ዘራፍ በል አማራ! (በላይነህ አባተ)
February 8, 2019
የቱርክን የግብጥን አንገቱን የቆረጥህ፣
የጣልያን ደንደስ ሁለቴ የሰበርክ፣
እንዴት አይጡ ጃርቱ ከጓሮህ ያስወጣህ?
ዘርህን ለይተው ሲሰልቡ ሲያመክኑህ፣
በቋንቋህ ለይተው ገደል ውስጥ ሲከቱህ፣
ዘርክን እያጠኑ ሲገርፉ ሲሰቅሉህ፣
ከቤጌምድር ሳይቀር ዛሬም ሲያሰድዱህ፣
ከኢዮብ በላይ ትእግስት ምንድን ሊሰራልህ?
እንኳን ጉራ ፈርዳን ጎንደር ከለቀቅህ፣
በህይወት መኖሩ ምን ሊፈይድልህ?
ከአርባ ዓመታት በላይ ታስረህ ተጨፍጭፈህ፣
በስድስት ሚሊዮን ቁጥርህን ቀንሰህ፣
ዛሬም እንደ ትናንት በስብከት ተታለህ፣
ጭራቅ ያሳደገው ፓስተርን ተማምነህ፣
ስንት ሰው እስቲቀር ማተብህ ይሰርህ?
ይቺ ዓለም ከጥንትም በጎን አትፈልግም፣
እንኳን የሰውን ልጅ ሰቅላለች አምላክም፡፡
ስለዚህ አማራ ቅድስናን አቁም፣
ከሰው ከፍ ብትል ከመላእክት አትደርስም፡፡
እንደ እሳት ተንቦግቦግ ተፋጅ እንደ ፍምም፣
ይኸን ላንተ መቼም የሚያስተምር የለም!
ዳይኖሶር እንዳትሆን ጭራሽ ከምድር ጠፍተህ፣
ዘራፍ በል አማራ ልክ እንደ ልማድህ!
በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)
የካቲት ሁለት ሺ አስራ አንድ ዓ.ም