ይድረስ ለክብረመንግስትና አካባቢው ልጆች!!!

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

Re: ይድረስ ለክብረመንግስትና አካባቢው ልጆች!!!

Postby ራስብሩ » Fri Sep 02, 2016 11:07 am

የጌታ ሰላም ከሁላችሁ ጋር ይሁን !
በዚህች ምንም ተስፋ ባልነበረኝ ቤት ውስጥ እንደገና መገናኘት መቻላችን ከምንም በላይ አስደስቶኛል ፡፡
ሰውነታችንን የረጋ መንፈስ ባልተሰማው ይልቁንም ክፉና የስነልቦናም ሆነ አካላዊ ድቀት እየደረሰብን ባለንበት አስቀያሚ ጊዜ ላይ ብንሆንም ቅሉ ጌታ መልካምን ነገር እንድናወራ እንድንወያይና የተቻለንንም እናደርግ ዘንድ የፈቀደበት ጊዜ ይህ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡

ለዋርካ እዘጋጆች ልባዊ ምስጋናችን ይድረሳቸው
አንፈራራ
አደቆርሳ
ባለሱቅ
ሞፊቲ
ሽልንግዬ
የግል
ቅሩንፉድ
ጎሳ እና ሌሎችም
ቤታችን እድሳትዋ አልቆ አገልግሎት ጀምራለችና ምርቃት ተጠርታችሁዋል !
ራስብሩ
This is Ras Biru Woldegebriel.......................!!

http://www.oyla22.de/userdaten/406/6554 ... s_Biru.jpg
ራስብሩ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 785
Joined: Thu Aug 25, 2005 6:49 pm

Re: ይድረስ ለክብረመንግስትና አካባቢው ልጆች!!!

Postby anferara » Sun Sep 04, 2016 2:40 pm

በስም እብ ከስንት ጊዜ በኋላ ተከፈተ? ራስ ብሩ እናመሰግናለን ስለ ቤቱ መከፈት ስለነገርከን፡፡

ነገር የተበላሸው ግን ድሮ ነው፡፡ ባለቤቶቹ ብዙ ጊዜ ነገሮችን እንዲያስተካክሉ ሲለመኑ፣ እሻፈረን ብለው ብዙ ደምበኞቻቸውን አጡ፣ እብዛኞቹንም ለፌስቡክ እስረከቡ፡፡ አሁን እነዚያን ሰዎች እንደገና ለመመለስ ከባድ ነው፡፡

አንድ ሰው ንግድ ስራ ውስጥ ከገባ ነቅቶ መስራት እለበት እንጂ በያዝ ለቀቅ የሚሆን እይደለም፡፡ የያዙትን ያስመልጣሉ ማለት ነው፡፡

ለማንኛውም የክብረ መንግስት ልጆች እንደምን ናችሁ፣ ሰላም ከናንተ ጋር ይሁን፡፡
anferara
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 445
Joined: Wed Sep 27, 2006 5:06 pm

Re: ይድረስ ለክብረመንግስትና አካባቢው ልጆች!!!

Postby አደቆርሳ » Sun Sep 04, 2016 5:57 pm

ቸርነቱ የማያልቅበት እግዚአብሄር ይመስገን እኔ በጣም ደህና ነኝ
ከአመታት በኋላ በሰላም መገናኘት መቻል በጌታ ፈቃድ ነውና ክብሩ ከፍ ይበል፤፤
አንፈራራችን ስምህን ሳይ ደስስስ አለኝ አልፎ አልፎም በፌስ ቡክ እመለከትሃለሁ
ራስ እንደምን አለህ ? ስላንተ ወሬም እሰማለሁ ያው በወሬው ቤትም እመለከትሃለሁ እናንተን ብቻም አይደለም ሁላችሁንም ማለት ይቀለኛል፡፡
መቼም በዚህ ጊዜና ወቅት ሌላ የምናወራበት ሁኔታና ሁኔታ የሚኖር አይመስለኝም ምክንያቱም ሃገራችን በታላቅ ህመም ላይ ትገኛለች፡፡
ዛሬ ከምሽቱ 2 ሰአት ሲሆን ቴሌቪዥን ተመልከቱ በመንግስት በኩል መከፋፈል የተፈጠረም ይመስላል፡፡
የኢትዮጵያ ህዝብ ያለበትንና የሚፈልገውን በትክክል የምታውቁ ዲያስፖራዎች እጅግ ትልቅ ትዝብት ላይ ወድቃችኋል
አኔ በበኩሌ Shame on you ዲያስፖራውያን እላለሁ
ጊዜና ጥሩ መንፈስ አጠራቅሜ ብቅ እላለሁ
ቸር ያቆየን
Image
kibremengist
አደቆርሳ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 977
Joined: Wed Aug 03, 2005 5:50 pm
Location: ethiopia

Re: ይድረስ ለክብረመንግስትና አካባቢው ልጆች!!!

Postby ራስብሩ » Thu Sep 08, 2016 9:19 am

ጤና ይስጥልኝ
በምንሰማው የእስር ቤቱ እልቂት ባጠቃላይ የሃገራችን ሁኔታ በጣም እጅግ በጣም አዘንኩ በዚህ ሁኔታ እስከመቼ መኖር እንደምንችል አላውቅም
እግዚአብሄር ትዮጵያን አደራ !!!
This is Ras Biru Woldegebriel.......................!!

http://www.oyla22.de/userdaten/406/6554 ... s_Biru.jpg
ራስብሩ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 785
Joined: Thu Aug 25, 2005 6:49 pm

Re: ይድረስ ለክብረመንግስትና አካባቢው ልጆች!!!

Postby ባለሱቅ » Fri Sep 23, 2016 4:51 pm

ዋው
ዛረ ገና ፓስ-ዎርዴን እገኘሁት
እንደምን ከረማቹልኝ ያገሬ ልጆች

የዛረ ሳምንት አላባ ነበርኩ... ከአላባ ሽማግለዎች የሰማሁትን ...ቁምነገር ይዤ ስክመጣ በሰላም በፍቅር ቆዩኝ
እሁን ትንሽ ጉዳይ እለችኝ ... ሸዋ-ሮቢት
እስከዚያው
ቸር ሰንብቱ
ከባንኮኒ ስር... ባለሱቅ
ባለሱቅ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1288
Joined: Mon Sep 27, 2004 6:20 am
Location: ethiopia

Re: ይድረስ ለክብረመንግስትና አካባቢው ልጆች!!!

Postby ባለሱቅ » Mon Nov 14, 2016 10:50 am

ማንንም ሳላስፈቅድ ከፈስ-ቡክ ኮፒ እድርገ ልጥፍ

ሰሙ ንጉስ ተባረክ እቦ

ለኛም ሰላምታ እቅርብልን ለሁሉም

አስደሳች ቅዳሜ(በሰሙንጉስ ገበየሁ)
ጥቅምት 26 ቀን 2009 ዓ.ም ( ኖቪምበር 26 ቀን 2016) በዘገየ ሀይሉ አነሳሽነት በደረጀ አምባዩ መኖርያ ቤት በቁጥር 15 የምንሆን ልጆች ተገናኝተን አስደሳች ግዜ አሳልፈናል፡፡ በውነቱ አብዛኛዎቻችን የተገናኘነው ከ30 እስከ 40 ከሚሆን ቆይታ በሃላ በመሆኑ የነበረው ስሜት እጅግ የሚገርም ነው፡፡ በወቅቱ የነበረውን ድባብ በመጠኑ ይህን ይምስል ነበር፡፡
ብዙዎቻችን በመልክ ተረሳስተናል ማለት ይቻላል፡፡ አንድ ሰው ወደ ቤት ሲገባ ማን ማን እነድሆነ ይጠየቃል፡፡ ከብዙ መደናገር በሃላ ሲለይ መቆጣጠር ያቅተዋል፡፡ ቤቱ በጩህት ይናወጣል፡፡ እንዲህ እንዲህ እያለ ከ40 ዓመት በፊት የነበሩ የእየአንዳንዳችን ባህሪ የልጅነት ተንኮሎች የቅፅል ስሞቻችን እየተነሱ ሳቁ ይቀልጣል፡፡ በእውነቱ ያለማጋነን እጅግ ስሜታዊ ከመሆናችን የተነሳ መደማመጥ እንኳን አልቻልንም ወደ እዚያ ዘመን የልጅነታችን ባህሪ ተመልሰን ነበር ማለት ይቻላል፡፡ በአጭር አገላለፅ 30 እና 40 ዓመት የነበረንን ህይወት ተመልሰን ለ 3 ሰዐት ያህል ኖረን ተለያየን ማለት ይቻላል፡፡ ምክንያቱም እያንዳንዱ የሚጠቀመው የቃላት አጠቃቀም ሳይቀር የዚያን ዘመን የሚያስታውስ ነው፡፡ ድባቡ በጥቂቱ ይህን የመስል ነበር ነገር ግን ሙሉ ድባቡን ለመግለፅ በእወነቱ ከእኔ አቅም በላይ ነው፡፡ በነገራችን ላይ አንዳንዶቾ የመጡት ቀድሞ ተነግሯቸው ሳይሆን እዚያው በዝግጅቱ ላይ እያለን ተደውሎላቸው ሰሜታቸውን መቆጣጠር ስላልቻሉ ከአዲስ አበባ ጥግ ተነስተው የመጡም ነበር፡፡ አንዳነዶቹም በሞባይል ማይክሮፎን በመጠቀም መልዕክቶች አስተላልፈዋል፡፡
ስብሰባው በዚህ ብቻ አልተጠናቀቀም በቀጣይ ሌሎች በዚህ ዝግጅት ያልተገኙ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችንን አካቶ ዘሌቄታ ባለው መልኩ መገናኘት ስለሚቻልበት ሁኔታ ውይይት ተደርጎ ከስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡
በነገራችን ላይ ይህን ሃላፊነት በግል የወሰድኩ ሲሆን በቅርቡ ድራፍት መተዳደርያ እያዘጋጀሁ ሲሆን እንዳለቀ ይህው እንደተጠናቀቀ እያንዳንዱ አስተያየት እንዲሰጥበትና እንዲያዳብረው ይደረጋል፡፡
ለመነሻ እንዲሆን ማህበሩ ከዚህ የሚከተል መልክ እንዲኖው ታስቧል፡፡
1. የማህበሩ አላማ፣
 ማህበሩ በተለምዶ እንደሚደረገው በሞት ወቅት የእድር አገልግሎት መስጠት ብቻ ሳይሆን በዋናነት በህይወት እያሉ መገናኘትነ አንድነትን ማጠናከር፣ መረዳዳት እንዲሁም ከተቻለ ለተወለድንበት አካባቢ ቋሚ የሆነ የሙያም ሆነ የገንዘብ አስተዋፅኦ ማበርከት ነው( ዝርዝሩ በደንቡ ላይ በተብራራ ሁኔታ የሚገለፅ ይሆናል)
2. የማህበሩን አወቃቀር በተመለከተ፣
 ማህበሩ ዋና አድራሻ አዲስ አበባ ሲሆን ከሀገር ውስጥ በተጨማሪ የሚከተሉት ቅርንጫፎች የኖሩታል፡፡
 የሰሚን አሜሪካ ቅርንጫፍ
 የአውሮፓ ቅርንጫፍ
3. የገንዘብ ምንጭ፣
 የእያንዳንዱን አቅም ባገናዘበ መልኩ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚኖሩ አባለት ወርሃዊ መዋጮ ይኖረዋል፡፡
 ለዚህም የሚሆን ከ3 ባላነሱ አባላት (ሴት እህቶቻችን በዋናነት ያካተተ) የሚንቀሳቀስ የባንክ አካውንት የሚከፈት ሲሆን የእራሱ የሆነ ሂሳብ ሹም እና አዲተር ይኖረዋል፡፡
4. የግንኙነት ሁኑታ፣
 ግንኙነታችን በአመት 2 ግዜ ሲሆን በአመት አንድ ግዜ በአውሮፓ፣ በሰሜን አሜሪካና በሌሎች የአለማችን ክፍሎች የሚኖሩ ወንደሞቻችንን አመቺ ግዜ በዋናነት ከግምት ውስጥ ያሰገባ ይሆናል፡፡
ከላይ የገለፅኩት አጠቃላይ ሁኔታውን ለማሳየት በመሆኑ የመተዳደርያ ደንቡ ድራፍት ወደፊት በታቻለ አቅም በየአድራሻችሁ እንዲደርሳችሁ ተደርጎ አስተያየት እንድትሰጡበት ይደጋል፡፡ ከዚያ በፊትም የሚመጡ አስተያየቶችን ለመቀበል ዝግጁ ነኝ፡፡ በዚህ አጋጣሚ በእለቱ ያልተገኛችሁ የአገር ውስጥ ወንድሞቻችን በስልክ ቁጥር 0922580352 በትደውሉልኝ ደስ ይለኛል፡፡ በአውሮፓ እና በአሜሪካ ለምትገኙ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን በአውሮፓ ለጊዜው ዘገየ ሀይሉ ብታገኙ ደስ ይለናል፡፡ ለሰሜን አሜሪካና በሌሎች ሀገሮች ለምትገኙ በተገኘው ዘዴ አናሳውቃችሃለን፡፡
በመጨረሻም በእድሜ ታናሻችን የሆነው አለማየሁ ፋንታ ላለፉት አመታት በፊስ ቡክ አማካይነት ለማገናኘት ሲያደርግ ለቆየው አስተዋፅኦ በእለቱ በተገኙት ተሳታፊዎች በጭብጨባ አድናቆት ተችሮታል፡፡
በእለቱ በዝግጅቱ ላይ የተገኙ፣
1. ነዋይ ተሾመ
2. ሰሙንጉስ ገበየሁ
3. አለማየሁ ተካ
4. ዘካርያስ ደሜ
5. ዳዊት ሃ/ማርያም
6. ሙሉሸዋ አበራ
7. ዘለቃች ቸርነት
8. ደረጀ አምባዩ
9. ዘገየ ሀይሉ
10. ራህመት ሁሴን
11. ሀብለወርቅ ተፈራ
12. ሲሳይ ተፈራ
13. ሀና ገ/መድህን
14. ገነነ ሃይሉ
15. መ/ር ህይወት ሀ/ማርያም
በእለቱ መምጣት ሳይችሉ በስልክ መልዕክት ያስተላለፉ
1. አክሊሉ ተስፋዩ
2. ተስፋዩ ድረሴ
3. አሰፋ መንግሰቴ
ባለሱቅ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1288
Joined: Mon Sep 27, 2004 6:20 am
Location: ethiopia

Re: ይድረስ ለክብረመንግስትና አካባቢው ልጆች!!!

Postby አደቆርሳ » Mon Nov 28, 2016 6:39 pm

መቼም ድንቅ ነው....... እንዲህ ያለውን መገናኘት እኔም እወደዋለሁ
ሰሙንጉስ ገበየሁ ሰላም ላንተ ይሁን እንደው ከወሬውም ከትዝታውም ጨለፍ ብታረግልን መልካም ነበር ፡
በመልክ መረሳሳት በርግጥ ሊኖር ይችላል እንደው ራሴን ስገምተው ግን ከጀርባ አይቼ ብቻ የጠራሃቸውን ሁሉንም እለያቸዋለሁ ብዬ አምናለሁ፡፡
ብዙ ልጆች ጋር በየመንገዱ ስንገናኝ የሚቸግረኝ ራሴን ማስተዋወቅ እንጂ እኔ አውቃቸዋለሁ ፡፡
አልፎ አልፎም የራስብሩን ልጆች ሳገኝ ማናገሩ ደስ ይለኝና ረሳሁህ ማነህ የሚለኝ ስለሚበዛ አልፌ መሄድን እየለመድኩት ነው፡፡
ለሁሉም ደስ የሚል ሁኔታ ነው ተባረክ ወንድሜ ሆይ፡፡
ቸር ያቆየን
Image
kibremengist
አደቆርሳ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 977
Joined: Wed Aug 03, 2005 5:50 pm
Location: ethiopia

Re: ይድረስ ለክብረመንግስትና አካባቢው ልጆች!!!

Postby አደቆርሳ » Tue Feb 07, 2017 1:18 pm

ጎበዝ ሰላም ነው ?
ባለሱቅ ለጤናህ እንደምን አለህ ? እኔ ቸሩ ፈጣሪ ይመስገን በጣሙን ደህና ነኝ
ባለፈው ቃል የገባህልኝን ምነው ዘነጋሃትሳ ? እንደ ዲያስፖራ ውሸታም ሆነህ ቀረህ ? አይ አይመስለኝም አንተ መልካም ሰው ነህ እንደ ዲያስፖራ ቀዳዳ አይደለህም፡፡ ምንድር ነው ብለህ ግራ እንዳትጋባ ያው ወሬ ነው ፡፡ አሪፍ ወሬ አቀብላችኋለሁ ብለህ ነበር መቼም ለኔ ወሬን የሚያህል ቁም ነገር እንደሌለ ታውቅ የለ ለዛ ነው፡፡

ራስብሩ ወንድሜ እስቲ ብቅ በል የማወጋህ አለኝ

እደቆርሳ ዘሃገረ እዶላ
Image
kibremengist
አደቆርሳ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 977
Joined: Wed Aug 03, 2005 5:50 pm
Location: ethiopia

Re: ይድረስ ለክብረመንግስትና አካባቢው ልጆች!!!

Postby ራስብሩ » Sat Apr 22, 2017 7:04 pm

ወዳጄ ሽሜው ( ሽሜ ጉጉ ) ሰላም ነህ ወይ ?
ውነትም ዘግቼሃለሁ ዛሬ ንዳጋጣሚ ነው ብቅ ስል ያየሁህ ብዙ ጊዜ ዋርካን ማየት እንደበፊቱ አይደለሁም ፡፡
ባለቤቱ ያቃጠለው ቤት ጯሂ የለውም..... ይባል የለ፡፡ አድሚኖቹ ቤታቸውን አበላሹት አሁን ማጠፊያው አጠረ ብቻ ዘግይቶም ቢሆን መልሰውታል መጠቀም የኛ ፋንታ ነው፡፡
ይገርምሃል አሁን ከፌስቡክ የዘላለም ስንብት ለመወሰን የቀረኝ በጣም ትንሽ ቀናት ናቸው ፡፡
ለሁሉም ወደቤታችን ተመልሰን እዚሁ እንቀጥላለን ሰላም ሁን፡፡
ደሞ ዲያስፖራን ጠቅ ሳታደርግ አታልፍም ምን ሆነህ ነው ? ምንህ ተነካ ?
ውረድብኝ እንግዲህ ........
This is Ras Biru Woldegebriel.......................!!

http://www.oyla22.de/userdaten/406/6554 ... s_Biru.jpg
ራስብሩ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 785
Joined: Thu Aug 25, 2005 6:49 pm

Re: ይድረስ ለክብረመንግስትና አካባቢው ልጆች!!!

Postby ራስብሩ » Tue Apr 17, 2018 11:08 am

ሠላም ለሁላችሁም ይሁን
በሚቀጥለው ዓመት ማለትም በ2019 የክብረመንግሥት 75ኛ የምሥረታ ዓመት በዓል ስለሚከበር
መልክቶቻችንን በዚህ መድረክ ላይ እንድናስተላልፍ አደራዬንም ጭምር አስተላልፋለሁ፡፡
የልጅነት ታሪክ
ደራሲያን አጫጭር ሥነጽሁፎቻችሁን
ገጣሚያን ግጥሞቻችሁን
ሙዚቀኞች ከሙዚቃዎቻችሁ ( ታሪካችሁን) ሌሎችም ያላችሁን የትዝታ ቋት ፈታ እያደረጋችሁ
ዓመታትን ወደኋላ ተመልሰን ክብረመንግሥትን እንድናስታውስ መድረኩ ተዘጋጅቷል፡፡
This is Ras Biru Woldegebriel.......................!!

http://www.oyla22.de/userdaten/406/6554 ... s_Biru.jpg
ራስብሩ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 785
Joined: Thu Aug 25, 2005 6:49 pm

Re: ይድረስ ለክብረመንግስትና አካባቢው ልጆች!!!

Postby ባለ-ሱቅ » Thu Aug 30, 2018 5:46 am

ሙከራ አንድ ሁለት አንድ ሁለት
ዋርካ የድሮ ስሜን ወስዶ አልሰጥ ቢለኝ በአዲስ ስም ብቅ አልኩኝ
ባለ-ሱቅ እባላለሁ
በቀደም ለታ ነው... ከአንድ የክብረመንግስት (አዶላ) ልጅ ጋር ቁጭ ብለን ስናወራ.... እንዴት እንደሆነ ባላስታወስኩት አጋጣሚ ስለሰርግ ተነሳ...
አዶላ ውስጥ ስንት ሰርግ ትዝ ይልሃል ብሎ ጠየቀኝ፡፡እኔም ትዝ የሚለኝን ቆጥሬ ነገርኩት ... ለኔ ትዝ የሚለኝ እራት ነበር....
1ኛ የሃጂ-ሃሰን ልጅ ስታገባ (ከድጃ ይመስለኛል.... ምንም ህፃን ብሆንም ትዝ ይለኛል.... የዚያን ጊዘ ወጣቶች ሰርግ ቤት ሲዘፍኑ..... አስኪ እንመካከር ... እርስ በራሳችን.... ዘር መለየት ይቅር ... አንድ ነው ደማችን.... እያሉ ሲዘፍኑ ትዝ ይለኛል....
2ኛ.. የመድኔ ልጅ ያገባች ግዜ.... ማስታውሰውእአስናቀ ገ/የስ ሰርጉን አድምቆ ሲመሻሽ እና መድረኩን ጥሎልኝ ሲሄድ... እኔ በአብዮት ዘፈን ተራዬን ማደምቀው እና መሳቂያ ምሆነው
3ኛ... ከለምለም ቤት በላይ ያለው የወለዬዎቹ ቤት ውስጥ የነበረው ሰርግ.... የማስታውሰው ደሞ... እነ-ፍቃዱ እቦምሳ የሚያዘፍኑኝ ዘፈን
በናፍቆት አለንጋ ጨክነሽ.. ልቤን የቀጣሽው
እቱ የምወድሽ ናፍቆቴ ነይ የት ነበር ያለሽው
የምች መዳኒት ስሙ ዳማከሴ
መሃረብ አይደለሽ አልከትሽ በኪሴ
ማታ በሁለት ሰእት እጠብቅሻለሁ
ኮሮንቲ ሲጠፋ ጉብ እልብሻለሁ....
የምትል ከየት እንደመጣች የማላቃት ግጥም እሱዋን ስል የሚሳቀው ሳቅ...እአይረሳኝም
በ4ኛ ደረጃ ማስታውሰው... የጋሽ በቀለ ልጅ ስታገባ.... ታደሰ ሚባል ይመስለኛል ባሉዋ... 02ቀበሌ.... አማረች ወይም ምናምን ጠጅ ቤት እካባቢ... ያለ ቤታቸው
እዛ ትዝ የሚለኝ.... በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ በራሴ ላይ ኤክስፐርመንት የሰራሁበት ስለሆነ.... ምክንያቱም.... ልጆች ሆነን ሲነገረን ያደግነው የክርስቲያን ስጋ ከበላህ ትሞታለህ .. ነው.... እኔ ደሞ... መሞት እንዴት እንደሆነ ... ቼክ ያደረኩበት ስለሆነ.... በፍፁም አይረሳኝም
እያልኩ ስቀድ ለግዋደኛዬ.... ተገርሞ አየኝና...
እኔ ግን አዶላ ውስጥ ያለ-አንድ ሰርጋ አላቅም አለኝ....
የማንን ስለው.... የጋሽ አሰጋኽኝ ቤት ሰርግ ብሎ ልቤን አቆመብኝ..... እኔ ካገር ከወጣሁ በሁዋላ ሆነ እንጂ እያመልጠኝም ነበር፡፡ ራስብሩ ና እኔ እንተዋወቃለን... ለምን ልቤ እንደቆመ
እና ስኪ ንገረኝ እልኩት የሚያውቀውን
ሳስበው ሳስበው... ብሎ ጀመረ
ሳስበው ሳስበው ያኔ እኔና ጌቱእአድማሱ ኩሽኔታ ለመንዳት መድሃኒያለም ዳገት ስንወጣ.... እንዲት ቆንጅዬ ልጅ.... ቀ----ይ ቆንጆ.... የአዶላ ፀሃይ ነክቶዋት የማያቅ ምትመስል ውብ የሆነች ልጅ... ከአንድ ማንነቱን ካማላቀው የ01 ልጅ ይመስለኛል... ከሱ ጋር ሆነው......
ይሄ መብራት ሃይል ጊቢው አለ እይደል.... እሱ ጋር ካለው ሳር ላይ ቁጭ ይሉና.... ይሉና...... ይሉና
እኛ ደሞ ተደብቀን እናያቸው ነበር... እኔና ጌቱ
አቤት ደስ ሲሉ ብታያቸው
ታውቃቸዋለህ ግን?... ብሎ ድንገት ሲጠይቀኝ... ከንዴት እለም ትካዜ ውስጥ ድንገት መንጥቆ አወጣኝ....
እያየሁዋቸው ነበር... እነዚያን ሁለት ውብ ልጆች.... ከመዳህኒያለም ጫካ ውስጥ ወጥተው... መብራት ሃይሉ ሜዳ ላይ ቁጭ ብለው... ሲጎነጫጩ
ወይኔ እኔ ብሆን ያኔ... በድንጋይይ አላስተርፋቸውም ነበር
ብዬ በጣም ቆጨኝ
ይሰማል ራስብሩ
እዎን በጣም ቆጨኝ... ጌቱን ወይም ጉዋደናዬን ባደረገኝ ብዬ... ቁጭትትትትት
ቆጨኝ የሚለውን የትእግስት ወዪሶን ዘፈን ጋብዤሃለሁ
አሃሃሃሃሃ
A Thing of beauty is a joy Forever
ባለ-ሱቅ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 5
Joined: Sat Sep 13, 2003 1:37 am
Location: united states

Previous

Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 0 guests