በአስር ሺዎች ከታጎሩበት እስር ቤት 115 የፖለቲካ እስረኞችን እፈታለሁ ሲል ወያኔ ተሳለቀ

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

በአስር ሺዎች ከታጎሩበት እስር ቤት 115 የፖለቲካ እስረኞችን እፈታለሁ ሲል ወያኔ ተሳለቀ

Postby ኳስሜዳ » Mon Jan 15, 2018 10:51 am

15 የፖለቲካው ቁማር ብክነት

አንድ መዝገብ ውስጥ = ከ70 በላይ ተከሳሾች ያሉት ሲሆን ከ200 በላይ መዝገቦች የፖለቲካ እስረኞች ክሶች ናቸው ። 200x70 = 14000 የፖለቲካ እስረኞች በአቬሬጅ አሉ ፤ የተፈቱት 115 ፦ የተበላው የወያኔ የፖለቲካ ቁማር ራሱን እያናወጠው መሆኑ ማሳያ ነው ።

ጠቅላይ አቃቢ ህጉ የሚፈቱት እሰረኞች የሚከተሉትን መስፈርቶች ያሟሉ ናቸው ብለዋል።

ህገ-መንግሥቱን ወይም ህገ-መንግሥታዊ ስርዓቱን የመናድ እንቅስቃሴ ላይ ያልተሳተፉ ወይም ያልመሩ
ምንጭ፡ ምኒሊክ ሳልሳዊ
በከፍተኛ የኢኮኖሚ አውታሮች ላይ ጉዳት ለማድረስ በተደረጉ እንቅስቃሴዎች ላይ ያልተሳተፉ ወይም ያልመሩ

የሰው ህይወት ያላጠፉ ወይም በአካል ላይ ከባድ ጉዳት ያላደረሱ እንዲሁም

በስርዓቱ ተጠቃሚ ሆነው ሳለ በሌሎች ገፋፊነት ወደ ሁከት እና ብጥብጥ የገቡ

ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ያሟሉ እስረኞች ከሁለት ቀናት የተሃድሶ ስልጠና በኋላ ይፈታሉ ተብሏል።
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2146
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Re: በአስር ሺዎች ከታጎሩበት እስር ቤት 115 የፖለቲካ እስረኞችን እፈታለሁ ሲል ወያኔ ተሳለ

Postby ኳስሜዳ » Tue Jan 16, 2018 5:03 pm

ዶክተር መረራ ጉዲና አይፈቱም ፤ ህወሃት መራሹ ቡድን ማጭበርበሩን አጠናክሮ ቀጥሏል

ዶክተር መረራ ጉዲና አይፈታም ጉዳዩ የሚታየው ከኢሕአዲግ ጉባዬ በኃላ ነው ። ዶ/ር መረራ ይፈታሉ የተባለው በስህተት ነው ሲል ነገሪ ሌንጮ መግለጫ ሰጥቷል ።

ህወሃት መራሹ ቡድን ማጭበርበሩን አጠናክሮ ቀጥሏል የተፈጠረበትን አጣብቂኝ አጭበርብሮ ለማለፍ ቀደም ሲል የፓለቲካ እስረኞችን እፈታለሁ ካለ ቡሃላ እንደገና መልሶ የፓለቲካ እስረኞች የሉኝም በማለት መካዱ ይታወሳል።

ይህ በእንዲህ እንዳለም እንደገና በድጋሜ ሰሞኑን የፓለቲካ እስረኞች ይፈታሉ በሚል አስገራሚ መግለጫ መስጠቱን ተከትሎ የዶክተር መረራ ጉዲና ክስም መቋረጡ እና በነገው እለት ሮብዕ ይፈታሉ የተባለ ቢሆንም በዛሬው እለት የኮሙኒኬሽን ሚኒስተሩ ዶክተር ነገሬ ሌንጮ ለጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ዶክተር መረራ ጉዲና አሁን አይፈታም የርሱ ጉዳይ ከሁለት ወር ቡሃላ ነው የሚታየው የሚል አሳዛኝ መግለጫ ሰጥቷል ።

ህወሃት መራሹ ቡድን በተለይም በኦሮምያ እና አማራ ክልል ላይ የተፈጠረበትን ከፍተኛ ህዝባዊ ተቃውሞና ቅራኔ በዘዴ ለማለፍም ታድሻለሁ እስረኞችን እፈታለሁ ማእከላዊን እዘጋለሁ በሚል የማደናገሪያ ተከታታይ መግለጫ ቢሰጥም ይሄ መግለጫ በተሰጠ ማግስትም በርካታ ዜጎች ስርአቱን ተቃውማችሗል በሚል ወደ እስር ቤቶች እየተጋዙ ይገኛሉ #BBN

በእስረኞች አፈታት ላይ ሌላ ውሸት!

~በፌደራል ደረጃ 115 ያህል እስረኞች ይፈታሉ ተብሎ ነበር!

~ሆኖው አንድ የእስረኛ ቤተሰብ ከእስረኞች ባገኘው መረጃ መሰረት እንደገለፀልኝ፣ ወደሰንዳፋ የተወሰዱት 111 እስረኞች ነበሩ!

~ ወደ ሰንዳፋ ከተወሰዱት መካከል ደግሞ በቂሊንጦ ቃጠሎ የተከሰሱት ዲንሳ ፉፋ እና ቶሎሳ በዳዳ ወደ ቂሊንጦ ተመልሰዋል! 109 እስረኞች ነው የሚፈቱት ማለት ነው! ከእነሱም መካከል ካልተቀነሰ ነው!

~ በጣም የሚያሳዝነው ደግሞ 115 እስረኛን እንፈታለን ሲሉ ሌላ የሌለ ማስረጃ እንደጨመሩ እየተገለፀ ነው። አብዲሳ ቦካ በቂሊንጦ ቃጠሎ ወቅት በጥይት እንደተገደለ እስር ቤቱም አምኗል። 115 ተብሎ በተጠቀሰው ዝርዝር ውስጥ የቂሊንጦ እስር ቤት ያስገደለው አብዲሳ ቦካም ተጠርቷል ተብሏል። ወደ ማሰልጠኛ ተወሰዱ የተባሉት 111 ናቸው። በመግለጫው ደግኔሞ 115 ይፈታሉ ተብሏል። እንግዲህ አራቱ እንደ አብዲሳ ቦካ የተገደሉት ናቸው ማለት ነው። ትህነግ/ህወሓት የኢትዮጵያ ህዝብን ለማሞኘት የተገደሉትንም እፈታለሁ እያለ ነው! ቁማሩ በተገደሉትም እስከመቀለድ ነው!
ምንጭ፡ ምኒሊክ ሳልሳዊ
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2146
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 8 guests