ምን አጣላቸው?

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

ምን አጣላቸው?

Postby ዘርዐይ ደረስ » Sat May 13, 2017 11:25 am

ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ፕሮቴስታንቶች ለረጅም ጊዜ ልዩነታቸው ይፋ እንዳይወጣ ሲጥሩ መቆየታቸውን ብዙዎቻችን የምናውቀው ነው::የትኛው ድርጅት አባል እንደሆኑ ሲጠየቁም ብዙዎቹ እኔ በድርጅት አላምንም ክርስትያን ነኝ፣በጌታ ነኝ፣ጌታን እንደ ግል አዳኜ ተቀብያለሁ፣ዳግም ተወልጃለሁ ወዘተ የሚል መልስ ነው የሚሰጡት::በዘንድሮው ሚያዝያ2009 ግን ለዘመናት የተሸፋፈነው ልዩነትና አንዳንዴም እስከ ጥላቻ የሚደርስ አለመግባባት ገንፍሎ አደባባይ ወጥቷል::እነዚህ ራሳቸውን ‚ወንጌላውያን‘ ብለው የሚጠሩት በመቶ የሚቆጠሩ ድርጅቶች ስብስብ ለመሆኑ ለዚህ ያበቃቸው ምንድነው?
ትክክለኛውን ምክንያት ለውስጥ አዋቂዎች ትቼ በይፋ የሚነገሩትን አንዳንድ ነጥቦች ልጥቀስ:-
በየዓመቱ የትንሳኤን በዓል ለማክበር በሚል እነዚህ ወንጌላውያን የድርጅት ልዩነት ሳያግዳቸው በአዲስ አበባ ስታዲየም ይሰበሰባሉ::ታዲያ በዘንድሮው ስብሰባቸው ላይ በራሪ ወረቀት ይሰራጫል::እንደሚባለው ከሆነ ወረቀቱን ያዘጋጁትና ያሰራጩት የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስትያናት ህብረት አባላት ናቸው::የዚህ ጽሑፍ ጭብጥ መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት ያላደረገ ትምህርት የሚያስፋፉ ድርጅቶች ስላሉ እነሱን ማውገዝ ነው::
ይህ ከሆነ ከ2 ሳምንታት በኋላ ሚያዝያ 23 ቀን 2009 ዓ.ም.የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስትያናት ኅብረት ባለ 10 ነጥብ የአቋም መግለጫ አወጣ::ይህን መግለጫ ተከትሎም የኢትዮጵያ ቪዥነሪ አብያተ ክርስትያናት ኅብረት የሚባለው ድርጅት የአቋም መግለጫው የኛን ኅብረት የሚመለከት ነው በሚል ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጠ::በዚህም ምክንያት ልዩነቱ እየተካረረ ሄደ::
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1089
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: ምን አጣላቸው?

Postby ክቡራን » Sat May 13, 2017 3:18 pm

ቪዥነሪ አብያተ ክርስቲያናት ስብስብ ነን የሚሉት የሌቦችና የሃሳዊ መሲሃን የመናፍቃን ስብስብ ነው ፡፡ በጣም ባለጌዎችና ራስ ወዳዶች ናቸው እንዳንዶቹ እንደ ቲቪ ኢቫንጄሊዝም መሆን ይፈልጋሉ፡፡ የሚገርመው ራሳቸውን የሚጠሩት ወንጌላዊ ወይንም ፓስተር ሳይሆን ሃዋርያ፣ ነቢይ፣ እያሉ ነው ፡፡ ትንሽ ቆየት ብሎ ከመካከላቸው እንዱ እኔ በሳት ሰረገላ የተነጥኩት ኤልያስ ነኝ እንደሚል አልጠራጠርም፡፡ ዘርአይ ድረስ በከፈትከው ር እስ ላይ ላይ ያንተ አቅዋም ምንድነው ? ጥያቄ ብቻ ነው ያቀረብከው ምን ሃሳብ እንዳለህ፣ ለማን እንደምትወግን ግልጽ አድረገህ አላስቀመጥክም፡፡
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7988
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Re: ምን አጣላቸው?

Postby ዘርዐይ ደረስ » Sat May 20, 2017 8:53 pm

ክቡራን:-
የራሴን ሃሳብ ከመስጠቴ በፊት በጉዳዩ ላይ የተሻለ ግንዛቤ ያላቸው ሰዎች ሊኖሩ ስለሚችሉ እነሱን ላስቀድም ብዬ ነበር::እስካሁን ን ካንተ በቀር አስተያየት የሰጠ ሰው ስለሌለ በእኔ በኩል ያለው ይህን ይመስላል::
ቪዥነሪ የሚባለውን እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ጨርሶ አላውቀውም ነበር::የድሮውን ኅብረትም ጠለቅ ብዬ አላውቀውም::እኔ እስከማውቀው የ7 ድርጅቶች ኅብረት ነበር::አሁን ግን ከ 20 በላይ ናቸው ይባላል::ኢትዮጵያ ውስጥ ፕሮቴስታንት የተባለ ሁሉ የድሮው ኅብረት አባልም ይመስለኝ ነበር::
ስለ ቪዥነሪው ኅብረት እንደተረዳሁት ኢህአዴግ ሥልጣን ከያዘ በኋላ የተለያዩ ግለሰቦች በየሠፈሩ አዳራሽ በመከራየት አባላትን እየመለመሉ በመሰላቸው መንገድ የሚሰብኩበት አጋጣሚ ተፈጥሮላቸው ነበር::ታዲያ የድሮው ኅብረት አባል ለመሆን ስላልቻሉ በ‘ተልዕኮ ለትውልድ‘ መሥራችና መሪ ዘላለም ጌታቸው አሰባሳቢነት በርካታ የመንደር አዳራሽ ተሰብሳቢዎች ኅብረት ፈጠሩ::ሁላችንም ‚ክርስትያኖች‘ ነን ለምን እንከፋፈላለን የሚሉ ድምጾችም ሳይሰሙ አልቀሩም::ያም ሆነ ይህ የቀድሞው ኅብረት መሪዎች ብዙ አባላቶቻቸው እየኮበለሉ ወደ አዲሱ ኅብረት የሄዱባቸው ይመስለኛል::በተጨማሪም አዲሶቹ ገደብ የሌለው የስብከትና የዶክትሪን ነፃነት ስላላቸው ከሞላ ጎደል ቋሚ ዶክትሪን ካላቸው የቀድሞው ኅብረት ጋር ለረጅም ጊዜ ሳይቃቃሩ አልቀሩም::እንግዲህ ቅራኔዎቹ ውስጥ ለውስጥ ሲብላሉ ቆይተው ነው ባለፈው ፋሲካ ሰሞን የፈነዱት::አዲሶቹ የቀድሞዎቹን በምን ነጥቦች ላይ እንደሚቃወሟቸው ባላውቅም የቀድሞዎቹ ግን:-
1)የብልጽግና ወንጌል ይሰብካሉ
2)ተጸልዮበታል በማለት እንደ አዮዲን ጨው፣ሚኒራል ውሃ፣ዘይት፣ወ.ዘ.ተ. ያሉትን ነገሮች ይሸጣሉ::
3)ሕክምና የሚከታተሉ ሰዎችን ከዛሬ ጀምሮ ተፈውሳችኋል በማለት መድኃኒታቸውን እንዲያቆሙ ያዛሉ::በዚህም ሳይድኑ ለከፋ ሁኔታ የተጋለጡ ሰዎች እንዳሉ ነው የሚነገረው::
4)መጽሐፍ ቅዱስን ሥርዓት ባለው መልኩ ሳይሆን በዘፈቀደ ይተረጉማሉ::
በነዚህና በሌሎችም ምክንያቶች ይመስለኛል የጸቡ መነሻ
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1089
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: ምን አጣላቸው?

Postby ክቡራን » Sat May 20, 2017 9:14 pm

ወንድሜ የድሮውንና ያሁኑን ክርስትና በደንብ የተረዳሀው አልመሰለኝም እንደውም አታውቀውም፡፡ ይሄን ርእስ የከፈተከው ጉዳዩ አሳስቦህ ሳይሆን ክፍተቱን አሳይተህ በልዩነቶች ለመሳለቅ ነው ፡፡ ሳስበው አንተ የክርስትና እምነት ተከታይ አልመሰልከኝም፡፡ አለመሆንህ ችግር የለውም፡፡ ችግሩ በልዩነቱ ከመሳለቅ ይልቅ ልዩኑቱን ለማጠጋጋት የተሳሳቱትን ለማስተካክል ወይንም ለማስተማር ምን እናድርግ??? የሚለውን ሃሳብ ብታነሳ አመለካከትህ ገዥ በሆነ ነበረ፡፡ "ነበረ " የምለው እንደዚህ አይነት ራሽናል አመለካከቶች ካንተ ስለማልጠብቅ ነው፡፡ ባለፈው ከሙስሊም ወዳጆቼ ጋር ልታጣላኝ ስትፈራገጥ ታዝቤሃለሁ፡፡ ያልኩትን እየደገምክ በመናገር ጅራፍ ስታጮህ ነበረ፡፡ በበጎች መካከል የምትመላለስ ቀበሮ ነገር ትመስለኛለህ .. ትክክል ነኝ??
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7988
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Re: ምን አጣላቸው?

Postby ዘርዐይ ደረስ » Sat May 20, 2017 11:05 pm

ወንድሜ የድሮውንና ያሁኑን ክርስትና በደንብ የተረዳሀው አልመሰለኝም እንደውም አታውቀውም፡፡


የድሮና የአሁን የሚባል ክርስትና የለም፡፡ክርስትና አንድ ነው፡፡

ይሄን ርእስ የከፈተከው ጉዳዩ አሳስቦህ ሳይሆን ክፍተቱን አሳይተህ በልዩነቶች ለመሳለቅ ነው ፡፡


ኢየሱስም እኮ ሰዱቃውያንና ፈሪሳውያንን ልዩነታቸውን እያሳየ ነበር የሚያጋልጣቸው፡፡

ሳስበው አንተ የክርስትና እምነት ተከታይ አልመሰልከኝም፡፡ አለመሆንህ ችግር የለውም፡፡


ታዲያ የምን ሃይማኖት ተከታይ እመስልሃለሁ?

ችግሩ በልዩነቱ ከመሳለቅ ይልቅ ልዩኑቱን ለማጠጋጋት የተሳሳቱትን ለማስተካክል ወይንም ለማስተማር ምን እናድርግ??? የሚለውን ሃሳብ ብታነሳ አመለካከትህ ገዥ በሆነ ነበረ፡፡ "ነበረ " የምለው እንደዚህ አይነት ራሽናል አመለካከቶች ካንተ ስለማልጠብቅ ነው፡፡


እዚህ ላይ አልተሳሳትክም፡፡ምክንያቱም እኔ የምፈልገው እንዲታረቁ ሳይሆን እንዲያውም ልዩነቱ እንዲባባስ ነው፡፡

ባለፈው ከሙስሊም ወዳጆቼ ጋር ልታጣላኝ ስትፈራገጥ ታዝቤሃለሁ፡፡ ያልኩትን እየደገምክ በመናገር ጅራፍ ስታጮህ ነበረ፡፡ በበጎች መካከል የምትመላለስ ቀበሮ ነገር ትመስለኛለህ .. ትክክል ነኝ??


የደጋገምኩት እኮ አንተ ስህተትህን አልቀበል ስላልክ ነው፡፡መጀመርያ ስለ ምክርህ አመሰግናለሁ ስትለኝ ያመንክ መስሎኝ ነበር፡፡ቆየት ብለህ ግን ምንም እንዳልተሳሳትክ ስትገልፅ ነው እንድትታረም የነገርኩህ፡፡እዚሁ ካልተራረምን እንደለመድነው ሌላ ቦታ ሄደን አፋችንን እንከፍትና ችግር ሊፈጠር ይችላል ብዬ ነው፡፡
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1089
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: ምን አጣላቸው?

Postby ክቡራን » Sun May 21, 2017 1:40 am

ዘርዐይ ደረስ/ ከዋርካ አራቱ ጠብደል ዘበኞች እንዱ ! wrote:
ወንድሜ የድሮውንና ያሁኑን ክርስትና በደንብ የተረዳሀው አልመሰለኝም እንደውም አታውቀውም፡፡


የድሮና የአሁን የሚባል ክርስትና የለም፡፡ክርስትና አንድ ነው፡፡

ይሄን ርእስ የከፈተከው ጉዳዩ አሳስቦህ ሳይሆን ክፍተቱን አሳይተህ በልዩነቶች ለመሳለቅ ነው ፡፡


ኢየሱስም እኮ ሰዱቃውያንና ፈሪሳውያንን ልዩነታቸውን እያሳየ ነበር የሚያጋልጣቸው፡፡

ሳስበው አንተ የክርስትና እምነት ተከታይ አልመሰልከኝም፡፡ አለመሆንህ ችግር የለውም፡፡


ታዲያ የምን ሃይማኖት ተከታይ እመስልሃለሁ?

ችግሩ በልዩነቱ ከመሳለቅ ይልቅ ልዩኑቱን ለማጠጋጋት የተሳሳቱትን ለማስተካክል ወይንም ለማስተማር ምን እናድርግ??? የሚለውን ሃሳብ ብታነሳ አመለካከትህ ገዥ በሆነ ነበረ፡፡ "ነበረ " የምለው እንደዚህ አይነት ራሽናል አመለካከቶች ካንተ ስለማልጠብቅ ነው፡፡


እዚህ ላይ አልተሳሳትክም፡፡ምክንያቱም እኔ የምፈልገው እንዲታረቁ ሳይሆን እንዲያውም ልዩነቱ እንዲባባስ ነው፡፡

ባለፈው ከሙስሊም ወዳጆቼ ጋር ልታጣላኝ ስትፈራገጥ ታዝቤሃለሁ፡፡ ያልኩትን እየደገምክ በመናገር ጅራፍ ስታጮህ ነበረ፡፡ በበጎች መካከል የምትመላለስ ቀበሮ ነገር ትመስለኛለህ .. ትክክል ነኝ??


የደጋገምኩት እኮ አንተ ስህተትህን አልቀበል ስላልክ ነው፡፡መጀመርያ ስለ ምክርህ አመሰግናለሁ ስትለኝ ያመንክ መስሎኝ ነበር፡፡ቆየት ብለህ ግን ምንም እንዳልተሳሳትክ ስትገልፅ ነው እንድትታረም የነገርኩህ፡፡እዚሁ ካልተራረምን እንደለመድነው ሌላ ቦታ ሄደን አፋችንን እንከፍትና ችግር ሊፈጠር ይችላል ብዬ ነው፡፡


ጎሽ እንዲህ ራስህን ግልጽ አድርገህ ስትመጣ ድስ ይላል ፈረንጅ ይሄን ሲያይ ምን ይላል መሰለህ now we can talk ይላል ...ክርስቶስ ሰዱቃውያንና ፈረሳውያንን ልዩነታቸውን ያሳየበት ሃረግና አንተ በኢቫንጄሊስቶችና በቪዝነሪዎች መካከል ያለውን ልዩንት ያነሳህበት ሃሳብ ይለያያል፡፡ ክርስቶስ ሊያስተምርበት ነው !! አንተ ግን ልትሳለቅበት ነው ፡፡ እንደውም በራስህ አማርኛ ይህን እልክ...
እዚህ ላይ አልተሳሳትክም፡፡ምክንያቱም እኔ የምፈልገው እንዲታረቁ ሳይሆን እንዲያውም ልዩነቱ እንዲባባስ ነው፡፡

ይሄ ያለህን አቅዋምና ማንነትህን ግልጽ አድርጎ ያሳያል፡፡ የሰላምና የፍቅር ሰው ሳትሆን ሸረኛ እባብ ተኩላና ቀበሮ ቅልቅል ( ወይንም የነሱ Heterogeneous mixture ) መሆንህም ያሳየህበት አገላለጽ ነው፡፡ ዋርካ ውስጥ ስም ዋጋ አይከፈልበትም፡፡ ያገኙትን አፈፍ ማድረግ ይቻላል፡፡ ዘርአይ ድረስ ብለህ ስም ለራስህ ስታወጣ ምን አስበህ እንደሆነ አሁን ምክንያቱን እልነገርህም፡፡ ወደ ህዋላ ሄጄ ከዚህ በፊት የጻፍካቸውን ጉዳዮች ማየት ይኖርብኛል፡፡ ጊዜ ሲኖረኝ ጽሁፎችህን ሪቪው አደርጋቸዋለሁ፡፡ ዋርካ ስነ ጽሁፍ ላይም የቃላት አቻ ፈልጉልኝ ብለህ የከፍተከውን አይቻዋለሁ፡፡ አስተማሪነቱ ወደር የለውም፡፡ መልካም ነው ፡፡ ማግኘት የምትፈለገውን ኦብጀክቲቭህን ለማየት ግን ሌሎች የከፈትካቸውን ክፍሎችም ማየት ይኖርብኛል ፤፤ ባጭሩ በጽሁፎችህ ላይ ሲንተንሲስና አናሊስስ ሰርቼ እውነተኛ ዘርአይ ደርስ ማን መህኑን ለማወቅ ጊዜ የሚፈጅብኝ አይመስለኝም፡፡ የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀረ አንተን ሳይሆን ሙሉ ህሳቤህን በእጄ አስገባለሁ የሚል ተስፋ አለኝ...እንደዛ ስልህ ልሞግትህ ነው ሌላ ነገር መስሎህ "ትን!!" እንዳይህልህ!! ሎል፡፡ ከቀደሙት ያዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ (ከ 66 ቱ ተራማጅና አማጽያን ትውልዶች አንዱ ትሆን??>) አንድ ጽሁፍ ላይ ስለ ሃይለስላሴ ዩኒቨርስቲ ውሎህ የተናገርክ መሰለኝ፡፡ ሃይማኖትህን በተመለከተ የምትፈልገውንና ህሊናህ ልክ ነው የሚለውን መከተል ትችላለህ፡፡ ተቃውሞ የለኝም፡፡ ላንዳንዱ አክሊል ላንዳንዱ ደሞ ቦርዴ ጠላ ይቀርብለታል፡፡ ታላቁ መጽሃፍ "' ሰው ሆይ የዘራሀውን ታጭዳለህ" ይላል....በምድራዊ ህይወትህ ምን ስትዘራ እንደነበርክ የምታውቀው እንተ ነህ፡፡ እኔ የፍቅር ማሳ ውስጥ ያለሁ ገበሬ ነኝ ፡፡ አንተ ራስህን ፈልገህ አግኘው፡፡
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7988
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm


Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests