ምንጃር ህዝባዊ አመፅ ተቀጣጥሎባታል!

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ምንጃር ህዝባዊ አመፅ ተቀጣጥሎባታል!

Postby ኳስሜዳ » Thu Nov 09, 2017 5:22 pm

ህዝቡ ጥያቄያችን ካልተመለሰ ንቅንቅ አንልም ብሎ ለሶስተኛ ቀን ዘልቋል። ፖሊስም ህዝቡ ላይ አልተኩስም ብሎ ከህዝቡ መወገኑ ከቦታው ተነግሮናል። ወያኔ ከገባ ጀምሮ እጅግ ዘግናኝ ጭቆና ከደረሰባቸውና በደላቸውን ሃገር እንዳያውቀው ከተደረጉ አካባቢዎች አንዱ የሽዋ አማራ ነው። ወያኔ የአማራን ህዝብ በጥቅል ብትፈርጅም የሽዋ አማራ አገዛዝ እያለች እነ አፄ ሚኒልክን ለማጥላላት ያልፈነቀለችው ድንጋይ የለም። በዚህ የተነሳ ህዝቡ በመሰረተ ልማት እጦት ተሰቃይቷል፣ በማንነቱ እንዲሸማቀቅና አንገቱን እንዲደፋ ተዘምቶበታል።

ይህ ግፍ ያንገፈገፈው ህዝብ በቃኝ ብሏል። ምንጃር ህዝባዊ አመፅ ተቀጣጥሎባታል። ከጎንደር የተነሳው የነፃነት ቋያ ድፍን ጎጃምን አዳርሶ ሸዋና ወሎ ደርሷል። በመላ የኦሮሞ ክልል የጎመራው ህዝባዊ አመፅ አሁን ከድፍን አማራው ጋር መዲናዋን በንተቀለቀለ የቁጣ ቀለበት ውስጥ ከቷታል።


Image
Image

Image
http://www.satenaw.com/amharic/archives/40988
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2140
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 6 guests