በክልላችን የሚሰሩትንም ሆነ የሚኖሩትን የአማራ ተወላጆች ሁሉ እናባርራለን-አብዲ ኢሌ

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

በክልላችን የሚሰሩትንም ሆነ የሚኖሩትን የአማራ ተወላጆች ሁሉ እናባርራለን-አብዲ ኢሌ

Postby ኳስሜዳ » Sat Oct 07, 2017 10:35 am

የሶማሌ ክልላዊ መስተዳድር ፕሬዚዳንት አብዲ ሞሀመድ ኦማር ወይም በቅጽል ስሙ አብዲ ኢሌ በክልላችን የሚሰሩትንም ሆነ የሚኖሩትን
አጠቃላይ የአማራ ተወላጆችን እናባርራለን ሲል መግለጫ አወጣ።

የክልሉ ፕሬዚዳንት ሰሞኑን ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር በመሆን በኦሮሞና በሶማሌ ክልል መካከል የተፈጠረው ጦርነት በኦሮሞ ህዝብ በኩል የቀድሞውን አምባገነናዊ የደርግ ስርዓት ለመመለስ ከመፈለግ የተነሳ ጦርነት ነው ሲል ክልሉን እንዳለ አቁስም ማስያዙን መግለጻችን
ይታወቃል።
Image

አቶ አብዲ ኢሌ ይህን በኦሮሞ ሕዝብ ላይ ከወሰደው አቋም በኋላ በሁለቱ ክልሎች ግጭት የነፍጠኛ፣ የባለፈው የደርግ ስርዓት ርዝራዥ የሆኑት አማሮች ከኦሮሞ ህዝብ ጎን በመሰለፍ የክልላችን ልዩ የፖሊስ ሃይል ላይ ከፍተኛ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ ከፍተዋል ሲል የአማራን ተወላጅ በጅምላ ከሷል። ለዚህ ደግሞ መፍትሄ በክልላችን የሚኖሩትም ሆነ የሚሰሩትን የአማራ ተወላጆች ከክልላችን ማባረር በመሆኑ ለውሳኔው ተግባራዊነት የካቢኔት አባላትን ለስብሰባ ጠርቻለሁ በማለት በራሱ ገጽ ላይ ይፋ አድርጓል።

እንደ አቶ አብዲ ኢሌ አባባል የኦሮሞው አክቲቪስት ጁሃር መሀመድ፣ ቄሮና ኦፒዲኦ በጥምረት አብረው የሚሰሩ ናቸው ሲል ከወነጀለ በኋላ በማያያዝ አማሮች ደግሞ በኦሮሞ የተወሰደብንን መሬት በመደገፍ ከኦሮሞ ጋር ወግነው የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ ስለከፈቱብን ወደ ክልላቸው ልናባርራቸው ወስኛለሁ ሲል ያትታል።

በኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች በተነሳ ጦርነት በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች ከሁለቱም ወገን የተገደሉ ሲሆን ቁጥሩም በግምት ከ75 ሺህ የሚበልጠው የኦሮሞ ተወላጆች ከሶማሌ ክልል ተባርሮ በሐረር፣ ድሬደዋ፣ አዳማና ጭናቅሰን መጠለያ ጣቢያዎች ተጠልሎ ለእንግልት መዳረጉ ይታወቃል።

አቶ አብዲ ኢሌ እነዚህ የዳግማዊ ምንሊክ የልጅ ልጅ ልጆችና የደርግ መንግስቱ ሃይለማርያም ርዝራዥ አማሮች በኦሮሚያና ሶማሌ ክልል የመሬት ይገባኛል ውዝግብ ከኦሮሞ ጎን በመቆማቸው ከሶማሌ ክልል እናባርራቸዋለን ሲል ዝቷል።
http://amharic.abbaymedia.com/archives/36945
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2140
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Bing [Bot], Google [Bot], Google Adsense [Bot] and 6 guests