ልማታዊ ሚስት ይስጣችሁ የዋርካ የፍቅር ተወያዮች..ሎል

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)


Re: ልማታዊ ሚስት ይስጣችሁ የዋርካ የፍቅር ተወያዮች..ሎል

Postby ክቡራን » Wed Jun 28, 2017 1:01 pm

ይሄን ፎቶ አይቶ እንዱ ምን ብሎ ጻፈ መሰላችሁ.." ፍየል እንዳያይሽ.." ሎል
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7709
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Re: ልማታዊ ሚስት ይስጣችሁ የዋርካ የፍቅር ተወያዮች..ሎል

Postby እንድሪያስ » Sun Dec 24, 2017 11:05 pm

ክቡራን wrote:Image
ክቡራን እንደምን አለህ ? እነ ሾተል፣ቆቁ፣ጥልቁ፣ዲጎኒ፣ተድላ፣አንፌቃ ወዘተ የት ገቡ :-D
እንድሪያስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1779
Joined: Fri Mar 19, 2004 10:55 pm
Location: *****

Re: ልማታዊ ሚስት ይስጣችሁ የዋርካ የፍቅር ተወያዮች..ሎል

Postby ዞብል2 » Fri Dec 29, 2017 11:00 pm

ሰላም ጋሽ እንድሪያስ አሁን ዋርካ ብቅ ያልከው፡የትኛውን መፅሄት አንብበህ ነው?ቅቅቅቅቅ
ዞብል2
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1931
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Re: ልማታዊ ሚስት ይስጣችሁ የዋርካ የፍቅር ተወያዮች..ሎል

Postby ሾተል » Thu Feb 01, 2018 10:34 am

እንድሪያስ wrote:
ክቡራን wrote:Image
ክቡራን እንደምን አለህ ? እነ ሾተል፣ቆቁ፣ጥልቁ፣ዲጎኒ፣ተድላ፣አንፌቃ ወዘተ የት ገቡ :-D


ወንድም እንድርያስ፡.፡እንደምን አላችሁልን?እኛ ደህና ነን አልን።ዋርካ የጠፋነው 1 በድንች ገንፎና በካሮት አጥሚት ተወጥራ ያደገች የማክዶናልድ ፕሮዳክት ሱሰኛ ቤት ማያስገባት የራሻ ችክ ለኑሮ ብዬ ይዤ አይገፉት ተራራ እየገፋሁ ባተሌ ሆኜ ነው።መቼም ለመኖር ሲባል ያለ ውሎ ይዋል የለ?ያንን በሰው ነበር የማየው አሁን ግን በኔ ደርሶ ቁጭ አለ።
ትንሽ ወደሁዋላ በወጣትኔቴ በዛ የዋርካ የተጡዋጡዋፈ የጨዋታ ዘመን የነበረኝን ጣፋጭ ጊዜ ወደ ሁዋላ እንደ ክላሽንኮፍ ቀላ ተስፈንጥሬ በትዝታ አለም ተንቡዋልዬ ያንን ጣፋጭ ጥሎ ጠያቂ ጉልበቴን ጨምሮ ሳስታውሰው ትማስ ወርቅ ውስጥ ተሸንቁሬ የምጠግብ አይመስለኝም ንበር።አይ ወጣትነት እንዴት ማለፍያ ነው?የዛኔ ቢሆን እንኩዋን ይቺን ትሬንታ ኩዋትሮ የምታክል ራሻ አይደለም አይፋ ጂፕ አንቶኖፍ ካርጎ ፕሌን የሚያክሉ ተሰልፈው ቢመጡ አንድ በአንድ ምሳቸውን አብልቼ አንጎላቸው ውስጥ ተወትፌ ሌት ተቀን እኔን እንዲያስቡ አደርግ ነበር።ሲያረጁ አያምሩ ሆነና ይሄው ዛሬ አንዲት የቢግ ማክ ሱሰኛ ላታም ራሻዊን እያጣጣምች መድረስ ከፈለገችበት ጣራ ለማድረስ አንድ ቀን ቀጥ ሳያደርገኝ ባይቀርም ያንን ኪኒና እየወሰድኩ ለ 10 ሰከንድ ከደረስኩ እሱም እኔው ሆኜ ነው፡.የምቅመው ኪኒን አዳብት ሲያደርግ በላዩ ላይ ዶዙን እየጨመርኩ እያባዛው እየዋጥኩ ነፍሱን ይማረውና እንደ ማይክል ጃክሰን አርተፊሻል ሆኔልሃለሁ።በዛ ላይ ጋግርታሙዋ ዝሆኔ የዛ ነገር ሱሰኛ ስለሆነች 10 ሰከንድም ይሁን 1 ደቂቃ የራሱ ጉዳይ ናና ቼ ፈረሴ በለኝ እያለች በየደቂቃው ማእድን ቆፋሪ እስክመስል ያንን የምወደውን ፕሮፌሽን እስክጠላው ድረስ የማእድን ጉርጉዋድዋን ታስቆፍረኛለች።
ምርር ብሎኛል።ባካል ሲያዩኝ ይቺ የሃምበርገር ቅልብ ደህና አድርጋ ይዛዋለች ነው የሚባለው..ከእሱዋ የተራረፈ አርተፊሻል ፍርፋሪ እየቀመስኩ ላዬ ያማረብኝ ይመስላል…ውስጤ ቢበላም ማለት ነው።ያው እርጅና መጥቶ እንደድሮው ሮጥ ሮጥ ብሎ እንዳይሰራ ጉልበቱ ከየት ይምጣ።ስለዚህ ያው ጣራ ያለው ቤት ውስጥ ለማደር ክምሬ ቪድዮ በአራት አቅጣጫ ደቅነን እንትን ስንል ተቀርጸን ፊልሙን እንቸብችበው ብትለኝም ያንን ፊልም ሰው አይቶ ምን የኛል ብዬ የማልልበት ደረጃ ስለደረስኩ እምቢ የምላትም አይመስለኝም።

ውይ አሁን እየተመነሁ ያለሁት ሰሞኑን የሮቦት ሚስትና ባል ፈልስመናል በቅርብ ጊዜ ገበያ ላይ ይውላል ብለዋልና እሱ ገበያ ላይ ወጥቶ እኔና እሱዋን ፋብሪካው ድረስ ሄደን እኔን የመሰለ መሸጦ ክሎን አድርገው በሮቦት መልክ ሰርተው ሲያበቁ የሰው ኪስም ይሁን አውልቄ ገዝቼላት ሮቦቱ ጋር የወር ፕሮግራም አውጥተን ተራ በተራ ብናስደስታት እያልኩ እመኛለሁ።ያው ክሎኔ ቢያግዘኝ ብዬ ባስብ ነው ይሄንን ያልኩት።

ይቺ ድንች አማራኝ ኖሮ ሴት ልጅ ሳይ ወንትድ ተብዬ ያዳምና የሄዋን ዝርያን ሳይ ፖሊስ እየመሰሉኝ ምንገድ ለምንገድ በፍርሃት ስሮጥ ላየኝ አይ ሾተል በክብርነታቸው ሆነው ለቀቁ የማይለን ማን ይኖር ይሆን?ወይ ነዶ።

እና ለዛ ሲባል ነው የጠፋነው እንጂ አለን።ተቆፍሮ የማይወጣ የማእድን ሳይት ሌት ተቀን ሰከንድ ከደቂቃ ሳንል እየቆፈርን ነው።

በጨዋታችን መሃል ዋርካ አሁን የደረሰችበት ሁኔታ አያሳዝን?የሳይበር ዋርካ ባልተቤቶች በቢሆናለም የሚኖር ፖለቲከኛ አይሉት ተቃዋሚ ብቻ በከብትነቱ የትየለሌ የሆነን ከብት አናስቀይምም ብለው ይሁን ዲላቸው ምን እንደሆነ ባይታወቅም እሱ በየደቂቃው ከየድረገጹ ቀራርሞ የሚያመጣቸውን ሰጥስጥ ቱልቱላ ምናምንቴ እዚህ እያመጣ በደደብነቱ ዋርካን ሲገል ዝም ብለዋል...እሱን የተናገረን አስፈንጥረው ያስወጣሉ።ስለዚህ ክብርነታችን የኢትዮጽያና ኢትዮጽያዊያን ሁኔታ ወደፊት ከመጉዋዝ እንደ ግመል ሽንት ወደ ሁዋላ ስለሆነ ስለ እኛም መስማት ማንበብ ማውራት ወደማቆሙ ደረጃ ላይ ነን።

እግዜር ክብሩ ይስፋ ትራምፕን የመሰለ አስቂኝ ግራ የገባው ፕሮእዚደንት አሜሪካ ውስጥ አስቀምጦልናል።እሱን በየደቂቃው ብከታተል ቢያንስ ሥስቅ እውላለሁና ጨዋታዬን ቀይሬ የኛ የነኩት አንድም ቦታ ላይ ለጊዜው መሳተፍ አቁሜ ሊያበስለኝ የሚችሉ ነገሮችን ከድሮው በበለጠ እየተከታተልኩ እያነበብኩ...ዶኩ ፊልሞችን እያየሁ የየአገሩን የፖለቲካ የታሪክ የመልከአምድር ወዘተ ሁኔታዎችን እንዴው ለማወቅ ያህል ወጥሬ እየተከታተልኩ እገኛለሁ።

የኛ ነገር ታጥቦ ጭቃ ስለሆነ በኛ የምኮራበት ስሜት እየሳሳ መጥቶዋል።
ዲያስፖራ ኮምፒውተር ጀርባ ሆኖ በሚለፈልፈው ፉከራ እውነት እየመሰላቸው ያገሬ ገበሬዎችና የገበሬ ልጆች በጥይት ይቆላሉ።ዘረኝነት ተስፋፍቶ ሁሉም ከዘሩ ጋር ተሸክፎ አንዱ ብሄር አንዱን እየሰደበ እያንቁዋሸሸየራሱን ከፍ እያደረገ በሚገኝበት ሰአት እንዴት ይሄንን የሚያይ የሚሰማ አንጎልና አይን ይኑረኝና እኛን እኛን ልሽተት?የሚገርመው የሰውን የቤተሰብ ብሄር እያሳደዱ ወደ አሳፋሪው ጥላቻቸው እንዲገባ በፌስ ቡክና በተለያዩ ማህበራዊ መገናኛዎች የሰውን አድራሻ እያሳደዱ ወንድም አለም አማራ ነህ አይደል…ኦሮሞ ነህ አይደል ወዘተ እያሉ ሊጀነጅኑና የተለከፉት ነቀርሳ ውስጥ ሰውን ሊያስዋኙ መልክት ሲልኩ ሳይ እስቃለሁ።የማይገባቸውን አንድነት ሲያስተምራቸው የፈረደበት ትግሬና ወያኔ ውስጥ ከተው ሰድበው ለሰደቡት ተመጣጣኝ የመልስ ምት ሳይሰጣቸው ሰውን ብሎክ የሚያደርጉት ነገር እራሱ ግርም ይለኛል።

ብቻ በዚህና በነዚህ ምክንያቶች ነው የድሮ የዋርካ ተሳታፊዎች የጠፋነው።

ለነ ቂጡ ሰፋ ማሩ ዋርካን ለጊዜ አስረክበን በወር አንዴም ቢሆን እንደዛሬው ብቅ ብለን የምናየው።መቼም ከጭንቅላት ያልተጻፈ ከዩዝለስ ዌብ ሳይቶችና ብሎጎች ኮፒ ፔስት እየተደረገ የሚመጣን ቅራቅንቦ ለማየት ሰው አይመጣ።

የሰፋ ስቴፓው ማሩን ኮፒ ፔስት ለማየት ስበር ዋርካ ከምመጣ ስለማይገባኝ ዩኒቨርስ ናሳ ጭንቅላቴ ውስጥ ዩኒቨርስቲ ከፍቶ በዛ ላይ የሳይንስ ቤተ መጽሃፍቶችን ቢገነባና በደሜ ውስጥ ቢሰጠኝም ሊገባኝ ከቶም የትየለሌ የሚሆነውን ስለ አዳዲስ የዩኒቨርስ ሚስጥሮች ጋር ብፋጠጥ ይሻላል።

ማለቴ ለመሳቅ የኔ ቻርልስ ቻፕሊን ትራምፕ ይበቃኛል።

እንድርያስ አስታውሰህ ስለጠየቅከን እናመሰግናለን።እነ ክቡራን የጠቀስካቸው ተላ ቁሉ ሳይቀር ባሉበት ቦታ ሰላም እንደሆኑ ተስፋ አደርጋለሁ።

ሰላምህ ይብዛ።

መልካም አዲስ አመት።

ሾተል ነን.…በክብርነታችን ሆነን አሁንም ኦስትርያ ዋና ከተማ ቭየና ነን።በሁለቱም አቅጣጫ ለሞቱብን ወገኖች ሃዘናችንን እንገልጻለን።የወገኖቻችንን ነፍስ ይማርልን።አሜን!!!
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
www.shottel.webs.com
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9618
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria


Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests