ለአቡነ ማቲያስ የተላካ የምእመናን ደብዳቤ

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

ለአቡነ ማቲያስ የተላካ የምእመናን ደብዳቤ

Postby እሰፋ ማሩ » Mon Apr 10, 2017 2:43 am

ለአቡነ ማቲያስ – የዝምታ ዋጋው ስንት ነው!? የሞራል ልዕልናስ ድንበሩ የት ላይ ነው!?
ecadforum April 9, 2017
መስቀሉ አየለ
በአስራ ዘጠኝ ሃያዎቹ መጀመሪያ ላይ ከአንደኛው የአለም ጦርነት ፍርስራሽ ውስ ጥ ገና በቅጡ ያልወጣው የሶቪዬት ቦልሸቪክ አብዮት ከነበረው አስከፊ የአገሪቱ ኢኮኖሚ ጋር እንዴት ተጣጥሞ መሄድ እንዳለበት ሊረዳው ከባድ ፈተና ሆኖበት ነበር።በወቅቱ ዋነኛ የሶቪየት ኤምፓየር የስንዴ ቀበቶ (ዊት ቤልት) ይባል የነበረውን የዪክሬን የእርሻ መሬት በግለሰብ ደረጃ የያዙ ሃብታም ገበሬዎች በመንግስት ስር ተደራጅተው በማሕር ለማምረት ባለመፍቀዳቸው የተነሳ ስታሊን በሚሊዮን የሚቆጠሩ የዩክሬን ገበሬዎችን ገደለ። ያን እልቂት ተከትሎ አገሪቱ ውስጥ ምርት የሚያመርት ሰው በመጥፋቱ የተነሳ በነበረው እረሃብ የዩክሬን ዜጎች ልጆቻቸውን ቀቅለው በልተዋል። በዚያ አስደንጋጭ ክስተት ግራ የተጋባው የዩክሬን አስተዳደር በዋና ከተማዋ ኬይቭ ዋና ዋና አደባባዮች ላይ “የሰውን ስጋ መብላት ነውር ነው ” የሚሉ መፈክሮችን ሰቅሎ እንደ ነበር ታሪክ በጥቁር ማህደር ላይ መዝግቦታል። ዴቶቭስኪ እንዳለው እግዚአብሔር ከሌለ የሚከለከል ነገር አይኖርም ። አምልኮተ እግዚአብሔርን ሗላ ቀርነት ብሎ ኮሚኒዝምን እንደ ሃይማኖት የተቀበለ ማህበረሰብ ይሕን ድርጊት ቢፈጽም አይገርምም።
ቦብ ጊዶልፍ ለሊቪንግ ኤይድ የገንዘብ መዋጮ ዝግጅት የድርቁን አስከፊነት በአካል ተገኝቶ ለመገምገም በሰባ ሰባት አመተ ምህረት የድርቁ እምብርት (ሆት ስፖት) ወደ ነበረው ወሎ ራያ ለመሄድ ገና ከአገሩ ሲነሳ ደርዘን ሙሉ በጣም የሰለጠኑ የሴኩቱሪቲ ቦዲ ጋርዶች ተቀጥረውለት የተጓዘው በቦታው ሲደርስ ግን ያየውና የታዘበው እራሱን ለሁለት የሚሰነጥቅ እውነት ነበር። የወሎ ገበሬዎች በጠኔ የተያዙ ህጻናቶቻቸውን በክንዳቸው ታቅፈው የዱቄት ወረፋቸውን በትእግስት አክብረው ሲጠብቁ የህጻናቶቹ ህይወት ያለፍ የነበረበትን መራር እውነት በታዘበበት ማታውን ቦዲ ጋርዶቹን ወዳገራቸው አሰናብቶ ብቻውን በተፈናቃዮች መንደር ለመክረም ተገዷል። ቦብ ጊዶል ከጥቂት ሳምንታት ቆይት ቦሃላ ወደ አገሩ ሲመለስ በቦሌ ኤርፖርት ላይ ሃጢያቱን ለአለም አቀፍ ጋዜጠኞች እንደ ተናዘዘው ዕቦዲ ጋርዶቹ የተቀጠሩልኝ ሰዎች (ከመራባቸው የተነሳ ሊበሉህ ይችላሉዕ የሚል ስጋት በመኖሩ ነበር ሲል ይቅርታ ጠይቆ ዛሬ ከህሊና እዳ ነጻ ሆኖ ይኖራል።አንድ ሰው ሌላውን መለካቱ በሚያውቀው ነገር ላይ ተመስርቶ መሆኑ የተፈጥሮ ህግ ነው። እኛ ደግሞ ኢትዮጵያውያን ነን።
ካሁን በፊት ለመግለጥ እንደ ሞከርኩት ወያኔዎች ለኢትዮጵያ አምባገነናዊ የአገዛዝ ቀንበር ብቻ አይደሉም፤ ዘረኛና ከፋፋይ ብቻም አይደሉም፤ ጸረ ሃይማኖትም ብቻ አይደሉም።ነገር ግን ሰውን ከመንፈስ ከፍታ የሚያወርዱ በጣም ስር የሰደዱ የሞራል ፈተና ጭምር እንጅ፣ እነሱ ገና ጫካ በአርማጮሆ ግንባር በኩል እያሉ በደርግ ጦር ለቀናት ተከበው ሲከርሙ የሚበሉት ቢያጡ እርስ በእርሳቸው እንዴት እንደ እንደ ተበላሉ ካነበብነውና ከተረዳነው እውነት ለመግለጥ ሞክሬ ነበር። ዛሬ በካህኑ መልከ ጸዴቅ እድሜ፣ ቅድስና እና ቁመት የሚለካውን የዚህችን አገር የሞራል መሰረት ለመናድ ሲነሱ ግብረ ሰዶማዊነትን ሲያስፋፉ፣ የህግ ማደሪያ የሆኑትን ጽላቶች ለገባያ ሲያቀርቡ፣ ነውር ያለባቸውን ነፍሰ በላ ታጋዮች ከመክርካቶ በተገዛ ቆብና ቀሚስ “ጳጳስ” አድርገው ሲሾሙ ብሎም ዛሬ ደግሞ ምድሩን የአህያን ደም በማፍሰስ ሲያረክሱ ከማንም በፊት ቀድመው ፊታውራሪ መሆን የነበረባቸው ቅዱስ ሲኖዶሱ ውስጥ በጴጥሮስ ወጳውሎስ፣ ተክለ ሃይማኖት ዘደብረ ሊቦናስ መንበር ላይ የተቀመጡት ነበሩ። እነርሱ ዛሬ ካህኑ ኤሊ በቤተ መቅደስ ጓሮ የተሰራውን ነውር አይቶ ዝም እንዳለ ዝም እንዳለ ዝም ብለዋልና ኤሊን የቀሰፈው መላከ ሞት ከበር ቆሞ ይጠብቃቸዋል።
የአንድ ህብረተሰብ ሞራል የሚጠበቀው በመርህ ነው።ህግም የሚወጣው እንዲህ ያሉትን እሴቶች ጠብቆ ወደ ሚቀጥለው ትውልድ ለማሻገር ነው። ለኛ ለኢትዮጵያውያውን ደግሞ ለአንድ ሽህ አመታት ባለትቋረጠው የጦርነት አዙሪት ውስጥ በደረሰብን መውደቅና መነሳት ሳንፈርስ የቆየንበት ምስጢሩ ይኸው ለድርድር ሳይቀርብ የኖረው የመንፈስ ከፍታችን ነው። ሶማሊያ በዚያድ ባሬ ስር መንግስት ነኝ እንዳላለች ዚያድ ባሬ ሲገለበጥ በፊሽካ የፈረሰችበት፣ ሊቢያ ጋዳፊን፣ ኢራቅ የሳዳምን መውደቅ ተከትሎ የፈረሱት አገዛዝ ብለው ካቆሙት መዋቅር ውጭ እነሱን እንዳገር ያቆመ ምንም አይነት የህብረተሰብ መስተጋብር ስላልነበራቸው ነው። ዛሬ እኛ ኢትዮጵያውያን በሰንበት የተቀዳ ውሃ መጠጣት የሃጢያት መጨረሻ ተደርጎ ሲወሰድባት በኖረችው አገራችን ውስጥ የአህያን ስጋ አርዶ መሬቷን የሚያረክስ በላዬ ሰብ ሲመጣ ዝም ማለት የሌለብን በዚሁ ከቀጠለ ነገ እኛን እንደ አገርም እንደ ማህበረሰብም የሚያቆመን ምንም ነገር ስለማይኖር ነው። ሃያ ሚሊዮን ያህል የሶቪየት ህብረትን ዜጎችን በቀይ ሽብር የገደለው ስታሊን እንዳለው ዕእኛ ህግ የሻርነው የመጀመሪያን ሰው የገደልን ቀን ነው፤ ከዚያ ቦሃላ የሆነው ሁሉ ግን የቁጥር ጉዳይ ነውዕ ነበር ያለው።ልጆቿን የበኩር ልጅና የእንግዴ ልጅ ብላ በምትለይ አገር የተወለዱና ትናንት በለጋ እድሜያቸው እረሃብን በስደት ሊያሸንፉ ተገፍተው መንገድ የገቡ አንድ ፍሬ ለጋ ወጣቶች በሊቢያ በረሃ አይሲስ ለተባለ የጨለማው አበጋዝ ለወደረው ሳንጃ “እምቢ ለማተቤ” ብለው አንገታቸውን በኩራት የሰጡት አያቶቻቸው ካሰመሩላቸው የማንነታቸ ውሃ ልክ ላለመውረድ እንደነበር አይናችሁን አፍጣችሁ የተመለከታችሁት ምስክር ሊሆንባችሁ እንደሆነ አታውቁም። ትውልድ እንደ ጅረት እየተከታተለ እንዲህ ዋጋ ሲከፍልባት በኖረችው አገራችን ላይ ነቢየ እግዚአብሔር እንደተናገረው “የበጉን ላት የምትበሉትም ሆነ ጸጉሩን የምትላጩት” እናንተው ሆናችሁ ሳለ ዛሬም ስርዓትና ህግ ሲጣስ ምድራችንም በአህያ ደም ስትረክስ ዝም ብላችሗል ።አባ ማቲያስ፤ ዘይሴሰይ እክልዬ አንሳ ሰኮናሁ ላእሌየ ተብሎ የተጻፈው በእናንተ ላይ ነው። የደጅህን ፍርፋሪ የበሉት ተረከዜን ነከሱኝ ማለቱ ነው።
የትንሳኤ በኩራት ሆይ፦ አቤቱ ሰናኦርን ባየኽበት አይንህ ተመክልከታቸው !!!
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1518
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm

Re: ለአቡነ ማቲያስ የተላካ የምእመናን ደብዳቤ

Postby እሰፋ ማሩ » Wed May 10, 2017 12:33 pm

በዘረኝነት ላይ የተመሰረተው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መዋቅር መልሶ እንዲደራጅና ሕጎቿ እንዲሻሻሉ ተጠየቀ
May 10, 2017 – ቆንጅት ስጦታው
በዘረኝነት ላይ የተመሰረተው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መዋቅር መልሶ እንዲደራጅና ሕጎቿ እንዲሻሻሉ ተጠየቀ የችግሮች ዋነኛ መንሥኤ፥ የሕግና የሥርዓት መጣስና ዘመኑን የዋጀ አለመሆን ነው፤ ተብሏል ቅዱስ ሲኖዶስ፥ ለውጡን የሚያስተባብርና የሚያስፈጽም አካል እንደሚሠይም ይጠበቃል ምልአተ ጉባኤው፣ በይደር በተያዘው የአዲስ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመትም እንደሚነጋገር ተጠቁሟል
ላለፉት ሁለት ሺሕ ዓመታት አያሌ ፈተናዎችን በመቋቋም ሐዋርያዊና ሀገራዊ ተልእኮዋን ስትወጣ የቆየችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ ችግሮች ዋነኛ መንሥኤ፥ “የሕግና የሥርዓት መጣስና ዘመኑን የዋጀ አለመሆን ነው፤” ያለው አንድ ጥናት፣ የቤተ ክርስቲያኒቱን ህልውና በማስጠበቅና ቀጣይነቷን በማረጋገጥ ለትውልድ ለማሸጋገር፣ መዋቅሯን መልሶ ማደራጀት፤ ሕጎቿን፣ ደንቦቿንና መመሪያዎቿን በፍጥነት በማስተካከል የለውጥ ሥራ ማካሔድ እንደሚኖርባት አሳሰበ፡፡
ጥናቱን ያቀረበው፥ በተመረጡ ሊቃነ ጳጳሳት፣ ሊቃውንትና ምእመናን ስብጥር የተቋቋመውና ባለፈው ዓመት ጥቅምት ላይ በቅዱስ ሲኖዶስ የተሠየመው ከፍተኛ ኮሚቴ ሲሆን፤ ችግሮችን ከሥር መሠረታቸው ለማረምና ለማስተካከል የሚያስችል አዲስ መዋቅርና አደረጃጀት እንዲሁም መሠረታዊ የሆኑ ሕጎችን፣ ደንቦችንና የአሠራር ሥርዓቶችን በመቅረጽና መልክ በማስያዝ የለውጥ ሥራውን የሚያካሒድ፣ ራሱን የቻለ የባለሞያ አካል መሠየምና በአስቸኳይ መተግበር እንደሚያስፈልግ አሳስቧል፡፡
ከላይ ወደ ታች፣ ከቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ እስከ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ የሚደርሰውን መዋቅር፣ ተግባርና ሓላፊነት፥ ከተጠሪነት፣ የሰው ኃይል አደረጃጀትና የማስፈጸም አቅም ጋራ በማዛመድ የገመገመው ጥናቱ፥ መዋቅራዊ አደረጃጀቱ በአግባቡ አለመዘርጋቱን፤ የዕዝ ሰንሰለቱ፥ የላላ፣ የተንዛዛ፣ ለሓላፊነትና ለተጠያቂነት የማያመች መሆኑ፣ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ዋነኛ ችግሮች በመሠረታዊ መንሥኤነት አስቀምጧል፡፡
የቋሚ ሲኖዶሱን መዋቅርና አደረጃጀት በቀዳሚነት ያነሣው ጥናቱ፣ የቅዱስ ሲኖዶሱን የዕለት ተዕለት ሥራዎች ለማከናወን በምልአተ ጉባኤ ቢወከልም፣ አባላቱ በየሦስት ወሩ መቀያየራቸው፣ ጉዳዮችን በስፋትና በጥልቀት አጥንቶ በመወሰን በኩል የአሠራር ችግር ማስከተሉን አመልክቷል፡፡
የፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት፣ ለፓትርያርኩ የአስተዳደር አገልግሎት ድጋፍና ለጽሕፈት ነክ ሥራዎች ቢታሰብም፣ ያለአግባብ ራሱን የቻለ ከፍተኛ የመዋቅርና የሥልጣን አካል አድርጎ እንደሚሠራ ጠቅሶ፥ “ለሕግና ሥርዓት መዛባት፣ ለመልካም አስተዳደር ዕጦትና ለመሳሰሉ ችግሮች ቀዳዳ የከፈተ አሠራር ሆኖ ታይቷል፤” ብሏል፡፡ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የቤተ ክርስያኒቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አካልና የሥራ መሪ ኾነው ሳለ፣ የቋሚ ሲኖዶሱ አባል ሆነው መሥራታቸውም ለቁጥጥር እንደማያመችና ፍትሕ ሊያዛባ እንደሚችል ጠቁሟል፡፡
የቁጥጥርና ምርምራ አገልግሎት፣ የሥርዓትና ሥነ ምግባር ኮሚሽን፣ የመንፈሳዊ ፍርድ ቤት፣ የሊቃውንት ጉባኤና የውጭ ጉዳይ መምሪያዎች፣ የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን፣ የመንፈሳውያን ኮሌጆች፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤትና መመሪያዎች፣ የአህጉረ ስብከት ጽ/ቤቶችና የሥራ ዘርፎች እንዲሁም የአጥቢያ ሰበካ ጉባኤ መዋቅራዊ አደረጃጀት፣ ሓላፊነትና ተጠሪነት፥ ከውጤታማ የአሠራር ሥርዓት፣ ከመፈጸም ብቃት፣ ከሥራ ቅልጥፍናና የውሳኔ አሰጣጥ አኳያ ያሉባቸው ችግሮች በጥናቱ ከተዳሰሱት መካከል ይገኙበታል፡፡
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አወቃቀር፣ እንደሌሎች አህጉረ ተመሳሳይ ሆኖ አለመደራጀቱንና “የቅዱስ ፓትርያርኩ ልዩ ሀገረ ስብከት ነው” የሚለው ድንጋጌም ግልጽ ባለመሆኑ ለበርካታ ውዝግቦች መነሻ መሆኑን ጥናቱ አስረድቷል፡፡ ይህን በመጠቀም፣ አንዳንድ የሀገረ ስብከቱ የሥራ ክፍሎችና የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት፣ “ተጠሪነታችን ለፓትርያርኩ ነው” በሚል ከሕግና ሥርዓት ውጭ በመሆን፣ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የሚሰጠውን አመራር ያለመቀበል አዝማሚያ እንደሚያሳዩና ይህም ለመልካም አስተዳደር ችግር፣ ለምዝበራና ለሌሎችም አግባብ ለሌላቸው ተግባሮች በር መክፈቱን ዘርዝሯል፡፡
በአጠቃላይ መዋቅርና አደረጃጀቱ፣ የቤተ ክርስቲያኒቱን ተልእኮ የሚያሳካና ዓላማዎችንና ግቦችን ለማስፈጸም የሚያስችል እንዳልሆነ፤ በተለይም፣ ሥልጣን ሁሉ ተጠቃሎ በአንድ ቦታ ተከማችቶ መገኘትና የሥራና የሓላፊነት ክፍፍል አለመኖሩን፤ የሥራ አስፈጻሚው ተግባርና የዳኝነቱ ሥራ ተቀላቅሎ እንደሚሠራና ለአሠራር ሥርዓት ክፍተትና ለፍትሕ መዛባት ምክንያት እንደሆነ ያስረዳው ጥናቱ፤ ሕግን የማውጣት፣ ሕግን የማስፈጸምና ሕግን የመተርጎም የሥልጣን መርሖዎች፣ ከቋሚ ሲኖዶሱ ጀምሮ በየደረጃው ተለያይተውና ተመጣጥነው በአጥጋቢ ሁኔታ የሚዘረጉበት ተቋማዊ ሁኔታ ሊኖር እንደሚገባ ጠቁሟል፡፡ መዋቅሩንና አደረጃጀቱን ከላይ እስከ ታች መልሶ የማደራጀቱና የማስተካከሉ ተግባር፣ ስትራቴጂያዊና መሠረታዊ በሆነ መልክ መፈጸም እንዳለበትና በጉዳዩ ላይ ቁርጠኛ አቋም ሊያዝ እንደሚገባ ጥናቱ አስገንዝቧል፡፡
ሕጎች፣ ደንቦችና መመሪያዎች ተሟልቶ አለመገኘትና ያሉትንም እንደየወቅቱ ሁኔታ እየታየ ማሻሻያ አለማድረግ፥ ለክፋትና ለተንኮል፣ ለግል ጥቅም ለተሰለፉ ወገኖች የተመቻቸ ሁኔታ እንደፈጠረላቸው ጥናቱ ጠቅሶ፤ የአሠራር ሥርዓቱን በአግባቡ ለማከናወን የሚያስችሉ ሕጎችና ደንቦች ያለመኖራቸውን በተጨማሪ መሠረታዊ መንሥኤነት አስቀምጧል፡፡
የበላይና ዋነኛ የሆነውና በሥራ ላይ የሚገኘው የ2007 ዓ.ም. ሕገ ቤተ ክርስቲያን፣ እጥር ምጥር ብሎ በግልጽ አቀራረብ፣ ጠቅላላ ድንጋጌዎችን፣ መሠረታዊ መርሖዎችንና ፖሊሲዎችን ይዞ በኮንስቲቱሽን መልክ እንደገና ተስተካክሎ እንዲጻፍና በየጊዜው ሳይቀያየር ቋሚና ዘላቂ እንዲሆን፤ ቃለ ዓዋዲው፣ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ደንብ በመሆኑ እንደገና ተሻሽሎ ሕጉን መሠረት በማድረግ፣ ሰበካ ጉባኤ ነክ የሆነው ተግባር ብቻ በሚገለጽበት ሁኔታ ተስተካክሎ እንዲጻፍ ማድረግ እንደሚያስፈልግ በመፍትሔነት የጠቆመው ጥናቱ፣ በአዲሱ መዋቅር የሚደራጀው የሥራ አስፈጻሚው አካል ተግባርና ሓላፊነቱን በብቃት ለመወጣትና ተጠያቂነትን ለማስፈን የሚያስችሉ የተለያዩ የሥራ ማስፈጸሚያ ሕጎችና ደንቦች(ቃለ ዐዋዲዎች) ሕገ ቤተ ክርስቲያኑን እያጣቀሱ መውጣት እንደሚኖርባቸው አመልክቷል፡፡
ከፍተኛ ኮሚቴው፣ የቤተ ክርስቲያኒቱን መዋቅር በሁለንተናዊ መልኩ መልሶ ለማደራጀትና ለማሻሻል ያስችላሉ ያላቸውን ሦስት የመዋቅር ለውጥ አማራጮችን ከማብራሪያዎቻቸው ጋራ በጥናቱ በማካተት ያቀረበ ሲሆን፤ ሕገ ቤተ ክርስቲያኑ፣ ቃለ ዓዋዲውና የሠራተኛ አስተዳደር ደንቡ፥ የመልካም አስተዳደርና የሥነ ምግባር ችግሮችን በመቅረፍ፣ ወጥ የሆነ የአሠራር ሥርዓት በመዘርጋት ዋነኛ ተልእኮዋን በብቃት ለመወጣት በሚያስችላት አኳኋን የሚሻሻሉበትን ይዘትና ሊይዟቸው የሚገቡ ዋና ዋና ሐሳቦችንም አመልክቷል፡፡
የቤተ ክርስቲያኒቱ ችግር እጅግ አሳሳቢና የለውጥ ሥራውም የሁሉንም ትብብርና ድጋፍ እንደሚጠይቅ ያስገነዘበው ከፍተኛ ኮሚቴው፣ ቅዱስ ሲኖዶሱ ችግሩን ለመፍታት ያሳየው ተነሣሽነትና ቁርጠኝነት ተገቢና ወቅታዊ መሆኑን ገልጿል፡፡
የአሁኑ የጥምር ኮሚቴው ጥናታዊ ሪፖርት፣ ቀደም ሲል በተለያዩ አካላት በቀረቡ ሰነዶች የተጠቆሙ የቤተ ክርስቲያኒቱ ችግሮችና መፍትሔዎች አሳሳቢነት በድጋሚ የተረጋገጡበት እንደሆነ የተናገሩ የቅዱስ ሲኖዶሱ ምንጮች፤ የርክበ ካህናት ምልአተ ጉባኤው፣ በመጪው ሳምንት ረቡዕ በሚጀመረው ስብሰባው፣ በዋነኛ አጀንዳነት በመያዝ የለውጥ ሥራውን በባለቤትነት በማስተባበር መልክና ቅርጽ የሚያሲዝ የባለሞያ አካል ሊሠይም እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡
በሌላ በኩል፣ ምልአተ ጉባኤው፣ ከባለፈው የጥቅምት መደበኛ ስብሰባው የተላለፈውንና የአዲስ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት በሚመለከተው አጀንዳ ዙሪያ ተነጋግሮ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1518
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm

Re: ለአቡነ ማቲያስ የተላካ የምእመናን ደብዳቤ

Postby እሰፋ ማሩ » Fri May 19, 2017 6:46 pm

ወያኔ በናሽቪል መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ሽንፈት ገጥሞታል፡፡ሆኖም ግን የፍርድ ቤት ወጭን ሁሌ የሚከፍለው የአባ ማቲያስ ሲኖዶስ ስለሆነ ወያኔ በዚህ መልኩ መግቢያ ቀዳዳ ሊያገኝ ነው፡፡

May 19, 2017 – EthiopianReview.com — 28 Comments ↓
ወያኔ በናሽቪል ቀራንዮ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ሽንፈት ገጠመው።
ግንቦት 11 ቀን 2009 ዓ. ም. ( May 19, 2017)
ወያኔ በናሽቪል ቀራንዮ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ሽንፈት ገጠመው።
ህዝበ ክርስቲያኑን በሰፊው እያነጋገረ ነው።
አንድ በጣም እያነጋገረ ያለው ጉዳይ የተከሳሾቹን ዕዳ የሚከፍለው ማነው የሚለው ነው። ቤተክርስቲያኗ እዘህ አጣብቂኝ እንድተገባ ያደርጉት በወያኔ ተንኮል፣ በአንዳንድ ወያኔን አገልጋይ በሆኑ ምዕመናንና እንዲሁም ብዙ ያልገባቸው ምዕመናን ባደርጉት የተሳሳተ እርምጃ ነው። ቤተክርስቲያኑ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ከተለያዩ [ከኤርትራውያን ወገኖቻችን ጋር ሳይቀር] አብረው በፍቅር ትኖር የነበረች ቤተክርስቲያን ነበረች። ቤተክርስቲያኗ የገንዘብ አያያዟን ጨምሮ እጅግ የሚያስደስት አሰራር የነባርት ነች። ነገር ግን በወያኔ ተላላክዎችና በአቡነ ፋኑኤል በኩል በተደረገው ዘመቻ ምክንያት ቤተክርስቲያኗ ብዙ ቦታ ተከፋፍላለች። በዚህን ወቅት ብዙ ንብረት ያከማቸችው ቤተክርስቲያን ብዙ ምእመናን ጥለው ሲወጡ በአብዛኛው የትግራይ ተወላጅ የሆኑት ወያኔዎችና ለዘብተኛ የሆኑ በብዛት ቀርተው ቤተክርስቲያኗን በመቆጣጠር ወደ ወያኔ ሲኖዶስ እንድትገባ አደርጓት። አሁን ያለው ሁኔታ እጅግ አሳፋሪ የሆነ ክርስቲያናዊ ያልሆነ ስነምግባር የሚታይበት መሆኑ ቀጠለ። በዚህ ፍርድቤት ዉሳኔ መሰረት የጠበቃውን ወጪ እንዲከፍሉ የተወሰነው የተከሰሱት ሊቀመንበሩ ሳሙኤልን ጨምሮ መሆን እንዳለበት ነው። ነገር ግን እኔ አቶ ሳሙኤልና መርጌታ አብይ የሚባሉት ከምእመናን እንዲከፈል እንዲሚፈልጉ ቅርባቸው ካሉ መረጃውን አግኝተናል። ሕዝቡን እያነጋገረ ያለው የፍርበቱን ወጭ ከሳሽ ያወጣውን ጭምር መክፈል ያለባቸው መጀመሪያ የርድ ቤቱ ሂደት እንዲጀመር ፊርማ የፈረሙ ሰዎች ሊሆኑ ይገባል የሚል ነው። ፊርማ የሰረሙት ሁሉ ግን አሁን ፍቃደኛ መሆናቸው አጠያያቂ እንደሚሆን ፊርማ ከፈረሙት አካባቢም ያገኘነው መረጃ ያሳያል። ምናልባት ይህ ለፍርድ ቤት የሚወጣውና ወያኔን የሚረዳ ገንዘብ ባልና ሚስትም ልያጋጭ እንደሚችል
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1518
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm


Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 4 guests

cron