የወሎ ህዝብ ከወያኔ ጋር ትንቅንቅ ውስጥ ነው!

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

የወሎ ህዝብ ከወያኔ ጋር ትንቅንቅ ውስጥ ነው!

Postby ኳስሜዳ » Thu Jan 25, 2018 2:10 pm

በወልድያ ሰላማዊ የጥምቀት አክባሪዎች ላይ የደረሰው ጭፍጨፋ ያስቆጣው የወሎ ህዝብ ከወያኔ ጋር ትንቅንቅ ውስጥ ነው!

በራያ ቆቦ ከፍተኛ የሆነ ህዝባዊ አመፅ እየተካሄደ ነው። በስርአቱ ንብረትና ተቋማት ላይ ህዝቡ ጥቃት እየወሰደ ነው። ከባድ ተኩስም እንደ ቀጠለ ሲሆን ቁጥሩ ያልታወቀ ሰው ከህዝቡም ከአጋዚም መውደቁ እየተዘገበ ነው።
ወደ ትግራይ የሚያሳልፈው መንገድ በህዝቡ ተዘግቷል።

አሁን አዲስ የመጣው መረጃ ግን አስደንጋጭ ነው። ወያኔ በህዝቡ ላይ ሄሊኮፕተር እንዳዘመተ መረጃ እየወጣ ነው። ይህ እውነት ከሆነ ከቅርብም ከሩቅም ያለ ህዝብ ካልተረባረበ እልቂት ሊያስከትል ነው። ወያኔ የከፈተውን ሁለገብ ጦርነት ለመመከት በአቅራቢያው ያለው የጎጃም፣ የጎንደርና የሽዋ ህዝብ እንዲደርስ ጥሪ እየተላለፈ ነው። ከወልቂጤ እስከወለጋ የተቀጣጠለው ህዝባዊ አመፅም ወሎ ውስጥ ካለው ጋር ተዳምሮ ሃገሪቱ የቀውስ ቀጠና ውስጥ ናት። ህዝቡ ተረባርቦ ወያኔን ካላስወገደ በየተራ ማለቅ ስለሆነ በተቀናጀ መልኩ ትግሉ እንዲቀጥል ጥሪ ሲተላለፍ ከርሟል።
የተቀናጀ የህዝብ ትግል ያሸንፋል
https://www.youtube.com/watch?v=_4WKYnBpeAQ
Image
Image
የቆቦ ህዝብ ለመላው ኢትዬጵያውያን አስቸኳይ የድረሱልኝ ጥሪ በማድረግ ላይ ይገኛል እባካችሁ ይህን መልዕክት ሸር በማድረግ ተባበሩ
Image
በአሁኑ ስአት የቆቦ ሕዝብ በትግራይ ወንበዴዎች በሒሊኮብተር እዬ ተደበደበ ነው ::
በጣም ከፍተኛ ጉዳት በሰላማዊ ህዝብ ላይ ደርሷን ::

መረጃ ቆቦ
ከዚህ በኋላ ህወሃቶች ወደኛ ሳይመጡ እኛ ወደነርሱ ነዉ የምንሄደዉ ይልሃል ቆቦ!
ይህ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን መርህ ሊሆን ይገባል ከእንግዲ እነርሱ ወዳሉበት በመሄድ መፋለም የመጨረሻዉ መፍትሄ ነዉ። ወደ ፖሊስ ጣቢያ እንሄዳለን… ወደ መኖሪያቸዉ እንሄዳለን… ወደ መከላከያ ካምፕ እንሄዳለን…. ወደ ዋና ጽሕፈት ቤታቸዉ እንሄዳለን…. እኛ ያለንበት ድረስ እየመጡ አይገሉንም…. እኛ እነርሱ ያሉበት ድረስ ሄደን ገድለናቸዉ እንሞታለን . . . .ከእንግዲህ ማን ወንዱ ማን ዉርዱ! እንደሆነ እንተያያለን ይልሃል የወሎዉ ሳተና ቆቦ።

ሁሉንም እያደሙ ተራበተራ እየሞትን አንቀርም ከእንግዲህ ቆቦን ጨርሰዉ ወደሚፈልጉት ሄደዉ ይገደሉ በሬሳችን ላይ ተረማምደዉ ነዉ የሚዘልቁት ወልዲያ ላይ ጥለዉ ቆቦ ላይ ቆርሰዉ አያድሩም የአማራይቱ ነበልባል።

ይህንን መልእክት ያደረሰን የብሄራዊ መረጃ ሳተናዉ ህዝቡ ዉስጥ ገብተዉ እንዳነጋገሩ የገለጹ ሲሆን ጠንከር ባለ መልኩ ይህን መልእክት አስተላልፈዋል ” በመሐበራዊ የመገናኛ ዘርፍ በዜና አዉታርነት መረጃ የምትለዋወጡ አካላቶች በሙሉ እባካችሁ ዜና ወይም መረጃ ስትሰሩ… የእንዲህ አካባቢ ወጣቶች እየመከሩ ነዉ ! ወይም ተነጋግረዉ ጨረሱ ! ህዝባዊ እንቢተኝነቱ ወደ እዚህ አካባቢ ሊስፋፋ ነዉ ! የሚሉ ጠቋሚ መረጃዎችን ከማቀበል እንድትቆጠቡ አደራቸዉን አስተላልፈዋል።
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2148
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Re: የወሎ ህዝብ ከወያኔ ጋር ትንቅንቅ ውስጥ ነው!

Postby ኳስሜዳ » Thu Jan 25, 2018 2:53 pm

ሌሊቱን ቆቦ በደፈጣ ታጣቂዎች ስትናጥ አደረች!!
የቆቦ ህዝብ እሰረኞችን ነፃ አወጣ


ከትላንትና ምሽት 11 ፥00 ጀምሮ በሰሜን ወሎዋ ራያ ቆቦ የተቀጣጠለው ህዝባዊ አመጽ ሊሊቱን ሙሉ ከተማዋን ሲንጥ ማደሩን ከስፍራው የሚገኙ የአይን እማኞቻችን ገልጸዋል።

እንደ አይን እማኞቻችን ገለጻ በቆቦ የተካሄደው ህዝባዊ ቁጣና ተቃውሞ በተደራጅ ሁኔታና ሁለገብ እንደነበር ሌሊቱን ሙሉ በመሳሪያ ቶክስ ስትናጥ ማደርዋን አያይዘው ገልጸዋል።

የቆቦው ህዝባዊ አመጽ መነሻውን ከከተማዋ መግቢያ 5ኪሎ ሆርማት እንዲሁም መውጫው 12 ኪሎ ሜትር ዋጃ ላይ መንገዶቹን በተጠናና በተደራጀ ሁኔታ የአጋዚም ሆነ የመከላከያ ሰራዊት እንዳይገባ መንገዶቹ ሙሉ ለሙሉ ከተዘጉ በሁዋላ መሆኑንና በሁለቱም አቅጣጫዎች ወደከተማዋ ለመግባት የሞከሩ የመንግስት ታጣቂዎች በደፈጣ ታጣቂዎች ጥቃት ስለተፈጸመባቸው ወደሁዋልቅ ለማፈግፈግ መገደዳቸውን ምንጫችን አክሎ ገልጾዋል።

በቆቦ ከተማ እከስርአቱ ጋር በማበር ህዝብን ሲያሰቃዩ ነበር የተባሉ የመንግስት ባለስልጣናትና በአካባቢው የሚኖሩ ለስርአቱ መረጃ በማቀበል የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች የጥቃቱ ሰለባ እንደነበሩ ለማወቅ ተችሎዋል።

በቆቦ ከተማ በተነሳው ህዝባዊ አመጽ የቆቦ ከተማ ማዘጋጃ_ቤት እና ተሽከርካሪዎ እንዲሁም ፍርድ_ቤት በእሳት መውደማቸውንና እስረኞችን ለማስፈታት የተደረገው ብርቱ ጥረት ግን ሊሳካ አለመቻሉን ምንጮቻችን ከስፍራው አያይይዘው ገልጸዋል።

ይህን ዘገባ እስካጠናከርኩበት ግዜ ከተማዋ በህዝብ ቁጥጥር ስር እንደሆነችና ከተማዋ እየተካሄደ የሚገኘው ህዝባዊ ተቃውሞ በተለያዩ ገሩፕ መሪዎች በተጠናና በተደራጀ ሁኔታ መሆኑንም ከመረጃ ምንጮች ለማወቅ ተችሎዋል።

የቆቦ ህዝብ እሰረኞችን ነፃ አወጣ

ለሊቱን ከ 6ግዜ በላይ ተሞክሮ ያልተሳካው የቆቦ እስረኞችን የማስፈታት ዘመቻ በህዝብ ያለተቋረጠ ትግል እስረኞች ነፃ ወጡ፡፡ ቆቦ ሁንም በከፍተኛ የመሳሪያ ተኩስና የእሳት ቃጠሎ እየታመሰች ነው፡፡እሰካሁን 3 የህዝብ ለጆች ሲሰዉ 2 የፌደራል ፖሊሶችም መገደላችው የአይን እማኞቻችን ከስፍራው ገልፀዋል፡፡
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2148
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 4 guests