ወያኔ አቶ ለማ መገርሳ ላይ ይፋ ዘመቻ ጀመረ

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ወያኔ አቶ ለማ መገርሳ ላይ ይፋ ዘመቻ ጀመረ

Postby እሰፋ ማሩ » Mon Feb 19, 2018 1:46 am

በብዙሃን ህዝባችን በተለይ በኦሮሞና በአማራ ወገኖች ተቀባይነታቸው እየጨመረ የመጣው የአቶ ለማ መገርሳ ጉዳይ ያበሳጨው ወያኔ በልሳኑ አይጋ ፎረም ስማቸውን ማጥፋት ጀመረ፡፡

አይጋ ፎረም ፈብርዋሪ 18 /2018
ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያምን ማን ይተካቸው?
በሃገራችን የተከሰተውን ሁከትና ብጥብጥ ተከትሎ በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ በራሳቸው
ፈቃድ ስልጣናቸውን ለመልቀቅ ጥያቄ ካቀረቡ በኋላ ይህችን "ክፍት የስልጣን ቦታ" ለመያዝ ከየአቅጣጫው
የሚሰማው ጩሆት በጣም የሚያስገርም ነው፡፡ የስልጣን ጥማት ለካ ከውሃ ጥማት የባሰ የሚያንገበግብ አምሮት
ኖሯል! ኮሎኔል መንግስቱ ሀይለማርያም በአንድ ወቅት የተናገሩትን ቃል በቃል በትክክል ባላስታውሰውም
"ይህችን ወንበር ለመያዝ ሁሉም ሰው ይመኛል፣ ወንበርዋ ግን አንድ ናት እስዋም እኔ ተቀምጨባታለሁ" ያሉት
ለካ ወደው አልነበረም፡፡
ኢትዮጵያ የምትባል ኢምፓየር ፈርሳ ኦሮሚያ ነፃ መውጣት አለባት ሲለን የከረመው ጀዋር መሃመድና የኦነግ
ደቀመዛሙርቱም ከጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ስልጣን መልቀቅ በኋላ የሃገሪቱ ቀጣይ ጠቅላይ ሚኒሰትር
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዚዳንት የሆኑት ክቡር አቶ ለማ መገርሳ መሆን አለባቸው የሚል በግልፅ የታወጀ
ዘመቻ ማካሄድ ጀምረዋል፡፡ "እኔ ባልቀምሰውም ኢትዮጵያዊነት ማለት ሓሺሽ ነው፣ ሱስ ነው፣ የግለሰብ
ስልጣንና ክብር ከሃገርና ከህዝብ በላይ ስላልሆነ ገደል ይግባ... ወዘተ" በሚሉ መሳጭ የሚድያ ንግግሮቻቸው
የታለሉ አንዳንድ የዋህ ኢትዮጵያውያንም ይህንን የጃዋርና ተከታዮቹን ሃሳብ ሲያስተጋቡ ይደመጣል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር የመሰለን ከባድ የመንግስትና የህዝብ ሃላፊነት ዝም ብሎ እንዲሁ የሚያዝ ስልጣን አይደለም፡፡
ለዚህ ከባድ የሃላፊነት ቦታ የሚመጥን የትምህርት ዝግጅት፣ ብቃትና ችሎታ እንዲሁም ልምድና ተሞክሮ
በአጠቃላይ ፈረንጆች merit የሚሉት መመዘኛ ከሁሉም በላይ ደግሞ በሃገራችን ካለው ተጨባጭ ሁኔታ
አንፃር፣ የብሔርና የሃይማኖት ብዝሃነታችንን የሚያስተናግድ፣ ዜጎችን በእኩል አይን የሚያይ ህዝባዊ አመለካከት
መላበስን ይጠይቃል፡፡
ከዚህ አንፃር ክቡር አቶ ለማ መገርሳ እስከአሁን ድረስ በተግባር ባሳዩት እንቅስቃሴ ለዚህ ከባድ ሃላፊነት
የሚያበቃ ችሎታ፣ የጠራና በተግባር የተፈተነ ህዝባዊ አመለካከት አላቸው ወይ ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው፡፡
ክቡር አቶ ለማ መገርሳ ከሁሉም በፊት ውስብስብ የሆነው ሃገራዊ፣ ከባቢያዊና አለምአቀፋዊ ሁኔታ በሚገባ
በመተንተን አመራርና ውሳኔ ለመስጠት የሚያስችል የትምህርት ዝግጅት፣ ቢያንስ የተፈጥሮ ክህሎት ያላቸው
መሪ አይመስሉኝም፡፡ የ12ኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተናን ብዙ ጊዜ ወስደው የረባ ውጤት ማግኘት ባለመቻላቸው
ከመንግስት የድጋፍ ደብዳቤ ተፅፎላቸው ሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ ገብተው በመከራ ትምህርታቸውን ከጨረሱ
በኋላ በኮሌጁ የሚሰጠውን ዲግሪ ይዘው በመውጣት እንደዘመኑ የሃገራችን ፖለቲከኞች ወደ ፖለቲካው አለም
የተቀላቀሉ ሰው መሆናቸው ይነገራላቸዋል፡፡
2
በዚህ ሁኔታ ከአንድ መቶ ሚሊዮን በላይ የሆነ የህዝብ ቁጥር እንዲሁም የተወሳሰበ የብሔረሰብና የሀይማኖት
ስብጥር ያለበትና በሚሊዮኖች የሚገመቱ በአስከፊ ድህነትና ኋላቀርነት የሚኖሩ ዜጎች የሚኖሩባት፣ በተወሳሰበ
ከባቢያዊ የፀጥታ ሁኔታና በፈረሱ መንግስታት የተከበበች ሃገር መምራት ቀላል አይመስለኝም፡፡ እንዲህ አይነት
ከባድ የሃገርና የህዝብ ሃላፊነት መሸከምን ካላስፈራ ምን ሊያስፈራ እንደሚችል በፍፁም አይገባኝም፡፡ ነጋ ጠባ
ጆሮአችንን ባደነቆረው ነገር ግን ምንም አይነት ህጋዊም ሆነ ዲሞክራሲያዊ መሰረት በሌለው የህዝብ ብዛት፣
የመሬት የቆዳ ስፋት...ወዘተ በሚለው መከራከሪያ ክቡር አቶ ለማ መገርሳ ሃገር የመምራቱን ሃላፊነት ተረከቡ
እንኳን ቢባሉ "አይ እኔ አልችለውም፣ ይከብደኛል" የማለት ድፍረት ሊኖራቸው ይገባል፡፡ ሃገር መምራት
በቤተሙከራ የሚገኝ ልምድና ብቃት አይደለም፡፡
ሃገር ለመምራት የሚያስችል ብቃትና ችሎታ መኖርን ለጊዜው ወደ ጎን ትተን ክቡር አቶ ለማ መገርሳ ምን
ስለሰሩ ነው ለዚህ ከፍተኛ ሃላፊነት የሚበቁት? ብሎ መጠየቁም ተገቢ ነው፡፡ ሁሉም እንደሚያውቀው እሳቸው
ስልጣን ከተረከቡበት ጊዜ ጀምሮ ላለፉት ሶስት አመታት የኦሮሚያ ክልል በሁከትና በብጥብጥ በመታመስ ላይ
የሚገኝ ክልል ነው፡፡ በብሔሩ ተወላጆችና ለትውልድ ከክልሉ ህዝብ ጋር ተጋብተውና ተዋልደው ሲኖሩ በነበሩ
የሌሎች ብሔር ተወላጆች ህይወትና ንብረት ላይ ከዚህ በፊት በሃገራችን ታይቶም ሆነ ተሰምቶ በማይታወቅ
መልኩ በየቀኑ ዘግናኝ የሆነ እልቂት እየደረሰ ነው፡፡ እሳቸው በሚመሩት የኦሮሚያ ክልል ዜጎች ፈልገው
ባልተላበሱት ማንነት እንደ አውሬ እየታደኑ በጭካኔ እየተገደሉና እየተጨፈጨፉ ነው፡፡ ክቡር አቶ ለማ መገርሳ
በሚመሩት ክልል እንዲህ አይነቱን የጭካኔ ተግባር ለማስቆም ጥረት አላደረጉም ብቻ ሳይሆን ቢያንስ አደባባይ
ወጥተው በማያሻማ ቋንቋ ድርጊቱን ሲያወግዙ አልሰማንም፡፡ የክልሉ ፕሬዚዳንት ስለኢትዮጵያውነት ለኛ
ባማርኛ ቋንቋ የሚያስተላልፉት ሆድን የሚያባባ መልእክትና ለቄሮ ጀሌዎቻቸው በኦሮሚኛ ቋንቋ የሚሰጡት
መመሪያ ለየቅል እንደሆነ መገመት ይቻላል፡፡ እሳቸው በሚመሩት ክልል በመፈፀም ላይ ያለው ይህ ዘግናኝ
ድርጊት በሃላፊነት የሚያስጠይቅ እንጂ ለበለጠ ሃላፊነትና ስልጣን የሚያበቃ ሊሆን አይችልም፡፡
ክቡር አቶ ለማ መገርሳና ጀሌዎቻቸው በክልላቸው ያቀጣጠሉት ዘርን ማእከል ያደረገ ሁከትና ብጥብጥ
የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ስልጣን ከተቆናጠጡ በኋላ ችግሩን ሃገራዊ መልክ በማስያዝ ኢትዮጵያን የማፍረስ
አላማ ያለው እና ከስድሳ አመታት በላይ የቆየው የነኦነግን የጥፋት አጀንዳ ለማስፈፀም የታቀደ እንዳይሆንም
መጠርጠር ያስፈልጋል፡፡
3
ከዚህ በተጨማሪ ቄሮዎችን በማደራጀት ሁከትና ብጥብጥ በማስነሳት በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት
በማድረስ ስልጣን ማግኘት የሚቻል ከሆነስ ሁሉም በየክልሉ የጎበዝ አለቃ እያደራጀ እድሉን ከመሞከር ወደኋላ
የማይልበት ምን ማረጋገጫ አለን? ማቆሚያውስ የት ሊሆን ይችላል ብሎ መጠየቁም ተገቢ ነው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያምን መተካት ያለበት ከኦሮሞ ብሔር ነው የሚባለው የክርክር መነሻም ግልፅ
አይደለም፡፡ አመራር ብቃትና ህዝባዊ አመለካከት መላበስን ይጠይቃል ከተባለ በህገመንግስቱ መሰረት ብቃትና
ህዝባዊ አመለካከት ያለው ከሌላ የሃገራችን ብሔር/ብሔረሰብ የተገኘ ጠቅላይ ሚነስትር መሆን የማይችለበት
ምክንያት ምንድነው? ምን ይከለክለዋል?
ቀጣዩ የሃገራችን መሪ ከኦሮሞ ብሔር መሆን አለበት ከተባለስ ከ35 ሚሊዮን በላይ ከሆነው የኦሮሞ ህዝብ
ውስጥ ከክቡር አቶ ለማ መገርሳ የተሻለ ብቃትና በተግባር የተፈተነ ህዝባዊ አመለካከት ያለው ሌላ የኦሮሞ
ብሔር ተወላጅ የለም ማለት ነው?
ህዝባዊ አመለከካከት ስለኢትዮጵያዊነት በሚድያ በመስበክ የሚገኝ ሳይሆን በተግባር ህዝባዊ ሆኖ መገኘትን
እንዲሁም የራስን ጨምሮ በማንኛውም ሀዝብ ላይ የሚፈፀም ፀረህዝብ ተግባራት አምርሮ መታገልን፣
የሚጠይቅ በመሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝን የሚተካ መሪ ኦሮሞን ጨምሮ ከየትም ብሔር
ይሁን ከየት ቢያንስ ይህንን ስብእና የሚያሟላና ህዝባዊነቱን በተግባር ያረጋገጠ ሰው መሆን አለበት፡፡
አምላክ ሃገራችንን ሰላም ያድርግልን፡፡
አለባቸው ሁነኛው
የካቲት 10 ቀን 2010
ፍንፍኔ/ሸገር/አዲስ አበባ
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1529
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 5 guests