የሄ የጥበብ ቤት በርኩሳን መናፍስት እየታመሰ ነው ፡፡

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

የሄ የጥበብ ቤት በርኩሳን መናፍስት እየታመሰ ነው ፡፡

Postby ክቡራን » Wed Oct 17, 2018 4:28 pm

በሚገርምና አሳዛኝ በሆነ ሁኔታ ግሩም ድንቅ ጠባቢያን፣ ቀላሚያን፣ ጸሃፊያን፣ ገጣማውያን፣ ክልሆታቸውን ያሳዪበት ጥበባቸውን ያስጎበኙበት አበባ ብእራቸውን ያስመሰከሩበት ይሄ የስነ ጽሁፍ መዘክር ባልታወቁ እርኩሳን መናፍስት አቅሉን ሲያጣ የዋርካ አድሚኖች ዝም ማለታችሁ ወይ ደክሞቻሁዋል ወይ ሊኪነ ጥበብ ዋጋ መስጠት አቁማችሁዋል ማለት ነው ፡፡ እርዳታ ከፈለጋችሁ ጊዜያዊ አድሚን አድርጉኝና ልጠርግላችሁ፡፡ ጥበብ ሲያምረኝ እዚህ ቤት እመጣ እንደነበር አስታውሳለሁ.... ይሄ ሰፈር የውቃቢ መንደር ሳይሆን አባ ከና በሉት!! ደሞ ለምን ተነካን ብላችሁ እንዳታባሩኝ፡፡ ጉልበታችሁ እኛ ቀናዎቹና ቅዱሳኖቹ ላይ ነው፡፡
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8385
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Re: የሄ የጥበብ ቤት በርኩሳን መናፍስት እየታመሰ ነው ፡፡

Postby ወንበዴው » Wed Oct 17, 2018 6:50 pm

የአሜሪካውን ምርጫ የጠለፉት ዝነኞቹ የሩስኪ ሃከሮች፤ ዋርካችንን ከስሯ ሊመነግሉብን ቆርጠው ተነስተዋል-ወዳጄ ክቡራን፡፡ By the way, where are 4ቱ የዋርካ ዘበኞች? በአዲሱ ካቢኔ አልተካተቱም እንዴ?
ወንበዴው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 318
Joined: Sun Aug 07, 2005 5:01 pm
Location: india

Re: የሄ የጥበብ ቤት በርኩሳን መናፍስት እየታመሰ ነው ፡፡

Postby ክቡራን » Fri Oct 19, 2018 12:19 am

የተከበርከውና የተወደድከው ወንበዴ ሆይ ፣ ባለኝ መረጃ ዛሬ ዋርካ ( ሳይበር ኢትዮጵያ ) አገራችን ውስጥ ያለምንም ፕሮኪሲ ማንም ሰው ሊጎበኘው ይችላል፡፡ ይህ ማለት አገራችን ያሉ አንባቢያን እዚህ ቤት ውስጥ ካሉ የጥበብ ሰዎች ቡዙ ነገር ሊቀስሙና ሊማሩ እነሱም የራሳቸውን የጥበብ ስራ ሊያሰፍሩ ይችላሉ፡፡ ገቢያው ሲመጣ የዋርካ አድሚኖች የምርቃና ይሁን ወይም የሞቅታ በማይታወቅ እንቅልፍ ላይ ያሉ ይመስለኛል ፡፡ አድሚኖቹ በድጋሚ ጥልቅ እንቅልፍ ላይ ናቸው ፡፡ እርኩሳን መናፍስቱም ዋርካ ስነ ጽሁፍን እየጋለቧት ነው፡፡
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8385
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Re: የሄ የጥበብ ቤት በርኩሳን መናፍስት እየታመሰ ነው ፡፡

Postby ክቡራን » Tue Oct 23, 2018 8:18 pm

ኦ ጥበብ ሆይ ! እነሆ ማረፊያሽ የት አለ ..
መውጊያሽስ ወዴት ነው ..??
አዚም አዙሪት ሲፈነጨብሽ ..
ሉሱፈር ሰይጣን ሲጨፍርብሽ...
አታሞ ድቤ ሲመታብሽ ..
ልሳነ እርኩሳት ሲጎሰመብሽ..
ኦ ጥበብ ሆይ...
ማረፊያሽ የት አለ ..
መውጊያሽስ ወዴት ነው..??
የሰገባሽ ዘንጉ... የብእርሽ ሃሞቱ ..
የልሳንሽ አውድ ..የኪንሽ ምጥቀቱ ..
እያየሁት ሞተ... ወዘናሽ ድምቀቱ፡፡
ነፍስ ይማር ብያለሁ፡፡
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8385
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Re: የሄ የጥበብ ቤት በርኩሳን መናፍስት እየታመሰ ነው ፡፡

Postby ክቡራን » Mon Oct 29, 2018 9:31 pm

ወዮዮዮዮዮ....!!
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8385
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Re: የሄ የጥበብ ቤት በርኩሳን መናፍስት እየታመሰ ነው ፡፡

Postby *Oww Gee » Fri Nov 02, 2018 9:31 pm

ክቡራን wrote:የተከበርከውና የተወደድከው ወንበዴ ሆይ ፣ ባለኝ መረጃ ዛሬ ዋርካ ( ሳይበር ኢትዮጵያ ) አገራችን ውስጥ ያለምንም ፕሮኪሲ ማንም ሰው ሊጎበኘው ይችላል፡፡ ይህ ማለት አገራችን ያሉ አንባቢያን እዚህ ቤት ውስጥ ካሉ የጥበብ ሰዎች ቡዙ ነገር ሊቀስሙና ሊማሩ እነሱም የራሳቸውን የጥበብ ስራ ሊያሰፍሩ ይችላሉ፡፡ ገቢያው ሲመጣ የዋርካ አድሚኖች የምርቃና ይሁን ወይም የሞቅታ በማይታወቅ እንቅልፍ ላይ ያሉ ይመስለኛል ፡፡ አድሚኖቹ በድጋሚ ጥልቅ እንቅልፍ ላይ ናቸው ፡፡ እርኩሳን መናፍስቱም ዋርካ ስነ ጽሁፍን እየጋለቧት ነው፡፡


አዎ! በስነስራት ይሰራል....
እንደ ማረጋጋጫ እኔን መውሰድ
ትችላለክ።
*Oww Gee
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 18
Joined: Sun Oct 29, 2017 2:33 pm

Re: የሄ የጥበብ ቤት በርኩሳን መናፍስት እየታመሰ ነው ፡፡

Postby ክቡራን » Fri Feb 08, 2019 12:32 am

መልካም ጅማሬ ነው ክቡራን አድሚኖች ቤቱን ማየት ጀምራችኋል፡፡ በርቱ፡፡
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8385
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Re: የሄ የጥበብ ቤት በርኩሳን መናፍስት እየታመሰ ነው ፡፡

Postby ክቡራን » Wed Apr 10, 2019 6:48 pm

ኦ ጥበብ ሆይ ! እነሆ ማረፊያሽ የት አለ ..
መውጊያሽስ ወዴት ነው ..??
አዚም አዙሪት ሲፈነጨብሽ ..
ሉሱፈር ሰይጣን ሲጨፍርብሽ...
አታሞ ድቤ ሲመታብሽ ..
ልሳነ እርኩሳት ሲጎሰመብሽ..
ኦ ጥበብ ሆይ...
ማረፊያሽ የት አለ ..
መውጊያሽስ ወዴት ነው..??
የሰገባሽ ዘንጉ... የብእርሽ ሃሞቱ ..
የልሳንሽ አውድ ..የኪንሽ ምጥቀቱ ..
እያየሁት ሞተ... ወዘናሽ ድምቀቱ፡፡
ነፍስ ይማር ብያለሁ፡፡

ወዮ!! መናፍስተ ዲጎኔዎች!!
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8385
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm


Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests