ወያኔ በስብሶ እየፈራረሰ ለመሆኑ በራሱ ልሳን አመነ

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ወያኔ በስብሶ እየፈራረሰ ለመሆኑ በራሱ ልሳን አመነ

Postby እሰፋ ማሩ » Wed Oct 25, 2017 4:06 pm

'ኢህአዲግም ልክ እንደ ቅንጅት በውስጡ በሰበሰባቸው እንቦጭ መሪዎቹ ለመፍረስ በጉዞ ላይ ያለ ድርጅት ነው'
አይጋ ፎረም 10-24-17-Muluuraya@gmail.com
በሀገራችን ላለፉት 26 አመታት በተለይም ደግሞ ከ1997 ዓ.ም ጀምሮ የፌደራል ስርአቱን የሚፈታተኑ ሂደቶች
አጋጥሟል፡፡ የደርግ ስርአት ከተወገደ ከ1983 ዓም ማግስት ጀምሮ የሀገሪቱን ሁኔታ የሚፈታተኑ በርካታ እክሎች
ያጋጠሙ ሲሆን በገዥው ፓርቲ /ኢህአዴግ/ ጥንካሬ እና የውስጥ አንድነት ምክንያት ሁሉም ችግሮች
እንዳመጣጣቸው በመመከት የሀገሪቱን ህልውና እና ሰላም እንዲሁም እድገት ማረጋገጥ ችሏል ፡፡ ሆኖም ግን
ኢህአዴግ ከ1977ዓ.ም ምርጫ ማግስት ወዲህ ኢህአዴግ ከፍተኛ ፈተና ውስጥ እንደገባ ይታወቃል፡፡ በ1997
ዓ.ም ሳይቀናጁ ቅንጅት ብለው የሰየሙ ፓለቲከኞች የተሰባሰቡበት ድረጅት (ቅንጅት) የምርጫ ቅስቀሳ ዋነኛ አጀንዳ
በማድረግ የጀመሩት የትግራይ የበላነይት በከፍተኛ ሁኔታ ተጠናክሮ የቀጠለው የአንድ ብሄር የበላይነት አለ አጀንዳ
እንደሽፋን በመጠቀም ሀገረቱን ከፍተኛ አደጋ ላይ እንድትገኝ አድርጓታል፡፡ በ1997 ዓ.ም በቅንጅት ስም
የተሰባበሰበው የፓለቲከኞች ስብስብ በጣም በሳል ለሀገር እድገትና ብልፅግና የሚተጉ አብዮታውያን የነበሩበትን ያህል
በሌላ በኩል ደግሞ በጣም ኋላቀር የፊውዳሎች ስብስብስም ስለነበር ልክ በአንደ የገበያ ቀን ተገዝቶ በቅርጫት
ውስጥ እንደተቀመጠ ጤነኛ እና የተበላሸ ቲማቲም የሚመሰል ነበር ፡፡ ቅንጅት በአንድ ቅርጫት ውስጥ
እንደተቀመጠ የተበላሸ እና ያልተበላሸ ቲማቲም የነበረ ድርጅት በመሆኑም የተበላሸው (ፊውዳሉ) ሀይል የበላይነት
ስለነበረው ያልተበላሸውን ጭምር እንዲበላሽ እና ቅንጅትም እንደ ድርጅት ተደፍቶ እንዲቀር አድርጓል፡፡ የኢትዮጵያ
ህዝብም ሰንቆት የነበረው የዴሞክራሲ ግንባታና የመድበለ ፓርቲ አማራጭ በአጭሩ ተቀጨበት፡፡
እንግዲህ ቅንጅት ባለመቀናጀቱ እና በውስጡ የተሰባሰቡ ሀይሎች የመጡበት የፖለቲካ አለመጣጣም (ፊውዳል እና
ተራማጅ) እንዲሁም በየተራ ሳይሆን ሁሉም በአንድ ጊዜ ወደ አንድ ወንበር ላይ ለመቀመጥ በመፈለጋቸው
በፉክክር እና በእልህ ድርጅታቸውን አፍርሰው እነሱም ተበታትኗል፡፡ ሆኖም ግን ቅንጅቶች ቢበታተኑም ዘርቷት
የሄዱት የአንድ ብሄር የበላይነትና ወደመጡበት እናባርራለን (ንብረት ወደ ቀበሌ ትግሬ ወደ መቀሌ) ሌላው በስፋት
እና ጎርናና ድምፅ ሲያቀነቅኗት የነበረችውን የኢህአዴግ አባላት የህወሀት ተላላኪዎች ናቸው የምትል የፌዴራል
ስርዓቱን ለማፍረስ እንደማደንዘዣ ይጠቀሙባት የነበረችውን ንግግር አሁን በከፍተኛ ሁኔታ ወደ ትግራይ ህዝብ
የበላነይት አለ ወደሚል መፎክር አድጎ ወደ ኢህአዴግ ድርጅቶችም ዘልቆ በመግባት ኢህአዴግ ለመሰረታት የብሄር
እና ብሄረሰብ አገር አጥርና መከታ ሁኖ እየጠበቃት ያለው የመከላከያ ሰራዊት ሳይቀር ኢላማ እንዲሆን ከፍተኛ
ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡ መንግስት የበላይ የበታች የሚባል የለም በአሁኑ ሰኣት በከፍተኛ ሁኔታ የመመጣጠኑ ስራ
ተሰርቷል የሚል ምላሽ ቢሰጥም ለሀገር ሳይሆን ለሆዳቸው ያደሩ ካድሬዎች የሀገርን ከፍጠኛ ሚስጥር የሆነውን
የመከላከያ አወቃቀር እና የሰው ሀይል ስብጥር ሳይቀር ይትኛው ብሄር ምን ያህል ወታደር ፤ጄኔራል፤ ኮነሬል፤ ወዘተ
እንደላው ካልተነገርን በሚል ሰበብ የሀገርን ሚስጥር በዜዴ እያስወጡ ለጠላት ሲያቀብሉ ሲያቀብሉ የቆዩ ሲሆንአሁንም በማቀበል ላይ ይገኛሉ፡፡
ሁሉም እንደሚያውቀው መከላከያ ሀይሉ የኢህአዴግ አባል ድርጅት የበታች ሹመኞች ሳይቀሩ በቪ 8መኪና ሲንፈላሰሱ ሰራዊቱ እያየ ዝም እንጂ ፤እኛ እኮ የታገልነው ህዝቡ እንዲያልፍለት እንጂ ግለሰቦዎች በሀገርሀብት እንዲጫወቱብ አይደለም ብሎ እንኳ እንዳይጠይቅ መከላከያ በህዝብ አስተዳደር ውስጥ አያገባውም ብለው
በህገመንግስቱ ስላሰፈሩ እና መከላከያ ሀይሉም ለሀገር የሚጠቅመን መንገድ ነው ብሎ በማመን ድንበሩን ብቻአየጠበቀ ይገኛል፡፡በመሆኑም የሀገራችን የመከላከያ ሀይል በጀግንነት እና በጥልቅ የሀገር ፍቅር ስሜት የሀገሩን ዳር ድንበር ማስከበር በመቻሉ እና ሁሉም የውጭ እና የውስጥ ሀይሎች መግብያ ቀዳዳ በማሳጣቱ ሊከበር፤ ሊሞገስ፤ ሊሸልም ሲገባው
የትግራይ የበላይነት አለ ብሎ ስሙን ማቆሸሽ ለምን??? የሀገር ዳር ድንበር አስደፍሮ ቢሆን እንደ ምንክንያትማቅረብ ተገቢ ነው ታድያ ለምን ጀግና ሆነ? ለምን በሄደበት የድል ሰራዊት ሆነ ብሎ መጠየቅስ ምን ይሉታል??ወይስ የጠላት ፍላጎት ስላከሸፈ እና አንዳንዶቹ በአቋራጭ በመፈንቅለ መንግስት ስልጣን ለመያዝ ስለሚያስቡ አሁንያለው የመከላከያ አወቃቀርና የሰው ሀይል ስብጥር እያለ እንደማይታሰብ ስለተረዱ ??? ለማንኛውም መልሱ ለእነሱእንተውውና ወደ ተነሳሁበት የኢህአዴግ ሁኔታ ልመልሳችሁ፡፡አሁን ያለው የኢህአዴግ ሁኔታ ልክ እንደፈረሰው ቅንጅት ኢህአዴግም በውስጡ ልክ አንድ ቅርጫት ውስጥእንደተቀመጠ በሽተኛና ጤነኛ ቲማቲም የተለያዩ ስብእና፤ አለማ እና ፍላጎት ያላቸው ሀይሎች ስብስብ የሆነይመስላል፡፡ ልክ የጣናን ሀይቅ የወረረው እንቦጭ ኢህአዴግም ምንም እንኳ በጥልቅ ታድሰናል እያለ ቢያወራም በውስጡ ባሉ እንቦጭ መሪዎች (ቢወቅጡትም እንቦጭ እንሚባለው) ቢታደሱም ያው በሆኑ ባለስልጣናት የተሞላየሆነ ይመስላል፡፡ ይህ የኢህአዴግ ወቅታዊ ሁኔታ ደግሞ ለራሱ ለኢህአዴግ ብቻ ሳይሆን ለሀገርም አደገኛ ነው፡፡የኢህአዴግ ድርጅቶች ግንኙነት የአላማ ብቻ ሳይሆን በደም የተሳሰረ ነው እያሉ ቢቦተልኩም ሀቁ ከዚህ አባባልያፈነገጠ ነው፡፡ እርግጥ ነው እስከአሁን በነበረው መርህ የሚመሩ እንዳሉ ምንም ጥርጥር የለውም ሀገራችንእስከአሁን በሰላም የቆየችውም የነዚህ ሰዎች መኖር ነው፡፡ ነገር ግን አሁን እነሱ እየተበለጡ በእንቦጭ መሪዎችየበላይነት እየተያዘባቸው፡፡ እንቦጭ የሆኑ መሪዎች ደግሞ ሰላም ሲደፈርስ የበለጠ ተጠቃሚ የሚያደርጋቸውእየመሰላቸው ሰላም እንዳይኖር በቁርጠኝነት እየሰሩ ይገኛሉ ፡፡ በእርግጥ አንዳንዶቹ ለሰላም እና መረጋጋት፤ለኮንፈረንስ፤ እየተባለ የሚያወጡት ሀብትም ቀላል አይደለም፡፡ባለፈው አመት በሀገራችን የተከሰተው ችግር በቀላሉ የሚታይ አይደለም፡፡ ሀገሪቱ ተሰነጣጥቃ ልትሰባበር ስትል ነውእንደገና ያገገመችው፡፡ በርካታ ዋጋ ተከፍሎ፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጆ፤ የምን ጊዜም ለሀገሩ ታማኝ የሆነውመከላከያ ሀይሉ አንዣብቦ የነበረው እጅግ ከባድ እና አስፈሪ ግርዶሽ በአጭር ጌዜ ጥበብ በተሞላበት ሁኔታአምክኖታል፡፡ሆኖም አሁንም ቢሆን በዚህ ወቅት በኢህአዴግ ውስጥ ያሉ እና ከኢህአዴግ ውጭ ያሉ የፓለቲካ መሪዎች ስራቸውንበአግባቡ ባለመስራታቸው በተለያዩ ቦታዎች ከፍተኛ ችግር ተከስቷል፡፡ኢትዮጵያ ሶማሌ እና በኦሮሚያ የተከሰተው ችግር ሊከሰት የሚገባው አልነበርም፡፡ በእርግጥ አርብቶ አደሮችአከባቢዎች በሳር ግጦሽ፤ በውሀ፤ እና በተለያዩ ጥቅቅን ምክንያቶች መጋጨት የነበረ፤ ያለ እና ሊኖር የሚችልነው፡፡ ነገር ግን አሁን በተከሰትው አይነትና ልክ ግን በጣም ኃላቀር እና ደካማ የሆኑ መንግስታት ባሉባቸውእንደ ደቡብ ሱዳን፤ ኮንጎ እና የመሳሰሉት ባሉበት እንጂ ኢትዮጵያ ውስጥ መከሰት አልነበረብም፡፡ ወሰን አከባቢግጭት ተፈጠረ ተብሎ በግጭቱ ያልዋለውን እና ያልነበረውን ንፁህ ሰው ማረድ እውነት ለመናግር ከየትኛውምወንጀል የበላይ ነው ብየ አምናለሁኝ፡፡ የጎሳየ አባል ያንተ ጎሳ አርዶብኛል ብሎ ደግሞ ንፁሁን ሰው በሰላምአግብቶ፤ ንብረት አፍርቶ ከሚኖርበት ቦታ ያለምንም ጥያቄ አሳድዶ ማባረርም ያረዱትን ያህል ከብደት ይነረዋል ብየ ባላምንም ወንጀል ነው፡፡ይህ ሁሉ እየሆነ ያለው የፌደራሉ መንግስት በቅንጅት ሰዎች የተወጋውን የህወሀት የበላይነት የምትባለው የማደንዘዣመድሀኒት የማደንዘዣው መድሀኒት ዶዝ በመጨመር የትግራይ የበላይነት ወደሚል አድጎ የበለጠ እንዲደነዝዝ እናበየቦታው እንቦጭ የሆኑ ለሆዳችው ያደደሩ እና የሚደክሙ ሆደሰፊዎች ስለወረሩት ነው፡፡እነዚህ ሆደሰፊ እንቦጭ መሪዎች ለህግና ስርአት መከበር ያለመታከት ሊሰሩ እና የህዝቡን ሰላም ማስከበር ሲገባቸውቅንጅቶች የለኮሱት የትግራይን ህዝብ የማንበርክከ ስልት በማስቀጠል ይገኛሉ፡፡እኔ እስከማቀው ድረስ የድሮው ኢህአዴግ የሀገሪቱ እድገት ተመጣጣኝ እንዲሆን በመተጋገዝ የሚያምን፤ በመርህየሚገዛ ነበር፡፡ ትግራይ አፋርን እያገዘ እንዲሄድ፤አማራ ቤንሻንጉልን እንዲያግዝ፤ ኦሮሚያ ሶማሌ ክልልን እንዲያግዝ፤ደቡብ ክልል ጋምቤላን እንዲያግዝ ወዘተ እና በሀገር ደረጃ የሚደረገው የልማት ጉዞ እጅ ለእጅ ተያይዘው ለማደግነበር ፡፡ በዚህ መርህ መሰረትም በተነፃፃሪ የተሸለ የሰው ሀይል ያላቸው ክልሎች እገዛ አድርገው የሚታይናየሚጨበጥ ለውጥ እንደመጣ ማንም የሚክደው ነገር አይደለም፡፡ሆኖም ግን በተለያዩ አከባቢዎች የሚከሰቱ ችግሮች የተለያዩ መነሻ ቢኖራቸውም ሁሉም ነገር ድሮ ድሮ ህወሀትአሁን ደግሞ የትግራይ ህዝብ እንደሆነ በማስመሰል ጠላትም ወዳጅም በማለይ ሁኔታ ወደ ትግራይ ህዝብ ይቀስራል፡፡በየክልሉ እና በፌደራል መንግስት ያሉ እንቦጭ መሪዎችም አሁን ላሉበት ደረጃ ሂወቱን ሳይሳሳ እዚህ ላደረሳቸውየትግራይ ህዝብ ጨከኑበት፤ እናም በየብሄራዊ ድርጅቶቻቸው ዋነኛ የመወያያ አጀንዳ ሆነ፤ዳግም ትግሬ ገዳይ ተባለ፡፡ይባስ ብሎ ባለፈው አመት ጎንደር ላይ የትግራይ ተወላጆችን የመግደል፤የማሳደድ ተግባራት እየተፎከረ፤ጃሎበልእየተባለ እንኳን ሊደረግ ሊታሰብ የማይችለውን ተግባር ተፈፀመ፡፡በጣም የሚገርመው ደግሞ አንዳንዶቹ የኢህአዴግ አባል ድርጅት መሪዎች በዚህ ሂደት በደስታ ብዛት በወቅቱየወለዱትን ልጃቸው ምንሊክ ብለው መጥሪያ አወጡና እወቁልኝ አሉ (ምናልባት ጃሎ በል ብሎ የፎከረው ሰውከፊሉ ተሳስቶ፤ ከፊሉ ኢሳቶች ለሚልኩለት ዶላር ተታልሎ ፤ ግመሹ ግን የምንሊክ ዘመን የሚመለስ መስሎት ሊሆንይችላል) የምኒሊክ አባት አላማ ግን አልገባኝም ምክንያቱም ሰውየው ምንሊክን ወይም ስማቸውን በጣም የሚወዷቸው ቢሆን የመጀመሪያ ልጃቸውን ነበር ምኒሊክ ማለት የነበረባቸው ፡፡ ምንሊክ ብለው እየጠሩልን ያለውልጅ አራተኛ ልጃቸውን እና በጃሎ በል ዘምን የተወለደውን ነው፡፡ በዚህ አላበቁም ልክ በአመቱ የልጄ ምንሊክ የአንድ አመት ልደት በአል እንኳን አደረሰህ በሉልኝ ብለው በፌስቡክ ሳይቀር ጠየቁን፡፡እንግዲህ ይህ በፌስቡክ እወቁልኝ ምንሊክ አንድ አመት ሞላው መልእክት ያሉን የዛሬ ወር አከባቢ ነው፡፡ይታያቹህ በዚህ ወቅት ድርጅታቸው ጥልቅ ተሀድሶ አደረግኩኝ ብሎ በተሀድሶ መንፈስ ስራ እየሰራሁኝ ነው በሚልበትወቅት ነው፡፡ እናም የአንድ ትልቅ ክልል አመራር ስንት እስትራተጂክ አመራር መስጠት የሚጠበቅበት መሪ፤እንዲህ አይነቱ መሪ ይታደሳል ተብሎ እጅግ በርካታ ብር አበል መልክ ወጭ የተደረገበት አመራር እዛው በነበረበትሁኖ ሲገኝ ምን ይባላል፡፡እንግዲህ ይህ አንድ ምሳሌ አነሳሁኝ እንጂ የአብዛኛው የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች እንቦጭ መሪዎች ባህሪ ነው(ቢታደሱም ባይታደሱም ያው ናቸው) የህዝቡን ገንዘብ ከማባከን ውጭ ውሀ ቢዎቅጡት እንቦጭ ነው እንደሚባለውነው፡፡በሌላ በኩል ግን ይህ ሁሉ ፉከራና ሽለላ ትክክል አይደለም ብለው የተጋፈጡ በጣም ጥቂቶች ግን ደግሞ ቆራጦች(ብአዴኖች እንደሚሉት ጥቂቶች ቆራጦች ያልተንበረክን ነገ እልፍ እንሆናለን ታሪክ ምስክር ነውያሉት በፅናትየአዳራሽ አንበሳውን ተፋለሙት እረ ተው ትክክል አይደለም የሚል ታጋይ ሲገኝ ሰላይ፤ ባንዳ፤ እየተባለእንዲሸማቀቅ ተደረገ፤) ፡፡ያም ሁሉ ታለፈ እና ጥልቅ ተሀድሶ ተብሎ ተገባ ታደሰን በተባለ ማግስት በኦረሚያ፤ በኢትዮ- ሶማሊ፤ በደቡብና በኦሮሚያ የተወሰኑ አከባቢዎች ግጭት ተፈጠረ በእርግጥ በጎንደር ተከስቶ የነበረው ግጭት አሁን የለም በህዝቡ ሰላም ፈላጊነት ተጠንስሶ የነበረው የትግራውያን ምንጠራ ተግባር የተወሰነ ጥፋት ከደረሰ በኃላ ቆሟል ፡፡
ነገርግን እጅግ በርካታ ሂወት እና በርካታ ንብረት ጠፍቷል ስለሆነም ለዘላቂ ሰላም ሲባል ጥፋጠኞች ልክ ጉራፈርዳ
በ2007 ዓም ጥፋት የፈፀሙትን ቃሊቲ ገብተው ሂሳባቸውን እያወራረዱ እናዳሉት የጉራፈርዳ ወረዳ አመራሮች
በጎንደርም መካሄድ አለበት፡፡ ጉራፈርዳ በአሁኑ ጊዜ ከ70% በላይ ከሰሜን የሄደ ህዝብ ይዛ ሳላምዋን ስጠብቃ
ከፎገራ ወረዳ ቀጥላ ምርጥ ሩዝ በማምረት ላ ትገናለች፡፡ ይህ የሆነው በአጥፊዎች እርምጃ ስለተወሰደ እንጂ
ስለተሸነገሉ አይደልም ስለሆንም በጎንደርም ሆነ በኦረሚያ እንደሁም በሶማሊ ክልል አጥፊዎችን ለሀጋራችን ዘላቂ
ሰላም ሲባል መቀጣት አለባቸው፡፡
ኢህአዴግ ቅንጅቶች የወጉት የህወሀት የበላይነት አለ የምትል የማደንዘዣ መድሀኒት ዶዙ ጨምሮ እንደ ህዝብ
እየተሳለ ያለው ሳንጃ ውሽት ነው ትግራይን ብቻ አይበላም ሊበላም አይችልም ምክንያቱም ኢትዮጵያዊ በሙሉ
ተበትኖ የሚኖርባት አገር ይዘን እንዱን ማባር አይቻለም ኢዚህ አንዱ ሲያባር ሌላኛው ደግሞ ሌላውን ማባረሩ
አይቀርም፡፡ ኢትዮ-ሶማሊ እና ኦረሚያ ማይት ይቻላል፤ ጌድኦ ዞን የተከናወነው ማስታወስ ጥሩ ነው፤ ስለሆነም
ለዚህ ሁሉ ችግር ክፍተት እየፈጠረ ያለው ደግሞ የኢህአዴግ አመራር በእንቦጨ መሪዎች መሞላቱ ነው፡፡ ቅንጅት
ቢጠፋ ለሀገራ ያደረሰው ጉዳት ቀላል ነው ባይባልም ሀገርን ግን አላፈረሰም፡፡ ኢህአዴግ ውስጥ የተሸሸጉት የሀገሪቱን
ሀብት ከማባከን ውጭ ለውጥ የማያመጡትን እንቦጭ መሪዎቹን ግን ያለርህራሄ ማስወገድ ይኖርበታል፡፡
-------------------------------------------------------------------------------------------------------
ማሳሰቢያ-እንቦጭ መሪዎች የሚሉዋቸው ቀና ቀና ማለት የጀመሩት እነገዱ እነ መገርሳ ወዘተ ሲበሉዋቸው ወይም እንደቀደመው ባንዳ ታምራት ላይኔ ስኩዋር በልቼ እያሉ ሲያስለፈልፉዋቸው እንሰማለን፡፡
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1548
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm

Re: ወያኔ በስብሶ እየፈራረሰ ለመሆኑ በራሱ ልሳን አመነ

Postby ዘርዐይ ደረስ » Wed Oct 25, 2017 9:37 pm

እሰፋ ማሩ፡-
የአይጋ ፎረም መልዕክት በደንብ የገባህ አልመሰለኝም፡፡
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1096
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: ወያኔ በስብሶ እየፈራረሰ ለመሆኑ በራሱ ልሳን አመነ

Postby እሰፋ ማሩ » Thu Oct 26, 2017 1:17 am

ዘርዐይ ደረስ
የአይጋ ፎረም ሃሳብ ገብቶኛል፡፡ሰሞኑን በብአዴን ውስጥ የተነሳው የወያኔ የበላይነትን የሚቃወመው ትግል ከቅንጅት የተወረሰ ነው በማለት ሊያስሩ የፈለጉትን ለመያዝ ቅድመዝግጅት ፕሮፓጋንዳ ነው፡፡ ዋናው ምልከታ ወያኔ ከመጀመሪያ በበሰበሰ የጎሳ መርህ ስልጣን ይዞ ህዝቡን የከፋፈለ መፈረካከሱን ራሱ ማመኑ ላይ ነው፡፡ፕሮፓጋንዳው በብአዴን ብቻ ሳይወሰን ወደኦህዲድና ሌሎቹ ተለጣፊዎችም ያመራል፡፡

ዘርዐይ ደረስ wrote:እሰፋ ማሩ፡-
የአይጋ ፎረም መልዕክት በደንብ የገባህ አልመሰለኝም፡፡
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1548
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests