ሃበሻ የሚለው መጠርያ አንድ ያደርገናል ወይስ ይከፋፍለናል?

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ሃበሻ የሚለው መጠርያ አንድ ያደርገናል ወይስ ይከፋፍለናል?

Postby ዘርዐይ ደረስ » Fri Jan 27, 2012 5:43 pm

ሰላም ለሁላችሁም እያልኩ:-

ከዋርካ ከራቀ ዓመታት ቢቆጠሩም አንድ ዋቆ የሚባል ንቁ ተሳታፊ አበሻ የሚለውን መጠርያ ትተን ኢትዮጵያ በሚለው ብቻ መጠቀም አለብን የሚል አቋም ይዞ ይንቀሳቀስ እንደነበር አስታውሳለሁ::ታዲያ ሰሞኑን የኦነግ ደጋፊዎች ነን የሚሉ ግለሰቦች በከፈቱት አንድ የpaltalk ክፍል ውስጥ የምሰማው ነገር በዚህና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ በጥልቀት እንዳስብ አድርጎኛል::በእርግጥ ኢትዮጵያዊነትንም ቢሆን የማይቀበሉ አሉ::ሆኖም ግን ኢትዮጵያዊነትን የሚቀበሉት ቢሆኑም እንኳ ሃበሻ የሚለው መጠርያ እኛን አይወክልም እንዲያውም እኛን አግልሎ ኤርትራውያንን የሚያካትት ነው ይላሉ::እኔ በዚህ ጉዳይ ላይ ምን ዓይነት አቋም እንደምይዝ ግራ ገብቶኛል::እናንተስ ምን ትላላችሁ?
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1175
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: ሃበሻ የሚለው መጠርያ አንድ ያደርገናል ወይስ ይከፋፍለናል?

Postby የዘመኑ ልሳን » Fri Jan 27, 2012 6:10 pm

አንዳንድ ሰዎች አበሻ እና አቢስንያ የሚለውን ቃል አማራና ትግሬን ብቻ የሚመለከት አድርገው ያቀርባሉ:: ይህን ነገር TPLF ሳይቀር ተጠቅሞበታል::

አንድ ሰው አበሻ አይደለሁም ካለ ምርጫው ነው ብንል እንኳን ሌላውን ግን አበሻ ነኝ አትበል የሚል ከሆነ ይህ ሌላ ጉዳይ ነው:: ፊት ከተሰጠው ትንሽ ቆይቶም ኢትዮጵያ የሚለው ቃል የነፍጠኛ ነው እንቀይር ከማለት አይመለስም::

ዘርዐይ ደረስ wrote:ሰላም ለሁላችሁም እያልኩ:-

ከዋርካ ከራቀ ዓመታት ቢቆጠሩም አንድ ዋቆ የሚባል ንቁ ተሳታፊ አበሻ የሚለውን መጠርያ ትተን ኢትዮጵያ በሚለው ብቻ መጠቀም አለብን የሚል አቋም ይዞ ይንቀሳቀስ እንደነበር አስታውሳለሁ::ታዲያ ሰሞኑን የኦነግ ደጋፊዎች ነን የሚሉ ግለሰቦች በከፈቱት አንድ የpaltalk ክፍል ውስጥ የምሰማው ነገር በዚህና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ በጥልቀት እንዳስብ አድርጎኛል::በእርግጥ ኢትዮጵያዊነትንም ቢሆን የማይቀበሉ አሉ::ሆኖም ግን ኢትዮጵያዊነትን የሚቀበሉት ቢሆኑም እንኳ ሃበሻ የሚለው መጠርያ እኛን አይወክልም እንዲያውም እኛን አግልሎ ኤርትራውያንን የሚያካትት ነው ይላሉ::እኔ በዚህ ጉዳይ ላይ ምን ዓይነት አቋም እንደምይዝ ግራ ገብቶኛል::እናንተስ ምን ትላላችሁ?
የዘመኑ ልሳን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2672
Joined: Tue Jun 07, 2005 7:16 am
Location: USA

Re: ሃበሻ የሚለው መጠርያ አንድ ያደርገናል ወይስ ይከፋፍለናል?

Postby ሓየት11 » Fri Jan 27, 2012 6:16 pm

ዘርዐይ

አንድን አገር አስተሳስሮ በአንድ ሊያቆያት የሚችል ነገር ጠንካራ የኢኮኖሚ አቅም መገንባት ሲቻልና ፍትሀዊ በሆነ መንገድ ዜጎች ከዚሁ የኢኮኖሚ አቅም እኩል ተጠቃሚ መሆን ሲችሉ ነው:: ከዛ ውጪ አንዴ ኦሮሞ አትበሉን ሌላ ጊዜ ራሳችሁን አበሻ ብላችሁ አትጥሩ ስለተባለ አንድ ሊያደርገንም ይሁን ሊበታትነን አይችልም:: አባቶቻችን ጋላም ይሁን አበሻ ከስሙ ችግር አልነበረባቸውም:: ችግሩ የመጣው ድህነት ሲስፋፋ, የኢኮኖሚ አድልዎ ሲታይ, ፍትህ ሲጓደልና ጭቆና ሲበዛ ወዘተ ነው :: እነዚህ ችግሮች ዛሬም እስካልተወገዱ ድረስ እነሱ የፈለጉትን ስም በመቀበል ወይም ያልፈለጉትን በመጣል የትም አይደረስም:!:ዘርዐይ ደረስ wrote:ሰላም ለሁላችሁም እያልኩ:-

ከዋርካ ከራቀ ዓመታት ቢቆጠሩም አንድ ዋቆ የሚባል ንቁ ተሳታፊ አበሻ የሚለውን መጠርያ ትተን ኢትዮጵያ በሚለው ብቻ መጠቀም አለብን የሚል አቋም ይዞ ይንቀሳቀስ እንደነበር አስታውሳለሁ::ታዲያ ሰሞኑን የኦነግ ደጋፊዎች ነን የሚሉ ግለሰቦች በከፈቱት አንድ የpaltalk ክፍል ውስጥ የምሰማው ነገር በዚህና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ በጥልቀት እንዳስብ አድርጎኛል::በእርግጥ ኢትዮጵያዊነትንም ቢሆን የማይቀበሉ አሉ::ሆኖም ግን ኢትዮጵያዊነትን የሚቀበሉት ቢሆኑም እንኳ ሃበሻ የሚለው መጠርያ እኛን አይወክልም እንዲያውም እኛን አግልሎ ኤርትራውያንን የሚያካትት ነው ይላሉ::እኔ በዚህ ጉዳይ ላይ ምን ዓይነት አቋም እንደምይዝ ግራ ገብቶኛል::እናንተስ ምን ትላላችሁ?
ሓየት11
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2945
Joined: Sun Apr 06, 2008 7:34 pm
Location: ላን'ሊይ

Re: ሃበሻ የሚለው መጠርያ አንድ ያደርገናል ወይስ ይከፋፍለናል?

Postby ዘርዐይ ደረስ » Tue Nov 05, 2019 9:19 am

ይህ ጉዳይ ኢትዮጵያ ውስጥ ከምን ጊዜውም በበለጠ አሳሳቢና አወዛጋቢ ሆኗል፡፡
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1175
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: ሃበሻ የሚለው መጠርያ አንድ ያደርገናል ወይስ ይከፋፍለናል?

Postby ቢተወደድ1 » Thu Nov 07, 2019 3:14 pm

ኦሮአማራን ጠይቅ፤ በመደመር ሂሳብ እየተቀነሰ ያለው ማህበረሰብ የበለጠ ማብራራሪያ ይሰጥሀል፡፡
ለነገሩማ ኦነግ በለንደን ስብሰባው ላይ ዶር. አብዮት ስልጣን ከመያዙ በፊት የተናገረው ነው፡፡ አበሻም ኢትዮጵያዊም አይደለንም ያሉት እነሱ ናቸው፡፡ ስለዚህ የአንድነት ጥያቄው ራሱ በጥያቄ ምልክት ዉስጥ ነው ያለው፤ በአሁኑ ሁኔታ፡፡
እነታማኝም በዲሲ ሰላማዊውን ሰልፍ ጀምረውታል፤ የጨረሱ መስሎዋቸው ነበር፡፡ እይ በአጭር ርቀት ማየት የሚያመጣውን ጣጣ ከ28 ዓመት በኋላ ተረዲት፡፡ ቂቂቂቂ
ቢተወደድ1
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 358
Joined: Thu Sep 01, 2016 8:48 am
Location: Bisheftu

Re: ሃበሻ የሚለው መጠርያ አንድ ያደርገናል ወይስ ይከፋፍለናል?

Postby ዘርዐይ ደረስ » Sat Nov 09, 2019 6:54 am

ቢትወደድ፡አፋርናሱማሌ አበሻ የሚሉት ክርስትያኑን ክፍል ነው ሲባል እሰማ ነበር፡፡አሁን ግን ክርስትያንም ሆኖ ሐበሻ እይደለሁም የሚለው የህብረተሰብ ክፍል ቁጥሩ ቀላል አይደለም፡፡
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1175
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests