ሰበር ዜና፣ ጄነራል ታደሰ ወረደ ሲከበብ ሌሎች 2 ጄነራሎችና ከፍተኛ መኮንኖች ተገድለዋል!

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ሰበር ዜና፣ ጄነራል ታደሰ ወረደ ሲከበብ ሌሎች 2 ጄነራሎችና ከፍተኛ መኮንኖች ተገድለዋል!

Postby ኳስሜዳ » Sun Jan 10, 2021 8:01 pm

ከአገር መከላከያ ሠራዊቱን በማስከዳት ተግባር ላይ ተሰማርተው የነበሩና በጦርነቱ ከሠራዊቱ ከድተው ጁንታውን የተቀላቀሉ ጄነራል መኮንኖች፣ ከፍተኛ መኮንኖች፣ መስመራዊ መኮንኖች እና የግል ጥበቃዎቻቸው ላይ እርምጃ መወሰዱንም የመከላከያ ሠራዊት ኃይል ስምሪት መምሪያ ሓላፊ ብርጋዴር ጄነራል ተስፋዬ አያሌው ለኢዜአ ገልጸዋል።

ብርጋዴር ጄነራሉ ጀግናው የአገር መከላከያ ሠራዊት፣ የፌዴራል ፖሊስ እና የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ጥምር ኃይል የፍተሻ ተግባሩን አጠናክሮ መቀጠሉንም ተገልጿል።

ብርጋዴር ጄነራል ተስፋዬ እንደገለጹት የቀድምው የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት እና ምክትል ፕሬዚዳንትን ጨምሮ ሰባት የጁንታው ሲቪል አመራሮች እንዲሁም ከመከላከያ ከድተው ጁንታውን የተቀላቀሉ አመራሮችም በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በዚሁ መሠረት እርምጃ የተወሰደባቸው፡-

1ኛ. ሜጀር ጄነራል ኢብራሂም አብዱልጀሊል፡- ቀደም ሲል የመከላከያ ሎጂስቲክ ሓላፊ የነበረ እና አሁን የጁንታው ሎጂስቲክ ሓላፊ የነበረ
2ኛ. ብርጋዴል ጄነራል ገብረኪዳን ገብረማርያም፡- የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ሓላፊ የነበረ እና በጡረታ ከተሰናበተ በኋላ ጁንታውን የተቀላቀለ
3ኛ. ዐሥር ከፍተኛ መኮንኖች
4ኛ. ሁለት መስመራዊ መኮንኖች
5ኛ. አንድ የክልሉ ረዳት ኮሚሽነር የነበረ እና ከፖሊስ ከድቶ ወደ ጁንታው የተቀላቀለ ናቸው።

በተጨማሪም የክልሉ ከፍተኛ ባለሥልጣን የነበሩ የጁንታው አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ብርጋዴል ጄነራሉ ገልጸዋል።

እነዚህም፡-
1ኛ. አቶ ዓባይ ወልዱ፡- የቀድሞ የክልሉ ፕሬዚዳንት የነበረ
2ኛ. ዶክተር አብርሃም ተከስተ፡- የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት የነበረ
3ኛ. ዶክተር ረዳኢ በርሄ፡- የክልሉ ኦዲተር ሓላፊ የነበረ
4ኛ. ዶክተር ሙሉጌታ ይርጋ፡- የክልሉ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ሓላፊ የነበረ
5ኛ. አቶ ዕቁባይ በርሄ፡- የሃይማኖት ጉዳይ ክትትል ሓላፊ የነበረ
6ኛ. አቶ ጌታቸው ተፈሪ፡- የክልሉ ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤትና የሰላም እና ደህንነት ሓላፊ የነበረ
7ኛ. ወይዘሮ ኪሮስ ሃጎስ፡- የክልሉ ማኅበራዊ ጉዳይ ሓላፊ የነበረች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጸዋል።

በተጨማሪም ሁለት ከመከላከያ ከድተው ጁንታውን የተቀላቀሉ ከፍተኛ መኮንኖች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፣ እነሱም ኮሎኔል ገብረእግዚአብሔር አምባዬ እና ኮሎኔል ትርፏ አሰፋ መሆናቸውን ብርጋዴር ጄነራሉ ገልጸዋል።
ኳስሜዳ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2894
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 7 guests