በወያኔ የሚገፋው ቴዲ አፍሮ ትግሬውን ከሞት አዳነ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

በወያኔ የሚገፋው ቴዲ አፍሮ ትግሬውን ከሞት አዳነ

Postby እሰፋ ማሩ » Mon Aug 28, 2017 5:47 pm

ይልቅስ ደስ የሚል ሁለት ነገር ልንገራችሁ !
August 28, 2017 – ቆንጅት ስጦታው
ቴዲ አፍሮ ላይ እየደረሰበት ያለው መንግሥታዊ ጫና ቀላል የሚባል አይደለም ፤ ሆኖም ግን እሱ እራሱ እንዲሁም የድምፃዊ ፕሮሞቶሮች እና አማካሪዎች በሚያደርጉት ከፍተኛ ጥራት ብዙ አስቸጋሪ ነገሮችን ተቋቋሞ ለማለፍ ጥረት እያደረገ እንደሆነ የሚታወቅ ነው። በተለይ የአድናቂዎቹ ድጋፍ እና እገዛም ቀላል የሚባል አይደለም። እነ ‘እንቶኔ’ የዓይነ ደረቅ ሥራቸው መልሶ ካላገረሸባቸው በስተቀር የብላቴናው ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሣሁን ቴዲ አፍሮ የሙዚቃ አልበም ምርቃት ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ እሁን ሊሆን እንደሆነ ለድምፃዊ ቅርበት ያላቸው የመረጃ ምንጮች እያመላከቱ ይገኛሉ። እሁድ ነሀሴ 28/2009 ዓ.ም ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ በሂልተን ሆቴል “ኢትዮጵያ” አልበም በደማቅ ሥነ ሥርዓት ይመረቃል። በእለቱ በዋነኛነት የተያዘው ፕሮግራም
☞ ቴዲ አፍሮ ከአቡጊዳ ባንድ ጋር በመሆን ከአዲሱ አልበሙ ዘፈኖችን የተወሰነውን ይጫወታል ፤
☞ የፍቅር እስከ መቃብር (ማር እስከ ጡዋፍ) ቪዲዮ ይመረቃል ፤
☞ ስለቴዲ አፍሮ የሙዚቃ ህይወት ከ20 ደቂቃ ያልበለጠ ፊልም ይቀርባል !!! ቀደም ብሎ ነሐሴ 21 ቀን 2009 ዓ.ም ተይዞ የነበረው የአልበም ምረቃ ፕሮግራም እንዲሰረዝ መደረጉ፣ እንዲሁም ለአዲስ አመት በሚሊኒየም አዳራሽ ሊካሄድ የነበረው የሙዚቃ ኮንሰርት በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር የህዝባዊ ስብሰባና ሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቂያ ክፍል ቀድሞ የተያዘ ፕሮግራም አለ በሚል ምክንያት ኮንሰርቱ እንዳይካሄድ ክልከላ ማድርጉ የሚታወስ ነው።

ሁለተኛ ! የዛሬ አምስት አመት በፑንትላንድ አደጋ ሊያደርሱበት በሞከሩ ሶማሊያውያን ላይ በወሰደው የመከላከል ዕርምጃ አንድ ሰው በመግደል ሌላኛው በመቁሰሉ በሞት እንዲቀጣ ወይም ገንዘብ እንዲከፍል ተወስኖበት የነበረው ኢትዮጵያዊ አስመሮም ኃይለ ሥላሴ ሊገደል 20 ደቂቃ ሲቀረው ቴዲ አፍሮ 700,000 ብር ከፍሎ የሞት ቅጣቱን አስቀርቶለት እንደነበር የሚታወሰ ነው። የመቀሌ ነዋሪ የሆነው አስመሮም ቴዲን የዛሬ አምስት አመት ከሞት ተርፌ ስመጣ በስልክ ነው ያገኘሁት፣ በግዜውም ሳመሰግነው “እኔን አታመስግን ይህን ያደረገው እግዚያብሄር ነው” ብሎኛል ። እኔ ግን በአካል አግኝቼ ማመስገን እፈልጋለሁ ። አምስት አመት ሙሉ ቴዲ አፍሮ ይገኛል የተባልኩበት ቦታ ሁሉ ብሄድ ላገኘው አልቻልኩም፣ ከእግዚአብሔር ቀጥሎ ሕይወቴን ያተረፈውን ቴዲ አፍሮን በአካል አግኝቼ ማመስገን እፈልጋለሁ ” እባካችሁ የምትችሉ አገናኙኝ ” በማለት ለኢትዮፒካሊንክ ተናግሯል ። ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ ከጥበብ ሥራው ባሻገር እሱ እንዲነገርልት ባይፈልግም ለወጎኖቹ በበጎ ሥራ አድራጎት ሁሌም እንደሚተጋ ለብላቴናው እጅግ በጣም ቅርበት ያላቸው ሰዎች ይናገራሉ። የእኔ የቅርብ ወዳጅ የሆነ የዓይን እማኝ ሆኖ የነገረኝ እሱ የህክምና ክትትል በሚያደርግበት ሆስፒታል ቴዲ አፍሮ አዲሱን “ኢትዮጵያ” አልበም ለሕዝብ ካቀረበ ከወራት በኋላ ፤ ህሙማንን እየተዟዟረ በመጎብኘት ምግብ በመመገብ እግዜር ይማራችሁ ይል እንደነበረ ፣ይሄን ሲያደርግ በትህትና እና በአክብሮት እሱነቱ እንዳይታወቅ ጥረተ እያደረገ አጀብ ሳያበዛ እንደነበረ ጭምር ወዳጄ ነገርኛል። ለድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሣሁን (ቴዲ አፍሮ) ፈጣሪ እረጅም እድሜና ጤና የስጠልን ፣አሜን !!!

(ይድነቃቸው ከበደ)
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1526
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm

Re: በወያኔ የሚገፋው ቴዲ አፍሮ ትግሬውን ከሞት አዳነ

Postby ጌታህ » Mon Aug 28, 2017 11:03 pm

ቅቅቅቅቅቅቅቅ.....አሰፋ ማሩ የዶንኪው ጏደኛ በጎ ሰራውን ማሳወቅ ያልፈለገ ሰው አንተና ቆንጂት ሰጦታው ይህ ደግሞ ይድነቃቸው የምትለው ባደባባይ መዘረገፉ ለምን አሰፈለገ...እናንተን ነበር ፍርድ ቤት ወስዶ ማሰቀጣት... እሱ በራሱና በፈጣሪው ብቻ እንዲሆን የፈለገውን ተግባር ማን አውጥታችሁ ዝርዝሩን ተርኩ ያላችሁ...ለመሆኑ ሂወቱን ያዳንከውን ሰው ለመገናኘት የሚከልክልህ ምን ይሆን...ከመሬት ተነሰትህ ነፍሱን ያዳንከው ሰው ቀረብ ብለህ ማነጋገርና መተዋወቅ ምን ይከለክለሃል...እናንተሰ ሰንት ተክፍሏችሁ ነው እሱነቱን ሳይታወቅ በጎ ሥራ ሰርቷል ብላችሁ የምታሰታውቁት...ሚሊኑም አዳራሸ እንዳይዘፍን በሆነ ባልሆነ ምክኒያት ተከለከለ ከምትሉ የራሱን አዳራሸ ለምን አይሰራም... ሚሊኒይም አዳራሸ መያዙና ነጻ መሆኑን ሳታረጋግጡ ነው እንዴ ሄዳችሁ መዘፈን የምትመኙት...ከተያዘሰ ሌላ ቀን መከራየት አይቻልም ወይሰ ጉራና የበለጠ ዘናን ለማግኘት እየጣራችሁ ነው !!!!

ጌታህ ከፒያሳ (አራዳ)

እሰፋ ማሩ wrote:ይልቅስ ደስ የሚል ሁለት ነገር ልንገራችሁ !
August 28, 2017 – ቆንጅት ስጦታው
ቴዲ አፍሮ ላይ እየደረሰበት ያለው መንግሥታዊ ጫና ቀላል የሚባል አይደለም ፤ ሆኖም ግን እሱ እራሱ እንዲሁም የድምፃዊ ፕሮሞቶሮች እና አማካሪዎች በሚያደርጉት ከፍተኛ ጥራት ብዙ አስቸጋሪ ነገሮችን ተቋቋሞ ለማለፍ ጥረት እያደረገ እንደሆነ የሚታወቅ ነው። በተለይ የአድናቂዎቹ ድጋፍ እና እገዛም ቀላል የሚባል አይደለም። እነ ‘እንቶኔ’ የዓይነ ደረቅ ሥራቸው መልሶ ካላገረሸባቸው በስተቀር የብላቴናው ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሣሁን ቴዲ አፍሮ የሙዚቃ አልበም ምርቃት ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ እሁን ሊሆን እንደሆነ ለድምፃዊ ቅርበት ያላቸው የመረጃ ምንጮች እያመላከቱ ይገኛሉ። እሁድ ነሀሴ 28/2009 ዓ.ም ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ በሂልተን ሆቴል “ኢትዮጵያ” አልበም በደማቅ ሥነ ሥርዓት ይመረቃል። በእለቱ በዋነኛነት የተያዘው ፕሮግራም
☞ ቴዲ አፍሮ ከአቡጊዳ ባንድ ጋር በመሆን ከአዲሱ አልበሙ ዘፈኖችን የተወሰነውን ይጫወታል ፤
☞ የፍቅር እስከ መቃብር (ማር እስከ ጡዋፍ) ቪዲዮ ይመረቃል ፤
☞ ስለቴዲ አፍሮ የሙዚቃ ህይወት ከ20 ደቂቃ ያልበለጠ ፊልም ይቀርባል !!! ቀደም ብሎ ነሐሴ 21 ቀን 2009 ዓ.ም ተይዞ የነበረው የአልበም ምረቃ ፕሮግራም እንዲሰረዝ መደረጉ፣ እንዲሁም ለአዲስ አመት በሚሊኒየም አዳራሽ ሊካሄድ የነበረው የሙዚቃ ኮንሰርት በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር የህዝባዊ ስብሰባና ሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቂያ ክፍል ቀድሞ የተያዘ ፕሮግራም አለ በሚል ምክንያት ኮንሰርቱ እንዳይካሄድ ክልከላ ማድርጉ የሚታወስ ነው።

ሁለተኛ ! የዛሬ አምስት አመት በፑንትላንድ አደጋ ሊያደርሱበት በሞከሩ ሶማሊያውያን ላይ በወሰደው የመከላከል ዕርምጃ አንድ ሰው በመግደል ሌላኛው በመቁሰሉ በሞት እንዲቀጣ ወይም ገንዘብ እንዲከፍል ተወስኖበት የነበረው ኢትዮጵያዊ አስመሮም ኃይለ ሥላሴ ሊገደል 20 ደቂቃ ሲቀረው ቴዲ አፍሮ 700,000 ብር ከፍሎ የሞት ቅጣቱን አስቀርቶለት እንደነበር የሚታወሰ ነው። የመቀሌ ነዋሪ የሆነው አስመሮም ቴዲን የዛሬ አምስት አመት ከሞት ተርፌ ስመጣ በስልክ ነው ያገኘሁት፣ በግዜውም ሳመሰግነው “እኔን አታመስግን ይህን ያደረገው እግዚያብሄር ነው” ብሎኛል ። እኔ ግን በአካል አግኝቼ ማመስገን እፈልጋለሁ ። አምስት አመት ሙሉ ቴዲ አፍሮ ይገኛል የተባልኩበት ቦታ ሁሉ ብሄድ ላገኘው አልቻልኩም፣ ከእግዚአብሔር ቀጥሎ ሕይወቴን ያተረፈውን ቴዲ አፍሮን በአካል አግኝቼ ማመስገን እፈልጋለሁ ” እባካችሁ የምትችሉ አገናኙኝ ” በማለት ለኢትዮፒካሊንክ ተናግሯል ። ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ ከጥበብ ሥራው ባሻገር እሱ እንዲነገርልት ባይፈልግም ለወጎኖቹ በበጎ ሥራ አድራጎት ሁሌም እንደሚተጋ ለብላቴናው እጅግ በጣም ቅርበት ያላቸው ሰዎች ይናገራሉ። የእኔ የቅርብ ወዳጅ የሆነ የዓይን እማኝ ሆኖ የነገረኝ እሱ የህክምና ክትትል በሚያደርግበት ሆስፒታል ቴዲ አፍሮ አዲሱን “ኢትዮጵያ” አልበም ለሕዝብ ካቀረበ ከወራት በኋላ ፤ ህሙማንን እየተዟዟረ በመጎብኘት ምግብ በመመገብ እግዜር ይማራችሁ ይል እንደነበረ ፣ይሄን ሲያደርግ በትህትና እና በአክብሮት እሱነቱ እንዳይታወቅ ጥረተ እያደረገ አጀብ ሳያበዛ እንደነበረ ጭምር ወዳጄ ነገርኛል። ለድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሣሁን (ቴዲ አፍሮ) ፈጣሪ እረጅም እድሜና ጤና የስጠልን ፣አሜን !!!

(ይድነቃቸው ከበደ)
ጌታህ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1209
Joined: Sat May 30, 2009 3:05 pm

Re: በወያኔ የሚገፋው ቴዲ አፍሮ ትግሬውን ከሞት አዳነ

Postby እሰፋ ማሩ » Tue Aug 29, 2017 11:03 pm

የወያኔው ኤምባሲ ሰራተኞች የሞት ፍርዱን ተቀብለው ኑዛዜውን ወደሃገር ቤት ለማስተላለፍ ሞከሩ፡፡በመሃሉ የመቀሌው ጉብል ኑዛዜ የለኝም ብሎ በሰይፍ ሊገደል ከጉድጉዋዱ ጎን ሲዘጋጅ ለኤምባሲው መልሶ በመደወል ጉዳዩ በገንዘብ ቅጣት እንዲቀየር ድርድር ተደርጎ በቴዲ አፍሮ የገንዘብ ዋስትና ከሞት እንደተረፈ የሰጠው አስደናቂ ምስክርነት እነሆ፡-
https://www.youtube.com/watch?v=We8F1u7KxHw
Last edited by እሰፋ ማሩ on Tue Aug 29, 2017 11:08 pm, edited 1 time in total.
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1526
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm

Re: በወያኔ የሚገፋው ቴዲ አፍሮ ትግሬውን ከሞት አዳነ

Postby ጌታህ » Wed Aug 30, 2017 4:08 am

ቅቅቅቅቅቅቅ...አሰፋ ማሩ የዶንኪው ጏደኛ ላንተሰ ሰንት ይሆን የተከፈለህ እንዲህ ያለ ፕሮፓጋንዳ የጀመርከው...በነጻ ነው ብለህ እንዳታሰቀኝ !!!

ጌታህ ከፒያሳ (አራዳ)

እሰፋ ማሩ wrote:የወያኔው ኤምባሲ ሰራተኞች የሞት ፍርዱን ተቀብለው ኑዛዜውን ወደሃገር ቤት ለማስተላለፍ ሞከሩ፡፡በመሃሉ የመቀሌው ጉብል ኑዛዜ የለኝም ብሎ በሰይፍ ሊገደል ከጉድጉዋዱ ጎን ሲዘጋጅ ለኤምባሲው መልሶ በመደወል ጉዳዩ በገንዘብ ቅጣት እንዲቀየር ድርድር ተደርጎ በቴዲ አፍሮ የገንዘብ ዋስትና ከሞት እንደተረፈ የሰጠው አስደናቂ ምስክርነት እነሆ፡-
https://www.youtube.com/watch?v=We8F1u7KxHw
ጌታህ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1209
Joined: Sat May 30, 2009 3:05 pm

Re: በወያኔ የሚገፋው ቴዲ አፍሮ ትግሬውን ከሞት አዳነ

Postby እሰፋ ማሩ » Tue Sep 05, 2017 7:44 pm

ለብቻው ቤተ-መንግስቱን ያንቀጠቀጠ ብላቴና፣ ቴዲ አፍሮ – ክንፉ አሰፋ
September 5, 2017 – Kinfu Assefa
ቴዲ አፍሮ
በነዚያ የነጠቡ ብዕሮች “ተራራውን ያንቀጠቀጠ” እየተባሉ ሲወደሱ የነበሩ ሁሉ እነሆ በአንድ ብላቴና ሲንቀጠቀጡ ከማየት የበለጠ ምስክር ከየትም ሊመጣ አይችልም። የ”ኢትዮጵያ” ስም ሲጠራ ብርክ እንደያዘው የሚሽመደመዱ፤ አንድ፣ ሁለት፣ ሶስት እየልን በጣት የምንቆጥራቸው የጥላቻና የበቀል ጉግማንጉጎች ለመሆናቸውም ትውልድን ደፍሮ ይናገርላቸዋል። የዚህ ቡድን አባላት ከመጠን ያለፉ ጭቃዎች መሆናቸውን እንኳ ለማወቅ ራሳቸውን በመስታወት የሚመለከቱ አይመስልም።

100 ሚሊዮን ሕዝብ እየመራ ያለው ይህ ቡድን በየትኛውም መመዘኛ ቢለካ አርቆ ማሰብ እና አስተዋይነት ይጎድለዋል። አስተዋይነት ደግሞ የታላላቆች ውድ ስጦታ ስለሆነ ከርካሽ ሰዎች አይጠበቅም። አበው ትተውልን ያለፉት አንድ ቅርስ፣ ያቺ የቀስተደመና ተምሳለት፣ ያቺ አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ባንዲራ ስትነሳ አጋንንት እንደለከፈው እርያ የሚክለፈለፉ የዘመናችን ጉዶች…. አንድ ነገር እንዳላቸው አንክድም። የበተ-መንግስቱ ታራ ደርሷቸው የተቀመጡት ትንሾች ያላቸው አንድያ ነገር መሃይምነት ብቻ ነው።ግና ኮንሰርት በመከልከል ቴዲን የጎዱ እየመሰላቸው ይልቅ ተወዳጅነቱን በእጥፍ ጨመሩለት።

አንድ ኢትዮጵያዊ፣ ቴዲ አፍሮ ሲያርበተብታቸው አየን። በጩኸት ሳይሆን በዝምታ፣ በሰይፍ ሳይሆን በዘለሰኛ፣ በጥላቻ ሳይሆን በፍቅር ብቻ የሚሰባብራቸው፣ ሰባብሮም ድል የሚያደርግ ጀግና። እንግዲህ በዚህ አይነት እጅግ በወረደ ተራ ነገር ይህን ድምጻዊ በገንዘብ ሊጎዱት ይችሉ ይሆናል። የህይወት ስንቅ የሆነው ፍቅር ግን ወዲህ ነው። የማይለወጥ የሚሊዮኖችን ፍቅር። እነ ደብረጽዮን አቅሙ ኖሯቸው ይህንን ቢነፍጉት ኖሮ ቴዲ ሊጎዳ ይችል ነበር። አንድ በቀነሱበት ቁጥር፣ በመቶ እጥፍ እንደሚጨመርበት ግን መቼም ሊያስተውሉት አይችሉም።

አያሌ እንቅፋቶችን አልፎ ዛሬ ምሽት ላይ በሂልተን ሆቴል ሊደረግ የነበረው የ”ኢትዮጵያ” አልበም ምረቃ ባይስተጓጎል ነበር የሚገርመን። ምክንያቱም አልበሙ “ኢትዮጵያ”፣ መልእክቱም ፍቅር እና አንድነት ነዋ! ይህ ደግሞ ኢትዮጵያን ሳይወድዷት ለሚገዙዋት ራስ ምታት ነው። ባንዲራዋን የሚጠሉ ሁሉ የሶስቱ ቀለማት መውለብለብ ያሳምማቸዋል።

ቴዲ አፍሮ፣ ፓርቲ ሳያቋቁም፣ በሶስትም ሆነ ባራት ሳይደራጅ፣ በአንዲት አልበም ብቻ ቤተ-መንግስቱን ያሸበረና የነቀነቀበት ምስጢር ይኸው ነው። የፈሪ ዱላቸውን የመምዘዛቸው ምስጢርም ኢትዮጵያዊነትን የመስበኩ ወንጀል ነው። አንድ ዜማ ወደ ፍርሃት ጥግ ሲገፋቸው የሚያደርጉትን ነገር ሁሉ አሳጣቸው። ኮንሰርቱን ሲያግዱ፣ የምርቃቱን ዝግጅት ሲከለክሉ፣ የባንዱን አባል ከሃገር ሲያባርሩ…

እርግጥ ነው። ብላቴናው ላውንቸር ወይንም ሚሳየል ሳይሆን ኢትዮጵያን ከጀርባው ይዟል። ዛሬ በዙፋን ሆነው ይፈርዳሉ። የግዜ ጀግኖች አሁንም በንጹሃን ዜጎች በድፍረት ፍርደ-ገምድል ውሳኔ ይበይናሉ። በዚህ ሁኔታ ለዘልዓለም የሚዘልቁም ይመስላቸዋል። ይህንን ሲያድደርጉ የሚተማመኑበት አንድ ነገር አለ። ፋጣሪን አይደለም። ሕዝብንም አይደለም። ጠመንጃቸውን ነው የታመኑበት። “የቆሙ የመሰለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ” ይላልና ቃሉ የዛሬ ፈራጆች ነገ እንደማይወድቁ ምንም ዋስትና የለም። በእርግጠኝነት የምንናገረው አንድ ነገር አለ። ትውልድ አምጿል። ልብ በሉ! በመጭው አመት አንድ አዲስ ነገር እናያለን። ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቧን ይጠብቅ
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1526
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm

Re: በወያኔ የሚገፋው ቴዲ አፍሮ ትግሬውን ከሞት አዳነ

Postby ቢተወደድ1 » Wed Nov 08, 2017 11:57 am

ማሞ

ይሄን ሁሉ የጻፍክለት አቀንቃኝ ስለነ ንጉስ ጦና ይዝፈንልን፤ ስለነ አባ ጅፋር ይዝፈንልን ስለ ገዳ ሲስተም ይዝፈንልን፡፡
የሱ ኢትዮጵያ የተመሰረተችው በነሚኒሊክ እ አረጋት እኮ፡፡ ለመሆኑ ለምን ዳግማዊ ተባሉ???

እሰፋ ማሩ wrote:ይልቅስ ደስ የሚል ሁለት ነገር ልንገራችሁ !
August 28, 2017 – ቆንጅት ስጦታው
ቴዲ አፍሮ ላይ እየደረሰበት ያለው መንግሥታዊ ጫና ቀላል የሚባል አይደለም ፤ ሆኖም ግን እሱ እራሱ እንዲሁም የድምፃዊ ፕሮሞቶሮች እና አማካሪዎች በሚያደርጉት ከፍተኛ ጥራት ብዙ አስቸጋሪ ነገሮችን ተቋቋሞ ለማለፍ ጥረት እያደረገ እንደሆነ የሚታወቅ ነው። በተለይ የአድናቂዎቹ ድጋፍ እና እገዛም ቀላል የሚባል አይደለም። እነ ‘እንቶኔ’ የዓይነ ደረቅ ሥራቸው መልሶ ካላገረሸባቸው በስተቀር የብላቴናው ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሣሁን ቴዲ አፍሮ የሙዚቃ አልበም ምርቃት ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ እሁን ሊሆን እንደሆነ ለድምፃዊ ቅርበት ያላቸው የመረጃ ምንጮች እያመላከቱ ይገኛሉ። እሁድ ነሀሴ 28/2009 ዓ.ም ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ በሂልተን ሆቴል “ኢትዮጵያ” አልበም በደማቅ ሥነ ሥርዓት ይመረቃል። በእለቱ በዋነኛነት የተያዘው ፕሮግራም
☞ ቴዲ አፍሮ ከአቡጊዳ ባንድ ጋር በመሆን ከአዲሱ አልበሙ ዘፈኖችን የተወሰነውን ይጫወታል ፤
☞ የፍቅር እስከ መቃብር (ማር እስከ ጡዋፍ) ቪዲዮ ይመረቃል ፤
☞ ስለቴዲ አፍሮ የሙዚቃ ህይወት ከ20 ደቂቃ ያልበለጠ ፊልም ይቀርባል !!! ቀደም ብሎ ነሐሴ 21 ቀን 2009 ዓ.ም ተይዞ የነበረው የአልበም ምረቃ ፕሮግራም እንዲሰረዝ መደረጉ፣ እንዲሁም ለአዲስ አመት በሚሊኒየም አዳራሽ ሊካሄድ የነበረው የሙዚቃ ኮንሰርት በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር የህዝባዊ ስብሰባና ሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቂያ ክፍል ቀድሞ የተያዘ ፕሮግራም አለ በሚል ምክንያት ኮንሰርቱ እንዳይካሄድ ክልከላ ማድርጉ የሚታወስ ነው።

ሁለተኛ ! የዛሬ አምስት አመት በፑንትላንድ አደጋ ሊያደርሱበት በሞከሩ ሶማሊያውያን ላይ በወሰደው የመከላከል ዕርምጃ አንድ ሰው በመግደል ሌላኛው በመቁሰሉ በሞት እንዲቀጣ ወይም ገንዘብ እንዲከፍል ተወስኖበት የነበረው ኢትዮጵያዊ አስመሮም ኃይለ ሥላሴ ሊገደል 20 ደቂቃ ሲቀረው ቴዲ አፍሮ 700,000 ብር ከፍሎ የሞት ቅጣቱን አስቀርቶለት እንደነበር የሚታወሰ ነው። የመቀሌ ነዋሪ የሆነው አስመሮም ቴዲን የዛሬ አምስት አመት ከሞት ተርፌ ስመጣ በስልክ ነው ያገኘሁት፣ በግዜውም ሳመሰግነው “እኔን አታመስግን ይህን ያደረገው እግዚያብሄር ነው” ብሎኛል ። እኔ ግን በአካል አግኝቼ ማመስገን እፈልጋለሁ ። አምስት አመት ሙሉ ቴዲ አፍሮ ይገኛል የተባልኩበት ቦታ ሁሉ ብሄድ ላገኘው አልቻልኩም፣ ከእግዚአብሔር ቀጥሎ ሕይወቴን ያተረፈውን ቴዲ አፍሮን በአካል አግኝቼ ማመስገን እፈልጋለሁ ” እባካችሁ የምትችሉ አገናኙኝ ” በማለት ለኢትዮፒካሊንክ ተናግሯል ። ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ ከጥበብ ሥራው ባሻገር እሱ እንዲነገርልት ባይፈልግም ለወጎኖቹ በበጎ ሥራ አድራጎት ሁሌም እንደሚተጋ ለብላቴናው እጅግ በጣም ቅርበት ያላቸው ሰዎች ይናገራሉ። የእኔ የቅርብ ወዳጅ የሆነ የዓይን እማኝ ሆኖ የነገረኝ እሱ የህክምና ክትትል በሚያደርግበት ሆስፒታል ቴዲ አፍሮ አዲሱን “ኢትዮጵያ” አልበም ለሕዝብ ካቀረበ ከወራት በኋላ ፤ ህሙማንን እየተዟዟረ በመጎብኘት ምግብ በመመገብ እግዜር ይማራችሁ ይል እንደነበረ ፣ይሄን ሲያደርግ በትህትና እና በአክብሮት እሱነቱ እንዳይታወቅ ጥረተ እያደረገ አጀብ ሳያበዛ እንደነበረ ጭምር ወዳጄ ነገርኛል። ለድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሣሁን (ቴዲ አፍሮ) ፈጣሪ እረጅም እድሜና ጤና የስጠልን ፣አሜን !!!

(ይድነቃቸው ከበደ)
ቢተወደድ1
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 218
Joined: Thu Sep 01, 2016 8:48 am
Location: Bisheftu

Re: በወያኔ የሚገፋው ቴዲ አፍሮ ትግሬውን ከሞት አዳነ

Postby እሰፋ ማሩ » Wed Nov 08, 2017 12:53 pm

ውድ የዋርካ ብቸኛው ወያንታ ቢትወደድ 1
ቴዲ አፍሮ ከኦሮሞ ከተወለደው የሙዚቃ ሊቅ ከኤሊያስ መልካ ችሎታን ያዳበረ ሁሉን ዘር የሚያከብር ነው፡፡እስኪ ጥቁር ሰው ድንቅ ዜማ ቴዲ የሁሉን ጎሳ አርበኞች ያወደሰበትን ስማ፡፡ከዚያም ወርቅ ዘር ብሎ ራሱን የካበ ኢህአዲግ ለብሄር ተዋጽኦ ብሎ አሰስ ገሰሱን አይሾምም በማለት ሌሎች ጎሳዎችን የናቀ ሙት መሪያችሁን የዘርና የጎሳ ደዌ አስወግድ፡፡
https://www.youtube.com/watch?v=IuyfK7NLosY
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1526
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests

cron