የአእምሮ በሽታ ( ፐርሰናሊቲ ዲሶርደር)

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

Postby ምክክር » Sun Nov 10, 2013 9:22 am

ቆቁ wrote:አስተዳደጋችን የሚያጠያይቅ ነው
በአጭሩ

1. የሐብታም ልጆች ከሆንን በቤተ ሰራተኛ ቅዘናችን እየተጠረገ ገላችን እየታጠበ ይሆናል ያደግነው
ከዛም አልፎ ከእናታችን ወይም ከአባታችን ጋር ያለን ግንኙነት እንደ የቤት ሰራተኛችን ያህል የጠነከረ ግንኙነት ያለው አይደለም ::

2. በድህነት ያደግን ከሆነ ደግሞ የእናታችን ፍቅር እጅግ የጠነከረ ነው ያለ እናታችን የምናውቀው ነገር የለም

3. የታደልን ከአባታችንም ከእናታችንም የጠነከረ ግንኙነት ያለን መልካም ፍቅር ይዘን ያደግንም እንኖራለን


እዚህ ላይ ነጥቡ ምን ያህል ፍቅር ነው ወላጆቻችን ለኛ ለልጆቻቸው የሰጡት የሚለው ጥያቄ ነው ለዚህ ለፐርሶናሊቲ ዲሶርደር ትንተና የሚዳርገን

ከሁሉም የበላይ ለመሆን
ከሁሉም በላይ ተወዳጅ ለመሆን
ከሁሉም በላይ በትምህርትም በገንዘብም ለመብለጥ ትግል
እኔ ብቻ ነኝ አዋቂው : እኔ ለእኔ አንተም ለእኔ በሚል መመሪያ መኖር ማለት የእአምሮ ዲሶርደር ነው

ከላይ በተመለክተነው የቤተ ሰብ ፍቅር ላይ ተመርኩዘን ፐርሶናሊቲስ ዲሶርደር ምን እንደሆነ እንመለከታለን


ሳይካትሪስቱ ቆቁ


እንዲያ ነው ቆቁ ፈር እያስያዝክ ቀጥልበት...
በወላጆች ፍቅርና እንክብካቤ ማደግ መታደል ነው:: ለዚህ ዋናው መሠረት የሁለቱ ተጓዳኞች መስተጣምር ይሆናል:: ቆቁ አባት የመሆን እድል ደርሶህ ከሆነ ልጅህ ገና ሲወለድና ስታቅፈው...."ወላጆቼ እንዲህ ይወዱኝ ነበርን?" ብለህ ራስህን መጠይቅህ አይቀርም:: እናም አባት ሆነህ ነው ይበልጥ ለወላጆችህ ያለህ ፍቅርና ክብር የሚጨምረው::

ለአስተዳደጋችን ዋናውን መሠረት የሚጥሉት ወላጆቻችን ናቸው:: ይሁንና አካባቢያችንና ሕብረተሰቡም ለአስተዳደጋችን የተጽእኖ ድርሻ አለው::

ወልደው ከብደው ከተወሰኑ የጋብቻ ዓመታት በኋላ በጭቅጭቅና በቅራኔ አንዱ ሌላዉን በማይፈልግበት ከርቭ ላይ ሲደርሱ....ባልና ሚስቱ ለመለያየት ይወስናሉ:: ልጆች ግን ሁለቱንም: አባታቸውንም: እናታቸውንም ይፈልጋሉ:: ስለዚህ ለልጆች ሲባል ሳክሪፋይስ...ኮምፕሮማይስ...የሚባል ከንሰሽን አለና አስታውስ!!

በዓለም ላይ ከባድ ሥራ ልጅ ማሳደግ ነው:: ለኃላፊነት ብቁ ካልሆንክ አትውለድ:: ስትጀምረው 25 ደቂቃ ቢሆንም ለመጨረስ ምናልባት 25 ዓመታት መኳትን ይኖራል:: እናም ለ25 ደቂቃ ፕሌዠር ብለህ የ25 ዓመታት ሚዘሪ እንዳታፈራ:: በጭንቅላትህ አስብ!

አባቴን እጅግ በጣም እንድወደውና እንዳከብረው ካደረጉኝ ምክንያቶች አንዱ እናቴን ይወዳትና ያከብራት ነበር:: አንድም ቀን ስትከፋበት አላየሁም:: ይህን እንዴት እንግለጸው ታድያ? ልጆች: አባታቸው እናታቸውን ሲያከብር ይደስታሉ...ይወዱታል:: እናትም አባታቸውን ስታከብር ይወዷታል:: (አስኪደው እስኪ በሳይካትሪስቶች ቋንቋ) የወላጆች የርስ-በርስ መከባበርና መዋደድ ልጆችን በፍቅርና በስነ-ምግባር እያነጸ ያወጣል!!!
ምክክር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 301
Joined: Thu Jun 26, 2008 10:10 am
Location: Super Earth

Postby ቆቁ » Wed Nov 13, 2013 6:23 pm1. የሐብታም ልጆች ከሆንን በቤተ ሰራተኛ ቅዘናችን እየተጠረገ ገላችን እየታጠበ ይሆናል ያደግነው
ከዛም አልፎ ከእናታችን ወይም ከአባታችን ጋር ያለን ግንኙነት እንደ የቤት ሰራተኛችን ያህል የጠነከረ ግንኙነት ያለው አይደለም ::


ምክክር ወዳጄ አንተው ባነሳኸው ነጥብ ላይ እንሂድበት እስቲ::

በሐገራችን ሐብታም የሚባሉት ወላጆች እና ልጆቻቸው እንዴት ነው ግንኙታቸው?

በአብዛኛው በሐብት የበለጸጉ ወላጆች ልጆቻቸውን ለቤት ሰራተኛ በመስጠት ነው የሚገላገሉት::

በትዳር ላይ የተመሰረተ ፍቅር ያላቸው በለጠጎች ባለትዳሮች በሐገራችን ባህል መሰረት ብዙም የተሙዋላ የፍቅር ገበታ አይቁዋደሱም:: ምክንያቱም የሐገራችን ስርዓት ባታዊ ስርዓት በመሆኑ::

ይህንን ስንል ባለጸግነት የቤተ ሰብ ፍቅር በወላጆች እና በልጆች መካከል እንዳይኖር ያደርጋል ማለት አይደለም::
ብዙ አይተው ተከባብረው ተፈቃቅረው የሚኖሩ ባለጸጎች ብሐገራችን ስላሉ::

በኢትዮጵያ የሐብታም ወላጆች እና ልጆቻቸው ፍቅር ብዙም በማይታወቅበት መንደር ነው እኔ ፈላስፋው ያደግሁት::

ይቺው መንደሬ የድሀ ልጆችን እና ወላጆቻቸውንም አስተዳደግም አሳይታኛለች::

በመካከለኛ ደረጃ የሚኖሩ ወላጆችንና ልጆችንም ኑሮ አሳይታኛላች::

በአጠቃላይ አንድ ልጅ ከሐብታም ከድሀ መወለዱ ሳይሆኑ ፐርሶናሊቲ ዲሶርደር የሚያመጣበት ቤተ ሰባዊ ፍቅር ሲጎድልበት ብቻ ነው::

ይህ ፍቅር ሲጎድልበት

"" እኔ ትክክል አይደለሁም :: እናንተም ትክክል አይደላችሁም"" በማለት የራሱን አጥፊ ጎዳና ይዞ መጉዋዝ ይጀምራል::

ቤተ ሰባዊ ፍቅር ማለት ምክክር ወዳጄ እንዳስቀመጠው

1. የወላጆች የርስ በርስ ፍቅር
2. የወላጆች ለልጆች ያላቸው ፍቅር ማለት ነው::

አንድ ልጅ በቤተ ሰባዊ ፍቅር ተኮትኩቶ ካደገ የሌላው የውጨው የሶሺያሉ ሕይወት ብዙም ይህንን ፍቅራዊ አስተዳደግ አይለውጥበትም::

ወላጆች የልጆች መሰረት በመሆናቸው በቤተ ሰባዊ ፍቅር ውስጥ ጣጣ ከመጣ በዚህ ጣጣ ውስጥ ያደገ ልጅ ከውጭው የሶሺያል ሕይወት ብዙም አይጠብቅም ስለሆነም ነው እንግዲህ

"" [u]እኔ ትክክል አይደለሁም እናንተም ትክክል አይደላችሁም "" የሚለው የፐርሶናሊቲ ዲሶርደር የሚከሰተው /u]

ይህ ዲሶርደር አጥፊ ነው

አጥፊነቱ
1, ራስን አጥፊ ነው
2. ማህበራዊ ኑሮን አጥፊ ነው


ምሳሌ
በዚህ ፐርሶናሊቲ ዲሶርደር የተነካ ግለሰብ ሒስ
(critics) አይቀበለም:: ምክንያቱም መመሪያው

"" እኔ ትክክል ባልሆንም እናንተም ትክክል አይደላችሁም "" የሚለው በመሆኑ::

እዚህ ላይ ነው እንግዲህ ትልቁ ችግር::

እዚህ ላይ ነው እንግዲህ ጣጣው::

ይህ ጣጣ የምንለው ነገር በቀላሉ የሚያልፍ ሳይሆን ውስጣዊ አካላትንና ራሱን ጭንቅላትን የሚበጠብጥ ሆኖ እናኘዋለን::

ሳይካትሪሱ ቆቁ
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4055
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Postby ቆቁ » Mon Dec 09, 2013 9:00 pm

1ኛው ሒስ አለመቀበል ነው ብለናል
ሁለተኛውስ ምን ይሆን ?
ሁለተኛው self pity የሚባለው ነው አሳዛኝ መምሰል ወይም እንዲታዘንለት የቆጥ የባጡን ማማረር ወይም እኔ እንዳልኩዋችሁ ያልኩት ቢሆን ኖሮ ! እድለኛ አይደለሁም ! ውይ የኔ ጣጣ ! የመሳሳሉት የማማረር ጠባዮች በዚህ በፐርሰናሊቲይ ዲሶርደር ይታያሉ::

ይህ self pity የሚባለው ነገር በዚህ በፐርሶናሊቲ ዲሶርደር የሚገኝ ግለሰብ እንዲታዘንለት ሳይሆን ከወደቀበት የፐርሶናሊቲ ኪሰራ ለመነሳት የሚያደርገው መንፈራገጥ ነው

ለምሳሌ "" እድለኛ አይደለሁም"" ለሚለው ማማረር በቅርብ የሚገኝ ዘመድ ወይም ጉዋደኛ እርዳታ ለመስጠት አይዞህ ምንም አትሆንም ችግር የለውም እኔ እረዳሀለሁ ቢለው

አሁንም ይህ በፐርሶናሊቲ ዲሶርደር የሚገኝ ግለሰግ

"" እኔ ትክክል አይደለሁም አንተም ትክክል አይደለህም"" ወደ ሚለው ዋሻ ይገባና ራሱን ለማጠናከር ይሞክራል::

ይህ ሁኔታ በፖለቲካው ዓለም ኪሳራ ውስጥ የገቡ ፖለቲከኞች የሚያንጸባርቁት ጉዳይ ነው ::

አንድ በፐርሶናሊቲ ዲሶርደር ውስጥ የሚገኝ ግለሰብ

1. ሂስ አይቀበለም ::
"" እኔ ትክክል ባልሆንም አንተ ትክክል አይደለህም""
ስለሆነም ሂስ አትሰጠኝም ሂስህንም አልቀበለም ወደ ሚለው ጎራ ይገባል::

2. ግራ ሲገባው በሆነ ባልሆነው ማማረር ይጀምራል: እርዳታ የሚሰጠው ሰው ሲመጣ
"" እኔ ትክክል ባልሆንም አንተ ትክክል አይደለህም በማለት "" ራሱን ለማጽናናት ይፍጨረጨራል::

እነዚህ ነጥቦች የማያቁዋርጡ የፐርሶናሊቲ ዲሶርደር ግለሰብ የሚገኝባቸው ምህዋሮች ናቸው::
ሌላውስ ?
በሚቀጥለው

ሳይካትሪስቱ ቆቁ
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4055
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: የአእምሮ በሽታ ( ፐርሰናሊቲ ዲሶርደር)

Postby ጎነጠ » Wed Dec 11, 2013 3:33 pm

ቆቁ wrote:ይህንን የዋርካ ጄኔራል ከለቀቅኩ ዘመናት አለፉ
ለመሆኑ በዚህ በዋርካ ጄኔራል ውስጥ ስንቶቹ ናቸው የዚህ የፐርሰናሊቲ ዲሶርደር በችታ የተጠናወታቸው?

ፐርሰናሊቲ ዲሶርደር ማለት ምን ማለት ነው ?

አንዱ ዘራፍ በማለት ነብዩ መሐመድ እንደዚህ ነው ይልና ያቅራራል
ሌላው ዘራፍ ይልና ኢየሱስ እንደዚህ ነው ይልና ይደነፋል

ሌላው ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ ሲጻፍ እኔ ተንቼ ነበር እንዴት ነው የተጻፈው ብሎ ሊጠይቅ ይሞክራል


ሌላው ደግሞ ቁርኣን እንዴት እንደተጻፈ ስለማላውቅ ያዙኝ ልቀቁኝ ይላል

ሌላው የእኔ እምነት ከአለም አንደኛ ነው በማለት ያለ የሌለውን ጉልበቱን በማፍሰስ ሲተረትር ይውላል::

ሌላው አነበበም አላነበበም እንኪያ ሰላምታ ውስት ይገባና ከስድብ አልፎ ልደባደብ ለማለት ይቃጣዋል :.

ምንድነው ችግራችን ?

ሳይካትሪስቱ ቆቁ


ሁሉም አይመለከተኝም ብሎ እንደ አህያ ተኝቶ የሚያንኮራፋውን ከምን ትመድበዋለህ
I love ethiopia
ጎነጠ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 103
Joined: Wed Aug 03, 2005 9:07 am
Location: ethiopia

Postby ቆቁ » Fri Jan 10, 2014 7:00 pm

ጎነጠ ወዳጄ
ይህ ፐርሶናሊቲ ዲሶርደር እንዲገለጽ ቦታና ጊዜ ይፈልጋል

ፈረሱም ያው ሜዳውም ያው እንደሚባለው

ሜዳው ኖሮ ፈረሱ ከሌላ ወይም ፈረሱ ሜዳው ካልኖረ ነገሮችን ለመግለጽ ያዳግታል


ፐርሶናሊቲ ዲሶርደር
በትዳር
በፖለቲካ ድርጅቶች
በስራ ቦታ በመሳሰሉት

አርፎ እንደ አህያ የተኛው የቱ ቦታ ነው በየትኛው ጊዜ ነው የሚለውን ጥያቄ መመለስ ያስፈልጋል::

አርፎ የተኛው በስራ ቦታ የደረሰበት ችግር ከሌለ ስለ ፖለቲካ ዴንታ ላይኖረው ይችላል::

እስቲ በዚህ በዋርካ ጄኔራል ላይ ያለውን የእስልምና እና የክርስትና እምነት ተከታዮች
በዋርካ ፖለቲካ ላይ የሚደረጉትን ውይይቶች እስቲ ተመልከት

እንግዲህ የዋርካ የውይይት መድረክ ሜዳ የዋርካ እድምተኛ ፈረስ በማድረግ ምሳሌህን ውስድ
ፈረሱም ያው ሜዳውም ያው እንዳልኩህ

አንዱ ሌላውን አይሰማም ሌላው ያንኛውን አያዳምጥም
አንዱ ሌላውን ሲቃረን ሌላው ሌላውን ሲቃረን

አንዱ ባልተወለደበት ዘመን ያለ ያለፈ ታሪክ ሲያባንነው
ሌላው ባልተወለደበት ዘመን ጉራውን ሲቸበችብ

እምነትን ማስተማር ቀርቶ : መረዳዳት መተሳሰብ ቀርቶ የእኔ ሐሳብ ከአንተ ሓሳብ ይበልጣል በሚል እንተሮፕይ ውስጥ ነው የምንገኘው አናርኪይ በፖለቲካው አጠራር በኬምስቲሪ አጠራር ኢንተሮፒ ውስጥ ነው የምንገኘው

ይህ ዲሶርደር በሳይኮሎጂ ሲተነተን ፐርሶናሊቲ ዲሶርደር ወይም ናርዚዝም የሚባለው ነው ናዚ ከሚለው ቃል ጋር እንዳይምታታብህ

ይህ በሽታ ዲዛዝተረስ የሆነ የህብረተ ሰብ ጠንቅ ነው


ፈላስፋው ቆቁ
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4055
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Postby ቆቁ » Sat Jan 11, 2014 5:45 pm

ፐርሶናሊቲ ዲሶርደር ወይም ናርዚስም የምንለው ዝም ብሎ በባዶ ሜዳ የሚነሳ ዲሶርደር አይደለም::

እዩኝ እዩኝ
መታወቅን
እኔ አውቃለሁ ማለትን
ክሪቲክ አለመቀበለን: ከዛም አልፎ መበርገግን
የኔ ብቻ ነው ትክክል ማለትን
እኔ እኔ እኔ ብቻ ማለትን
ዝናን መፈለግን የመሳሰሉት ናቸው

ይህ ክራይቴሪያ እንዲሙዋላ ማለትም በክሪቲክ እንዳይደፈር ሁሉንም አውቃለሁ ለማለት ዝናን ለማትረፍ የግድ አንድ ግራውንድ ያስፈልጋል
ይህ ግራውንድ የምንለው ነገር በሕዝቦች መካከል የሚገኝ ማህበራዊ ግንኙነት ይሆናል

ይህ ማህበራዊ ግንኙንት
የፖለቲካ ድርጅት
የስራ ቦታ
የኩዋስ ቡድን
በትዳር ዓለም
በቤተ ሰብ ዓለም በመሳሰለው

አደገኛው የፐርሶናሊቲ ዲሶርደር ሁኔታ ግለሰብን ዲስትራክቲቨ በሆነ መንገስ ጥገኛ ማድረግ ይሆናል

ይህም ማለት ዲስትራክቲቭ ባህርይ ይዞ ዲስትራክቲቭ በሆነ መንገስ ግለሰብን ተብትቦ መያዝ ይሆናል

በዚህ ዲስትራክቲቭ ጠባይ ፐርሶናሊቲ ዲሶርደር ያለበት ግለሰብም ሆነ ጥገኛው ግለሰብ በጠቅላላው በሳይኮሎጂካል ዲሶርደር ይደቃሉ

ጥገኛው በሌላ መልኩ
ኛርዚስቱ በሌላው መልኩ ሁለቱም ይደቃሉ
ጥገኛውን ከጥገኝነት ነጻ ማውጣት እጅግ አስቸጋሪ የሆነ የሳይኮሎጂካል ፕሮሰስ ነው

ናርዚስቱን ከናርዚስትነ ማውጣት አይቻልም ቢባል ስህተት አይሆንም ከዛኛው የበለጠ አስቸጋሪ ነው


አንድን ናርዚስት የተናገረውን አያውቀውም ቢያውቀውም ስህተት መስሎ ከታየው አልተናገርኩም ብሎ ሲክድ አያፍርም እፍረት የሚባል ነገር አይታይበትም
ወይም አውቄ ነው የተናገርኩት በማለት ሊደመድም ይችላል ::
ባህል ሐይማኖት የሚባል ነገር አይመለከተውም ሰውን ማክበር ወይም ትህትና የሚባል ነገር በፍጹም የሚጠቀሱ አይሆኑም::

ጭንቅላቱ ዞሮበት የሌላውንም ጭንቅላት አዙሮ በመጨረሻው ዘመን ግራ ገብቶት እስኪሰናበት ድረስ አንድን በፐርሶናሊቲ ዲሶርደር የሚገኝን ግለሰብ መርዳትም ማከምም አይቻልም

እረዳለሁ ስትል
እኔ ትክክል አይደለሁም አንተም ትክክል አይደለህም ምኑን አውቀህ ነው የምትረዳኝ ምን ኖሮህ ነው የምትረዳኝ

አክማለሁ ስትል
አንተ ምኑን አውቀህ ነው እኔን የምታክመኝ
እኔ ትክክል ባልሆንም አንተም ትክክል አይደለህም ወደ ሚለው መሰረታዊ ጭግር ውስጥ ስለሚዘፈቅ

ቀንና ሰዓት ተገጣጥመው አንድን እርዳታ ከአንድ ግለሰብ ቢቀበል ለምሳሌ ሐኪም

አሁንም ዝናን ለማትረፍ የማይዘላብደው ነገር አይኖርም
የኔ ሐኪም ከአለም አንደኛ ነው
የኔ ሐኪም በጣም ቆንጆ ነው
የነ ሐኪም የሚነዳው መኪና

ገለመሌ ገለመሌ እያለ በመቀባጠር ራሱን ሲክብ የሚገኝ ዲሳስተር ውስጥ የሚገኝ ግለሰብ ነው


ይህ ግለሰብ የፖለቲካ ስልጣን ላይ የተቀመጠ ለታ ወይም
ወይም ይህ ግለሰብ በሐይማኖት ስም ትልቅ ቦታ የያዘ ለታ
ያን ጊዜ ነገር አበቃ ማለት ነው ::
ስር የሰደደ ፐርሶናሊቲ ዲስኦርደር ወይም የዚህ ፐርሶናሊቲ ዲሶርደር ምኞት

ታላቅ መሆን
ድንጋይ አምጪው አፈሩን ዋጪው ታላቅ መሆን
ዘፋኝ ሆኖ ታላቅ መሆን
ፖለቲከኛ ሆኖ ተናጋሪ መሆን ስልጣን ፍለጋ
በስራ ቦታ መሪ መሆን ሁሉንም አውቃለሁ ማለት
በሐይማኖት በኩል አዋቂ መሆን እኔ ብቻ ነኝ ለእግዜር ለአላህ የቀረብኩኝ ማለት የመሳሰሉት ከብዙዎች ጥቂቶቹ ናቸው

እንደዚህን ያለ ዝና ሲፈልጉ ጥገኛ እያስከተሉ ይሆናል ጉዞው ጥገኛው ደግሞ ከለሳቸው ማን አለ :: ካለሳቸው በአለም አንደኛ አለ:: ካለሱ ማን ዘፋኝ አለ : ካለ እሱ በስተቀር እንዴት ሊሆን ይችላል በማለት አብሮ መጨፈር ይሆናል

ይህ መጨፈር ግን የጤና ሳይሆን ተተብቶ በመታሰር የተዘረጋ ወደ አማኑኤል የሚወስድ በሽታ ነው

ፈላስፋው ቆቁ
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4055
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: የአእምሮ በሽታ ( ፐርሰናሊቲ ዲሶርደር)

Postby ቆቁ » Tue Oct 18, 2016 10:14 pm

እኔ የምለው ሁሉም መበጨጭ ጀመረ እንዴ ?
ፖለቲከኛው ፡ ሐይማኖተኛው ፡ ፍቅረኛው ፡ ስፖርተኛው በሙሉ መበጨጭ ጀመረ እንዴ ?
በጭጭ እንግዲህ የሐገሬ ልጅ ሁላ!! ተስማምቶ መኖር ካቃተህ ፡ተከባብሮ መፈቃቀር ካቃተህ ፡ መንገዱን ጨርቅ ያድርግልህ በጭጭ! በጭጭ !በጭጭ !!!
የመበጨጫ መንገዱ ሰፊ ነው
1. የለላውን ሐይማኖት እንዳልነበር በማድረግ መበጨጭ
2. የለላውን ብሄር እንዳልነበረ በማድረግ መበጨጭ
3. ያልተወለዱበትን ያልነበሩበትን ታሪክ በመተንተን ብርችንችን ብሎ መበጨጭ ፡ ከዛም ፖለቲካ ነው ብሎ ጮቤ መርገጥ
4. መቀበጣጠር ፡ የተናገሩትን አለማወቅ ፡ የጻፉትን አለማስታወስ ፡ የሰሙትን መርሳት፡ ያዩትን መካድ፡ ዝም ብሎ መንተባተብ
5.
ሳይካትሪስቱ ቆቁ
ይቀጥላል
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4055
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: የአእምሮ በሽታ ( ፐርሰናሊቲ ዲሶርደር)

Postby ቆቁ » Fri Oct 21, 2016 8:59 pm

የበጨጨው ሁላ

የሂንዱ ሜዲቴሽን በጦርነት ወይም በቻት ዝብርቅርቅ አይደለም እውሮፓና አሜሪካ የገባው
ሜዲቴሽን ፤ ራይኪ ፤ ሌሎችህም የቻይናና የሂንዱ የፊዚካል ልምምዶች በሰላማዊ ፍቅር ነው እያዘገሙ የገቡት
እምነት ሲተላለፍ እንደዚህ ነው ለገባው ሁላ
ለምሳሌ ክሪያላይሶን እያልክ ብትሰግድና ሶላት ብትሰግድ ሁለቱም አንድ ናቸው
ነገር ግን እምነትህ የግልህ ነው
ሐገር የጋራ ሐይማኖት የግል እንደተባለው ማለት
የማይሆን የእብዶች ቲዎሪ ይዞ ስለ ቁርዓን ስለ ስላሴዎች ፡ በማያውቁት ነገር ጥቂት በጣም ጥቂት አነቦ መዘበራረቅ
መዘበራረቅ ብቻ ሳይሆን ጨርቅን ጥሎ ማበድ ነው
በሰው ምነት ገብቶ ከመፈትፈት እስቲ የራስን እምነት ለመግለጽ ሞክሩ
የተገለጸውን እምነት ከመቃወም ይልቅ የተሻለውን ወስዶ ያልተሻለውን ጥሎ ወይም አርፎ በራስ እምነት አተኩሮ መከባበሩ አይከፋም ይላል
ሳይካትሪስቱ ቆቁ
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4055
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: የአእምሮ በሽታ ( ፐርሰናሊቲ ዲሶርደር)

Postby ቆቁ » Mon Oct 31, 2016 4:34 pm

ዋናው የፐርሰናሊት ዲሶርደር ችግር
መወያየት አለመቻል ነው
ውይይት
ከአንድ ዲሶርደርድ ከሆነ ግለሰብ ጋር መወያየት በጣም አስቸጋሪ ነው ምክንያቱም እውነትን ለመቀበል ስለሚያስቸግረው ፡፡
ለአንድ ዲሶርደርድ ለሆነ ግለሰብ እውነትም ውሸትም ሁለቱም አንድ ናቸው የሚፈልገው በንግግር ወይም በውይይት ራሱን የበላይ አድርጎ ማስቀመጥ እስከሆነ ድረስ
እውነትም ይነገር ፡ ውሸትም ይነገር እንደፈለገው ይሁን ነው መልሱ
ይህ ሁኔታ በማናጀሮችና የፖለቲካ ስልጣን ባላቸው ግለሰቦች ላይ የሚታይ እውነታ ነው፡፡
እኛ የተናገርነው መሬት አይወድቅም በማለት ማናጀሮች በስራቸው የሚገኙትን ሰራተኞች መከራ ስቃይ ያሳያሉ ፡
ፖለቲከኞች ከኛ በላይ የሚያውቅ አንድም የለም በማለት ሕዝባቸውን ያንገላታሉ
በዚህ መካከል ሕዝቡ ተንገላታ ሰራተኛው ተሰቃየ የሚባል ነገር ቢነሳ መንገላታት መሰቃየት ማለት ስለማይገባቸው ፡ የሚገባቸው ትእዛዜን ወይም የኔ ሐሳብ አልቀበል አሉ ስለሆነ ፡ በሁለቱም የስራ ረድፎች ዘንድ በማናጀሮችና በፖለቲከኞች ዘንድ ዲክታተርነት ይታያል
ልዩነቱ
ከማናጀሮች በመላቀቅ ሌላ ስራ በመፈለግ፤ ወደ ቤተ ክርስቲያን ፡ ወደ ቤተ እስላም ወይም ወደ ሳይካትሪስት በመሄድ ወይም በድህነት መኖር ሲቻል
ከፖለቲከኞች ግን እስራትና ሞት ይሆናል የሚጠብቅህ ከሳይኮሎጂካል ጭንቀት ባሻገር
ሳይካትሪስቱ ቆቁ
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4055
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: የአእምሮ በሽታ ( ፐርሰናሊቲ ዲሶርደር)

Postby ቆቁ » Thu Dec 08, 2016 6:21 pm

ይህ በሽታ እንደ ለሎቹ በሽታዎች ለሕክምና የሚያመች ወይም እንደ ሌሎች በሽተኞች አልጋ ላይ የሚያጋድምም በሽታ አይደለም
እነዚህ ግለሰቦች ቁመናቸው ሲታይ ጤነኛ ይመስላሉ ፡ እለባበሳቸው ሽክ ነው ፡ አነጋገራቸው ምንም ስህተት የለበትም፡ አዋቂም ሊሆኑ ላይሆኑ ይችላሉ የሳይንስ የተፈጥሮ የሐይማኖት የፖለቲካ ተመራማርዎችም ሊሆኑ ይችላሉ ፡ ችግሩ ያለው በሶሺያል ግንኙነት ላይ ይሆናል ፡ በሰው ልጆች መካከል ማለት ነው፡፡
በሽታው የጭንቅላት መዛባት ዓይነት ነው፡፡
ትክክለኛውን ዓለም እንደሌለ መቁጠር ዓይነት በሽታ ነው
በፐርሶናሊቲ ዲሶርደር የተበረዘ ግለሰብ የራሱን ዓለም ፈጥሮ የሚጉዋዝ ፍጡር ነው
" እኔ ትክክል አይደለሁም አንተም ትክክል አይደለህም"" የሚለው የፐርሶናሊቲ ዲሶርደር ሲተነተን
ግለሰቡ ትክክል መሆኑን አለመሆኑን አያውቀውም፡ ለማወቅም ችሎታ የለውም ፡ ቢያውቀውም ግድ የለውም ጭንቅላቱ ስለተዛባ ማለት ነው፡፡
የሆነ ነገር ስራ፡ ትክክል አይደለህም
የሆነ ነገር ተናገር ፡ትክክል አይደለህም
የሆነ ነገር ጻፍ ፡ትክክል አይደለህም
በዚህ ፐርሶናሊቲ ዲሶርደር በተለከፈ እጅ ውስጥ የገባ ግለሰብ ( ቪክቲም) መኖሩን እስከሚጠላ የራሱን ማንነት እስኪስት ድረስ በራሱ ማማረር ይጀምራል ማለት ይሆናል
ዛሬ ደግሞ ምን አደረግሁ ?
ዛሬ ምን ይመጣ ይሆን ?
ነገስ ምን ይመጣ ይሆን ?
ይህ ግለሰብ ( ቪክቲም) ከላይ የተጠቀሱትን ጥያቄዎች በአእምሮው እያመላለሰ ሊወጣው የማይችለው አዘቅት ውስጥ ይገባል ( ዲፕረሽን ፡ እብደት )
ሳይካትሪስቱ ቆቁ
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4055
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: የአእምሮ በሽታ ( ፐርሰናሊቲ ዲሶርደር)

Postby ቆቁ » Mon Jun 05, 2017 6:22 pm

እኔ ትክክል ካልሆንኩ አንተም ትክክል አይደለህም ከሚለው የፐርሶናሊቲ ዲሶርደር በመነሳት ሳይካትሪስቱ ቆቁ የሳይበር የፐርሶናሊቲ ዲሶርደርን ለመመልከት በፍልስፍናው ይሞክራል
በሳይበር የnarcissistic personality ባህርይ በሰው ልጆች በግልጽ ከሚታየው የሶሺያል ግንኙነት የተለየ ነው

ዛሬ ደግሞ ምን አደረግሁ? ዛሬ ምን ይለኝ ይሆን? የሚለው የቪክተም ባህርይ በዚህ በሳይበር ጨረባ አይታይም

ዛሬ ምን ጽፎ ይሆን የሚለው ነው
ዛሬ እገሌ ምን ጻፈ ? በማለት ወይም ይህንን ብጽፍ እገሌን አናድደዋለሁ የሚል ነው

በዚህ በሳይበር ጨረባ የሚታየው እኔ ትክክል ነኝ አንተ ትክክል አይደለህም ፡ እኔ ትክክል ካልሆንኩ ደግሞ አንተም ትክክል አይደለህም

ምክንያቱም በዚህ በሳይበር ጨረባ እስከ ዛሬ ድረስ አንድም የሳይበር ተጫራቢ የተግባባበት ጨረባ ወይም የተስማማበት ጨረባ ስለማይገኝ

ሁለት ወይም ሶስት ሰዎች ግሩፕ ይመሰርቱና በየመድረኩ ሲጫረቡ ማንበብ የተለመደ ነገር ሆኖአል ፡፡ለችግር መፍትሄ መፈለግ ወይም ለምን እንጨነባበራለን ለሚለው ጥያቄ መልስ ለማግኘት የሚሞክር የሳይበር ተጫራቢ የለም ፤

ተጫራቢው ሁላ የሚደሰተው በአንድ እዲስ በተከፈተ የጨረባ ውይይት የመጨረሻው ጸሐፊ በመሆኑ ብቻ ነው የሚደሰተው የሚኮፈሰው ፡፡

የመጨረሻው ጸሐፊ ፡ የመጨረሻው ተናጋሪ ጋር ተመሳሳይ ነው
በሚቀጥለው
በዚህኛው ጨረባ የመጨረሻው ጸሐፊ በሌላ ጊዜ የመጀመሪያው ጸሐፊ ይሆንና የመጨረሻው ለመሆን ሲንሰፈሰፍ እንድተረበሸ ተኝቶ እንደተረበሸ ይነቃና የመጨረሻውን ቃል ለመትፋት ሲዘላብድ .... ሲዘላብድ .... ሲዘላብድ .....
ሳይካትሪስቱ ቆቁ
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4055
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re:

Postby እሰፋ ማሩ » Tue Jun 06, 2017 6:31 pm

ቆቁ
እዚህ ቤት ከተሰጡት አስተያየቶች ልቤ የሚቀበለው ከታች ያቀረብኩት የፀዋር አባባል ነው፡፡የዚህ አይነት ፐርሰናሊቲ ችግር ያለበት ዋርካ ላይ እንእባብ የሚናደፍ የወያኔ ተቀጣሪ መሆኑ ብዙዎች የሚመሰክሩበት አለ፡፡ችግሩ ከፐርሰናሊቲ ዲስኦርደር በላይ ክሮኒክ ደረጃ የደረሰ ነው፡፡ምክር የሚቀበል አይደለም እየተንጠራራ ያለአቅሙ ላርም ይላል፡፡
ፀዋር wrote:እምነታቸውን የማያውቁ:: ስለሚያመልኩት ነገር ምንም ግንዛቤ የሌላቸው:: ሳያነቡ እንዳነበበ ሰው ለመከራከር አፋቸውን የሚከፍቱ:: ስለ ራሳቸው ምንም አይነት ግንዛቤ ሳይኖራቸው የሰዎችን ጤና ለመመርመር የሚከጅሉ:: ወዘተረፈ እንዳሉም መጠቆም ነበርብህ :D

ችግር ስትል ከጠቀስካቸው ቦታዎች መካከል አንዱ ላይ ራስህን ገልጸህ ቢሆን ኖሮ የጤነኛ ሰው ትዝብት እንለው ነበር:: But as the explanation on symptom of Narcissistic Personality Disorder shows, patients tend to believe that they are better than others and that it is the others who are sick :lol:

ቆቁ wrote:ጌታ ወዳጄ
ጥያቄ መጠየቅና መልስ መጠበቅ የጤናማ ሰዎች የኑሮ ዘዴ ነው::

ነገር ግን እነዚህ ፐርሶናሊቲ ዲሶርደር ያለባቸው ሰዎች መጠየቅ አይፈልጉም ማስረዳትም አይችሉም::
ማለትም ጤናማ የሆነ ውይይት ከነዚህ ግለሰቦች ጋር ማካሄድ በጣም የሚከብድ ነገር ነው::


እኔ ብቻ ነኝ ትክክል
እኔ ብቻ ነኝ ከሁሉ በፊት ሚስጥሩን ያገኘሁት
እኔ ብቻ ነኝ ከሁሉ በፊት መጽሐፉን ያነበብኩት
እኔ ብቻ ነኝ ከሁሉም በላይ ቅዱስ ቃሉ( ቁርዓንም ሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ) በትክክል የገባኝ
ያለ ኔ ቅዱስ ቃሉን ማንም መናገርም ሆነ መስበክም አይችልም በሚል ቅናት የተወጠሩ ቀናተኞች ናቸው::

በሌላ በኩል ደግሞ ቅዱስ ቃሉ ትክክል አይደለም የሚሉ ተቃራኒዎች አሉ እነዚህም በዚህ በሽታ የተለከፉ ናቸው

ትክክል አይደለም ሲሉ ደግሞ እኔ ብቻ ነኝ ምስጢሩን የማውቀው ለማለት ይከጅላቸዋል
የሚያነቡት አይገባቸውም ቢገባቸውም በጣም ትንሽ ነው ከዚህ ትንሽ እውቀት የተነሳ ነው እንግዲህ ካለኔ በስተቀር ማንም አያውቅም በማለት የቆጥ የባጡን ሲቀባጥሩ የሚታዩዝት

የሚያስለፈልፍ አባዜ ይባላል በአማኑኤል የዲክሽነሪ አጠቃቀም

ይህ በሽታ አደገኛ ነው አደገኛነቱ እንደሚከተለው ይተነትናል

ፐርሶናሊቲ ዲሶርደር ያለባቸው ግለሰቦች
ወደ ሐኪም ቤት መሄድ አይፈልጉም ምክንያቱም በሽታቸው ስለማይታወቃቸው ሳይሆን ስለሚደነግጡና ለዘላለም ጤነኛ የመሆን ፍላጎት ስላላቸውና በጣም ስለሚያፍሩ

እንደዚህ ያሉ ግለሰቦች ለዘላለም ትክክል የሆነ አስተሳሰብ እንዳላቸው ያወራሉ ማለትም አንሳሳትም ከሰው በላይ የምንገኝ ፍጡራን ነን ብለው ይገምታሉ

ሐሳባቸውን የሚቃረን ግለሰብ ካለ ቶሎ ብለው ይበግናሉ ከዛም ይዋሻሉ የዋሹት ሲታወቅባቸው በዋሹት ነገር አያፍሩም በዛው በውሸታቸው ይቀጥሉበታል:: ማስካካትም ይከጅላቸዋል


በዚህ በዋርካ ጄኔራል የሚገኝ መላው አባል ሁላ ይህ በሽታ አለበት ማለት ሳይሆን ነገር ከነዚህ ግለሰቦች ጋር በዚህ መልኩ እንኪያ ሰላምታ ከቀጠለ በጠቅላላው የዋርካ ጄኔራል ታዳሚ ሁላ ችግሩ ያሳስበዋል::

ሌላው ፐርሶናሊቲ ዲሶርደር ደግሞ
የነዚህ ግለሰቦች ጽሁፍ በጥሞና በማንበብ ሌሊት ሌሊት የሚቃዠው ይሆናል ይህ ደግሞ ሌላው ኤክስትሪም ነው ማለት ነው::
ስለዚህኛው ኤክስትሪም ማውራት አያስፈልግም ምክንያቱም ችግሩ ሲበዛበት ወደ ዶክተር ብቅ ማለቱ ስለማይቀር
ሳይካትሪስቱ ቆቁ
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1550
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm

Re: የአእምሮ በሽታ ( ፐርሰናሊቲ ዲሶርደር)

Postby ቆቁ » Sun Jun 18, 2017 4:00 pm

ቆቁ
እዚህ ቤት ከተሰጡት አስተያየቶች ልቤ የሚቀበለው ከታች ያቀረብኩት የፀዋር አባባል ነው፡፡የዚህ አይነት ፐርሰናሊቲ ችግር ያለበት ዋርካ ላይ እንእባብ የሚናደፍ የወያኔ ተቀጣሪ መሆኑ ብዙዎች የሚመሰክሩበት አለ፡፡ችግሩ ከፐርሰናሊቲ ዲስኦርደር በላይ ክሮኒክ ደረጃ የደረሰ ነው፡፡ምክር የሚቀበል አይደለም እየተንጠራራ ያለአቅሙ ላርም ይላል፡፡


ወዳጀ አሰፋ ማሪ
በነገራችን ላይ ከጸዋር ጋር መልካም የሆነ ውይይት ማሳለፋችን ትዝ ይለኛል፡ ነገር ግን አንተ እንደጻፍከው ዓይነት ጽሁፍ ለመለዋወጥ ጊዜ አልነበረንም ጊዜ ቢኖረንም አልፈለግንም ነበር ፡፡ ከላይ አንተ በኔ ስም ለለጠፍከው ዝባዝንኬ ለደቂቃም ቢሆን ቦታ አልነበረንም፡፡
የምልህ ነገር ቢኖር የተቀበልከው አምላክ ምህረቱን ይላክልህ ይሆናል ምክንያቱም በሽታህ በዶክተርም ወይም በሳይካትሪስት የሚድን ነገር ስላልሆነ

ወዳጀ አሰፋ ማሩ
እዝናለሁ ለዚህ ጥቅስህ ፡ ደገምከው ይህንን ነገር ፡ ከዚህ በፊት ክቡራን ነገሩን አስቀምጦት ነበር

በነገራችን ላይ የክቡራን ደጋፊ ነው ለዚህ ነው እንደዚህ ያልከኝ ብለህ እንዳትረግመኝ አደራ ! አደራ ! አደራ!
ብትለኝም አይደንቀኝም ነገር ግን እኔነቴን ለማዋረድ ያልጻፍኩትን እንደጻፈ ማድረግህ እኔን ሳይሆን አንተን ማን እንደሆንክ የሚያስቀምጥ ጉዳይ ይሆናል ፡፡

ያልጻፍኩትን ነገር ጠቅሰህ ( ኮት አድርገህ) ቆቁ የጻፈው ነው ለማለት ከሆነ ፍላጎትህ፡ ወንድሜ ወንድሜ እልሃለሁ እኔ ሳይካትሪስቱ ቆቁ ልጠቅሰው በማልችል በሽታ ተመርዘሃል ማለት ነው ፡፡ ይህም ማለት ጠላትህንም ወዳጅህንም መለየት ያልቻልክ፡ ወይም የማትችል የተበታተነ ነገር የሆንክ ብኩን ዜጋ በመሆንህ በጣም እዝናለሁ
መሳደብ መብትህ ነው መራገጥም መብትህ ነው ከዛም አልፎ መዘላበድም መብትህ ነው ማጭበርበርም መብትህ ሊሆን ይችላል እጅ ከፍንጅ እስካልተያዝክ ድረስ
ሳይካትሪስቱ ቆቁ ( ቻው ቻው ከሚለው መጽሓፉ )
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4055
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: የአእምሮ በሽታ ( ፐርሰናሊቲ ዲሶርደር)

Postby እሰፋ ማሩ » Mon Jun 19, 2017 1:38 am

ቆቁ -በሌላ ክፍል እጁ በወገኖቻችን ደም የጨቀየ የወያኔን ባለስልጣን ቴድሮስ አድሃኖም አፍሪካዊ ነው አትቃወሙት የምትል የግፈኞች ተባባሪ መሆንህን ተረድቻለሁ፡፡ዋርካ ላይ ብዙዎች የመሰከሩብህ የወያኔ ቫይረስ ያለብህ ነህ !የአይጥ ምስክር ድንቢጥ ሆነና ዋርካ ላይ የተጠላውን የወያኔን ጀሌ ተከትለህ እኔን ስትዘልፍ የምታሳዝን ነህ፡፡ፈጣሪ በህዝባችን ላይ ለምትሰሩት ግፍ ዋጋችሁን ይክፈላችሁ!
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1550
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm

Re: የአእምሮ በሽታ ( ፐርሰናሊቲ ዲሶርደር)

Postby ቆቁ » Fri Jul 07, 2017 3:22 pm

እሰፋ ማሩ wrote:ቆቁ -በሌላ ክፍል እጁ በወገኖቻችን ደም የጨቀየ የወያኔን ባለስልጣን ቴድሮስ አድሃኖም አፍሪካዊ ነው አትቃወሙት የምትል የግፈኞች ተባባሪ መሆንህን ተረድቻለሁ፡፡ዋርካ ላይ ብዙዎች የመሰከሩብህ የወያኔ ቫይረስ ያለብህ ነህ !የአይጥ ምስክር ድንቢጥ ሆነና ዋርካ ላይ የተጠላውን የወያኔን ጀሌ ተከትለህ እኔን ስትዘልፍ የምታሳዝን ነህ፡፡ፈጣሪ በህዝባችን ላይ ለምትሰሩት ግፍ ዋጋችሁን ይክፈላችሁ!

ፐርሶናሊቲ ዲሶርደር ይሉሃል ይሄ ነው፡፡
በኔ ከላይ የተጻፈው አርእስት የፐርሶናሊቲ ዲሶርደር የሚመለከት ነበር ነውም ፡፡
የአንተ ትንተና ግን ለየት ያለ ቢሆንም የፐርሶናሊቲ ዲሶርደር ችግር መሆኑን ለመረዳት አያዳግትም፡፡
ነፍሱ ምህረቱ ይላክልህ ሌላ ምን እልሃለሁ? ምህረት ማለት እብደት ማለት እንዳልሆነ ከገባህ ነው ይህንን የምልህ

ይህ አጀንዳ እኮ አንተ ስለጠራኽው ግለሰብ መወያያያ ሳይሆን እንዳንተ ላሉ ፐርሶናሊቲ ዲሶርደር ላለባቸው የተጻፈ አጀንዳ ነው ፡፡

የገረመኝ ምስክር መደርደርህ ነው ፡፡ በሌለ አነጋገር ፡ በምናብ ውስጥ የተዘፈቅህ ግለሰብ መሆንህ ይገባህ ይሆን ?

ለአንድ ፐርሶናሊቲ ዲሶርደር ውስጥ ለሚገኝ ግለሰብ ምስክር ኖረ አልኖረ ፋይዳ የለውም

ሲመቸው ምስክር አለ ይላል ካልሆነ ደግሞ ማን አንተን መስካሪ አደረገህ ይልና ያርፈዋል ምክንያቱም " እኔ ትክክል ካልሆንኩ አንተም ትክክል አይደለህም" ስለሆነ የናርሲስቲክ ፐርሶናሊቲ ዲስኦርደር ጠባይ

ፐርሶናሊቲ ዲሶርደር ያለበት ግለሰብ፡

1፣ የሚጽፈውን አያውቅም ቢጽፍም ጻፍኩ አይልም፡ እኔ የጻፍኩት የጻፍኩትን አይደለም ነገር ግን የምጽፈውን የጻፍኩት ነው የሚለው

2. የሚጽፈውን ነገር የት እንደጻፈ አያውቅም ፡ ስለምን እንደጻፈም አያውቀውም ፡የሚጻፍበትን ቦታ ቢነግሩትም መስማትም ሆነ ማንበብ አይፈልግም የተጻፈውን ነገር የሚፈልገው ዋርካ ላይ ሳይሆን ኒዎርክ ታይምስ ላይ ወይም ታይም መጋዚን ላይ ነው

3. ደገፈም ሆነ ተቃወመ ሁሉም አንድ ነው በፐርሶናሊቲ ዲሶርደር ውስጥ ለተዘፈቀ ግለሰብ ከደገፍክ ተቃወምክ ነው ከተቃወምክ ደገፍክ ነው ወይም ደገፈ ተቃወመ ቃላቱ ብቻ ሳይሆን ፊደሉም ተመሳሳይ ነው የሚሆንበት፡ ፊደሉ ካለተመሳሰለ በእንግሊዘኛ ፊደል አንድ መሆን አለበት በማለት የዌብስተር ዲክሽነሪ ላይ ተጻፈ የሚል ግለሰብ ነው

እኔ ትክክል ካልሆንኩ አንተም ትክክል አይደለህም
እኔ ከተበላሸሁ አንተም የተበላሸህ ነህ

ሳይካትሪስቱ ቆቁ
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4055
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

PreviousNext

Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest