የዓባይ ጣር የህዝብ ቁጥር መጨመርና የአካባቢ ብክለት

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

የዓባይ ጣር የህዝብ ቁጥር መጨመርና የአካባቢ ብክለት

Postby እሰፋ ማሩ » Thu Oct 19, 2017 4:05 am

የዓባይ ጣርየህዝብ ቁጥር መጨመርና የአካባቢ ብክለት
ቢቢሲ የብሪታኒያ የዜና ስርጭት-18 ኦክተውበር 2017
የተለያዩ ፍሳሾችም ተፋሰሱን ስለሚቀላቀሉ የዓባይ ውሃ ጥራትም እየቀነሰ ነው
የዚህን ልዩ ዘገባ የመጀመሪያ ክፍል ማንበበብ ከፈለጉ ይህን መጫን ይችላሉ።
ዓባይ ከመነሻው ጣና ሐይቅ ተነስቶ ታላቁን የህዳሴ ግድብ አቋርጦ ሱዳን ርዕሰ-ከተማ ካርቱም ይደርሳል።
በመጨረሻ ጥቁርና ነጭ አባይ በሚገናኙበት ቦታ ወንዙ በዝግታ ተንጣሎ መደበኛ ቅርጹን ይይዛል።
በየጊዜው እየተስፋፋች ከመጣችው ከተማ የሚወጡ የተለያዩ ፍሳሾችም ወንዙን ስለሚቀላቀሉ የዓባይ ውሃ ጥራትም እየቀነሰ ይመጣል።
የህዝብ ቁጥር መጨመር በህሉም የአካባቢው ሃገሮች እየታየ ነው፡፡የግብጽ ህዝብ ቁጥር ከአውሮፓውያኑ 1960 ጀምሮ ከአራት እጥፍ በላይ ጨምሯል። ኢትዮጵያም በየዓመቱ 2.5 ሚሊዮን የሚሆን ህዝብ ትጨምራለች። የተፋሰሱ ሀገራት ህዝብ ቁጥር በአውሮፓውያኑ 2050 በእጥፍ ጨምሮ 500 ሚሊዮን ሊደርስ በሚያስችለው መንገድ እየተጓዘ ነው።ጥቁር ዓባይና ነጭ ዓባይ ካርቱም ላይ ይገናኛሉ፡፡
"ሁልጊዜም ወንዙን በአግባቡ አንይዘውም፤ ለሁላችንም እንደሚበቃ ስናስብ ቆይተናል'' ይላሉ መሃንዲሱና በትርፍ ጊዜያቸው አሳ የሚያጠምዱት የሱፍ አቡግራውን።
አሁን አሁን ዘወትር ማምሻውን የሚይዙት አሳ ብዛት ከአስር አመት በፊት ከነበረው አንድ አስረኛውን ብቻ ነው።ምናልባት አሁን እኛ በጣም ሳንበዛ አልቀረንም'' ይላሉ።
ካርቱምን የገጠማት ችግር የሌሎቹም የተፋሰሱ ሀገራት ከተሞች ማሳያ ነው።ባለፉት ጥቂት አስርት ዓመታት ካርቱም በየጊዜው እየሰፋችና ይዞታዋም እያደገ ቢመጣም የቆሻሻ ውሃ ማስወገጃ ሥርዓቷ ግን ብዙም ዕድገት አላሳየም።
በቂ የሆነ የቆሻሻ መጣያ በሌለበት ሁኔታ ፋብሪካዎችና የንግድ ተቋማት ፍሳሻቸውን በራሳቸው መንገድ ማስወገድን መርጠዋል።
እናም ከጦር መሣሪያ ፋብሪካ መርዛማ ፍሳሾች ጀምሮ፤ በዝሆን ቀንድ ግብይት ምክንያት የሚጣሉ የእንስሳት የሰውነት ክፍሎች በደለል ወደተሞላውና በኬሚካሎች ወደ ተበከለው ውሃ ይደፋሉ።
የሱዳን የሲቪል ማህበረሰብ አባላት መዳከማቸው ደግሞ ሁኔታውን አባብሶታል።
የሸማቾች ጥበቃ ቡድን መሪ በመንግሥት ላይ የአካባቢ ጥበቃን በተመለከተ ከፍተኛ ግፊት በማሳደሩ ምክንያት በአውሮፓውያኑ 2014 አስራለች።
እናም ሌሎች የአካባቢ ተቆርቋሪዎች ተመሳሳይ ዕጣ እንዳይገጥማቸው በመስጋት ዝምታን መርጠዋል።
የአሸዋ ክምሮች
በሰሃራ አድርጎ ወደ ሰሜን ሲጓዝ ዓባይ ቀዝቀዝ ብሎ በዝግታ ያዘግማል።
ወንዙ ከሚያልፍባቸው ከተሞች ሁሉ ሞቃታማ ወደሆነው ካሪማ ከመድረሱ በፊት ደግሞ በአሸዋ ፒራሚዶች በኩል ያልፋል።
በዚህ አካባቢ ያሉ አርሶ አደሮች በሰው ሰራሽም ሆነ በተፈጥሮአዊ ምክንያት የመጣባቸውን ፈተና እንዴት እንደሚቋቋሙ ያውቁ ነበር፤ አሁን ግን አዲስ ፈተና ገጥሟቸዋል።
ምክንያቱም በረሃው አንዳንድ ጊዜ እስከ 150 ሜትር ድረስ የሚጠበውን የሚታረስ መሬታቸውን በአስገራሚ ፍጥነት እያካለለ ነው።
ሰፋፊ ስር ያሏቸው የበረሃ ዛፎችን መትከሉም ሆነ በዘንባባ ቅጠሎች አጥር መስራቱ ከአሁን በኋላ ዋጋ አይኖራቸውም።
ኦስማን አብዱል ሞኣቲ
የስንዴ ማሳውን ለማልበስ የተቃረበውን የአሸዋ ክምር እያሳየ ''የዚህን ቦታ ካርታ የአካባቢ ሚንስትሩ ቢያዩት ምኑንም ሊያውቁት አይችሉም'' በማለት በቀልድ መልክ ስጋቱን የተናገረው ኦስማን አብዱል ሞኣቲ ነው።
ይህን መሰል ክስተቶች በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ በአባይ ሸለቆ የታችኛውም ሆነ የላይኛው ክፍል በየቦታው እየተፈጠሩ ናቸው።
የተባበሩት መንግስታት የአካባቢ ፕሮግራም እንደገለጸው በረሃው ባለፉት 30 ዓመታት ወደ ደቡባዊ ካርቱም 120 ኪሎሜትር ተስፋፍቷል።
ሙቀቱም ቢሆን ከፍተኛ ደረጃ ላይ በመድረስ የወንዙን ትነት እያፋጠነው ነው።
በሰሜናዊ ሱዳን ደግሞ በብዙ ቦታዎች በረሃማነትን ለመከላከል የእነርሱ ጉልበት ቢያስፈልግም ወጣት አርሶአደሮች ፊታቸውን ወደ ሌላ መስክ አዙረዋል።
በአቅራቢያቸው በወርቅ ማዕድን ፍለጋ ላይ በተሰማሩ ባለጸጎች ቃል እየተሳቡ ወደዚያው ይሄዳሉ።የሱዳን አርሶ አደሮች ሥራቸውን በመቀየር ላይ ይገኛሉ
አንዳንድ የመሬት ባለቤቶች ደግሞ ከኢትዮጵያ፣ ከኤርትራና ከሱዳን ዳርፉር መጥተው ለጉዟቸው ተጨማሪ ገንዘብ መቋጠር የሚፈልጉ ስደተኞችን በእርሻቸው ላይ ያሰራሉ።
ሌሎች ደግሞ የእርሻ መሣሪያዎቻቸውን እየጣሉ ወደ ከተሞች ይሰደዳሉ።
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1504
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 7 guests