ግርማይ ሐድጎ(ጥቅምት ፳፱ ቀን ፲፱፻፳፩—ግንቦት ፲፭ ቀን ፳፻፲ )

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ግርማይ ሐድጎ(ጥቅምት ፳፱ ቀን ፲፱፻፳፩—ግንቦት ፲፭ ቀን ፳፻፲ )

Postby ዘርዐይ ደረስ » Fri May 25, 2018 6:16 pm

ዝነኛው የዘፈን ግጥምና ዜማ ደራሲ ሻለቃ ግርማይ ሐድጎ በተወለዱ በ፹፱ ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።የክብር ዘበኛ ኦርኬስትራ አባል በነበሩበት ወቅት ለጥላሁን ገሠሠ፣ለማህሙድ አሕመድ ለብዙነሽ በቀለና ሌሎችም ድምፃውያን በርካታ ዜማዎችና ግጥሞች መስጠታቸው ይታወቃል።
Last edited by ዘርዐይ ደረስ on Sun May 27, 2018 2:28 pm, edited 1 time in total.
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1175
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: ግርማይ ይሕደጎ (ጥቅምት ፳፱ ቀን ፲፱፻፳፩—ግንቦት ፲፭ ቀን ፳፻፲ )

Postby እሰፋ ማሩ » Sat May 26, 2018 9:10 pm

ዘርአይ ተከታታይ ተመሳሳይ ዝክሮችህን አደንቃለሁ፡፡የሞተ መውቀስ ባህላችን ባይሆንም ግርማ ሃድጎ ሚሲቱን ልጆቹን ጥሎ ኤርትራ ስትገነጠል የኮበለለ 'የናጽነት' ተብዬ ብሄራዊ መዝሙራቸውን ያቀናበረም መሆኑ ቢወሳ ነውር ይሆን?ሞት አይቀርም ስም አይቀበርም ሆነና ታላቁን የሃገራችን ዘመናዊ ሙዝቃ አቀናባሪ ተስፋዬ ለማን በዘከርንበት እሱንም ለሃገራችን ሙዚቃ እድገት ያደረገውን ማውሳቱ ተገቢ ነው፡፡
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1550
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm

Re: ግርማይ ሐድጎ(ጥቅምት ፳፱ ቀን ፲፱፻፳፩—ግንቦት ፲፭ ቀን ፳፻፲ )

Postby ዘርዐይ ደረስ » Sun May 27, 2018 2:26 pm

እሰፋ ማሩ
አንተ እንደምትለው ቢሆን ኖሮ አሜሪካ ያሉት ልጆቻቸው እንዴት አብረዋቸው ለመኖርና እስከ መጨረሻው ሊንከባከቧቸው ቻሉ?አእንደ ሰማሁት ከሆነ የቀብር ሥነ ሥርዐታቸውም የተፈፀመው እዚያው ዩ∙ኤስ∙ኤ (ፊኒክስ አሪዞና) ነው።የተሳሳተ መረጃ ደርሶህ እንዳይሆን። በነገራችን ላይ የአባታቸውን ሥም አሳስቼ ነበር።ያንተን ሳይ ነው ትዝ ያለኝ።ይሕደጎ ሳይሆን ሐድጎ ነው።ፀሐይቱ በረከትም በያዝነው ሳምንት አርፋለች።
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1175
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: ግርማይ ሐድጎ(ጥቅምት ፳፱ ቀን ፲፱፻፳፩—ግንቦት ፲፭ ቀን ፳፻፲ )

Postby እሰፋ ማሩ » Sun May 27, 2018 10:18 pm

ዘርአይ
ሻለቃ ግርማይ ወያኔ አዲስ አበባ ሳይገባ ወደኤርትራ ሄዶ የሻቢያ ሌላው ፈጣሪ ወልደአብ ወልደማሪያምን ከስደት ተቀብሎ በኤርትራ ከሃያ አመታት በሁውላ ቆይቶ በቅርቡ ወደአሜሪካ የገባው በእድሜና በጤና ችግር ነው፡፡ዋርካ ኢትዮጲያዊነትን ያልካዱትን ስትዘክር ደስ ይላል ግርማይ ሃድጎ ግን ኢትዮጲያን ከቶ አላሰባትም አላከበራትም፡፡ሆኖም ግን ለኢትዮጲያ ፍቅርና ክብር የሚታይባቸው በረከት መንግስተአብ የመሰሉትን ከኤርትራ ባለፈው በማየታችን ደስ ብሎናል፡፡ግርማ ልኡል የሚባል የሙዚቃ ሰው ለምን ግርማ ሃድጎ ሚስቱንና ልጆቹን ትቶ ወደ ኤርትራ ሄደ ተብሎ ሲጠየቅ 'ግርማ ሚስቴም እናቴም ቤተሰቤም ኤርትራ ነች ብሏል' ይል ነበር፡፡የግርማ ሚስት ጥሩነሽ ይመር የድሮ ክብርዘበኛ ተወዛዋዥ ብቻዋን በቺካጎ ነበረች ከብዙ አመታት በሁውላ ቤተሰቡ ሲቀላቀል የዘመሩትና የመሰከሩት ቀጥሎ ይታያል፡፡ሌላዋ ከያኒ ጸሃይቱ ባራኪ ቋቲ በምትባል የኤርትራ መንደር ጎንደር ድንበር ላይ ተወልዳ በጎንደር ያደገች በሱዳን በኩል ሆላንድ ገብታ ለኤርትራ መገንጠል የተፋለመች ነች ስለኢትዮጲያችን ያለችውን ምንም ስላላየሁ የምለው የለኝም፡፡
https://www.youtube.com/watch?v=yS1jnxDusMw
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1550
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm

Re: ግርማይ ሐድጎ(ጥቅምት ፳፱ ቀን ፲፱፻፳፩—ግንቦት ፲፭ ቀን ፳፻፲ )

Postby ዘርዐይ ደረስ » Sat Jun 02, 2018 8:30 pm

እንደጠረጠርኩት የተሳሳተ መረጃ ነው ያቀረብከው።
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1175
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia


Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest