ሰአት ርእሰ ብሄር ተብየው ሃይለመለስም የአደንዛዥነቱ ማስረጃ እስኪደርስ ድረስ ዶላሩን እንበላለን ብለዋል፡፡
----------------------///////////////////////////////////////////////////////--------------------------------------------------------------///////////////////////////////

በጫት ተሸነፍን ይሆን? በሲቲና ኑሪ
May 14, 2017 – ቆንጅት ስጦታው
በጫት ተሸነፍን ይሆን?
በሲቲና ኑሪ (አዲስ አድማስ ጋዜጣ )
ሰሎሞን የኔነነህ (ስሙ ለዚህ ጽሑፍ ሲባል የተቀየረ) ኑሮውን መቐለ ከተማ ያደረገ፣ ወደ አዲስ አበባ በሚመጣባቸው የስራ አጋጣሚዎች የመገናኘት ዕድሉ ያለን የረጅም ዓመታት ወዳጄ ነው። በቅርቡ እንደወትሮው ሁሉ ከሰሎሞን ጋር ተገናኝተን ስለ ሥራ፣ ኑሮና ልጆች ከተጠያየቅን በኋላ፤ በድንገት:
“ጫት አቆምኩ” አለኝ በድል አድራጊነት ስሜት፤እኔም ‹‹በእውነት?›› አልኩት፤
ፈጠን ብሎ ‹‹አዎ! አቃተኝ! ልጆቼን ከትምህርት ቤት ማምጣት ተሳነኝ፣ እንዴት ልነሳ ጫቱን ትቼ” አለኝ እጆቹን እያወራጨ።ጫት ሁለመናውን ሽባ አድርጎት እንደነበር ለማወቅ ፊቱን ማየት ብቻ በቂ ነበር፡፡ ሰሎሞን ጫት በዘመናችን ያመጣው ጣጣ አይነተኛ ማሳያ (microcosm) ነው፡፡ ከሰሎሞን ተነስተን ስንቶቹ ከስራ ገበታቸው እንደተፈናቀሉ፣ ትዳራቸውን እንደበተኑና ከኑሯቸው እንደተጣሉ መናገር የአደባባዩን እውነታ መድገም ነው የሚሆንብን።
“The poison leaf”
ብሪታኒያ ወደ አገሯ በዓመት ከሚገባው 2560 ቶን ጫት ላይ 2•5 ሚልየን ፓውንድም አመታዊ የታክስ ገቢ እንደምታስገባ ሪፖርቶች ያሳያሉ። ነገር ግን ይህ ትርፍ ጫትን ወደአገሯ እንዳይገባ ከማድረግ አላገዳትም። የቱንም ያህል ከአንዳንድ የፓርላማ አባላት ተቃውሞ ቢገጥመውም፣ በመጨረሻም ጫት በአደንዛዥ እፅነት ተመድቦ ከተከለከሉ እፆች ተርታ ለመካተት በቅቷል። ለክልክለው መሰረት የሆነውም የዓለም የጤና ድርጅት ጥናቶች ናቸው፡፡
ጫትን አስመልክቶ ሁለገብ ርዕሶችን በማካተት ከስምንት ዓመታት በፊት “The Khat Controversy: Stimulating the Debate on Drugs” በሚል ርዕስ በአራት ፀሃፍት የተዘጋጀው ጥናት የጫትንና የአዕምሮ ጤናን ግንኙነት አስመልክቶ 41 የተለያዩ ጥናቶችን ጨምቆ ያቀረበ ሲሆን በውጤቱም ጫት የአዕምሮ ጤና ችግርን አባባሽ ብቻ ሳይሆን ዋነኛ መነሻም እንደሆነ ያስረዳል::በጫት የጤና ጠንቅነት ላይ እጅግ ብዙ ጥናቶች በተለያዩ ደረጃዎች የተሰሩ ሲሆን፣ ከላይ ካነሳነው በተጨማሪ በሳኡዲ አረቢያው ጃዘል ዩኒቨርሲቲ ጥናት ያቀረቡት ዶ/ር ሁሴን አጊሌ በየመን ውስጥ በ1118 አዲስ የተወለዱ ህፃናት ላይ የተደረገ ጥናትን ጠቅሰው እንዳመላከቱት በሕፃናቱ ላይ የክብደት መቀነስ እንደሚታይና ይህም የሆነው በእርግዝና ወቅት እናቶች ጫት ተጠቃሚ ስለነበሩ እንደነበረ ይገልፃሉ። ከዚህም ሌላ የሆድ ድርቀት፣ እንቅልፍ ማጣት፣ የአዕምሮ እረፍት ማጣት፣ ጥርስ/ድድ (dental cavities) ጉዳት መድረስና ደም ግፊትንም የመሳሰሉ የጤና መዛባቶችን እንደሚያስከትል ዶክተሩ “Health and Socio-economic Hazards Associated with Khat Consumption” ጽሁፋቸው ላይ አበክረው ገልፀዋል። ከተለያዩ ጥናቶችና የቤተ ሙከራ ግኝቶች በመነሳት የዓለም የጤና ድርጅት (WHO) ጫት Cathine እና Cathinone የተባሉ አደገኛና መራዥ ንጥረ ነገሮችን መያዙን በጎርጎሮሳዊያኑ አቆጣጠር በ2006 ባደረገው አሰሳም ይፋ አድርጓል።
“Leaf of Allah”
‹‹ጫት ፈጣሪ የሚወደው ዛፍ ነው፡፡ በፈጣሪ ተባርኮ ለእኛ የተሰጠን ውድ ስጦታ፡፡ ይህ የተባረከ ዛፍ ላይ ሰው ምንም ስልጣን የለውም፡፡ የተለያዩ ሰዎች ጫትን ለማጥፋትና ለመቆጣጠር ዋጋውን በማናር ጭምር ሞክረዋል፤ ማንም ግን አልተሳካለትም፡፡ ጫት እኮ ተራ አትክልት አይደለም፤ ጫት የአላህ ቅጠል (leaf of Allah) ነው፡፡››
ይህን የሚሉን አደም አልዩ ጄላን የተባሉ የአወዳይ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ሽማግሌ ሲሆኑ፤ ዶ/ር ሕዝቅኤል ገቢሳ ከአስራ ሶስት ዓመታት በፊት “Leaf of Allah Khat & Agricultural Transformation in Harerge, Ethiopia, 1875–1991” በሚል ርዕስ ባሳተሙት የጫትን የመቶ ዓመታት የምስራቅ ኢትዮጵያ ታሪክ በሚያወሳው መጽሐፋቸው ካናገሯቸው ግለሰቦች አንዱ ናቸው፡፡ ለሽማግሌው ዓደም ጫት ኢኮኖሚያዊ፣ ማሕበራዊና መንፈሳዊ መሰረት የሆነ በፈጣሪ ትዕዛዝ ለሰው ልጆች የተበረከተ ስጦታ ነው። ይህ ስሜት ግን የዓደም ብቻ አይደለም፡፡
ካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ በፈረንጆቹ መስከረም 2016 የደቡብ ክልልን እንደመነሻ ወስዶ ባስጠናው ጥናት በርካታ ቤቶች የጓሮ አትክልት ልማትን ወደ ጫት ማሳነት መቀየራቸውን ተከትሎ ለምን ወደዚህ ዘርፍ እንደገቡ ጠቅለል ያለ ፅሁፍ አቅርቦ ነበረ። በጥናታዊ ጽሑፉ እንደተመለከተውም በ1980 ከ40 አባወራዎች አንዱ ብቻ የጫት ማሳ እንደነበረው ጠቅሰው የነበረው ሲሆን፣ ከ1990 ወዲህ ግን ከ40 አባወራዎች ውስጥ 38ቱማሳቸውን ወደጫት ማሳነት እንደቀየሩት ያመላክታል፡፡ ይሄም አዲስ እውነታ ለእንሰትና ለተለያዩ ዛፎች ተይዞ የነበረው ቦታ እንዲቀንስ ማድረጉን ጥናቱ ጠቁሟል። አያይዞም ይህ እውነታ ያካባቢው አርሶ አደሮች ወደ ሌሎች ከተሞች አስቤዛ ሽመታ እንዲወጡ ማድረጉን ጥናቱ ላይ የተሳተፉ ግለሰቦችን ጠቅሶ ይገልጻል፡፡ በአስገራሚ ሁኔታም አንድ በጥናቱ ላይ የተሳተፉ ግለሰብን ጠቅሶ ለ20 ዓመታት በጫት ልማት ላይ እንደነበሩና አሁን ግን ወደ ቀድሞ እርሻቸው አይናቸውን መልሰው እንዳዞሩ በማተት ለዚህም እንደ ገፊ ምክንያት የሆነው በቤተሰባቸው ውስጥ ለምግብነት የሚውል የአትክልት እጥረት እንደሆነ ያትታል፡፡

ይህ ጥናት የሲዳማ ዞን ገበሬዎች የጓሮ አትክልታቸውን ወደ ጫት ማሳነት የቀየሩበትን ምክንያት ሲዘረዝር፤ የተሻለ ገንዘብ ማስገኘቱና የዘር አቅርቦት እና ማዳበሪያ እጥረት መኖሩን መሆናቸውን የጥናቱን ተሳታፊዎች አጣቅሶ ይገልፃል። እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ አቆጣጠር ከ1990 እስከ 2000 ባሉት አስር ዓመታት ውስጥ የጫት ዋጋ ከ9 ብር ወደ 45 ብር ከፍ ማለቱንና ያም በየ300 ኪ.ሜ ራዲየስ ውስጥ 20 የተለያዩ የጫት ገበያዎች እንዲከፈቱ ምክንያት ሆኗል ይላል።
ይሄንና መሰል ጥናቶች የሚያመላክቱት ነገር ቢኖር ጫት የኢትዮጵያን ግብርና ምን ያክል ሊቀይረው እንደሚችልና ራሷን መመገብ ያልቻለች አገር ላይ እንዲህ ያለ ተጨማሪ ፈተና ሲደረብ ደግሞ ‹‹በምግብ ራስን መቻል›› የሚባለውን ጉዳይ ወደ ተረትነት ሊቀይረው እንደሚችል ማሳያ ነው።
“The Dollar Leaf”
በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ጫት ከቡናና ከጥራጥሬ ምርቶች ጎን ለጎን የውጭ ምንዛሬ በማሰገኝት ተወዳዳሪ ያልተገኘለት ቅጠል ሆኗል፡፡ ‘The Dollar Leaf’ የሚለው ቅጥያውም ዘልቆ እየተሰማ ይገኛል፡፡ ለአገሪቱ አዲሱ የኢኮኖሚዋ ዋልታ ጫት በመቶ ሚሊዮን ዶላሮችን በየዓመቱ የሚያሳፍስ ቅጠል እንደሆነ የቅርብ ጊዜ መንግስታዊ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡የጫት ምርትን ከአገራችን ወደ ውጭ መላክ የተጀመረው በደርግ ዘመን ቢሆንም ኢሕአዴግ ስልጣን ከያዘበት 1983 ወዲህ በዘርፉ የሚገኘው የውጭ ምንዛሬ እያደገ ይገኛል፡፡ በ1983 ዓ.ም በዘርፉ የወጪ ንግድ ከ56 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የገንዘብና ኢኮኖሚ ቢሮ መረጃዎች ሲያመላክቱ፤ ከላይ ለመጥቀስ የሞከርኩት የካምብሪጅ ዩንቨርስቲ ጥናት ከ1990 ወዲህ ከአገር ውስጥ ሽያጩ ውጪ በጎርጎሮሳዊያኑ ጫትን ለውጭ ገበያ የማቅረቡ ሒደት በመንግስት ደረጃ፣ ለአብነትም በ2007 ዓ•ም ከጫት ንግድ 332 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ መገኘቱን የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን መረጃዎች ይጠቁማሉ። ከ2008 እስከ 2012 ዓ.ም 275 ሺ ቶን ጫት ወደ ውጭ በመላክ ከ 1.5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ለማግኘት ታቅዶ እየተሰራ እንደሆነ መንግስታዊው ዕቅድ ይጠቁማል።
በአጭሩ እጅግ እያደገ የመጣውና በጫት ላይ መሰረት በሚያደረገው የውጭ ንግድ ይህ በዓለማቀፍ ተቋማት እንደ መርዘኛ አደንዛዥ እፅ በሚቆጠር የሰብል አይነት ላይ ይሄን ያህል መደገፍ (rely) ለጊዜው ለአገሪቱ ዶላር ቢያመጣላትም ዘላቂ ያልሆነ፣ ቋሚና ዓለማቀፋዊ ተቀባይነት ያላቸውን ምርቶች ገፍቶ በኋላ አገሪቱን ታላቅ ኪሳራ ላይ እንዳይጥላት የሚያሰጋ ነው፡፡
ጫት በዓለማቀፍ ተቋማት በመርዘኝነት የታወቀ ቅጠል ሆኖ እያለ በኢኮኖሚያዊና ማሕበራዊ ምክንያቶች ስርጭቱ እጅግ እየሰፋ መሔዱ የማይካድ እውነት ቢሆንም ከዚህ ድምዳሜ ላይ ጥርጣሬ እንዳላቸው የሚገልፁ ግለሰቦችም አልጠፉም፡፡ ዶ/ር ኤፍሬም ተሰማ ከእነዚህ ተጠራጣሪዎች መካከል አንዱ ናቸው፡፡ ዶ/ር ኤፍሬም ለዶክትሬት ማሟያቸው በሰሩት ሥራ ላይ የጫትን አዎንታዊ ጎን ለማጥናት ሙከራ አድርገዋል። አያይዘውም በ1960ዎቹና 70ዎች በነበረው የትግል ንቅናቄ ወቅት ጫት የነበረውን አስተዋፅኦ ይገልጻሉ፡፡ በትግሉ ላይ ለነበሩ ወጣቶች ጫት የጀርባ አጥንት እንደነበረ አስረግጠውም ይናገራሉ፣ “ወጣቶቹ ፓምፍሌቶችን በማባዛት፣ ማርክሲስት ሌኒናዊ ርዕዮተ ዓለምን ሌሊቱን ሙሉ እያጠኑ ለመቆየት ጫት አስተዋፅኦ ነበረው” ይላሉ ዶክተር ኤፍሬም። በወቅቱ የነበረው እድገት በህብረት ዘመቻም ወጣቶቹን ከጫት ጋር ለማስተዋወቅ የራሱ የሆነ አስተዋፅኦ እንደነበረው ያትታሉ። በተጨማሪም እስከ 13ኛው ዘመን የሚመዘዝ ታሪካዊ ዳራ ያለውና በአብያተ ክርስቲያናት እና በገዳማት እንዲሁም በሙስሊሙ ማሕበረሰብ ውስጥ የተለያዩ አስዋፅኦ ያበረከተ ቅጠል እንደሆነ አበክረው ይናገራሉ፡፡ አስከትለውም ጫት ላይ ሕግና ፖሊሲ ከመርቀቁም በፊት ሰፊ ጥናት እንደሚያስፈልግና በዘርፉ ላይ ለመስራት የሚሳተፉ ቡድኖች ጥልቅ ምርምርን አድርገው ‹‹ጫት ይከልከል›› አልያም ‹‹አይከልከል›› የሚለው ነገር ቢወሰን የተሻለ ይሆናል ይላሉ።
ዶክተር ኤፍሬም ለዚህ ሐሳባቸው ሰሚ ያጡም አይመሰልም። ባሳለፍነው ዓመት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የምሁራን ስብሰባ ላይ የተገኙ ከጎንደር የመጡ መምህር የወጣቱን የጫት ሱሰኝነት ተከትሎ መንግስት ምን እንዳሰበ ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጥያቄ አቅርበው የነበረ ሲሆን፣ ጠቅላይ ምኒስትሩም የዶክተር ኤፍሬምን ጥርጣሬ በሚያንጸባርቅ መልኩ “ጫትን የመቃወም የመደገፍ አቋም የለኝም፣ ጫት ይጠቅማል፣ አይጠቅምም የሚሉ ወገኖች ምርምር አድርገው ተከራክረው ያሳምኑን። ያኔ በማስረጃ ጎጂ ነው ከተባለ እናስቆማለን፣ እስከዛው ድረስ ግን የሚያስገኘውን ዶላር እየበላን እንቆያለን” የሚል አስገራሚ መልስ ሰጥተው መንግስት ጫትን ለመቆጣጠር ፖሊሲ የማርቀቅም ሆነ ሕግ የማውጣትም ፍላጎት እንደሌለው ጠቆም አድርገው ነበር።ይህ በምዕራቡ ዓለም ከሚታየው የዓለም ሙቀት መጨመር ጋር ተያይዞ ከሚነሳው ክርክር ጋር እጅግ ተመሳሳይነት ያለው ሆኖ ነው ያገኘውት፡፡ ምንም እንኳን ለመቶ ዓመታት የተሰሩ እጅግ ብዙ የዓለም ሙቀት መጨመርን አስመልክቶ ጥናቶች ቢኖሩም አንዳንድ የአየር ንብረት መለወጥን የሚክዱ (Climate change deniers) ሊቃውንት ግን ‹‹የለም፤ የዓለም ሙቀት መጨመር ብሎ ነገር የለም›› ብለው በመካድ ለአንዳንድ ፖለቲከኞች የተሳሳታ የፖሊሲ ግብዓት ሲያቀርቡ ይታያል፡፡ ጫትና ተያያዥ ጉዳዮችን አስመልክቶም እጅግ ብዙ ጥናቶች የቅጠሉን ጎጅነት በመግለፅ በአገሪቱ ላለው የአዕምሮ ጤና መዛባት ላይ የራሱን አስተዋፅኦ እያበረከተ እንደሚገኝና፣ ኢኮኖሚያዊና ማሕበራዊ ኪሳራው እጅግ ብዙ እንደሆነ፤ እንዲሁም የንግድና የእርሻ ትስስር ላይ እጅግ አሉታዊ ተጽእኖዎች እንደሚያሳድሩ ቢጠቁሙም ‹‹የጫትን ጎጅነት የሚያመላክት ማስረጃ እስኪቀርብልን ድረስ የሚያስገኘውን ዶላር እየበላን እንቆያለን›› የሚለው የመንግስት ምላሽ በመግቢያዬ የጠቀስኩት ሰሎሞንና እሱን መሰሎቹ ቤት ሲበተንና የአዕምሮ ጤና መዛባት ከመቼውም ጊዜ በላይ በዜጎች ላይ ከተከሰተ በዃላ እርምጃ ቢወሰድ “ቀድሞውን ነበር እንጂ መጥኖ መደቆስ አሁን ምን ያደርጋል ድስት ጥዶ ማልቀስ” እንዳይሆንብን ያሰጋል።
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1504
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm

Re: ጫት ብዙ ዶላር ስለሚያስገኝ በአደንዛዥነት አልተቆጠረም

Postby humaidi » Wed May 17, 2017 8:14 am

እሰፋ ማሩ ቆንጅትን አንዴ ጫቱን ብትሞክር ኬፏን ነቅንቆ የጫት ያለህ ያሰኛታል፣ ሌላ ጊዜ አትተወውም፣ የዋዛ አይደልም ጫት !!!!! እንደ ካቲካላ አያሰተኛም !!! ከንቅልፏ ሰተነሳ የጫት ያለህ ያሰኛታል፣ ድንበሯን ጥሳ አትሄድም፣ ለሁሉ ጊዜም አሰታውሺን !!!!!!!!!!!!!! ሱሰኛ ያደርግሻል የጫት ያለህ ያሰኝሻል ሁሌ እንደ ሲጋራ ሱሰ ብን ያረግሻል ብለህ ንገርልኝ ! ደንበኛ ሱሰኛ ትሆኛለሸ !!!!! ካልቃመችው እንደ ሱሰኛ ያቅለበልባታል !!! ጤና ይሰጥለኝ ... አምሰግናለሁ .... ታሪኩን ሳታውቁት ዝም ብላችሁ ሰለ ጫት ትናገራላችሁ !!!!!

እሰፋ ማሩ wrote:ጫት በአለም ጤና ድርጅት በአደንዛዥ ሱስ አስያዥነት የተመዘገበ ቢሆንም በሃገራችን ብዙ ዶላር ስለሚያስገባ በአደንዛኝነት ሊታወቅ አልቻለም፡፡ፕሮፌሰር ህዝቅያስ ገቢሳ አንድ ሰሞን ሪፖርተር ጋዜጣ ላይ አደንዛዥ አይደለም ስላሉ ተገቢ የሙያ ተቃውሞ ቀርቦላቸው ነበር፡፡ በአሁኑ ሰአት ርእሰ ብሄር ተብየው ሃይለመለስም የአደንዛዥነቱ ማስረጃ እስኪደርስ ድረስ ዶላሩን እንበላለን ብለዋል፡፡

humaidi
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1741
Joined: Tue Jan 03, 2006 11:50 am

Re: ጫት ብዙ ዶላር ስለሚያስገኝ በአደንዛዥነት አልተቆጠረም

Postby እሰፋ ማሩ » Wed May 17, 2017 1:50 pm

የሃገሪቱ መሪ ተብዬ ገቢ እስካስገኘ ጫት ቢስፋፋፍ ግድ እንደሌለው ቢናገርም ህዝቡ ጫት መቃምን እያስቆመ ነው፡፡

ጫት በየቦታው እንዳይቃም፣ የጎጃሟ ሞጣ ከተማ በህግ ከልክላለች!!!
May 14, 2017 – ቆንጅት ስጦታው
የጫት ነገር!!…. ጫት ሽንት ሽንት ስለሚል ረጅም መንገድ እንኳ አያስጉዝም፡፡ ደግሞ ያቃዣል፡፡ከዛ ዱካክ ይለቃል!!!!ጫት በየቦታው እንዳይቃም፣ የጎጃሟ ሞጣ ከተማ በህግ ከልክላለች!!!
የሺሃሳብ አበራ
ኢትዮጲያ ካላት 70 ሚሊየን ሄክታር የሚታረስ መሬት 7 % (500 ሺ ሄክታር ) በጫት ተሸፍኗል፡፡ከአፍሪካ ጅቡቲ፣ሶማሊያ ፣በከፊል ኬኒያ ጫት መቃም ህጋዊ የሆነባቸው ሀገራት ናቸው፡፡ … የሶማሊያ ወታደር ጫት ሲቅም በአልሸባብ በራሱ መሳሪያ ይገደላል፡፡ጫት ለሶማሊያ አለመረጋጋት የራሱ አሉታዊ አስተዋፅኦ አለው፡፡ የየመንም እንደዚሁ፡፡በየመን 40% ውሃዋ ለጫት ይውላል፡፡የዓለም ጤና ድርጅት ግን በ 1972 ዓም ጫትን ጎጂ እፅ ብሎ ከፈረጀው በኋላ በአውሮፓ ና በአሜሪካ ተከልክሏል፡፡ የሙስሊም ሀገራት ሊቃውንት በሂጅራ የዘመን ስሌት በ 1402 5 ኛ ወር ላይ ከቀን 27-30 በተካሄደ ጉባኤ ጫት መቃም ተወግዟል፡፡ሀራም ሆኗል፡፡በሳውዲ፣በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ
… ጫት መቃም ወንጀል ነው፡፡ባለፈው ወር 20 ኢትዮጵያውያን ጫት ይዘው ተገኝተው በኩዌት እስርቤት ይገኛሉ፡፡
…….. በየመን በሄክታር ከጫት ገቢ 2.5ሚሊየን ዶላር በዓመት ገቢ ይገኛል፡፡እናም የየመን አርሶአደሮች ጫት አምራች ናቸው፡፡ግን ጫት ህዝቡን አደንዝዞ ዛሬ ላይ የመን የሞት ባድማ ሁናለች፡፡ …. ከወሎ ዮኒቨርሺቲ የተሰራ ጥናት እንደሚያመለክተው አማኑኤል ካሉ የአዕምሮ ሁሙማን መካከል 80% በጫት ና መሰል ሱሶች የታመሙ ናቸው፡፡ጫት የዕለት ምግብ እየሆነ ነው፡፡በ 2004 ዓ/ም ገቢዎች ና ጉምሩክ ባለስልጣን በጫት ላይ ተጨማሪ ታክስ 5% ጥሎ ነበር ፡፡ግን ተግባራዊ አልሆነም፡፡
… ዛሬ ላይ ጫት የጎጃምን ና የጎንደርን ማሳ ተቆጣጥሮታል፡፡ሀይ ባይ ካልተገኘ የፎገራ-ሩዝ፣ የጎንደር ሰሊጥ፣የጎጃም ጤፍ በጫት መተካቱ አይቀርም፡፡እንዲያውም ጣናም በጫት ተክል ስለተከበበ መጠኑ በከፍተኛ ደረጃ ሊቀንስ ይችላል፡፡ጫት ሲበዛ ውሃ መጣጭ ተክል ነው፡፡ .. በጣና የሚመረተው የባህርዳር ጫት ከድሬዳዋ እስከ ሀዋሳ ስሙ ይጠራል፡፡.እያሳሳቀ፣የዋህ፣ብሩህ ስሜትን ለጊዜው እየፈጠረ ጫት ነገን ይገላል፡፡በአማራ ክልል ከሚመረት ጫት 80% በሀገር ውስጥ ይቃማል፡፡ምንዛሬም አያመጣም፡፡በእርግጥ የጫት ገበያን እነ ሶማሊያ ሊዘጉት ዳር ደርሰዋል፡፡የመንም 20% ተጨማሪ ታክስ ስለጣለች ከጫት የሚገኝ ምንዛሬ አይኖርም፡፡የጫት ዓለም አቀፍ ገበያ እየተዘጋ ነው፡፡ የምንዛሬ አማራጭ ሊሆን አይችልም፡፡ስለዚህ የሚመረተው ሁሉ በሀገር ውስጥ መቃም ከተጀመረ ሀገሪቱ ሙሉ ቃሚ ትሆናለች፡፡አሁን በአንዳንድ አካባቢዎች ከሰዓት በኋላ ቢሮ ይዘጋል፡፡ሱቅ ዝግ ነው፡፡በቃ በጫት በስራ ላይ አድማ ይመታል፡፡ጫት ሲበዛ አስናፊ ነው፡፡ በእስልምናም በክርስትናም ጫት እንዲቃም አይበረታታም፡፡

…. ጫት ሽንት ሽንት ስለሚል ረጅም መንገድ እንኳ አያስጉዝም፡፡ ደግሞ ያቃዣል፡፡ከዛ ዱካክ ይለቃል፡፡ከሁሉም ነገር የከፋው ግን ለሌሎች ሱሶች መንገድ መሪ መሆኑ ነው፡፡ጫት የሚቅም በብዛት ያጨሳል፡፡ይጠጣል፡፡ጫት ብዙ ችግር ያስከትላል ፡፡ ያም ሆኖ ግን ጫት ጉባኤ ጠርቶ የሚያገናኘው ብዙ ደንበኛ አለው፡፡ …. ጫት በየቦታው እንዳይቃም፣ የጎጃሟ ሞጣ ከተማ በህግ ከልክላለች!!!ሌሎች ከተሞችም አካባቢኛ ህግ እየሰሩለት ነው፡፡
ከአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1504
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm

Re: ጫት ብዙ ዶላር ስለሚያስገኝ በአደንዛዥነት አልተቆጠረም

Postby humaidi » Wed May 17, 2017 1:59 pm

እድሜ ለወያኔ ትበል የጎጃሟ ሞጣ ከተማ ! ወያኔ የሰጣትን መብት ተጠቅማ በህግ ጫት መቃም ከልክላለች ! ብራቮ ወያኔ ብለናል !!!

እሰፋ ማሩ wrote:የሃገሪቱ መሪ ተብዬ ገቢ እስካስገኘ ጫት ቢስፋፋፍ ግድ እንደሌለው ቢናገርም ህዝቡ ጫት መቃምን እያስቆመ ነው፡፡

ጫት በየቦታው እንዳይቃም፣ የጎጃሟ ሞጣ ከተማ በህግ ከልክላለች!!!
May 14, 2017 – ቆንጅት ስጦታው
የጫት ነገር!!…. ጫት ሽንት ሽንት ስለሚል ረጅም መንገድ እንኳ አያስጉዝም፡፡ ደግሞ ያቃዣል፡፡ከዛ ዱካክ ይለቃል!!!!ጫት በየቦታው እንዳይቃም፣ የጎጃሟ ሞጣ ከተማ በህግ ከልክላለች!!!
የሺሃሳብ አበራ
ኢትዮጲያ ካላት 70 ሚሊየን ሄክታር የሚታረስ መሬት 7 % (500 ሺ ሄክታር ) በጫት ተሸፍኗል፡፡ከአፍሪካ ጅቡቲ፣ሶማሊያ ፣በከፊል ኬኒያ ጫት መቃም ህጋዊ የሆነባቸው ሀገራት ናቸው፡፡ … የሶማሊያ ወታደር ጫት ሲቅም በአልሸባብ በራሱ መሳሪያ ይገደላል፡፡ጫት ለሶማሊያ አለመረጋጋት የራሱ አሉታዊ አስተዋፅኦ አለው፡፡ የየመንም እንደዚሁ፡፡በየመን 40% ውሃዋ ለጫት ይውላል፡፡የዓለም ጤና ድርጅት ግን በ 1972 ዓም ጫትን ጎጂ እፅ ብሎ ከፈረጀው በኋላ በአውሮፓ ና በአሜሪካ ተከልክሏል፡፡ የሙስሊም ሀገራት ሊቃውንት በሂጅራ የዘመን ስሌት በ 1402 5 ኛ ወር ላይ ከቀን 27-30 በተካሄደ ጉባኤ ጫት መቃም ተወግዟል፡፡ሀራም ሆኗል፡፡በሳውዲ፣በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ
… ጫት መቃም ወንጀል ነው፡፡ባለፈው ወር 20 ኢትዮጵያውያን ጫት ይዘው ተገኝተው በኩዌት እስርቤት ይገኛሉ፡፡
…….. በየመን በሄክታር ከጫት ገቢ 2.5ሚሊየን ዶላር በዓመት ገቢ ይገኛል፡፡እናም የየመን አርሶአደሮች ጫት አምራች ናቸው፡፡ግን ጫት ህዝቡን አደንዝዞ ዛሬ ላይ የመን የሞት ባድማ ሁናለች፡፡ …. ከወሎ ዮኒቨርሺቲ የተሰራ ጥናት እንደሚያመለክተው አማኑኤል ካሉ የአዕምሮ ሁሙማን መካከል 80% በጫት ና መሰል ሱሶች የታመሙ ናቸው፡፡ጫት የዕለት ምግብ እየሆነ ነው፡፡በ 2004 ዓ/ም ገቢዎች ና ጉምሩክ ባለስልጣን በጫት ላይ ተጨማሪ ታክስ 5% ጥሎ ነበር ፡፡ግን ተግባራዊ አልሆነም፡፡
… ዛሬ ላይ ጫት የጎጃምን ና የጎንደርን ማሳ ተቆጣጥሮታል፡፡ሀይ ባይ ካልተገኘ የፎገራ-ሩዝ፣ የጎንደር ሰሊጥ፣የጎጃም ጤፍ በጫት መተካቱ አይቀርም፡፡እንዲያውም ጣናም በጫት ተክል ስለተከበበ መጠኑ በከፍተኛ ደረጃ ሊቀንስ ይችላል፡፡ጫት ሲበዛ ውሃ መጣጭ ተክል ነው፡፡ .. በጣና የሚመረተው የባህርዳር ጫት ከድሬዳዋ እስከ ሀዋሳ ስሙ ይጠራል፡፡.እያሳሳቀ፣የዋህ፣ብሩህ ስሜትን ለጊዜው እየፈጠረ ጫት ነገን ይገላል፡፡በአማራ ክልል ከሚመረት ጫት 80% በሀገር ውስጥ ይቃማል፡፡ምንዛሬም አያመጣም፡፡በእርግጥ የጫት ገበያን እነ ሶማሊያ ሊዘጉት ዳር ደርሰዋል፡፡የመንም 20% ተጨማሪ ታክስ ስለጣለች ከጫት የሚገኝ ምንዛሬ አይኖርም፡፡የጫት ዓለም አቀፍ ገበያ እየተዘጋ ነው፡፡ የምንዛሬ አማራጭ ሊሆን አይችልም፡፡ስለዚህ የሚመረተው ሁሉ በሀገር ውስጥ መቃም ከተጀመረ ሀገሪቱ ሙሉ ቃሚ ትሆናለች፡፡አሁን በአንዳንድ አካባቢዎች ከሰዓት በኋላ ቢሮ ይዘጋል፡፡ሱቅ ዝግ ነው፡፡በቃ በጫት በስራ ላይ አድማ ይመታል፡፡ጫት ሲበዛ አስናፊ ነው፡፡ በእስልምናም በክርስትናም ጫት እንዲቃም አይበረታታም፡፡

…. ጫት ሽንት ሽንት ስለሚል ረጅም መንገድ እንኳ አያስጉዝም፡፡ ደግሞ ያቃዣል፡፡ከዛ ዱካክ ይለቃል፡፡ከሁሉም ነገር የከፋው ግን ለሌሎች ሱሶች መንገድ መሪ መሆኑ ነው፡፡ጫት የሚቅም በብዛት ያጨሳል፡፡ይጠጣል፡፡ጫት ብዙ ችግር ያስከትላል ፡፡ ያም ሆኖ ግን ጫት ጉባኤ ጠርቶ የሚያገናኘው ብዙ ደንበኛ አለው፡፡ …. ጫት በየቦታው እንዳይቃም፣ የጎጃሟ ሞጣ ከተማ በህግ ከልክላለች!!!ሌሎች ከተሞችም አካባቢኛ ህግ እየሰሩለት ነው፡፡
ከአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት
humaidi
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1741
Joined: Tue Jan 03, 2006 11:50 am

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests