ሰላም ለሁላችሁም እያልኩ:-
ወንዳታ:-
Orbit ምሕዋር መስሎኝ!ተፋሰስማ ወንዝ ከሆነ ለምን አዲስ ቃል አስፈለገው?
ክሪስታል:-
አንተ በሁለተኛ ሙከራህ ያልከው የተፋሰስ አንደኛው ትርጉም ትክክል ነው::ግን የምርት ተፋሰስ ሲባልስ?
Monica****:-
እኔም እኮ ግራ የተጋባሁት ለዚህ ነው::እነዚህ ቃላት ድሮ ያልነበሩ መሆን አለባቸው::ወይስ ሰምቼአቸው አላቅም ብል ይሻል ይሆን?አንዳንዶቹ amharaized የሆኑ ቃላት ይመስላሉ::ከግዕዝ ወይስ ከትግርኛ?የሚያውቅ ቢነግረን!
ዝርዝሩ:-
አባባልህ ሊሆን ይችላል::ግን አንዳንዶቹ 'ወያኔያዊ' ባልሆኑ የፕሬስ ውጠቶች ላይም ሲነበቡ ታይተዋል::ወይስ እነዚህን ቃላት የተጠቀመ ሁሉ አፍቃሬ ወያኔ ነው ማለት ነው?ያም ሆነ ይህ ትርጉማቸውን ግን ማወቁ ይከፋል ትላለህ?
crypto:-
አሸንዳ ተፋሰስ መባሉን አላውቅም ነበር::ፈለክ ድሮም የነበረ ቃል ሲሆን ፕላኔት ማለት ነው::ሥነ ፈለክ ስለ ፕላኔቶች የሚያጠና ሳይንስ ይሆን?astronomy ሥነ ከዋክብት ነው መሰለኝ የሚባለው::ሥነ አንተ እንዳልከው ጥናትን ሊያመለክት ይችላል::ግን ለምሳሌ እንደ ሥነ ሥርዓት የመሰሉ ቃላት ምን ሊባሉ ነው?የሥነምህዳር ትርጉም ግን ግልፅ አልሆነልኝም::