ብርጋዴር ጀነራል መላኩ ሽፈራው ስርዓቱን ከዱ

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬


Re: ብርጋዴር ጀነራል መላኩ ሽፈራው ስርዓቱን ከዱ

Postby ኳስሜዳ » Fri Oct 06, 2017 9:07 pm

የጠቅላይ ሚኒስተሩ የፕሮቶኮል ሃላፊ ስር ዓቱን ከድተው አሜሪካ ላይ ጥገኝነት መጠየቃቸውን ይፋ ማድረጋቸውን ካስታወቁ አንድ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የሕወሃት መንግስት ሰራዊት አባል የሆኑት ብርጋዴር ጀነራል መላኩ ሽፈራው በተመሳሳይ መክዳታቸው ታወቀ::

የሕወሃት መንግስት በከፍተኛ ክፍፍል ውስጥ እንዳለ እየተነገረ ባለበት በዚህ ወቅት በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ውስጥ እያገለገሉ የነበሩት ብርጋዴር ጀነራል መላኩ ሽፈራው ስርዓቱን ከድተው በአሜሪካ ጥገኝነት መጠየቃቸው የሚጠበቅና ሌሎችም የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት በተከታይነት የሚያደርጉት ነው ሲሉ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ::

ብርጋዴር ጀነራል መላኩ ሽፈራው ጥሩነህ ከአንድ ወር በፊት በአሜሪካ የተካሄደውን የጸረ አይሲስ ስልጠና ለመውሰድ ለመካፈል ወደዚያው ማቅናታቸውን የሚገልጹት ምንጮች በዚያው አሜሪካ መቅረታቸው ታውቋል::

በመከላከያ ሰራዊቱ ውስጥ ባለው የሕወሃት የበላይነት የተነሳ በርካታ የጦር መኮንኖች ደስተኛ እንዳልሆኑ የሚነገር ሲሆን የአማራና የኦሮሞ ተወላጅ የጦር መኮንኖች በዘራቸው እንደሚሰደቡ በተደጋጋሚ መዘገቡ አይዘነጋም:: ብርጋዴር ጀነራል መላኩ ሽፈራው በቅርቡ በሰራዊቱ ውስጥ ያሉትን ያልተሰሙ ምስጢሮች ያዝረከርኩታል ተብሎ እየተጠበቀ ነው:::

በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ውስጥ ያለውን ጉድ ሳዲቅ አህመድ በሚከተለው መልኩ ዘግቦት ነበር:: ይመልከቱት::
http://www.zehabesha.com/amharic/?p=81276
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2148
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests

cron