የፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት መግለጫ!

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

የፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት መግለጫ!

Postby ኳስሜዳ » Sat Sep 26, 2020 5:15 pm

“አሸባሪና አገር በታኝ ቡድን ጋር ምንም ዓይነት ኅብረት የለንም” -የፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት:: አሸባሪና አገር በታኝ የሆነ አጀንዳ ካላቸው ቡድኖች ጋር አንዳችም ዓይነት ኅብረት የለንም ሲል የኢትዮጵያ ፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት አስታወቀ። ጥምረቱ በላከው መግለጫ የፌዴራሊስት ኃይል ሆኖ ለመቀጠል በሀሳብም ይሁን በኢኮኖሚ አሀዳዊ ቁመና ይዞ መቀጠል ተገቢ አይደለም ብሏል። ሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ሕወሓት) የፌዴራሊስት ኃይሎችን በመጠቀም የሥልጣን ጥማቱን ለማሳካት ሲፍጨረጨር ተመልክተነዋል ብሏል ጥምረቱ። ሕወሓት አሁንም ከፌዴራል ኃይሎች ጋር እየሰራሁ ነው በማለት የትግራይን ሕዝብ እያሳሳተ እንደሆነም አስታውቋል። ሕወሕት ከፌዴራሊስት ኃይሎች ጋር እየሰራሁ ነው በማለት ኅብረተሰቡን እያወናበደ እንደሚገኝ ጥምረቱ አመልክቷል።

በፌዴራሊስት ኃይሎች ጥላ ሥር የተሰባሰብን አካላት ሕወሓትን ከዚህ በፊት አባረን ውይይታችንን በአዲስ አበባ እያካሄድን እያለ ከፌዴራሊስት ኃይሎች ጋር እየሰራሁ ነው በማለት ኅብረተሰቡን እያወናበደ እንደሚገኝ ጥምረቱ ገልጿል።

የሕወሐት እውነተኛ ማንነት ደግሞ ሀገርን በፌዴራል እሳቤ አስተዳድራለሁ በሚል የይስሙላ የክልል አስተዳደር ዘርግቶ የእርሱን ሀሳብ ብቻ ሲያስፈፅም የነበረ መሆኑን ጥምረቱ አመልክቷል።
ሕወሓት ሀገር ያመነጭችውን ሀብት በኢፍትሐዊነት በማካበት ለአመራሮቹና ለቤተሰቦቻቸው የግል መፈንጫ ሲያደርግ የነበረ ኃይል መሆኑን መግለጫው አስታውሷል። መግለጫው አያይዞም ሕወሓት መሻሻል የማያሳይና ወቅታዊውን የሀገሪቱን ፖለቲካ የማይዋጅ፤ የሀሳብ ድርቀት የገጠመው ሆኖ በመገኘቱ ሕወሐትና ኢዲህንን በይፋ ከጥምረቱ መሰናበታቸውን ህዝቡ እንዲረዳ አሳስቧል።

የኢትዮጵያ ብሕር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ይህን ተረድው በሥማችን እየነገደ ያለውን የሕወሐት ቡድን ከጥምረቱ ጋር በጋራ በመሆን እንዲታገል ጥሪ አቅርቧል። ሕወሐት እያራመደ የሚገኘው አቋም ኢትዮጵያ በፌዴራላዊ አስተዳደር እንዲሁም ፍትሃዊነትና እኩልነት ባረጋገጠ መልኩ እድትመራ የሚፈለግ አይደለም ብሏል - ጥምረቱ በመግለጫው። ሕወሓት ከዚያ ይልቅ “እኔ ከሞትኩ …” በሚል አመለካከት ˝እኔ ካልመራኋት ትበታተን˝ የሚል አደጋ ከፊታችን የደቀነ መሆኑን መግለጫው አትቷል። ሕወሓት ኢትዮጵያን ለውጭ ጠላቶች አሳልፎ ለመስጠት የማያመነታ በመሆኑ በሕግ አግባብ እንዲጠየቅና እንዲታረም እየሠራ መሆኑንም ጥምረቱ አስታውቋል።
Image
ኳስሜዳ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2676
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Re: የፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት መግለጫ!

Postby ቢተወደድ1 » Mon Sep 28, 2020 12:59 pm

አማራን አባይን ተሻግረው ምን ያህል እንዳሞኙዋቸው በአደባባይ ከተነገረን በኋላ፤ ባሕር ዳር ጠርተው ያሞኛቸውን ግለሰብ ካባ አልብሰው ሸለሙት፡፡ ቂቂቂቂ
ይሄን የመሰል ስብእና በአደባባይ ሲሸጥና ሲዋረድ ማየት በ21ኛው ክ/ዘመን የፊልም ክንውን እንጂ እውነት አይመስልም ነበር፡፡
አይ አማራ (ብአዴን) ይሄን ያህል ነው ዜሮ ያገባችሁት፡፡ ያ ግራ የገባውስ አብን የምትሉት፤ ለዚህ ምላሽ አይኖረውም?? እንደዚህም ዘቅጣቹህ አልታያችሁም፡፡ አቤት በላይ ዘለቀ ይሄን ቢሰማ ምን ያረጋችሁ እንደነበር መተንበይ አይከብድም፡፡ ግን ያምርባቹሃል ቀጥሉበት፤ በርቱ፡፡
በአደባባይ ወጥቶ መሳደብ፤ ሰውን ማንቋሸሽ፤ ጥላሸት መቀባት ለሽልማት የሚያበቃ ቢሆን ኖሮ ሕወሃት እነ ታማኝ፤ አበበ ገላውና ኢሳትን ከነግብር አበሮቹ ስንት በሸለመ ነበር፡፡ ለነገሩ ግን የአማራ ክልል ገዢዎች እውነታው ስላስደሰታቸው ባሕር ዳር ድረስ ጠርተው ሸለሙት፡፡ ጉድ በል አማራ; ዳስህን ጥለህ ሃዘን ተቀመጥ፡፡ እንደዚህም ተዋርዳቹህ አታቁም፡ መዋረዱንም የታለመዳችሁን ነው የምትመስሉት፡፡ ማን ነበር እስኪ አስታውሱን፤ የህወሃት ተላላኪ ነበርን ያለው? አገር የተበጠበጠችውም ተላላኪ ለሃላፊነት እንደማይበቃ ብቃታቹህ የታየበት የስራው ውጤት በመሆኑ ነው፡፡ ተላላኪነቱን ግን እንደቀጠላችሁበት ነው፤ ለግብጽና ኤርትራ፡፡ ማለቅለቁንም ተክናችሁታል፡፡ ታሪክ ሳይሆን እኛው እንፋረዳቹሃልን፡፡
ታማኝና ቴድሮስ ካሳሁን እናንተንም ክስተቱን አይታቹህ ምንም እንዳልተፈጠር አንደበታቹህ ሲዘጋ ስናይ፤ አፋቹህ ለሰብአዊነትና ለዲሞክራሲ ሳይሆን የዘር ጥላቻን ሲያርከፈክፍ እንደነበረ ካወቅን ውለን ስላደርን አልገረመንም፡፡ ይሄን አይታቹህ ግን ዝም ትላላቹህ ብሎ ያሰበ አልነበረም፡፡ እናንተም አብራቹህ ደነዘዛቹህ?
የሚቀጥለውን ድራማ ለማየት ያብቃን፤
ሁለተኛውን ሽልማት ጎንደር ከተማ ታስተናግዳለች፡፡
ቢተወደድ1
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 392
Joined: Thu Sep 01, 2016 8:48 am
Location: Bisheftu


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 7 guests