ብርጋዴን ጀነራል ከበደ ሸሪፍ ይባላል ተንቤን አካባቢ የጁንታዉን ጦር ይመራ ነበር የኢትዮጵያ መከላክያ ሰራዊት 31 ኛ 22 ኛ ንስር ክፍለጦር አዛዥ የነበረ ሲሆን ህወሓት በከፈተው ጦርነት የጁንታውን ልዩ ሀይል በትግራይ ክልል ሲመራና ሲያደራጅ የነበረና በመንግስት በጥብቅ የሚፈለግ ነበር:: ብ/ጄ ከበደ ሸሪፍ የጁንታውን ጦር እየመራ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በተደረገበት ጥቃት የሚመራው ልዩ ሀይል ተበትኖ ብ/ጄ ከበደ ህይወቱ ማለፉ ተረጋግጧል:: ከብ/ጄ ከበደ ሸፊፍ ጋር የነበሩና ለግዜው ማንነታቸውን መለየት ያልተቻሉ ስድስት የህወሓት የጦር መኮንኖች ህይወታቸው አልፏል::
ብ/ጀነራል ፀጋዬ ማርክስ ይባላል የቀድሞ 31 ክፍለጦር አዛዥ እና የማእከላዊ እዝ ምክትል አዛዥ የጄኔራል አበባዉ ታደሰ ምክትል ነበር፣ ብ/ጄ ፀጋዬ የመራው የትግራይ ልዩ ሀይል በኢትዮጵያ መከላክያ ሰራዊት ተደምስሶ ብ/ጄ ፀጋዬ ህይወቱ ማለፉ ተረጋግጧል::