ቅንጥብ ጣቢ

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

Re: ቅንጥብ ጣቢ

Postby ዞብል2 » Wed Apr 10, 2019 12:03 am

ጨለማ ከጨለማ ውስጥ አያወጣንም፤ይህን ማድረግ የሚችለው ብርሃን ብቻ ነው፡፡
ጥላቻ ከጥላቻ ውስጥ አየወጣንም፤ይህን ማድረግ የሚችለው ፍቅር ብቻ ነው፡፡
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2341
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Re: ቅንጥብ ጣቢ

Postby እሰፋ ማሩ » Wed Apr 10, 2019 12:12 am

በትክክል ይህ ለሃገራችን ወቅታዊ ሁኔታ የሚሰራ የጥበብ ንግግር ነው ተባረክ፡፡ጨለማው ወያኔ የሚዲያ የፖለቲካ ጥፍነጋና አፈና በባለተራው ከተጀመረ የባሰ ጨለማና እልቂት ስለሚከተል የወቅቱ መሪዎች ለዚህ ምሳሌ መሆንና ጨለማን በጨለማ ሳይሆን በብርሃን ማጥፋት ይገባቸዋል ዶር አብይም በን ግ ግ ሩ ያደረገው ይህንኑ ነው ተግባራዊ ያደርግ ዘንድ እንጠብቃለን እንደግፋለን፡፡
ዞብል2 wrote:ጨለማ ከጨለማ ውስጥ አያወጣንም፤ይህን ማድረግ የሚችለው ብርሃን ብቻ ነው፡፡
ጥላቻ ከጥላቻ ውስጥ አየወጣንም፤ይህን ማድረግ የሚችለው ፍቅር ብቻ ነው፡፡
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1550
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm

Re: ቅንጥብ ጣቢ

Postby ዞብል2 » Thu Apr 11, 2019 12:53 am

አብይ ሆይ ያለ ምንም ሰንሰለት የለቀቅከው ኦነግ ዛሬ ህዝብና አገር እያደማ ነው፡፡አንተንና ተከታዮችህን ለመብላት እንደማይመለስ ልቦናህ ያውቀዋል፡፡የጊዜ ጉዳይ ነው፡፡ትላንት በአንቀልባ እሽሩሩ የተባለው ኦነግ ዛሬ ገዝፎ እንቀልባውን በጥሶ አዛዩን ሊያጠቃ ምንም አልቀረውም፡፡ኦነግ አዝሎት ያመጣውን ያጠፋ እንደሆን እንጂ፤ ኢትዮጵያና ኢትይጵያዊያን ራሳቸውን ለመጠብቅ እጅ ለእጅ ተያይዘው ለሃገራቸው ዘብ ይቆማሉ!!!!
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2341
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Re: ቅንጥብ ጣቢ

Postby ዞብል2 » Fri Apr 12, 2019 12:40 am

"የምህረት አድራጊና የምህረት ተቀባይ ግንኙነት መኖር የዲሞክራሲ ዋስትና አይሆንም"፡፡ይልቁንም የበላይና የበታች የአዛዥና የታዛዥነት ቁርኝነት ነው፡፡እኔ በነፃነት እናገራለሁ የሚል ህዝብና ነፃነትና መብትህን አከብራለሁ የሚል መንግስት ይኖር ዘንድ ነው የረዥሙ ትግላችን ማጠንጠኛው፡፡የህንን የሚገድብ ሁኔታ፤ማስፈራሪያ፤ለበጣ፤ትዕዛዝ ወዘተ..... ዛሬም ጊዚያዊ ማስታገሻ እንጂ ዘላቂ ፈውስ አይደለም፡፡

የህዝብ አደራ የሥልጣን ጥም መወጫ፡፡የወንበር ፍቅር ማሞቂ ያም አይደለም፡፡የግል ዝና ማካበቻም አይሆንም፡፡የፖለቲካ ሽኩቻ ማደያ ሊሆንም አይገባም፡፡የጀብደኝነት ወሸነኔ ዘመንም አይደለም፡፡የዉስጥ-አርበኝነት(ኦነግ) የበግ ለምድም ሊሆን ከቶ አይችለም፡፡የህዝብ አደራ የዳተኝነትና የአድርባይነት መሸፋፈኛም ሊሆን አይገባውም፡፡

መቼም ቢሆን መቼ የህዝብ አደራ በግልፅ፤የህዝብን ጥቅም ማስጠበቂያ ሃላፊነት ነው፡፡በአግባቡ ካልያዙት፤ዙፋኑን ካገኘ በሁዋላ የሚይዝ የሚጨብጠውን አጥቶ "ምነው ይሄን ዘውድ የሰጡኝ ዕለት እራስ ባል ኖረኝ ኖሮ?" እንዳለው ንጉስ መፀፀቻ ይሆናል፡፡
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2341
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Re: ቅንጥብ ጣቢ

Postby ዞብል2 » Wed Apr 24, 2019 11:49 pm

".....ኬንያ ናይሮቢ አንዲት መዝናኛ ቤት ተገኝቼ እየተዝናናሁ ነው፡፡
ቤቱ እንደ ፓርቲ ቤት ያለ ነው፡፡
ባንዱ ጥግ መጠጤን ይዤ ፤የዳንሱ ወለል ላይ ጥንድ ጥንድ ይዘው የሚደንሱ ወጣቶች አያለሁ፡፡
በዚህ መሃል ላይ የባሕር ሃይል ልብስ የለበሱ እንግሊዛዊያን ነጮች ገቡ፡፡
አንዱ እንግሊዛዊ ቀጥታ ወደ ዳንሱ ወለል በመሄድ ከወዳጁ ጋር እየደነሰ ያለውን ኬንያዊ በካልቾ መታው፡፡
ኬንያዊው ተርበድብዶ ወዳጁን ጥሎ ሄደ፡፡ እንግሊዛዊውም ከኬኒያዊቱ ጋር መደነስ ጀመረ፡፡
በእንግሊዛዊው ድርጊት በጣም ተናደድኩ፡፡ከመቀመጫዬ ተስፈንጥሬ ወደ ወለሉ አመራሁ፡፡
እኔም እንግሊዛዊውን በካልቾ ጠልዤ ኬንያዊቱን ተቀበልኩ፡፡
ትንሽ ከእስደንስኩ በሁዋላ ለተቀማው ኬንያዊ አስረከብኩ፡፡
ይህን ፈፅሜ ወደ መቀመጫዬ ሳመራ እንግሊዛዊው የጠየቀኝ አንድ ጥያቄ ነበር "ኢትዮጵያዊ ነህ?" የሚል"

ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማሪያም
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2341
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Re: ቅንጥብ ጣቢ

Postby ክቡራን » Thu Apr 25, 2019 12:10 pm

ወይ ጉድ ሰው በዚህ እድሜው ግን ይዋሻል ? ያውም በህማማት ሳምንት!! ወይ መአልቲ!! አለ ቻይና፡፡
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8385
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Re: ቅንጥብ ጣቢ

Postby ዞብል2 » Thu Apr 25, 2019 11:59 pm

አቦይ ክቡራን ፕሮፌሰሩ በጎልማሳ ዘመናቸው ፤ በናይሮቢ ከተማ የምሽት ዳንስ ቤት ፤የገጠማቸውን ገጠመኝ የልደት በዓላቸውን ምክንያት በማድረግ ለማስታወስ በድጋሚ የተፃፈ ነው፡፡አንተ ግን ወሬ አገኘሁ ብለህ ለትችት ሰፍ አልክ፤ከረፈፍ ወያኔ ቅቅቅቅቅቅቅ
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2341
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Re: ቅንጥብ ጣቢ

Postby ዞብል2 » Sat Apr 27, 2019 9:50 pm

"መልካም የትንሳዔ በዓል ለሁላችንም ይሁን"
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2341
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Re: ቅንጥብ ጣቢ

Postby ዞብል2 » Wed May 01, 2019 7:01 pm

እውነታው ሁሉም ኢትዮጵያዊ፤እየተገፋ እየሞተ ነው፤እኔ በበኩሌ የማንኛውም ኢትዮጵያዊ ብቻ ሳይሆን፤የሰው ልጅ በማንነቱ እየተለየ ከቀዬው ሲፈናቀል፤ሲደበደብናሲገደል ፤ሰብዓዊነት የጎደለው በደል ሲፈፀምበት ያመኛል፡፡ችግራችንን ግን መፍታት የምንችለው በተናጠል ሳይሆን፤ አንድ ላይ እንደ ሰው ማንነታችን ስንቆም ነው!!
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2341
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Re: ቅንጥብ ጣቢ

Postby ዞብል2 » Thu May 02, 2019 12:55 am

ከወራት በፊት የሱሉልታ ከተማ ከንቲባ፤ከ30ሺ በላይ የሚሆን ቤት አፈርሳለሁ ካላፈርስኩ ጣቴ ይቆረጣል ብላለች፤ የወያኔ አለቃ የነበሩትም ወዲ ዜናዊ ፤የቡና ነጋዴዎችን ሰብስበው ጣት እቆርጣለሁ ብለው ፎልለዋል፡ህገ ወጥነትን በህግ እንጂ አካልን ለማጉደል በመዛት አይደለም፡፡ የህግ የበላይነት በሚከበርበት ሀገር ቢሆን ከንቲባዋ ህግ ፊት ትቆም ነበር፡፡
አሁንም የሱሉሉታ፤የለገጣፎ .........ወዘተ አካባቢዎች ችግር ሊፈታ የሚችለው በህግ እንጂ፤ ቤት በማፍረስና ወገኖቻችን መድረሻ በማሳጣት አይደለም፡፡
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2341
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Re: ቅንጥብ ጣቢ

Postby ክቡራን » Fri May 03, 2019 12:18 am

እረ እየተስተዋለ ጎበዝ !! ስድስት ቁጥርና ሶስት ቁጥር አውቶብሶች ላይ ወደ ገበያ የሚሄዱ ወላጅ እናቶቻችንን መቀነት በመፍታት፣ ቦርሳ በመክፈት የታወቀ የእጅ ባለሟል እንዴት ሆኖ የሰብአዊ መብት ተሙጏች ነኝ የሚለን ?? የስምንተኛው ሽ መምጫ ምልክት ይሆን??? ወይ መአልቲ አለ ቻይና!! ሎል፡፡


ዞብል2 wrote:እውነታው ሁሉም ኢትዮጵያዊ፤እየተገፋ እየሞተ ነው፤እኔ በበኩሌ የማንኛውም ኢትዮጵያዊ ብቻ ሳይሆን፤የሰው ልጅ በማንነቱ እየተለየ ከቀዬው ሲፈናቀል፤ሲደበደብናሲገደል ፤ሰብዓዊነት የጎደለው በደል ሲፈፀምበት ያመኛል፡፡ችግራችንን ግን መፍታት የምንችለው በተናጠል ሳይሆን፤ አንድ ላይ እንደ ሰው ማንነታችን ስንቆም ነው!!
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8385
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Re: ቅንጥብ ጣቢ

Postby ዞብል2 » Fri May 03, 2019 8:32 pm

በአደባባይ የሚደረጉ የሃሳብ ሙግቶችና ዉይይቶች ሶስት ነገሮችን ይጠይቃሉ፡
1ኛ.በሚናገሩበት ጉዳይ ጥልቅ ዕውቀት
2ኛ.ሃሳብን በነፃነት መግለፅ
3ኛ.በዚህም የሚመጣውን፤ተጠያቂነት የመቀበል የሚያስችል ድፍረት እና ሥልጡን የሆነ የሃሳብ አገላለፅ ናቸው፡፡

የቡርቃ ዝምታ መፅሐፍ ውሸት ነው ሲባል ቄሮና የኦሮሞ ምሁራን በሰልፍና ዛቻ ሰውን ፀጥ ማሰኘት፤አማራ የሚባል የለም ያለን ሰው በክስ አፉን ለመሎጎም መዳዳት፤የታሪክ ውጤት ምርምሩን የሚናገር እንደ ፕሮፌሰር ሃይሌ ላሬቦ አይነት ምሁርን በዛቻ እና በስድብ እንካ ሰላምታ መግጠም፤የሃሳብ ነፃነት ላይ ያነጣጠረ ዘመቻ ነው፡፡
ይህ አይነቱ እንቅስቃሴ በጊዜ ካልተገራና ካልተወገደ እያደር የፖለቲካ ባህል ይሆናል፡፡
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2341
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Re: ቅንጥብ ጣቢ

Postby ዞብል2 » Mon May 06, 2019 9:26 pm

"ዝም ብንል ብናደባ ዘመን ስንቱን አሸክሞን
የጅልነት እኮ አይደልም፤እንድንቻቻል ገብቶን"

"ያለፈ ጥረታችንን ሳስታምመው ትዝ ሲለኝ
ከሞከር ነው ነገር ይልቅ ያልሞከርነው ነው የሚቆጨኝ"

ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2341
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Re: ቅንጥብ ጣቢ

Postby ዞብል2 » Wed May 08, 2019 12:28 am

"እምዬ ሚንሊክ ይህንን አልሰማ
በፋሲካው ሌሊት ገደፍኩኝ በሳማ"

**ልጅ እያሱን ተናግረሀል ተብሎ በፋሲካ ሌሊት በሳማ የተገረፈ ገጣሚ የገጠመው፡፡

ወያኔዎች በልማት ስም ያፈናቀሉን ይበቃል፤በህገ ወጥ ግንባታና፤በግሪን ኤሪያ ስም፤ በኦዴፓ መጤ ከንቲባዎች የሚደረገው ሰብዓዊነት የጎደለው ማፈናቀል ይቁም፡፡
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2341
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Re: ቅንጥብ ጣቢ

Postby ዞብል2 » Thu May 09, 2019 12:31 am

በዚህ አያያዛችን ኢትዮጵያ እግር ቢኖራት፤ ምን ዓይነት ህዝብ ነው የተሸከምኩት ብላ፤ አራግፋን ብን ብላ ትጠፋ ነበር፡፡
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2341
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

PreviousNext

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests