በኢትዮጵያ ትክክለኛ ለውጥ ሊያመጣ የሚችለው ሕዝብ ብቻ ነው!!!

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

በኢትዮጵያ ትክክለኛ ለውጥ ሊያመጣ የሚችለው ሕዝብ ብቻ ነው!!!

Postby ኳስሜዳ » Tue May 15, 2018 3:01 pm

ወያኔ የኢትዮጵያን ሕዝብ ለማወናበድ እንዴት ቆርጦ ተነሥቷል ባካቹህ???

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ትናንትና “የለውጥ እንቅፋት ነው!” በማለት የብሮድካስቲንግ (የሥርጭት) ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር (መሪ) ዘርዓይ አስገዶምን አባረሩ መባሉን ሰማን፡፡ ከዚያ አስቀድሞ አቶ ዐባይ ፀሐዬ ታገደ ብሎ ወሬ አናፍሶ ነበረ፡፡

ዛሬ ደግሞ የውጭ ግንኙነት ስትራቴጂክ (ስልት) ጥናት ኢንስትቲዩት (ማዕከል) ዋና ዳይሬክተር ጀነራል (ጠቅላይ መሪ) የሆኑትን አቶ ስብሐት ነጋን (አቦይ ስብሐትን)፣ ዶ/ር (ሊ.ማ) ካሱ ኢላላን ከፖለሲ (መመሪያ) ጥናትና ምርምር ማዕከል፣ አቶ በለጠ ታፈረን ከተቀናጀ የመሬት አጠቃቀም አቅድና ፖሊሲ (መመሪያ) ዝግጅት ፕሮጀክት (አቅደ ሥራ)፣ አቶ ታደሰ ኃይሌን ከንግድና ኢንዱስትሪ (ምግንባብ) የፖሊሲ (መመሪያ) አቅድ አፈጻጸምና ክትትል፣ እና አቶ መኮንን ማን ያዘዋልን ከፖሊሲ (መመሪያ) ምርምር ማዕከል በጡረታ እንዲያርፉ ማድረጋቸውን ዶ/ር (ሊ.ማ) ዐቢይ አሕመድ በጽ/ቤታቸው በኩል ገልጸዋል ተብሏል፡፡ በቀጣይም ረጅም ጊዜ በመንግሥት ኃላፊነት ቦታዎች ላይ ያገለገሉትን እንዲያርፉ የማድረጉ ሥራ ይቀጥላልም ብለዋል ተብሏል፡፡

እኔ የምለው ጠ/ሚ ዐቢይ ይሄንን ያህል ሥልጣንና ጡንቻ ካላቸውና ለለውጥ ቁርጠኛ ከሆኑ፣ ለሕግ የበላይነት መረጋገጥ ከተነሡ፣ ተጠያቂነትን ለማስፈን ከጨከኑ፣ ሙስናንና የአሥተዳደር ብልሹነትን ለመዋጋት ከወሰኑ፣ ለሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ (መስፍነ ሕዝባዊ) መብቶች መከበር ከቆሙ ምነው ታዲያ ካቢኔያቸውን (ሸንጓቸውን) ሲያዋቅሩ በሕዝብ ላይ አረመኔያዊ ግፍ የፈጸሙትን መልሰው ሾሟቸው??? ከግሞስ በፈጸሙት የሀገር ክህደት፣ ግፍ፣ ወንጀልና ሙስና ተጠያቂ እንዲሆኑ ማድረግ አለብዎት እንጅ ከዘረፉት በላይ የተቀናጡ (ቪላ) ቤቶችና መጦሪያ በመንግሥት ወጭ ተሰጥቷቸው እፎይ ብለው የሚኖሩበትን ዕድል መስጠቱ ነው እንዴ ፍትሑ፣ ለውጡ፣ ተጠያቂነቱና ቁርጠኝነቱ???

ቀሪ እጅግ በርካታ የፖለቲካና የሕሊና እስረኞችስ ለምን በሙሉ እንዲፈቱ አልተደረገም??? “በጡረታ ማሳረፍ!” የተባለው ነገርስ ምነው “ጄኔራሎቹን” (ራሶቹን) እና ሌሎች የጦር አለቆቹን ሳያካትት ቀረ??? በእነ ኤፈርት የወያኔ ሕገወጥ የዝርፊያ ድርጅቶችና የብዙኃን መገናኛዎች ላይስ ለምን ውሳኔ ሳያስተላልፉባቸው ቀሩ??? “በቀጣይ እርምጃ ይወሰድባቸዋል!” ልትሉን ነው ወይስ ይሄ ፈጽሞ የማይታሰብ ነገር ነው???

ስለሆነም ይህ ድርጊት የወያኔ ሕዝብ የማወናበጃ ተግባር እንጅ ትክክለኛና ቁርጠኛ የለውጥ እርምጃ አይደለም!!! ትክክለኛው ለውጥ ሊመጣ የሚችለው በኢትዮጵያ ሕዝብ ብቻና ብቻ ነው!!!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2212
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Re: በኢትዮጵያ ትክክለኛ ለውጥ ሊያመጣ የሚችለው ሕዝብ ብቻ ነው!!!

Postby እሰፋ ማሩ » Tue May 15, 2018 7:28 pm

ህሊና ያለው የሚመሰክረው ለውጡ ህዝባችን በተለይ ወጣቱ ህይወቱን ከፍሎ የተገኘ ነው፡፡ዶ/ር አብይ ከግፈኛ ድርጅት በቅለው ይህን ማሳየታቸው የሚደገፍ እንጂ ይህ ጽንፈኛ በየጊዜው የሚሰጠው ትችት ተገቢ አይደለም፡፡ከአፓርታይድ የበቀለው ዴክለርክ ከሶቪየት የተገኘ ጎርቫቾቭ ይህን ያህል ለውጥ ያለማድረጋቸው ስለሚታወስ ይህን ነቃፊ አደብ ግዛ ማለት የግድ ነው፡፡ሌላ ትግል ካለህ ወይ በሱዳን ያለበለዚያ በኤርትራ ግባና ከመሰሎችህ ጋር ሞክር ቅቅቅ
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1550
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm

Re: በኢትዮጵያ ትክክለኛ ለውጥ ሊያመጣ የሚችለው ሕዝብ ብቻ ነው!!!

Postby ኳስሜዳ » Thu May 17, 2018 1:30 pm

አሰፋ! የስደት ኑሮ ሰልችቶህ እንደነ ሌንጮ ለታ አገር ቤት መግባት ካማረህ መንገዱን ጨርቅ ያድርግልህ ምንም ምክንያት ሳታበዛ ሹልክ ብለህ መግባት ነው ኩርጥና ክትፎ ይጠብቀሃል! በተረፈ ትግሉን ለመጀመር መች አዲስ ሆንኩና ነው ካንተ ማእዘኑ ከጠፋበት ሰው ምክር የምፈልገው፡፡ ወደድክም ጠላህም ወያኔ የሚወድቀው በትጥቅ ትግል ብቻ ስለሆነ የትጥቅ ትግሉ በሰሜን ጀምሮ ወደ ሌላው ክፍል በመዛመት እንደሚጠናቀቅ እስረግጬ እነግርሃለሁ፡፡ ለጠቅላላ እውቀት እንዲሆንህ አብዮት ስልጣን ከያዘበት ግዜ ጀምሮ፣

በአማራ ብሔር ላይ ያነጣጠር ጥቃት ቀጥሉዋል፣

በቤንሻንጉል ዘር ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ሳይቆም በጂማ ሊሙ ሦስት አማሮች ሌሊት ላይ በገጀራ ታርደው መገደላቸውን ምንጮቻቸውን ጠቅሰው የአማራ አክቲቪስቶች ይፋ አድርገዋል።

በጂማ ሊሙ ዛሬ የሚከበረውን የክርስቶስ እርገት ለማክበር በማታ ወደ ጨንጊ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን በመጓዝ ላይ የነበሩ ሦስት የአማራ ብሔር ተወላጆ በገጀራ ታርደው ሕይወታቸው ሲያልፍ አንድ ሌላ በጽኑ ቆስሎ ሆስፒታል ገብቱዋል።አንድ ሰው በከባድ ጉዳት ሕክምና ገብቷል፡፡ ይህን መሰሉ ጥቃት አዲስ አለመሆኑን ያስታወሱት አክቲቪስቶች በ1999 ዓም በርካታ አማሮች በሻሻ አቦ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በገጀራና በእሳት መገደላቸውን በምሳሌ ጠቅሰዋል።

ትናንት በተፈጸመባቸው የጭካኔ እርምጃ ሕይወታቸው ያለፈው ሶስት ሰዎችን በስም ጠቅሰው ይፋ አድርገዋል። እነዚህም አስማማው አማረ ፣መርሻ መኮንን እና መኳንንት የተባሉ መሆናቸውን ጠቅሰው የቆሰለው ብርሀኑ ጌቱ ደግሞ በከፍተኛ ሁኔታ ጉዳት ደርሶበታል ትብሉዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በቤንሻንጉል ክልል ትልልንት በአሰቃቂ ሁኔታ በስለት ተወጋግቶና ተሰልቦ ጉዳት የደረሰበት የ14 ዓመቱ አቸፈር ላይ ከተወሰደው በተጨማሪ ዛሬም በአማራ ተወላጆች ላይ ድብቅ ጥቃት ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን በቀስት እየተወጉ የሞቱና ዐይናቸው የፈሰሰ መኖራቸውን የመረጃ ምንጮቻቸውን ጠቅሰው ጽፈዋል።

በደቡብ ኢትዮጵያ በጌዴኦ ዞን አጎራባች በኦሮሚያ ክልል የምዕራብ ጉጂ ዞን ከ ሁለት መቶ ሺ ሚሊዮን በላይ የሆኑ የጌዴኦ ብሔር ተወላጆች በግፍ ተፈናቅለዋል፣

በሶማሌ ክልል በቀጠለው ተቃውሞ በፊቅ ዞን በሁለት ከተሞች 11 ሰዎች ተገድለዋል፣

በዚህ አጋጣሚ የወያኔንና እንደ አብዮት ያሉ ተላላኪዎች ሴራ በቅርቡ እርቃኑን ይወጣል፡፡


እሰፋ ማሩ wrote:ህሊና ያለው የሚመሰክረው ለውጡ ህዝባችን በተለይ ወጣቱ ህይወቱን ከፍሎ የተገኘ ነው፡፡ዶ/ር አብይ ከግፈኛ ድርጅት በቅለው ይህን ማሳየታቸው የሚደገፍ እንጂ ይህ ጽንፈኛ በየጊዜው የሚሰጠው ትችት ተገቢ አይደለም፡፡ከአፓርታይድ የበቀለው ዴክለርክ ከሶቪየት የተገኘ ጎርቫቾቭ ይህን ያህል ለውጥ ያለማድረጋቸው ስለሚታወስ ይህን ነቃፊ አደብ ግዛ ማለት የግድ ነው፡፡ሌላ ትግል ካለህ ወይ በሱዳን ያለበለዚያ በኤርትራ ግባና ከመሰሎችህ ጋር ሞክር ቅቅቅ
Last edited by ኳስሜዳ on Thu May 17, 2018 4:43 pm, edited 1 time in total.
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2212
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Re: በኢትዮጵያ ትክክለኛ ለውጥ ሊያመጣ የሚችለው ሕዝብ ብቻ ነው!!!

Postby እሰፋ ማሩ » Thu May 17, 2018 1:58 pm

ኳስሜዳ
ለህዝባችን የተፈጠረውን አጋጣሚ በመጠቀም የወያኔን የከፋ የግፍ አገዛዝ መፋለም ከግለሰብ የህይወት ምርጫ ንየተለየ ነውና ወደሃገርቤት መመለስን ከሚሰጠው ተጨባጭ ምክር ጋር ባታያይዝ ይመረጣል፡፡ያቀረብኩት ሰአሊ አምሳሉ በሚል በተከታታይ የወቅቱን በጎ ነገሮች ሳያገናዝብ ለሚተች ሲሆን አሱ አንተ ከሆንክም መልካም፡፡ስለትግሉ በበረባሶ ደርጉን ስፋለም ወያኔንም በዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ላይ ጭፍቸፋ ካደረገበት ጀምሮ ከጉዋዶቼ ጋር ስዋጋ ቆይቼ ለስደት ስለበቃሁ ይህን መባሌ የሚያስደንቅ አይደለም፡፡የዶር አብይን መልካም ጅማሬ መቀበሉ ህሊና ያላቸው መሪዎች ከውጭ ኦባንግ ሜቶ ሻለቃ ዳዊት ፕሮፌሰር አል ፕሮፌሰር መሳይና ሌሎቹም ከሃገር ቤት ፕሮፌሰር መስፍንና የተቀሩት የተቀበሉትን በዚህ ግለሰብ ስለተተቹ በኔ መደገሙ አይገርመኝም፡፡ በዶ/'ር አብይ ጅማሮ ማንም ቅን ህሊና ያለው የሚገነዘበውን በጎ ነገር መደገፍ 'ሃገር ቤት ናፈቀህ ክትፎ አማረህ' ብሎ መተቸት በጣም ያስቃል፡፡ሃገር ቤት ያለው ህዝባችንና የዶ/ር አብይ አመራር ችግሮቹን በሚገባ በመረዳት የተዘራውን የዘር ጥላች ሲነቅሉ በማየት ላይ ነን፡፡ ይህ ተሳክቶ ሃገራችን መልካም ደረጃ ትደርሳለች የሚል ተስፋ አለን፡፡በተረፈ ለኢትዮጲያ የ100 አመት የቤት ስራ ሰጠሁ ያለ የራሱን ህዝብ በሰቆቃ የሚያሰቃይ ኢሳያስ አፈወርቂ ፕሮጀክት ተዋናዮች ሃገራችን ይደግፋሉ ብለን አንጠብቅም፡፡ የየዶ/ር አብይን በጎ ስራ መደገፋችን ይቀጥላል አብረን 'ኢትዮጲያ ለዘላለም በክብር ትኑር' እንላለን፡፡
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1550
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests