እንዲኽ ሆነላችሁ::
ከላይ ተጀምረው ያላለቁት ታሪኮች ይቀጥላሉ::ያው የአንባቢ ብዚ እንጂ የተሳታፊ ነገር እዚህ ስለማይታይ ምን አልባት ባለጌ እንባላለን ብላችሁ አስባችሁ ስለሆነ ችግራችሁ ይገባኛል ነገር ግን ምንም ሪያክሽን ካላሳያችሁ በምን አውቄ ፍላጎታችሁን ላሙዋላ?በፈለገኝ ጊዜ በራሴ ስሜት ልሂድ እንጂ::
እና የተጀመረው ያልቃል አይዞን::ትንሽ ችግሩ ፖለቲካ ሩም ከብቶች አብዝቼ እያረባሁ ስለሆነ ከስተው እንዳያዋርዱኝ ቶል ቶሎ መኖ እየጎዘጎዝኩላቸው ጊዜዬውን ወደ እዛ አድርጌ ነው::
በሉ ዛሬ ሁለት ጨዋታ ይዤላችሁ ከች ብያለሁና አንብቡኝ::
ባለፈው ሳምንት ነበር::ቀኑ ጭጋጋማና ቀዝቃዛ ነበር::ጊዜው ቅዳሜም እሁድም ነበር::ለትልቅ ነገር ግብዴ ፈተና ውስጥ ነበር ያለነው::ቅዳሜንና እሁድን ሙሉውን ቀን የሚያውለን ፈተና::ከፈተናው በፊት የቤት ስራም ነበር::እውቅ ፕሮፌሰሮች ዶክተሮችና ቀለሜዋዎች የሚታዘቡበት የቤት ስራም,ፈተናም ብላችሁስ?
እኔ ሆዬ በክብርነታችን ሆነን ስንንዘላዘል ለካስ የቤት ስራውን ሳንሰራ ቆይተን ነበርና እንደ ነገና እንደ ነገ ወድያ የምናቀርበውን ነገር የግድ በአንድ ለሊት ውስጥ ሰርተን መጨረስ እንዳለብን በዶክተሯ ፈታኛችን ተነግሮን ነበርና ምንም እንቅልፍ ሳናይ የቤት ስራውን ስንሰራ አደርንና ሳንተኛ ቢነጋ በዛው ወደ ምንሰባሰብበት....ወደ ምንገመገምበት...ወደ ምንፈተንበት ቦታ በሳይክሌ ጣጣ መጣጣዬን ይዤ ሄድኩ::
ሁሉም ተፈታኝ በተሰማራበት የህይወት ጎዳና ህልሙን እውን ያደረገና እውን በሆነው ህልሙ እንጀራ ይበላበታል...ታላቅ ተብሏል....ክብር አግኝቶበታል.....እያገኘበትም ነው.....ስምም አለው....ከራሱ አልፎ ለሌላውም እየተረፈ ነው.......
ፈተናው እራስን ይዞ በመቅረብ የሚፈተኑት ፈተና ነው::ያለኽን...ያዳበርከውን.....እየኖርክበት ያለውን.....በራስ መተማመን የሰጠኽን አሁን ከተማርከው ጋር ቀላቅለኽ ምን ያኽል አንተነትህን አተልቀኸዋል....ለሌላውስ ሀላፊነት ቢሰጥኽ ምን ያኽል ማካፈል ትችላለኽ ነው:::
ከዛ ጊዜው ደረሰና እንደነገርኩዋችሁ ሳልተኛ ባደርኩበት ፊቴ ቁርሴን ምናምን ቀማመስኩና ሁለት ቀን ሙሉ በዚህ ብርድ ደጃፍ ላይ ገትሮ የሚያውለኝ ቦታ ልሄድ ተነስቼ ሄጄ እዛ ከተኮለኮሉት ጋር እኔም ተቀላቀልኩና ተኮለኮልኩ::ምስጋና ለፈጣሪ ይግባውና በሰላም አውሎ በሰላም አሳድሮ በሰላም ከትላልቆች ጋር እኔንም አተልቆ አዋለኝ.....ለሱ ምን ይሳነዋል?እንደ ሰው ሀጥያት ምን ሰው ...እንደኔ ሀጥያት ቢሆን እዛው ኬንያ በረሀ ውስጥ ባስቀረኝ ነበር....እንደሱ መሀሪነት ከቁጥር በላይ ይቅር ባይነት. በየደቂቃው ሀጥያት ብሰራም በየሰከንዱ ይቅር እያለኝ ይኼው በአምሳሉ የሰራውን ሰውነት በተለያየ መንገድ እያረከስኩት ቢሆንም እሱ በኢጾብ እያጠበኝ አለሁ::
ወደ ጨዋታው ልውሰዳችሁና
እናማ ልክ ሁላችንም መሰባሰባችን እንደታወቀ ፈታኞቹና ታዛቢዎቹ ሂር ዊ ጎ አሉን::
የመጀመርያውን ፈተና የተፈተነችው ሴሬና ስትሆን ሴሬና በሞዴልነት ስራ የምትሰራ ሲሆን የህልሟ እውንነት ከኦስትርያ እስከ ኒውዮርክ ድረስ ነው የተዘረጋውና ተዘርግቶም የሚመላለሰው::አፍናጫዋ ግትር ቢሆንና በአበሾች የውበት መለክያ አፍንጫዋ ከውቦችም ውብ ተደርጎ ቢያስቆጥራትም ነገር ግን በአውሮፓ የውበት ስታንዳርድ ጎራዶች ውብ በተባሉበት ቦታ ላይ የውብነት መዳልያ የሚጠለቅላት አይመስልም.....ግን ቢሆንም እንዴት እንዳመለጠች እኔንጃ ብቻ ሞዴል ነች.....ሰውነቷ ግን የማንም ሴትና ወንድ ህልም ነው::ብዙም አጭር ባትባልም ሜትር ከ 70 ትሆናለች::ቅጥን ያለው ሰውነቷ በፓንትና በጡት ማስያዣ ሆና ስትታይ በስፖርት የተገነባ በጣም የሚያምርና ሆዷ በሲክስ ፓክ የተከፋፈለ ነው::ሆዷ ላይ ያለው ሲክስ ፓንክ አፍ ከመግባት አወጣት እንጂ ይቺ በልታ የማትጠረቃ እስኪባል ድረስ ያሰድባት ነበር::ክብርነታችን እንደታዘባት ደግሞ በጣም ትበላለች.....ክላስ ውስጥ በነበርንበት ወቅት የማትበላው ምንም ነገር የለም::ጣፋጭና ኦቾሎኒማ ለጉድ ነው የምትከተው....ግን የት እንደሚገባ እንጃ እንጂ ምግብ በልታ የምታውቅም አትመስልም::ያንን ሰውነት ያየ ሁሉ የማይፈዝ የለም::በዛ ላይ ከርል አድርጋ የለቀቀችው ረጅሙ ጫካ የሚመስለው ጽጉሯ ከምትለዋውጣቸው የፊት ኤክስፕረሽኖች ጋር ፕሮፌሽናል ፎቶዎቿን ያየ ዋው ታድላ....ይቺን ነበር ብሎ የማይመኛት የሚኖር አይመስለንም::
እናላችሁማ ሴሪን የመጀመርያዋ ተፈታኝ ሆነችና ፈተናውን መፈተን ጀመረች::ፈተናው ታድያ የቤት ስራ ያለበት ሰው የቤት ስራውን ይዞ በመምጣት ተፈታኞቹን እያሳተፈ የቤት ስራውን በተፈታኖች ላይ መስራት ነው::ይዤ መጥቻለሁ የሚለውን ነገር አንጠፍጥፎ እያሰራ ፈተናውን ተፈትኖ ማርክ ማግኘት ነው::እድለኛ ሆነችና ሴሬን የቤት ስራዋን በእኛ ላይ የሰራችው ሱድዮ ውስጥ ስለነበር ብርድ አልነካንም ነበር:::ለዛውምበሙዚቃ ታጅበን ስለነበር ስንሰራ የነበረው ደስ ይል ነበርና አይተን የማናውቀውን ልብ ውልቅ የሚያደርገውን ውስብስብ የሆነ ነገርን አሳይታን ላብ በላብ አድርጋን የቤት ስራዋን ሰርታ ጨረሰችና ለተከታዮአ ተፈታኝ አስተላለፈች::
ምንም ሳናርፍ ሌላ ፍጋት ጀመረ::
መጣን::
ሾተል ነን......