ትግሉ ደቡብ ህዝቦችንም ያካትታል

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ትግሉ ደቡብ ህዝቦችንም ያካትታል

Postby እሰፋ ማሩ » Tue Feb 13, 2018 12:28 pm

በወያኔ ላይ የሚደረገው ትግል ደቡብ ህዝቦችንም ያካትታል፡፡በሁሉም ክልል የደቡቡ ሃይለማርያምን የመሰሉ ባንዳዎች መኖራቸው ይታወቃል፡ሆኖም ግን ሰሞኑን በደቡቦች ላይ በጎንደር የተደረገ ስድብና ወከባ መቆም ያለበት መስናክል ነው፡፡በደቡብ የኮንሶ ወገኖችና የሰሞኑ የከምባታ ትግል ጠንካራ መሆኑና በወያኔ ጭፍጨፋ ያለመዳፈኑ ይስተዋል፡፡
-------------------------===============================-----------------------------

የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች በአርባ ምንጭ ተጫዋቾች ላይ ስድብና ጥቃት ፈፀሙ ።
February 13, 2018 – ቆንጅት ስጦታው
በወንድማገኝ አንጁሎ ሲሳይ

በጎንደር ፋሲለደስ ስታዲየም አርባ ምንጭ ከተማን ያስተናገደው ፋሲል ከተማ 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡ ውጤቱ የኳስ ባህሪው ነውና ለአሸናፊው ድሉን ለተሸናፊው ደግሞ ሽንፈቱን መቀበል ግድ ነበርና ሁለቱም ቡድኖች ውጤታቸውን በፀጋ ተቀብለዋል፡፡ ነገር ግን በጨዋታው ወቅት ጎንደርንና መላውን የፋሲል ከተማ እግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎችን የማይወክሉ የተወሰኑ የፋሲል ደጋፊዎች ነን ባዮች በአርባ ምንጭና በአርባ ምንጭ ተጫዋቾች ላይ ያደረሱት ማሸማቀቅ፣ ስድብና፣ በደል በመቀጠልም ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ የሜዳውን ዙሪያ በመክበብ የአርባ ምንጭ ተጫዋቾችን በማይመለከታቸው አጀንዳ ከመሳደብ ባለፈ ድንጋይ በመወርወር አናስወጣም እስከማለት የተደረሰበት ሂደት ከምንም በላይ ለአርባ ምንጭና ለልዑኮቿ የማይገባ ኢትዮጵያዊ ያልሆነ ፀያፍ ምግባር እንደሆነ መግለፅ እፈልጋለሁ፡፡ እናም በዚህ ፀረ ሕዝብ በሆነው ድርጊት ለተሳተፉ የፋሲል ደጋፊ ነን ባዮች የሚከተለውን ለማለት እሞክራለሁ፡፡
አዎ ……እኛ አርባ ምንጮች፤ እኛ ጋሞዎች ነን!!! እናም የድምፃዊ ጌትሽ ማሞን “እንከባበር” ዜማን እየጋበዝኳችሁ በድጋሚ “እንከባበር” እላችኋለሁ!!!
አርባ ምንጭ — የወንዶች ሃገር፤ የጀግኖችም ምድር ናትና እንከባበር!!!
“ጋሞ” ከሁሉም ኢትዮጵያዊ ወንድሞቹ ጋር በፍቅርና በጨዋነት እየኖረ ያለ “የሰላም ጀግና” ሕዝብ ነውና እንከባበር!!!
ጎንደር ቴዎድሮስ እንዳለ ሁላ አልተነገረላቸውም እንጂ እኛም ጋ አርባ ምንጭ ብዙ ጀግኖች ቴዎድሮሶች አሉ!!!
አህያውን ፈርቶ ዳውላውን ለሚመስለው ፀረ ኢትዮጵያዊ ድርጊታችሁ እንከባበር!!! የፈሪ ዱላ!!!
ትላንት አጨብጭባችሁ ላስገባችሁት፣ ዛሬ ግን ለምትሰደቡት ምንም አይነት ነገራችሁ እኛን ባይመለከተንም የማይመለከተንን እኛን አርባ ምንጮችን በማይመለከተን አጀንዳ ለመስደብና ለማገት መሞከራችሁ ብልግና፣ ውርደትና፣ አሳፋሪ ምግባር ነውና እንከባበር!!!በፋሲል መንደር፤ በጀግኖቹ ምድር፣ በቴዎድሮስ ሀገር ለመላ ኢትዮጵያዊያን አሻራችን፣ ታሪክና፣ ባህላችን በሆነችው በውቧ ጎንደር ከተማ መገኘት ወይም መፈጠር ያልነበረባችሁ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን በተግባር ሳይሆን በዲስኩር ለማላዘን የምትሞክሩ ናችሁና እንከባበር!!! አሳት አመድ ሲወልድ ምን ይደረጋል?
ሶከር ኢትየጵያ እንደገለፀው ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ የአርባ ምንጩ ምክትል አሰልጣኝ የሚከተለውን አስተያየት ነበር የሰጠው፡፡
“የጨዋታውን ውጤት የቀየሩት ደጋፊዎች እና ዳኛው ናቸው”። ዳኛው ቶሎ ቶሎ ጨዋታውን ስለሚያቋርጠዉ እኛ መጫወት አልቻልንም። በተደጋጋሚ ሰአት ሲያባክኑ እና ጨዋታው ሲቋረጥ ካርድ አላሳየም።ምንም እንኳን ተጫዋቾቻችንን/ልዑኮቻችንን አግታችሁና ሰድባቻሁ ብትልኩልንም
የፋሲል ስፖርት ክለብ ብሎም የደጋፊ ማህበሩ ስለተፈጠረው ነገር ጠቅሰው በስፖርታዊ ጨዋነት መርህ ይቅርታ መጠየቅ አለባቸው፡፡
በሁለተኛው ዙር የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ፋሲል ከተማ እግር ኳስ ክለብ አርባ ምንጭ መምጣቱ የማይቀር ነውና ቡድናችሁን ይዛችሁ አርባ ምንጭ በምትመጡበት ጊዜ እኛ አርባ ምንጮች የአበባ ጉንጉን በመያዝ እንደምንቀበላችሁና ጋብዘን እንደምንልካችሁ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ፡፡
እኛኮ “ጋሞዎች” “ጋሞ ጎፋዎች” ነን!! ምድራችን ደግሞ “አርባ ምንጭ”!!! ኢትዮጵያ ሀገራችን፤ ኢትዮጵያዊነት ደግሞ “ዜግነታችን” ነው!!!እናም እንከባበር!!!
ወልቃማ ደሬ፤
ሚዚዲ ካልሲዲ ዬዲዚያሲ፤
ኑደሬ ጋሞ ጎፋ ኦይቻ አርባ ምንጬ
ሚዚዲ ካልሲ ዬዴስ አባያ ጫሞ ሞሌ!!
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1526
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 7 guests