ምኒሊክ በውጫሌ የዓቢይ መልስ ለዋሽንግተን፡የገዳ ስርዓት በምኒሊክ አማካይነት ተጠናቁዋል ፡፡

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ምኒሊክ በውጫሌ የዓቢይ መልስ ለዋሽንግተን፡የገዳ ስርዓት በምኒሊክ አማካይነት ተጠናቁዋል ፡፡

Postby ቆቁ » Fri Oct 11, 2019 9:45 pm

የቻሉ ያግዙናል
ያልቻሉት ይተዉናል
ያልገባቸው ይተቹናል
ያልፈለጉን ይቃወሙናል
እኛ ግን ወገባችንን ጠበቅ አድርገን የጀመርነውን ጨርሰን ሪባኑን እንቆርጣለን እንጂ ተስፋ አንቆርጥም


ይሄ ፍልስፍና ነው አይደለም እስቲ ሕዝቄል ጋቢሳን እንጠይቀው፡፡
አቦይ ስብሃት ነጋ ምን ይላል ስለዚህ ፍልስፍና
ሕዝቄል ጋቢሳ የቱ ጋ ነው ከላይ በተጠቀሰው ፍልስፍና ቦታው የሚደበው
ስብሃት ነጋ የቱ ጋ ነው ከላይ በተጠቀሰው ፍስልፍና ቦታው የሚመደበው

በነገራችን ላይ "መደመር " የሚለው ፍልስፍና ነው እንዴ
መደመር የመስቀል ምልክት ነው እንዴ?
መቀነስስ የምን ምልክት ይሆን የእንጨት
ማባዛትስ የምን ምልክት ይሆን ?
ማካፈልስ የምን ምልክት ይሆን?

በጠቅላላው የላቲን ፊደሎች የምን ምልክት ይሆኑ
የአማርኛ ፊደሎች የምን ምልክት ይሆኑ
እንደውም የእንግሊዘኛው T ፊደል የሮማውያን መስቀል ስለሚመስል መማር የለብንም ማንበብብም የለብንም
X የሚለው ፊደልና የማባዛት ምልክት ስለሚመሳሰሉ ምስጢራዊ የሆነ ነገር ስላለበት ከዛሬ ጀምሮ አናባዛም
እንዴት ያለ ነገር መጣ
መደመር ማለት መታዘል አይደለም ይህንን እንዳትዘነጉ
ፈላስፋው የየትየለሌው
Last edited by ቆቁ on Sun Mar 01, 2020 5:27 pm, edited 4 times in total.
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4345
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: ምኒሊክ በዓድዋ ዓቢይ በስቶክሆልም

Postby እንድሪያስ » Sat Oct 12, 2019 10:29 am

16 አመት ዋርካ ላይ ኖርክ አይበቃህም አባቴ ?
እንድሪያስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1826
Joined: Fri Mar 19, 2004 10:55 pm
Location: *****

Re: ምኒሊክ በዓድዋ ዓቢይ በስቶክሆልም

Postby ቆቁ » Sat Oct 12, 2019 4:15 pm

አይ እንድርያስ
ምነው ጠፋህ ነፍሱ?
አንድ ዓመት ነው መሰለኝ የምበልጥህ ? አይገርምም ?
የዛሬ 15 ዓመት ነው የምንትወዋቀው መሰለኝ ልበል ?
የት ገቡ ሌሎቹ ወንድሞቻችን?
ወይ ጉድ ዘመን ይሮጣል እድሜ ይጨድዳል፡፡
የምሰማችው ነገሮች እንደገና ልጅ እያደረጉኝ ነው አንተንስ ያስረጁህ ይሆን ወይስ ያሳድጉህ ይሆን ?
መስመራቸውን የለቀቁ እና የጨደዱ የወረቀት ነብሮች የሚደሰኩሩዋቸው ነገሮችና እነሱን የሚያስተናግዱ የሚዲያ ሰዎችና ጣቢያዎች እንደገና ልጅ ወጣት እያደረጉኝ ነው ወንድሜ
ሰላም ነህ ጤና ነህ
ፈላስፋው የየትየለለው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4345
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: ምኒሊክ በዓድዋ ዓቢይ በስቶክሆልም

Postby ቆቁ » Sat Oct 12, 2019 5:04 pm

የማይሳሳት ፍጡርም ሆነ ፈጣሪ የለም

ሰይጣን ተሳስቶ ነው ወደ ምድር የተወረወረው ይለናል ቅዱስ ቃሉ
የሰው ልጅ ስህተት ሰርቶ ነው ከምድረ ገነት የተባረረው ይለናል ቅዱስ ቃሉ
እግዚአብሄር ሰውን በመፍጠሩ አዘነ ይለናል ቅዱስ ቃሉ

ይሄንን የሚገባው ፍጡር የአንድ ሐገር መሪ አይሳሳትም ከስህተቱ አይማርም የሚል ከሆነ ራሱ ተሳስቶእል ማለት ይሆናል
ስለሆነም ነው
የመደመር ምልክት የመስቀል ምልክት ነው የሚሉ ምሁራን በሚዲያ ከሚደሰኩሩብን እንዴት አድርገው ዓቢይን መርዳት እንደሚችሉ ለምን አይነግሩንም
ስለ መስቀል ከተወራ
ራሱ የሰው ልጅ እጁን ወደ ግራ ና ቀኝ ሲዘረጋ የመስቀል ምልክት ይሆናል
እንደውም መስቀል የተሰራው የሰውን ልጅ ለመስቀል እስከሆነ ድረስ ራሱ የሰው ልጅ የመደመር ምልክት ነው
እያልን ስንፈላሰፍ መዋል ነው እንግዲህ ?
እንድውም ከ A እስከ Z ያሉ የላቲን ፊደሎች የያዙት ምስጢራዊ መልእክት እንዳለ ነው የተደረሰበት
የላቲን ፊደል ለአፍሪካ ወይም ለኩሽ ምኑ ነው ለሴምስ ምኑ ነው ብለን ብንጠይቅስ
ምስጢሩ በባይናሪ የመደመርና የመቀነስ የማባዛት እና የማካፈል ከዛም በአንድ እስከአሁን ባልታወቀ ስሌት በቅርብ ጊዜ ይደረስበታል ተብሎ ይገመታል
የሂሳብ ስሌት ምልክቶች
መደመር የሰው ልጅ እጁን ወደ ግራና ቀኝ ዘርግቶ ሲተኛ የሚያሳይ የፊዚካል ነጸብራቁ ሲሆን
መቀነስ ደግሞ የሰው ልጅ እጆቹን እጥፎ ሲተኛ የሚያሳይ የፊዚካሉ ነጸብራቁ ነው
ማባዛት እጆቹን ወደ ላይ ሰፋ አድርጎ ዘርግቶ እና እግሮቹን ሰፋ በማድረግ ዘርግቶ ሲቆም የሚታይ የፊዚካሉ ነጸብራቅ ነው
ማካፈል ሶስት የመቀነስ ምልክቶች የሚታዩበት ትዕይንት ነው
ይህ የመቀነስ ምልክት ሲተነተን
÷ / —
የማካፈል ምልክት ምስጢራዊ ነው
የመካከለኛው ምልክት የመቀነስ ምልክት ሲሆን
ይህ ደግሞ የሰው ልጅ እጆቹን አጣጥፎ ተጋድሞ የሚያሳይ ነጸብራቅ ነው
ከላይ እና ከታች ያሉት ነጥቦች ደግሞ ሁለት የመቀነስ ምልክቶች በ180 ዲግሪ ዞረው ተቀምጠው የምናይበት ምልክት ነው፡፡
እዚህ ላይ ነው ምስጢሩ
የማካፈል ምልክት ትልቁ ምስጢር ነው
እንዴት እና ለምን የመቀነስ ምልክት ( የሰው ልጅ ተጋድሞ የሚያሳየው የፊዚካል ነጸብራቁ ) የ180 ዲግሪ ግማሽ ዙሪያ ለምን ሆነ የሚለውን ሲመራመር ነው ፈላስፋው 16 ዓመታት በዋርካ ስር እንደ እንደ ቅድመ አያቶቹ የተቀመጠው፡፡
ቅድመ አያቶቼ በዋርካ እና በሾላ ዛፍ ስር ተቀምጠው ነበር የተጣላ የሚያስታርቁት
የመደመር እና የመቀነስ ከዛም የማባዛትና የማካፈል ስሌት በመጠቀም ነበር በየገበያው ተሳስበው ይኖሩ የነበረው
ይላል ፈላስፋው የየትየለሌው
ሂሳብ እንዴት እና መች ተጀመረ የሚለውን እመለስበታለሁ
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4345
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: ምኒሊክ በዓድዋ ዓቢይ በስቶክሆልም

Postby ቆቁ » Mon Oct 14, 2019 7:54 pm

1."መደመር "ማለት ላልገባው ፕሮፌሰርና መሰሉ
ለዓቢይ ኖቤል ሽልማት በአንድ በኩል ብቻ ድጋፍ ሲሰጥ በሌላ በኩል የድጋፍ ሰልፍ አልተደረገም
ይህ የመደመርን ምልክት የሚያሳይ ይሆን ነበር ፡፡ እንዴት ?
ለምሳሌ የሁሉም ኢትዮጵያ አስተዳደር ተመካክሮበት ቢሆን ኖሮ
መላው ኢትዮጵያ ከሰሜን እስከ ደቡብ ፤ ከምስራቅ እስከ ምእራብ ለሽልማቱ ድጋፍ በአንድ ቀን ወይም በተለያየ ቀን ይወጣ ነበር
ገብቶህ ይሆን?
2. ሐይማኖትህ ምንድነው ሲባል የኦሮሞ ተወላጅ " አማራ " ነኝ ይላል ላልከው ዶክተር
ይህንን ተራ የሆነ የጆክ ወሬ እንደ ሪሰርች አምጥተህ በሚዲያ ማንጸባረቅህ በጣም የሚያስቅ ነው፡፡
እስቲ ልጠይቅህ አንድ የእስልምና አማኝ የሆነን የኦሮሞን ተወላጅ ሐይማኖትህ ምንድነው ብለው ብትጠይቀው " ቱርክ" ነኝ ይላል ማለትህ ይሆን
እስቲ ልጠይቅህ አንድ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ የኦሮሞ ተወላጅ እምነትህ ምንድነው ተብሎ ቢጠየቅ " ጀርመኝ" ነኝ ይላል ማለትትህ ይሆን?
ኦነሲሞስ ነሲብ የመጀመሪያው ወደ ፕሮቴስታንት እምነት የተለወጠ የኦሮሞ የሐይማኖት አባት ነው እሱ እምነትህ ምንድነው ተብሎ ቢጠየቅ ስዊድን ነኝ ይላል ማለት ይሆን ?
በነገራችን ላይ በእምነታችን እንኮራለን ፡ በታሪካችን እንኮራለን እኛ ብቻ አይደለንም ያለፈ ታሪካችን ምንም ይሁን ምንም አያሳፍረንም እንኮራበታለን
እስቲ ልጥቀስልህ
ቦረንችቻ ፣ አዶከብሬ፣ አተቴ ፡ ታሪካችን እምነታችን ፡ ባህላችን አይደለም ? የአንተስ ባህል ታሪክ እምነት አይደለም፡፡ የአንተ ባይሆን የቅም ቅም አያቶችህ እምነት ባህል ታሪክ አይደለም ?

በተለይ እኔ ፈላስፋው በህይወቴ እና በትዝታዬ አሁንም የማከብረው እስከ መጨረሻው የማረሳው የግንቦት ልደታና አድባር
ግንቦት 1 ቀን በእኩል ቀን መከበሩን ነው፡፡
ለመሆኑ
አድባር ምንድነው ? ግንቦት ልደታስ ?
በሌላው ትንተናህ ስለ ባህል እና እምነት የሆነ ነገር ለማለት ሞክረሃል፡፡
እምነት ባህል ነው ?
ባህል እምነት ነው ?
ክርስትና ከደማስቆስ እስከ ሮም እንዴት አድርጎ ነው የተጉዋዘው ፡ እስቲ በጥናትህ ና በምርምርህ አስረዳኝ ፡፡
ባህል ከሆነ እስቲ መግለጫ ስጠኝ ፡፡ እስልምና ባህል ነው ፡ ክርስትና ባህል ነው ፡ የየትኛው ሐገር ባህል?

ፈላስፋው የየትየለሌው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4345
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: ምኒሊክ በዓድዋ ዓቢይ በስቶክሆልም፣ ኦስትሪያ ፣ኦስሎ

Postby ቆቁ » Thu Oct 17, 2019 7:48 pm

ዘርዓይ ደረስ ወዳጀ
ባቀረብከው ሐሳብ መሰረት የዚህን አርእስት ለመለወጥ ተገድጃለሁ
ይህም ምን ያህል እነዚህ ሶስት ከተሞች በአንድ ግለሰብ ምክንያት እንደተሳስሩ ለማሳየት ነው
ይህንን ለማወቅ ጊዜው ቀላል በመሆኑ ብዙ ጊዜ የሚወስድብህ ሊሆን አይችልም
ከዚህ በመነሳት የብሄር ብሄረ ሰቦች ሕዝቦች የሚለው የተምታታ ቃል ከዚህ በፊት አንተ እንደጠቀስከው የተዘበራረቀ መሆኑን እንድታረጋግጥ ይረዳሃል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ
ብሄር፤ ብሄረሰቦች ፤ ሕዝቦች ብለው መግለጫ ያወጡት ራሳቸው የቃሉንን ምንነት አያውቁትም
እንደዚህ ያሉ ቃላቶች በየጊዜው የሚያጋጥሙን የተጀቦኑ ቃላቶች ናቸው
እንደዚህ ያሉ የተጀቦኑ ቃላቶች ድንግርግር አድርገው ያደነጋግሩህና
1. እንዳትጠይቅ
2. እንዳትመልስ
3. ለማስረዳት እንዳትችል
4. በዝምታ እንድትዋጥ ያደርጉሃል ፡፡
ከዛም አልፎ እንዳትንገር ፡ አንገትህን አቀርቅረህ እንድትቀር የሚያደርጉ ቃላቶች ናቸው
እንደዚህ ያሉ የተጀቡዋቦኑ ቃላቶች የሚታወቁ በሳይኮሎጂ እንጂ በፖለቲካ ወይም በፍልስፍና አይደለም፡፡
አስቲ ራስህ የሆነን ግለሰብ ብሄር ፡ ብሄረ ሰቦች ፡ ሕዝቦች ማለት ምንድነው ብለህ ጠይቅ
ምን ዓይነት መልስ ታገኝ ይሆን ?
ፈላስፋው የየትየለሌው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4345
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: ምኒሊክ በዓድዋ ዓቢይ በስቶክሆልም፣ ኦስትሪያ ፣ኦስሎ

Postby ቆቁ » Wed Oct 23, 2019 8:00 pm

ሰላም ከጤና ጋር

አይጡዋ ወደ ማሰችው ጉድጉዋድ ስትሮጥ መንገዱ ሁላ ታጥሮባት ወዴት ትሂድ ?

መንገዱን ያጠሩት ደግሞ ድመቶች አይጦችን ሲያሳድዱ ሳይሆን አይጦች እርስ በራሳቸው የማሱት ጉድጉዋድ አቅጣጫ ጠፍቶባቸው ሲተረማመሱ ነበር

አክቲቪስት ለመሆን የፖለቲካል ሳይንስ መማር አስፈላጊ አይደለም፡፡ ለሰው ልጅ መብት ለመከራከር እና ጠበቃ ለመቆም የሰው ልጅ መሆን ብቻ ነው የሚያስፈልገው ፡ ገበሬም አክቲቪስት መሆን ይችላል

አክቲቪስት የሆነ ግለሰብ በቦዲ ጋርድ ታጅቦ ሲሄድ አይተይንም ሰምተንም አናውቅም


ፖለቲካል ሳይንስ የማይጠቅም ትምህርት ነው ፡፡ ያለ ፖለቲካል ሳይንስ የሰው ልጅ መንግስትን ፈጥሮ ሲተዳደር ነበር

የፖለቲካል ሳይንስ ተማሪ ሰውን ከማበጣበጥ በስተቀር ሌላ ሙያ ስለሌለው ብኩን ዜጋ ነው፡፡
የፖለቲካል ሳይንስ ምሩቅ ከፖለቲካ ስራው ቢወጣ ሌላ ብጥብጥ ፈጥሮ ለመኖር የሚፈልግ ግለሰብ ለመሆኑ ከራሱ ከትምህርቱ መረዳት ይቻላል፡፡ ምላሱን አስረዝሞ ከመቅደድ በስተቀር ሌላ ነገር አያውቅም፡፡
በዙ ወረቀት በፖለቲካል ሳይንስ መስክ ውስጥ መጻፍ ማለት የስራ ልምድ እንደ ማግግኘት አይቆጠርም ምክንያቱም ወረቀት የሚቃጠል ነገር በመሆኑ በሐገራችን ደግሞ የስኩዋር መጠቅለያ ወይም የሽንት ቤት ወረቀት በመሆኑ ፡፡

በአሜሪካና በአውሮፓ ከ14 እስከ 25 ዓመት የሚገኝ ወጣት በፖለቲካው ዓለም ገብቶ ሰላማዊ ሰልፍ ቢያደርግ መንገድ እየዘጋ ሱቅ እየዘረፈ ወይም ሐገር እያወደመ አይደለም የኩዋስ ጨዋታ ሆሊገን ግን ተመሳሳይ የቦዘኔ ባህርይ እንዳላቸው ነው የሚሰማው፡፡

ድል የወጣቱ ኢትዮጵያዊ ( የቄሮም ሆነ የፋኖ ) ቢሆንም ድሉን መገንባት ይጠበቅበታል እንጂ ለማፈራረስ ከሆነ ትግሉ ባላስፈለገ ነበር

የድርጅቶች መዋሃድ ሐገር ያጠናክራል እንጂ አያፈርስም ነገር ግን የድርጅቶች ተነጣጥሎ ደፈጣ ውስጥ መግባት ሐገር ይበትናል

ሕ0]የቄሮ ማተረማመስ ማንን ጠቀመ ?[/size]
ህ) ግለሰቡን
ለ) የኦሮሞን ሕዝብ
ሐ) የኦሮሞን ወጣት
መ) መልሱ የለም
ይድረስ ለኢትዮጵያ ወጣት ( ቄሮ ወይም ፋኖ ) እንደ እንዝርት የሚያሾርህ እንደ ጎማ የሚያሽከረክርህን ተከትለህ አትግበስበስ
ይድረስ ለኢትዮጵያ ወጣት ከሰው ጋር አብሮ ለመኖር መስማማት ያስፈልጋል የተበረዘ የትላንትና ታሪክ እየሰማህ በስሜት አትንጉወድ፡፡
ፈላስፋው የየትየለሌው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4345
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: ምኒሊክ በዓድዋ ዓቢይ በስቶክሆልም፣ ኦስትሪያ ፣ኦስሎ፤ በራሺያ

Postby ቆቁ » Thu Oct 24, 2019 5:00 pm

ደግሞ በራሺያ ደገመው ፡
ለፖለቲካል ሳይንቲስቱ ፡
ስለ ፖለቲካ ብዙ መጣጥፎች ለጣፈው
ስለ ፖለቲካ በመላው ዓለም በመዙዋዝዋር ብዙ ለሚያውቀው

በነገራችን ላይ መንግስት ሲመሰረት በፍቅር በሰላም የተመሰረተበት የዓለም ክፍል ይኖራል ብለህ ትገምታለህ ብዬ አላስብም
አሜሪካ በለው አውሮፓ ያለ እልቂት መንግስት አልተመሰረተም
አንዱ በአንዱ ላይ በመቁዋዘም ነው መንግስትን የመሰረተው

"እኛም ነቅተናል ጉድጉዋድ ምሰናል
( በነገራችን ላይ አይጦች የሚያልቁት በድመት ምክንያት ሳይሆን የቆፈሩት እና የማሱት ጉድጉዋድ አናታቸው ላይ እንደ አዲስ አበባ ቤቶች እየተደረመስ መሆኑን እንዳንተ ገጠር ላደገ ወጣት መንገሩ በጣም ይከብዳል )
ሞታችንም መቃብራችንም ኦሮሚያ ይሆናል ብለን ጠቅለን ገብተናል" አልክና
ሳይውል ሳያድር ልክ በክፍለ ዓለማችን እንደተፈጠረው የመንግስት አፈጣጠር ክስተት በሐገራችንም ተፈጠረ ፡፡

መልካም ነው
ሁላችንም የምንፈልገው ይህንኑ ነው ፡
እትብታችን በተቀበረበት መቀበርን ሁላችንም የምንፈልገው ነው

ለመሆኑ ለአንት መታሰቢያ " አክቲቪስት ስለሆንክ " ምን ዓይነት ሐውልት ይሰራልኛል ብለህ ትገምታለህ ?
እንደ ምኒሊክ ያለ ሐውልት ወይስ እንደ ሐይለስላሴ ወይስ እንደ ቴዎድሮስ ወይስ እንደ ዮሐንስ ?

አይ ችግር ጥቂት ማወቅ አደገኛ ነው አሉ
ፈላስፋው ቆቁ
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4345
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: ምኒሊክ በዓድዋ ዓቢይ በስቶክሆልም፣ ኦስትሪያ ፣ኦስሎ፤ በራሺያ

Postby ቢተወደድ1 » Thu Oct 24, 2019 8:07 pm

ከምን ጎረቤት ይሻላል ..... ቤት ነው የሚባለው?
ሚኒሊክ ሰራዊት ላከ እንጂ የአድዋው ጀግና ራስ አሉላ ናቸው፡፡ ታሪክ አታባዳ

ቆቁ wrote:የቻሉ ያግዙናል
ያልቻሉት ይተዉናል
ያልገባቸው ይተቹናል
ያልፈለጉን ይቃወሙናል
እኛ ግን ወገባችንን ጠበቅ አድርገን የጀመርነውን ጨርሰን ሪባኑን እንቆርጣለን እንጂ ተስፋ አንቆርጥም


ይሄ ፍልስፍና ነው አይደለም እስቲ ሕዝቄል ጋቢሳን እንጠይቀው፡፡
አቦይ ስብሃት ነጋ ምን ይላል ስለዚህ ፍልስፍና
ሕዝቄል ጋቢሳ የቱ ጋ ነው ከላይ በተጠቀሰው ፍልስፍና ቦታው የሚደበው
ስብሃት ነጋ የቱ ጋ ነው ከላይ በተጠቀሰው ፍስልፍና ቦታው የሚመደበው

በነገራችን ላይ "መደመር " የሚለው ፍልስፍና ነው እንዴ
መደመር የመስቀል ምልክት ነው እንዴ?
መቀነስስ የምን ምልክት ይሆን የእንጨት
ማባዛትስ የምን ምልክት ይሆን ?
ማካፈልስ የምን ምልክት ይሆን?

በጠቅላላው የላቲን ፊደሎች የምን ምልክት ይሆኑ
የአማርኛ ፊደሎች የምን ምልክት ይሆኑ
እንደውም የእንግሊዘኛው T ፊደል የሮማውያን መስቀል ስለሚመስል መማር የለብንም ማንበብብም የለብንም
X የሚለው ፊደልና የማባዛት ምልክት ስለሚመሳሰሉ ምስጢራዊ የሆነ ነገር ስላለበት ከዛሬ ጀምሮ አናባዛም
እንዴት ያለ ነገር መጣ
መደመር ማለት መታዘል አይደለም ይህንን እንዳትዘነጉ
ፈላስፋው የየትየለሌው
ቢተወደድ1
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 507
Joined: Thu Sep 01, 2016 8:48 am
Location: Bisheftu

Re: ምኒሊክ በዓድዋ ዓቢይ በስቶክሆልም፣ ኦስትሪያ ፣ኦስሎ፤ በራሺያ

Postby ቆቁ » Fri Oct 25, 2019 3:54 pm

ስማ በትንሹም በትልቁም ?
የዋርካ ቄሮ ሆንክ እንዴ ?
Ethiopian forces

Shewa forces; Negus Negasti Menelik II: 25,000 rifles / 3,000 horses / 32 guns[7]
Semien forces; Itaghiè Taytu: 3,000 rifles / 600 horses / 4 guns[7]
Gojjam forces; Negus Tekle Haymanot: 5,000 rifles[7]
Harar forces; Ras Makonnen: 15,000 rifles[7]
Tigray and Hamasen forces; Ras Mengesha Yohannes and Ras Alula (Abba Nega): 12,000 rifles / 6 guns[7]
Wollo forces; Ras Mikael: 6,000 rifles / 5,000 horses[7]
Forces of the Ras Mengesha Yohannes Atikim: 6,000 rifles[7]
Forces of Ras Oliè and others: 8,000 rifles[7]
In addition there were ~20,000 spearmen and swordsmen as well as an unknown number of armed peasants.[7]

በደምብ ተመልከታቸው የአድዋ ጀግኖቻችንን
ማን በዚህ ድል ያልተካፈለ ኢትዮጵያዊ አለ ብለህ ነው ?
ኢትዮጵያ ማለት እነዚህ ጀግኖቻችን ናቸው

የእነዚህ ጀግኖች ስም በአንድነት ሲጠራ ኢትዮጵያ ማለት ይሆናል እንጂ ብሄር ብሄረሰቦች ሕዝቦች የሚል ትርጉም አልባ አደናጋሪ ቃል አይደለም፡፡
አሉላ አባ ነጋ ስትል ምኒሊክን፡ መጥራትህ ነው
ጣይቱ ብጡልን ስትጠራ አሉላ አባ ነጋን መጥራትህ ነው
ራስ መኮንን ስትጠራ ንጉስ ተክለ ሐይማኖትን መጥራትህ ነው
ገረሱ ዱኪ ስትጠራ ራስ መንገሻን መጥራትህ ነው ፡፡
እያልክ እያልክ ስትጠራ
አድዋ ስትል ወረኢሉ ማለትህ ነው
ዶግአሊ ስትል እምባላጌ ማለትህ ነው
ወረኢሉ ስብለህ ስትጠራ የቀበና ድልድይ መጥራትህ ነው
እያልክ እያልክ ስትጠራ
ምኒሊክ ስትል ኢትዮጵያ
አሉላ አባ ነጋ ስትል ኢትዮጵያ እያልክ እያልክ
መጨረሻው ላይ
[size=200]ኢትዮጵያ ላይ ትቀራለህ /size]
ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞት ኢትዮጵያ ይሉሃል ይህ ነው

ምን ለማለት ፈልገህ ይሆን ፡ የብሄር ብሄረ ሰቦች ሕዝቦች ፕሮፓጋንዳ የተጠናወተህ ዓይነት ፍጡር ነህ መሰለኝ

የኖቤል የሰላም ሽልማቱስ የተሰጠው ለማን ነው ?

ፈላስፋው የዬትዬለሌው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4345
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: ምኒሊክ በዓድዋ ዓቢይ በኦስሎ ፡ የገዳ ስርዓት በምኒሊክ አማካይነት ተጠናቁዋል ፡፡

Postby ቆቁ » Thu Oct 31, 2019 9:12 pm

እስቲ ወደ ቁም ነገሩ
ፕሮፌሰር አስመሮም አና የገዳ ስርዓት
የገዳ ስርዓት በየስምንት ዓመቱ በቅደም ተከተል ወታደራዊ ኢኮኖሚያው ፖለቲካዊና መንፈሳዊ ሐላፊነቶችን የሚሸከም የመደቦች [የሉባዎች] ሥርዓት ነው አያንዳንዱ ገዳ መደብ ለአንድ የተወሰነ ወቅት[ ስምንት ዓመት] በስልጣን ላይ ይቆያል ይህ በስልጣን ላይ የሚደረግ የስምንት ዓመት ቆይታ የሚጀምርረውና የምፈጸው መደበኛ በሆነ የስልጣን ሽግግር ክብረበዓል ነው ስልጣን ተረካቢው መደብ ስልጣኑን ከመረከᎇ በፊት ቀደምት ትውልዶች ያልወረሩትን አካባቢ በወረራ መያዝ አለበትይህ ለየት ያለው ጦርነት ቡታ ይባላልቡታ በየስምንት ዓመቱ ሳይተጉዋጎል የሚደረግ ጦርነት ነው
እዚህ ላይ ፈላስፋው አንድ ጥያቄ አለው
እስከ መቸ ድረስ ይህ ጦርነት ሳይተጉዋጎል
ይደረጋል
?
ይህ ሳይተጉዋል የሚደረግ ጦርነት እስክ ወዲያኛው እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ቢጉዋዝ መድረሻው
የት ነው ?


ፈላስፋው በኢትዮጵያዊነቱ እና በኦሮሞ በሉት በአማራ በትግራይ በሉት በሻንቅላ ወይም በጉራጌ ወይም በወላይታ በስማንያ የኢትዮጵያ ክቡራን ልጆች ኩራት እየተሰማው የሚዘባነነው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4345
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: ምኒሊክ በዓድዋ ዓቢይ በኦስሎ ፡ የገዳ ስርዓት በምኒሊክ አማካይነት ተጠናቁዋል ፡፡

Postby ቆቁ » Sun Nov 03, 2019 8:59 pm

የገዳ ስርዓት ኢትዮጵያን ለመመስረት ከክርስትና እምነትና ከእስልምና እምነትት ጋር በመሆን ታላቁን ሚና ተጫውቶአል

ከጎንደር እስከ ባሌ ፡ ከቆቦ እስከ ነቀምት የትኛው የየትኛው ወገን እንደሆነ ለመለየት እስከሚያስቸግር ድረስ ታሪካዊ ሂደት ተከናውኖእል

ፕሮፌሰር አስመሮም እንዳስቀመጡት " በየስምንት ዓመቱ የሚደረግ የማይተጉዋጎል ጦርነት" ያሰለጠነው ኢትዮጵያዊ ነው ኢትዮጵያን የመሰረተው፡ ይህ ግጭት በዘመነ መሳፍንት በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል የተከሰተ እንደነበረ ታሪክ ፍርጥርጥ አድርጎ ያስረዳል፡፡

አንባቢ ሆይ አማርኛ መናገር ዘርን እንደማይወክል ከብዙ በጥቂቱ የምታውቅ ይመስለኛል

ምኒሊክ ራሱ በገዳ ትውፊት ሰልጥኖ ከዛም በገዳ ትውፊት የሰለጠነውን ጦር ይዞ ነው ኢትዮጵያን ኢትዮጵያን ያደረገው
ተቃውሞ ወይም ተጨማሪ ሐሳብ አለ ?

ዓቢይ ከዚህ ስርዓት የወጣ መሪ ነው ብለን እናስባለን በመሆኑንም እርስ በርሱ የተደበላለቀ ችግር ቢያጋጥመውም እንደ ምኒሊክ በአሸናፊነት እንደሚወጣ በቀጥታ እኛ ፈላስፋዎች ይገባናል

እስክንድር ነጋን በተመለከተ ለመላው ከውጭ ወደ ሐገር ገብተው በቦዲጋርድ ለሚጠበቁ ጥሩ ምሳሌ እየሰጠ በመሆኑ ከሱ ትምህርት መውሰድ ይቻላል ፡፡አስተሳሰቡም ትክክል ለመሆኑ ፈላስፋው አንድም ጥርጣሬ የለውም ፡፡ ዓቢይም ሆነ ታከለ ኡማ፡ እስክንድርን የወደሁዋላ መከተላቸው ባይቀርም ሁኔታዎችን ማስተካከል ግን የሚጠበቅባቸው ይሆናል

ሌላው የፖለቲካ ፓርቲ አባል ፖለቲካ በጉዋደኝነት ሳይሆን በሰለጠነ አስተሳሰብ ሐሳብን ማቅረብ ማለት ነው፡፡ እገሌ እንደዚህ ካለ እኔም እንደሱ እለልሁ የሚል የጭነት አስተሳሰብ ፖለቲካ ሳይሆን እንደ አህያ ዳውላ መጫን ነው፡፡ ትንተናውን ለወደፊቱ እናስቀምጠው

ፈላስፋው የየትየለሌው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4345
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: ምኒሊክ በዓድዋ ዓቢይ በኦስሎ ፡ የገዳ ስርዓት በምኒሊክ አማካይነት ተጠናቁዋል ፡፡

Postby ቆቁ » Mon Nov 04, 2019 9:22 pm

እስቲ እናውራ


ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሰላምና ደህነንት ማውራት ከተፈለገ፡ እንዴት ነበር የነገስታቱ ሁኔታ ብለን መከራከሩ ወይም መዘበራረቁ የሞተን እንደ መውቀስ ይሆናል ብሎ ፈላስፋው ያምናል፡፡
የየትኛው የዓለም ክፍል ነው በሞቱት ነገስታት እና ባለፈ ታሪክ ሲነታረክ ሲከሳከስ የሚታየው
የባግዳድ ፡ የደማስቆስ ጦርነት ?

ኮሙኒስም የነገስታት ታሪክ አልነበረም፡ የፓሪስ ኮሙን የነገስታት ታሪክ አልነበረም፡የነ ማርክስ መጣጥፍ የነገስታት ታሪክ አልነበረም
የተማሪዎቹ እንቅስቃሴ የፊውዳሉን ስርዓት ለመጣል ከዛም በጎሳ ለመፈነካከት ነበር?
እንዴት ከእኩልነት የተማሪዎች እንቅስቃሴ ወደ ጎሳ እንቅስቃሴ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ትግል ተወነጨፈ ?
ከፊውዳሉ ስርዓትስ በሁዋላ
የእንዱስትሪ አብዮት መጣ ከዛስ ?
የሰው ልጅ ከስራ ጭቆና የሚወጣበትን ትግል ጀመረ ከዛስ?
የነገስታቱ ታሪክ የቱሪስት መስህብ ሆኖ ታሪክ ቀረ
ከዛስ ?
ትምህርት፣ የስራ እድል ፣ ከዛስ?
ጤንነት ፡ከዛስ?
ሰው በሰውነቱ ተከብሮ የሚኖርባት ሐገር ፡ ከዛም ያለብዝበዛ ብልጽግና ፡የሚሉት ጥያቄዎች የዓለምን ክፍል እያተራመሱ በሚገኙበት ሰዓት
እኛስ ?
እኛማ ከኢንዱስትሪ አብዮት በፊት እንደነበረው የመሳፍንት አገዛዝ እየተተራመስን እንገኛለን፡፡
ምን ተይዞ ጉዞ
በሚቀጥለው ምርጫ ምን ተይዞ ይሆን ለምርጫ የሚቀረበው ?
ብሄርን ሆስቴጅ አድርጎ ለምርጫ መቅረብ ? ያ የሚያጠያይቅ ይሆናል ይላል ፈላስፋው
ወደ አለፉት ነገስታት ስንመለስ የጁሊየስ ሴዛር ቤተ መንግስት ፍርስርራሽ የሚሊዮን ቱሪስት መሳቢያ ሆኖእል
ከዛም በአንበሳ መንጋ የተገደሉትም ግላዲያተሮች ሌሎች በሱ አገዛዝ የተደመሰሱ በሙሉ ስለ ዛ ጉዳይ ምኑም ምናምኑም ትዝ አይላቸውም
በመጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈውም ለትዝታ ብቻ ነው እንጂ ፋይዳ የሚያመጣው ነገር እንደሌለ ሁሉም የሚያውቀው ነው፡፡

እኛስ ለምን እንደዛ አንሆንም ?
የስራ እድል ፡ ኢዱኬሽን ፡ ጤንነት ፡ ደህነነት ፡ ስለ አካባቢ ጽዳት ስለ ኢንቫይሮሜንት ፡ ስለ ደን ፡ ስለ መንገድ ፡ ስለ ትምህርት ቤት
ስለ ጤና ጣቢያ ፡ ስለ ጡረታ መሻሻል ፡ ስለ ደመወዝ የመሳሰሉት የሰውን ልጅ ወደ ብልጽግና እኩልነት የሚመሩ ጉዳዮች እያሉ ለምን ወደማይሆን ሌላ የክልል ምሽግ እንገባለን፡፡

ፈላስፋው የየትዬለሌው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4345
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: ምኒሊክ በዓድዋ ዓቢይ በኦስሎ ፡ የገዳ ስርዓት በምኒሊክ አማካይነት ተጠናቁዋል ፡፡

Postby ቆቁ » Thu Nov 07, 2019 11:20 pm

እስቲ እናውራ
ብሄር ብሄረሰቦች ህዝቦች የሚለው ማደናገሪያ ቃል መቸ ተጀመረ ?
ብሄር የሚለው ቃል ሐገር ማለት ነው ትርጉሙ ወይም እግብአብሄር የሚለውን ቃል ብንወስደው ብሄር የሚለው ቃል እዚህ ላይ ዩኒቨርስንም ያካትታል ፡፡ እግዚአብሄር ማለት ፈጣሪ ማለት ነው ፡፡
ጥያቄው እዛ አይደለም ?

የብሄር አቀንቃኖች ከብሄር በታች ያለውን ለምን ለመርሳት አስፈለጋቸው?
ለመሆኑ ሐገራችን በብሄራት መከፋፈል የጀመረችው መች ነው?
ከብሄር በታች ሌላ ነገር ይኖር ይሆን ለምሳሌ ጎሳ ?
በትክክል ጎሳ ነበር ይህንን ጎሳ ለማውራት ግን ጽንፈኛ ብሄር አክራሪዎች መናገር አይፈልጉም፡፡
በቁዋንቁዋ አንድ ሆነው በጎሳ መናደፍ እንደነበረ ታሪካችን ያስረዳናል ፡፡ ከጎረቤት ሱማሊያም መማር አያቅትም
ቁዋንቁዋ የአንድን ሕዝብ መግለጫ ቢሆንም ነገር ግን የሰብዓዊ መብት ማስከበሪያ መሳሪያ አይደለም፡፡
ባህል የአንድን ሕዝብ መግለጫ ነገር ቢሆንም የሰብዓዊ መብትን ማስከበሪያ መሳሪያ አይደለም
ለምሳሌ ጥንቆላ በአንድ ባህል ውስጥ ብቻ የሚፈጠር አይደለም በየባህሉ ይለያይ እንጂ ጥንቆላ በመላው ዓለም የሚገኝ ነገር ነው ፡፡
በጥንቆላ አማካይነት አንድ ሰው ለሞት ቢዳረግ የሰብዓዊ መብትን መጣስ ነው
ከዛስ በጎሳ ታሪክ ውስጥ የሰው ልጅ ሰብዓዊ ህልውናው እንዴት ነበር የተረጋገጠው ?

ለዚህም ነው ፈላስፋው ፖለቲካ መንግስትና ሕገመንግስት ከመጀመሪያው መጀመር ይገባቸዋል የሚለው
ይህ የመጀመሪያው ደረጃ ሰብዓዊ መብትን ማክበርና ማስከበር ነው ነው
ማክበር ሲባል እያንዳንዱ ግለሰብ የእያንዳንዱን ግለሰብ ሰብዓዊ ሕልውና ማክበር ሲገባው ከዛ ያለፈውን እዳ ደግሞ መንግስት ያስከብራል ማለት ይሆናል
በጅምላ እየጀቦኑ የብሄር የሐይማኖት እያሉ እሪ ማለትን ትቶ ግለሰባዊ ጥፋትና ግለሰባዊ መብቶች ሕጋዊ መፍትሄ ማግኘት እንዲኖርባቸው በጋራ መልፋቱ ለሐገርም ለወገንም ይጠቅማል፡
ይላል ፈላስፋው ቆቁ
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4345
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: ምኒሊክ በዓድዋ ዓቢይ በኦስሎ ፡ የገዳ ስርዓት በምኒሊክ አማካይነት ተጠናቁዋል ፡፡

Postby ቆቁ » Fri Nov 08, 2019 7:00 pm

አንድ ሐሳብ አለኝ ዓቢይ

በሰላም ግቡ ብለህ ያስገባሃቸውን በሰላም ውጡ ብለህ ብትሸኛቸው ሁሉም ነገር ሰላምና ፍቅር ይሆናል
ቆቁ ፈላስፋው የየትየለሌው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4345
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Next

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 6 guests