በ ባሕርዳር በተጣለዉ ፈንጂ ሕብረተሰቡን ማሳሳቻ ድራማ ለመስራት የታቀደው ከሸፈ

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

በ ባሕርዳር በተጣለዉ ፈንጂ ሕብረተሰቡን ማሳሳቻ ድራማ ለመስራት የታቀደው ከሸፈ

Postby ኳስሜዳ » Tue Aug 15, 2017 7:24 pm

በባሕር ዳር ሐምሌ 30 2009 እና ነሐሴ 6 2009 በሕወሐት የደሕንነት አባላት የንግድ ተቋም ላይ እና በአመራሮች ላይ ኢላማ ተደርጎ የተጣለዉ ቦንብን አስመልክቶ አገዛዙ ሕዝቡን ያሳምንልኛል በማለት ለፖለቲካ ፍጆታ ለማዋል የፊልም ቀረጻ ለማድረግ አስቦ ለዚሁ አላማ ከተጠሩት ዉስጥ አንድም ወጣት ፈቃደኛ ሳይሆን መቅረቱ ታዉቋል።

አገዛዙ ላይ ከፍተኛ ድንጋጤን የፈጠረዉ ይኸዉ በሐምሌ መጨረሻና በነሐሴ መጀመሪያዎቹ የተጣለዉ ፈንጂ በሚገባ ጥናት ተደርጎበት የተጣለ ነዉ በማለት የሕዝቡን ምልከታ ለማስቀየር ቦንቡን የወረወሩትን በቁጥጥር ስር አዉለናል የሚል የፊልም ቀረጻ እንዲካሔድ የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽሕፈት ቤት ለሚመለከተዉ ክፍል በላከዉ ሪፖርት መሠረት በትናንትናው ምሽት ጥምር የፀጥታ ኮሚቴው ተሰብስቦ ቀረፃ እዲደረግ መወሰኑ ተገልጿል።

የፊልም ቀረጻው ዋና አላማ በአንድነት ኃይሎች የሚደርሰዉ ይኽ ጥቃት በአገዛዙ ላይ ከፍተኛ ድንጋጤን በመፍጠሩና ሕዝቡን አረጋግተን ቅቡልነት እናገኛለን ከሚል ከንቱ ምኞት እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል። ለዚህ የፊልም ቀረጻ የተመረጠዉ ወጣት የቀረበለት ማማለያ በሚሠራዉ ሥራ ላይ እድገት እንደሚያገኝ እና በቅርቡ ደሞ በዉጪ አገር ባሉ የኢትዮጵያ ኢምባሲዎች ዉስጥ ሥራ እንደሚሰጠዉ የተነገረዉ ቢሆንም መልኬ በቴሌቪዥን የሚታይ ከሆነ አልፈልግም በማለቱ የፖሊስ ኮማንደር የሆኑት ኮማንደር ዋለልኝ ሰጠ በንዴት ወደ እስር ቤት እንዲገባ ትዕዛዝ ሰጥተዉ በእስር ላይ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።

ከብሔራዊ መረጃ፣ ከፖሊስ መረጃ እና ሌሎች የስርዓቱ ደጋፊ ከሆኑ ሲቪል ግለሰቦች በመጣመር ሊሠራ የታሰበዉን ፊልም የሚተዉን ተቀያሪ ግለሰብ በማዘጋጀት የብሔራዊ መረጃ ክፍሉ ስልጠና ሰጥቶት ለፊልም ቀረጻዉ መዉጣታቸዉንም የደረሰን ሪፖርት ያሳያል። ለዚህ ፊልም ቀረጻ ስልጠና የተሰጠዉ ግለሰብ ፊልሙን ለመሥራት ቦንቡ ተጥሏል በተባለበት ቦታ መሰማራታቸዉም ታዉቋል። ፊልሙን ለመቅረጽ የፖሊስ ፊልም ቀራጮች ብቻ እንዲሆኑ የተወሰነ ሲሆን ይኽም የሆነበት ዋነኛ ምክንያት የአማራ መገናኛ ብዙሃን ላይ እምነት በማጣታቸዉ እንደሆነም ለዝግጅት ክፍላችን የደረሰዉ ሪፖርት ያሳያል።

http://amharic.abbaymedia.com/archives/34231
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2140
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 5 guests