ጣጥፈናል ተናግረናል ፡ ለማስረዳት ሞክረናል ፡ ከድጡ ወደ ማጡም እንዳይሆን መክረናል፡፡

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ጣጥፈናል ተናግረናል ፡ ለማስረዳት ሞክረናል ፡ ከድጡ ወደ ማጡም እንዳይሆን መክረናል፡፡

Postby ቆቁ » Sat Feb 17, 2018 10:47 am

ጠቅላይ ሚኒስቴር ፍቅረ ስላሴ ወግ ደረስ
ጠቅላይ ሚኒስቴር ታምራት ላይኔ
ጠቅላይ ሚኒስቴር መለሰ ዜናዊ ??
በመጨረሻም
ጠቅላይ ሚኒስቴር ሐይለማርያም ደሳለኝ


ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር
ፈላስፋው ቆቁ
Last edited by ቆቁ on Sun Feb 18, 2018 7:57 am, edited 1 time in total.
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4044
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: ጣጥፈናል ተናግረናል ፡ ለማስረዳት ሞክረናል ፡፡

Postby ፉኚዶ ተራራ » Sun Feb 18, 2018 4:01 am

ቀጣዮቹ ደግሞ.....

ጠቅላይ ሚ/ር አህመዲን ያሲን
ጠቅላይ ሚ/ር ሲስተር ሰሎሜ ማስረሻ
ጠቅላይ ሚ/ር ሲልዶሮ ደበሌ
ጠቅላይ ሚ/ር ዶ/ር ዓወት በርሄ ......እያለ ይቀጥላል

ከኢህ አዴግ ጋር ሲጉዋዙ፤ቀና ነው መንገዱ.....

ከሰላምታ ጋር...
ሙክታር በድሩ
በኢትየጵያ ፌደራላዊ መንግሰት፤ የአስቸኩዋይ ጊዜ አዋጅ አሰከባሪ ኮሚቴ ቡድን መሪ
ፉኚዶ ተራራ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 99
Joined: Wed Jul 17, 2013 6:34 pm
Location: americas

Re: ጣጥፈናል ተናግረናል ፡ ለማስረዳት ሞክረናል ፡፡ ከድጡ ወደ ማጡም እንዳይሆን መክረናል፡፡

Postby ቆቁ » Sun Feb 18, 2018 7:56 am

ወይዘሮ ሰሎሜ ናቸው መሰለኝ ባልሳሳት
ከዘላለም ባርነት የአንድ ቀን ነጻነት ያሉት

ዋ ሶቅራጥስ ፡

የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዘላለም ይኑር

ከዘላለም ባርነት የአንድ ቀን ነጻነት
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4044
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: ጣጥፈናል ተናግረናል ፡ ለማስረዳት ሞክረናል ፡ ከድጡ ወደ ማጡም እንዳይሆን መክረናል፡፡

Postby ቆቁ » Tue Feb 20, 2018 9:51 pm

ያልገባኝ ነገር አለ
እስርበቶች ሙዚየም ከሆኑ ሙዝየሞቹ ምን ሊሆኑ ነው ?

ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4044
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: ጣጥፈናል ተናግረናል ፡ ለማስረዳት ሞክረናል ፡ ከድጡ ወደ ማጡም እንዳይሆን መክረናል፡፡

Postby ዘርዐይ ደረስ » Tue Feb 20, 2018 10:58 pm

ቆቁ:- ሌላውን ተወውና የሚከተለውን ጉዳይ መርምረህ እንደ ኃይለማርያም ራስህን ነፃ አውጣ::ህወሓት የማይገባውን ሥልጣን ይዞ አልለቅ ብሏል::አንተም የማይመጥንህን ፈላስፋነት ሙጥኝ ብለሃል::
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1096
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: ጣጥፈናል ተናግረናል ፡ ለማስረዳት ሞክረናል ፡ ከድጡ ወደ ማጡም እንዳይሆን መክረናል፡፡

Postby ቆቁ » Wed Feb 21, 2018 5:37 pm

ዘርአይ ያልተጻፈ እኮ ነው የምታነበው ወይም እኔ ያልጻፍኩትን፡፡
ስማ እኔ እኮ የማነበው የጻፍኩትን ነው አንተ ግን እንደ እሳቸው የተጻፈልህን ነው የምታነበው

ሙዚየም እስርቤት ከሆነ እስርቤት ምን ሊሆን ነው እኮ ነው ጥያቄዬ
ወይስ እስረኞች እንደ ሙዝየም እቃ ሊታዩና ሊጎበኙ ነው ማለት ይሆን ?
ይገባሃል የምጽፈው ወይስ እንደ እሳቸው የተጻፈላቸውን ነው የምታነበው ?
ለመሆኑ እሳቸው ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ናቸው ያነበቡትን የጻፉት ?
እኔ ፈላስፋው
ፈላስፋ ሆኜ ፈላስፋ ያልሆንኩት
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4044
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: ጣጥፈናል ተናግረናል ፡ ለማስረዳት ሞክረናል ፡ ከድጡ ወደ ማጡም እንዳይሆን መክረናል፡፡

Postby ቆቁ » Fri Feb 23, 2018 4:15 pm

እስቲ እንቀጥል ፡፡
በአንድ ወቅት አቦይ ስብሃት ሲናገሩ " ኢሕዲግ ራሱን ያጠፋል" ብለው ነበር ፡፡
ምን ማለታቸው ነው ብዬ መመራመሬን ፡ መፈላሰፌን አላቆምኩም ነበር ፡፡
ኢሐዲግ ያልፈጠረው ነገር የለም ብዬ ፍልስፍናዬን ልጀምር ፡

ብርሃኑ ነጋን የፈጠረው ኢሐአዲግ ነው እንዲሰደድም ያደረገው ኢሐአዲግ ነው

ጃዋርን የፈጠረው ኢሕዲግ ነው

የኦሮሞን ሕዝብ ንቅናቄ የፈጠረው ኢሕአዲግ ነው

የወልቃይትን ችግር የፈጠረው ኢሕአዲግ ነው

ቅንጅትን የፈጠረው ኢሐአዲግ ነው ፡ እነ ፕሮፌሰር ፡ መስፍንን አስሮ የፈታው ኢሐዲግ ነው

ብርቱካም ሜዴቅሳን የፈጠረ ያሰረ የፈታ ፤ ለብርቱካን ሜዴቅሳ መሰደድ ምክንያት ኢሕአዲግ ነው

ለስዬ አብርሃ መታሰር ፡ መፈታት ከዛም መሰደድ ምክንያት ኢሐአዲግ ነው

ለዋልድባ ገዳም መናጥ ምክንያቱ ኢሐአዲግ ነው

ለኢንቨስትሜንት መፈጠር ምክያቱ ኢሐአዲግ ነው ለገበሬው መባከን ምክንያቱ ኢሐአዲግ ነው

ለቀለበት መንገድ መሰራት ምክንያቱ ኢሐዲግ ነው

በጠቅላላው ለክፉውም ለመጥፎውም መነሳት ኢሐዲግ ነው

ለኮሎኔል ደመቀ መታሰርማ መፈታም መሰረቱ ኢሐዲግ ነው

ለነ እስክንደር መታሰርም መፈታትም መሰረቱ ኢሐአዲግ ነው

ለነ በቀለ ገርባ መታሰርም መፈታትም መሰረቱ ኢሕአዲግ ነው

ከዛም በመቀጠል
ራሳቸውን አቦይ ስብሃት ነጋን ሐፍት በሐፍት ያደረገ ራሱ ኢሐዲግ ነው

ለዚህም ነው እቦይ ስብሃት ነጋ " ኢሐዲግ ራሱን በራሱ ያጠፋል " ብለው በትክክል ያስቀመጡትፈላስፋው
ፈላስፋ ሆኖ ፈላስፋ ያልሆነው፡ ፈላስፋ ሳይሆን ፈላስፋ የሆነው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4044
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: ጣጥፈናል ተናግረናል ፡ ለማስረዳት ሞክረናል ፡ ከድጡ ወደ ማጡም እንዳይሆን መክረናል፡፡

Postby ቆቁ » Mon Feb 26, 2018 6:19 pm

እውነት ውሸት ሆኖ ውሸት ከገነነ
ውሽት እውነት ሆኖ ውሸት ካሳመነ
ፍቅርና ሰላም እንደ ጢስ በነነ

በአንድ ወቅት ክቡራን የሚባል አንድ ወዳጅ እዚህ ዋርካ ላይ ነበረኝ፡፡

አሁን የት እንዳለ ወይም የት እንደገባ አላውቅም፡፡

እንደዚህ ነው ጉዳዩ ፡፡

በጎንደር በወልቃይት በተነሳው ግጭት አቶ በረከት ስምኦን ወደ ቦታው ተጉዘው ነበር ይልና በመጀመር ፡
የጎንደር ሕዝብ ለመከራከር እና ጥያቄው መልስ እንዲያገኝ ለመወያየት ሲጠይቅ

አቶ በረከት ስምኦን " እኛ ከሕዝብ ጋር ልንደራደር አልመጣንም ፡ እኛ የሕዝብ አሽከር ነን " ብለው መመለሳቸውን በማስመር
" እንደዚህ ነው ምሁር ፡ እንደዚህ ነው አዋቂ ማለት " ማለቱ ትዝ ይለኛል

እኔም ፈላስፋው በነገሩ ተገርሜ በጣም ነበር የተደነቅሁት ፡፡

ከትላንት ወዲያ የኮሎኔለ ደመቀን ንግግር ሳዳምጥ ደግሞ ፍልስፍናዬ መጣብኝ

ኮሎኔል ደመቀ " ጥያቄውን ወዴት እንዳደረጉት አላውቅም ያም ሆነ ይህ ጥያቄያችንን የት እንዳደረጉት እንጠይቃለን "ነበር መልሱ

ክቡራን ወንድሜ ብቅ በል እስቲ አሁንስ ምን የምትለው ይኖር ይሆን ?

ዘመኑ የወሬ ሆነና ስንቀባጥር ለነገ አለማለታችን ነው ፈላስፋ ሳይሆን ፈላስፋ ያልሆነው ፡ ፈላስፋ ሆኖ ፈላስፋ የሆነውን የሚያሳዝነው

እውነት በመናገሬ ካቴና ከተሰጠኝ ውሸት ብናገር ምን ይሰጠኝ ይሆን ?
ውሸት በመናገሬ ካቴና ከተሰጠኝ እውነት ብናገር ምን ይሰጠኝ ይሆን ?

እውነትም ውሸትም መናገር አንጻራዊ ነው ?
አንጻራዊ ግን እውነትም ውሸትም መናገር አይደለም፡፡
በሚቀጥለው ወጣቱ ትውልድ
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4044
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: ጣጥፈናል ተናግረናል ፡ ለማስረዳት ሞክረናል ፡ ከድጡ ወደ ማጡም እንዳይሆን መክረናል፡፡

Postby ቆቁ » Fri Mar 02, 2018 7:39 pm

ለምን ለ እኛ ለወጣቶች ስልጣን አታስተላልፉም ነበር ጥያቄዋ ያን ጊዜ ለተሰበሰበው ሕዝብ ስትናገር
የሰማት የለም ያስተዋላትም የለም ሕጻን ነች ወጣት ነች በማለት ይመስላል ለጥያቄዋ መልስ ሳታገኝ ስብሰባው ተዘጋ
ሰመሐር መለሰ ዜናዊ ነበረች ባለፈው እና ለመጀመሪያ ጊዜ ታይታ ይህንን ሐሳብ የገለጸለቸው

ምን ታይቱዋት ነበር በማለት ፈላስፋው ከፍልስፍናው አልወጣም ፡፡

አዎ የእድሜ ባለጸጋ መሆን
ሐብት በሐብት መሆን
በገንዘብ መዋኘት ሆነና ነገሩ

የተነሱበትን ዓላማ እዛው ከተነሱበት ቦታ ጥለው ሌላ ዓላማ ማፈብረክ ጀመሩ
በፍጹም ከኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ የተለየ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር የማይመሳሰል እና ለኢትዮጵያ ሕዝብ የማይጥም ዓላማ ይዘው ገንዘብ ላይ ሙጥኝ ማለትን ጀመሩ
እድሜ ይረሳና እየጃጁ በመምጥታት የያዙትን አለቅም ብለው 90 ዎቹ ውስጥ ሲገቡ የ11 አመት ወጣት የሆኑ የሚመስላቸው ብዙ ናቸው ለምሳሌ ሙጋቤ የቅርብ ምሳሌ ነው

1. የኔ ፍልስፍና ለምን የሰመሐር መለሰ ዜናዊ ጥያቄ ሳይመለስ ቀረ?
2. ሰመሐር ወጣቱ ስትል የትኛው ወጣት ማለቱዋ ይሆን
የእባትን ምክር መስማት ጥሩ ነገር ቢሆንም የልጅን ትንበያ እና ብልህ አመለካከት መናቅ ደግሞ አደገኛ ነው
እንዳልሰሙ ሆኖ ማለፍ ደግሞ ከድጡ ወደ ማጡ ይዘፍቃል
ይላል ፈላስፋው .
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4044
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: ጣጥፈናል ተናግረናል ፡ ለማስረዳት ሞክረናል ፡ ከድጡ ወደ ማጡም እንዳይሆን መክረናል፡፡

Postby ፉኚዶ ተራራ » Sun Mar 04, 2018 3:54 am

የዋርካው ሶቅራጥስ ቆቁ

ሰምሃልም ሆነች የቾምቤ ልጅ ትእግስት መንግስቱ- ስልጣን ማግኘት ከፈለጉ-- ህዝቡን ቀስቅሰው-- ጀንጅነው - አሳምነው ከተመረጡ ጠ/ሚር የማይሆኑበት ምክንያት የለም፡፡ አስመራ ካፌ በረንዳ ላይ ቁጭ ብሎ የሻእቢያን ትራፊ እየለቃቀሙ ግን- ስልጣን ሊገኝ አይችልም፡፡

ወጣት እማዋይሽ ተገኑ ዘለቀ
በእናርጅ- እናውጋ ልዩ ወረዳ- የሲቪክ አገልግሎት መምሪያ ሃላፊ
ፉኚዶ ተራራ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 99
Joined: Wed Jul 17, 2013 6:34 pm
Location: americas

Re: ጣጥፈናል ተናግረናል ፡ ለማስረዳት ሞክረናል ፡ ከድጡ ወደ ማጡም እንዳይሆን መክረናል፡፡

Postby ቆቁ » Sun Mar 04, 2018 5:43 pm

ይገባኛል ፡፡
ባልተወለዱበት ፡ ባልነበሩበት፡ እንደተወለደ ፡ እንደነበረ፡ ታሪክ፡ ማውራት፡ ቢቻል፡ እንግዲህ፡ እንደነዚህ ፡ልጆች፡ ሆኖ ፡መወለድ፡ ነው፡ የሚያስፈልገው፡፡

ይህም፡ ሲባል ፡እነዚህን፡ ጉብሎች፡ መናቅ፡ ግን ፡አያስፈልግም ፡፡ ለልጆች፡ ይታያቸዋልና ፡፡

ሕጻናትን፡ ተዉአቸው፡አትከሉዋቸው፡ ወደኔ፡ ይመጡ፡ ዘንድ፡ ተብሎአልና፡፡

ችግርን ፡የማያውቁ፡ ስለ፡ ችግር፡ ሲያወሩ፡፡

ድህነትን፡ የማያውቁ፡ ስለ፡ ድህነት፡ ሲያወሩ፡፡

ኢትዮጵያዊነትን፡ የማያውቁ፡ ስለ፡ ኢትዮጵያዊነት፡ ሲያወሩ፡ ደግሞ፡ ሌላው፡ የሚገርም ፡ታሪክ፡ ነው ፡፡

የሚያሳዝነው በተወለዱበት በነበሩበት ታሪክ አልፈው ነገር ግን በገንዘብ እና በስልጣን መጋረጃ ዓይናቸውና ጭንቅላታቸው ተጋርዶ የነበረውን እንዳልነበረ ያልነበረውን እንደነበረ ለማስቀመጥ ሲወናጨፉ መመልከቱ ነው ፡፡

ችግራችን ችግር ሆኖ አያለ የሚዲያው ጠረባ ደግሞ በፍጹም እልገባኝም ፡፡

አንድን ፡ቀላልን ፡ዓረፍተ ፡ነገር ፡90፡ ደቂቃ ፡ሙሉ፡ መተንተን ፡፡ከዛም ፡እልፎ ፡ የሆነ፡ ያልሆነውን፡ በመደጋገም ፡መዘበራረቅ፡ ሰላምና፡ ነጻነት፡ ሳይሆን፡ ውዥንብርንና ፡እለመረጋጋትን፡ የሚያመጣ ፡ሆኖ ፈላስፋው፡ ተመልክቶታል፡፡

የወሬ ፡እርማጌዶን፡፡ የሚዲያ እርማጌዶን
ይሉሃል ይህ ነው፡፡

ሌላው ፡ደግሞ፡ በችግር፡ ላይ፡ ችግር፡ ፈጥረው፡ ፎቶ፡ ለመነሳት፡ ጸጉራቸውን፡ የሚያበጥሩት፡ ናቸው፡ የማይገቡኝ፡ ለዛውም ፡ጥርሳቸውን፡ ፈገግ፡ በማድረግ ፡፡

የቁንጅና፡ ውድድር፡ ሆነ፡ እንዴ፡ የሐገራችን፡ ችግር ?

ፈላስፋ ሆኖ ፈላስፋ ያልሆነው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4044
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: ጣጥፈናል ተናግረናል ፡ ለማስረዳት ሞክረናል ፡ ከድጡ ወደ ማጡም እንዳይሆን መክረናል፡፡

Postby ቆቁ » Sat Mar 10, 2018 1:10 pm

ችግራችን ሶስት ነው
1. የሚዲያ እርማጌዶን
2. የመሪዎቻችን የበስተሁዋላ ጣጣ
3. የተቃዋሚዎች መፍትሄ አልባ መንግስት

በነዚህ በሶስት ነጥቦች ብንፈላሰፍበትስ ? ብሎ ፈላስፋው እንደሚመለስበት ይፈላሰፋል

ፈላስፋው አዲስ የሆነበት ነገር ፡

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስለ ሐገራችን አጥብቀው ማስረዳታቸው ፈላስፋውን በጣም ነው የደነቀው፡፡
ደግ ሰው አይጥፋ ይላል ፈላስፋው
ደግ መንግስት ይኑር ይላል ፈላስፋው

ነገር ግን በእውነት በኢትዮጵያችን እና በመሪዎቻችን መካካል እንደዚህ ያለ እውቀት ያለው ሰው ጠፍቶ ነው እሳቸው ይህንን ሁላ ሐገር አቁዋርጠው ሐሳብ እንዲሰጡ የተደረገው ?

እሳቸው የእሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሪዎቻችን እስኪማጠኑ ድረስ መሪዎቻችችን ምን ነካቸው ?

በነገራችን ላይ ሰላም ሰፈነ ወይስ ?

ለመሆኑ ሰላም አልነበረም እንዴ ?

አገጩን ይዞህ የሚያዝነው ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4044
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: ጣጥፈናል ተናግረናል ፡ ለማስረዳት ሞክረናል ፡ ከድጡ ወደ ማጡም እንዳይሆን መክረናል፡፡

Postby ቆቁ » Thu Mar 15, 2018 9:40 pm

ጥይት የተሰራው ሰላምን ለማምጣት ሳይሆን ሰላምን ለመበጥበጥ እኮ ነው፡፡
ጥይት ለፍቅር የሚሆን ስጦታም እይደለም፡፡
ጥይትን ሲሰሩ ሰዎች ፈነጠዙ
ጥይትን ሲተኩሱ ሰዎች አለቀሱ
ይህ ሁኔታ እስከ አሁን ድረስ ሰዎች ሊገባቸው ባለመቻሉ እሁንም ይተኩሳሉ አሁንም ይፈነጥዛሉ እሁንም ያለቅሳሉ
ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4044
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: ጣጥፈናል ተናግረናል ፡ ለማስረዳት ሞክረናል ፡ ከድጡ ወደ ማጡም እንዳይሆን መክረናል፡፡

Postby ቆቁ » Wed Mar 28, 2018 9:17 pm

ለጠቅላላው ችግር ምክንያት የሆነው ማነው ? እሱ ነው ፡፡
እኛ ለችግሩ ምክንያት ብንሆንም የችግሩ ምክንያት ማነው ? እሱ ነው
እኛ ለችግሩ ምክንያት መሆናችንን ቢያውቅም እሱ ነው የችግሩ ምክንያት
የችግሩን ምክንያት እኛ መሆናችንን ከተናገረ እሱ ነው የችግሩ ፈጣሪ
ችግሩን እኛ ብንፈጥረውም ለችግሩ ፈጠራ ዋናው ምክንያት እሱ ነው
እሱ ነው ፡ እሱ ነው ፡ እሱ ነው፡
እኛ እንደ ጲላጦስ ነን ፡፡ ችግሩን የፈጠረው እሱ ነው እኛ ችግሩን ፈጥረን ብንፈጥረውም
ወይ የዘመናችን ቁዋንቁዋ
ፈላስፋው ቆቁ
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4044
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: ጣጥፈናል ተናግረናል ፡ ለማስረዳት ሞክረናል ፡ ከድጡ ወደ ማጡም እንዳይሆን መክረናል፡፡

Postby ቆቁ » Sun Apr 01, 2018 8:08 pm

በሐገራችን ሰላምና ስልጣን ሁለት " ወንድማማቾች" ናቸው ፡፡

በሐገራችን ሰላም ይመጣል ተብሎ የሚታሰበው በጠመንጃ ነው
በሐገራችን ስልጣንን ለመያዝ የሚታሰበው በጠመንጃ ነው ፡፡

ሰላምን ለመፍጠር ጠመንጃ ፤
ሰላምን ለመበጥበጠጥ ጠመንጃ፤

ስልጣንን ለመያዝ ጠመንጃ ፤
ስልጣንን ለመልቀቅ ጠመንጃ ፤

ያ ዘመን አልፎ
ስልጣን በሰላም ፤ ሰላም በውይይት፤ የሚተካበት ዘመን ይመጣ ይሆን ?

ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4044
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Next

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest