የፖለቲካል ፡ሳይንስ፡ ምሩቅ ፡ወይስ፡ የሆሊገን፡ መሪ !
በፈስ፡ ቡክ፡ ሐገር፡ ተቃጠለ፡፡
በፈስ፡ ቡክ፡ እሪታው፡ ተቀጣጠለ፡፡
በፈስ፡ ቡክ፡ ዘረፋው፡ ተጡዋጡዋፈ፡፡
በፈስ፡ ቡክ፡ ሰው፡ አለቀ፡፡
በፈስ፡ቡክ፡ ቤት፡ ተቃጠለ፡፡ ንብረት ወደመ፡፡
ፈስ ቡክ ታህሪር አደባባይ ሁሴን ሙባረክን ለመጣል ባደረገው አስተዋጽኦ በመላው ዓለም አድናቆንት ሲያተርፍ
በኛስ ?
በፈስ፡ ቡክ፡ ሐገር፡ ተቃጠለ፡፡
በፈስ፡ ቡክ፡ እሪታው፡ ተቀጣጠለ፡፡
በፈስ፡ ቡክ፡ ዘረፋው፡ ተጡዋጡዋፈ፡፡
በፈስ፡ ቡክ፡ ሰው፡ አለቀ፡፡
ፈላስፋውን፡ ቀልቡን፡ የሳበው፡ ተደረገ ፡ለተባለው፡ የስልክ ፡ጥሪ፡ ማን ፡አንደሆነ ፡የማጣራት ፡ተግባር፡ ይከናወናል ፡የሚለው፡ የሽመልስ፡ አብዲሳ፡ አነጋገር፡ ነው ፡፡
ለመሆኑ፡ በውድቅትም ፡ሆነ፡ በጠራራ ፡ጸሐይ ፡ ማን ፡አንደደወለ፡ ተጣርቶ፡ ቢታወቅ፡ የጠፋውን፡ ንብረት ፡. የጠፋውን፡ የሰው፡ ሕይወት ፡ማስመለስ ፡ይቻል ፡ይሆን ?
በነገራችን፡ ላይ፡ ራስህ፡ ሽመልስ፡ አብዲሳ፡ አንደዚህ፡ ያለ፡ ጥሪ ፡ለጠባቂዎችህ፡ ቢላክ፡ በፈስ፡ ቡክ ፡ድረሱልኝ፡ ልትል ፡ይሆን?
ከዛስ፡ ማን ፡ይደርስልህ ፡ይሆን? ፖሊስ፡ ወይስ፡ ቄሮ?
ሽመልስ፡ ሆይ፡ ለፖለቲካል፡ ሳይንቲስቱ፡ ቦዲ፡ ጋርድ፡ ከማቆም ፡ቄሮን፡ መበታተን፡ የመጀመሪያው፡ ተግባርህ ፡መሆኑን ፡የዘነጋህ፡ ይመስላል፡፡
ለኢትዮጵያ ፡ወጣቶች፡ ስራ ፡መፈለግ ፤
የስራ፡ ስልጠና፡ የሚያገኙበትን፡ መስክ መክፈት፤
በአውቀት፡ አንዲያድጉ፡ ማድረግ፡ ዋናው፡ የስራ፡ ነጥቦችህ ፡መሆን ፡ይገባቸዋል ፡ይላል፡ ፈላስፋው፡፡
ይድረስ፡ ለሚመለከተው፡ ሁላ ፡፡
የፖለቲካል፡ ሳይንቲስቱ፡ ቦዲ፡ ጋርዶች፡ በስልክ፡ ይነሱ፡ ተባለ፡ አይነሱ፡ ተባለ፤ የፖሊስ፡ አዛዥ ይደውል ፡ ግለሰብ፡ ይደውል፡ ያ፡ አይደለም፡ ጥያቄው ፡፡
የሰው፡ ልጅ፡ ተቀጠፈ፡፡
ንብረት፡ ወደመ፡፡
ሐገር፡ ተተረማመሰ፡፡
ሆሊጋኒዝም ፡በፖለቲካል፡ ሳይንስ ፡የሚመራ፡ አይደለም ፡፡
የሆሊገኑ መሪ
እኔን፡ ወጥመድ፡ ውስጥ፡ ሊከቱኝ፡ ነው፡ ይበል፣
ወይም፡ ተንኮል፡ አለበ፡ት ይበል፤
ወይም፡ ሴራ፡ ነው፡ ይበል፡ ያ ፡አይደለም፡ ጥያቄው ፤
የሰው፡ ልጅ፡ ተቀጠፈ፡፡
ንብረት፡ ወደመ፡፡
ሐገር፡ ተተረማመሰ፡
አንግዲህ የሆሊገኑ መሪ በፈስ ቡክ ለማንኛውም የስልክ ጥሪ ( ወፍ፡ በረረ ፡ ነፋስ፡ ነፈሰ፡) ብሎ ፡በፈሳ፡ ቁጥር፡ ሐገር፡ ሊተረማመስ፡ መሆኑ፡ አልገባህ ፡ይሆን?
ለመሆኑ የሚቀጥለው ለሆሊገን መሪ የሚደወለው ስልክ ምን አይነት የጥሪ መልክት ይኖረው ይሆን?
ሐገር፡ የሚያተረማመስ፤
ወይስ፡
ቺኮችን፡ የሚያሳሳቅ፡፡
ፈላስፋው የየትየለሌው