ትግሬ እጠላለሁ !ዘረኛ ግን አይደለሁም::

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

Postby ዘርዐይ ደረስ » Fri May 20, 2011 8:35 pm

ገራዶ wrote:
ሰላም ዘርአይ

አንድ ትግሬ ያንተን እና የሌሎችን አስተያየት እንዲያነብ ቢጋበዝ ከት ከት ብሎ ነው የሚስቅባችሁ.ምን ያህል የፖለቲካ ቂላ እና ጂላጂል አስተሳሰብ እንዳላችሁ ነው ሊነግራች ሁ የሚነሳው.ይህ ያለቀለት እና የበሰበሰ የነፍጠኛ አስተሰስብ
ነው ብሎ ይነግርሀል. እንዲያዉም ከ19ኛው ክፍለዘመን ወድ 21ኛው ክፍለ ዘመን ያልተሸጋገረ ጦጣ ብሎ ይቀልድብሀል.
ለአንድ ትግሬ ያለፈው 20 አመት በታሪካቸው አይተዉት የማያውቁት በአማራ መቃብር ላይ ገዢ መደብ እንዲሆኑ ያስቻላቸው ወርቃማ ታሪካዊ ዘመናቸው ስለሆነ አንድነት ብትላቸው የእግር ሰንሰለት ስለሚመስላቸው ይጣሉሀል.

ወያኔ ማለት ትግራይ ሲሆን ትግሬ ማለትም የሁለቱን ዉህደት እቅፍ ድግፍ አድርጎ የያዘ ማለት ነው.
ስለዚህ መጃጃሉን ቆም አድርገን እነዚህ ሰወች አመድ እና አቡውራ ላይ የጣሉትን ኢትዮጵያዊነት እንዲያድሱ አንድ ብቸኛ እድል መስጠት ይገባል ከሚሉት ነኝ.
ሪፈረንደም ይሰጣቸው እና በግልጽ ይንገሩን.ከዚህ በሁዋላ
እየተቁዋሰሉ መኖር እና መቀጠል አያስፈልግም እላለሁ.


ሰላም ገራዶ:-

በዚህ አመለካከትህ የማልስማማባቸው በርከት ያሉ ምክንያቶች አሉ::እኔ የማውቃቸው አብዛኞቹ የትግራይ ተወላጆች ትግሬ ስለሆኑ ብቻ የወያኔ-ኢህአዴግ ደጋፊ ተደርገው መታየትን እንደ Discriminationነው የሚቆጥሩት እንጂ አንተ እንደምትለው አይደለም::በዚህም ምክንያት ወያኔና የትግራይን ህዝብ ለይቶ የሚያይ ሰው ሲያጋጥማቸው ደስ ሊላቸው ይገባል እንጂ ለምን ይከፋሉ?በተለይ ከ1997 ምርጫ በኋላ የነበረውን ሁኔታ መለስ ብዬ ሳስታውስ የጅምላ ጥላቻና ስሜታዊነት የነገሰበት ወቅት ነበር::ገዢው ፓርቲና ደጋፊዎቹ እንዲሁም በተቃዋሚው ጎራ ያሉ አንዳንድ ጭፍኖች ይህ ሁኔታ እንዲረግብ ሳይሆን የበለጠ እንዲጋጋል የሚፈልጉ ይመስላል::ይህ አቋም ግን የአንድ ሰሞን የፖለቲካ ''ጥቅም'' ሊያስገኝ ቢችልም ለአገራችን ዘለቄታዊ ሰላምና ለህዝቧ ደህንነት አደገኛ እንደሆነ ህሊናውን መጠቀም ለቻለ ሁሉ የሚሰወር ጉዳይ አይመስለኝም::በነገራችን ላይ እኔ ይህን ርእስ ስከፍት በገሃዱ ዓለም የማውቃቸውን ሰዎች እንጂ ፓልቶክ ላይ ወይም በዚህ ዋርካ መድረክ ላይ የሚናገሩትንና የሚፅፉትን ማንነታቸውን ግን የማላውቃቸውን ግለሰቦች እያሰብኩ አይደለም::
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1092
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Postby ዘርዐይ ደረስ » Fri Sep 30, 2011 10:35 pm

ሰሞኑን በዚህ ጉዳይ ላይ ፓል ቶኮች የተሻሻሉ ይመስላል::ዋርካ ግን ብሶባታል::
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1092
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Postby ደም » Fri Sep 30, 2011 11:46 pm

this is like saying i kill people but i am not murderer lol
ደም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 293
Joined: Thu Jul 28, 2011 4:13 am

Postby ወዲ_ኒውዮርክ » Sat Oct 01, 2011 12:21 am

It really doesn't matter whether Neftegna hates us or not. We know for sure Neftegna is absolutely inconsequential in modern Ethiopia.

What we want from Neftegna is not their love, its their respect that we seek. And we all know they respect us like nobody because we have kicked their ass time and again. We are talking about some real ass kicking here.

The hate the coward Neftegnas have towards us is very empowering for us Tigrayans. Its the source of our motivation and invincibility.
ወዲ_ኒውዮርክ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 112
Joined: Mon Nov 26, 2007 4:17 am

Postby መለስ ዜናዊ1 » Sat Oct 01, 2011 2:09 am

የ ትግራይ ህዝብ ምን አጠፋ ነው የምትሉኝ ለዘመናት ተንቆ ይነበረን ህዝብ በማንነቱ እንዲኮራ ሰላረገ ነው ነገ መንግስቱን መልስልን እንዳትሉ ብቻ የህዳሴው ግድብ ይገነባል እድሜ ለኢሀዲግ የትግራይ ህዝብም ወደ እድገት አገሪቱን ይመራል በዚህ ቃር ቃር የሚለው ካለ ይበለው አመሰግናለሁ.
መለስ ዜናዊ1
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 29
Joined: Sun Mar 21, 2010 4:55 am
Location: mekele

Re: ትግሬ እጠላለሁ !ዘረኛ ግን አይደለሁም::

Postby ዘርዐይ ደረስ » Sun Jul 08, 2018 11:27 am

የኰሎኔሉ ስልጣን መያዝ ካመጣቸው የጎንዮሽ ጉዳቶች አንዱ በትግራይ ህዝብ ላይ ከተለያዩ አቅጣጫዎች እየተካሄደ ያለው የጥላቻ ዘመቻ ነው።በአንድ በኩል ከኤርትራ ህዝብ ጋር እንቀራረብ እየተባለ በሌላ በኩል ደግሞ ኢትዮዮጵያዊውን የትግራይ ህዝብ ማራቅ ምን የሚሉት ፖለቲካ ነው?
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1092
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: ትግሬ እጠላለሁ !ዘረኛ ግን አይደለሁም::

Postby እሰፋ ማሩ » Sun Jul 08, 2018 9:14 pm

በዶ/ር አብይ ላይ ያለህ ጥላቻ ስር የሰደደ ነው፡፡'ትግሬን እጠላለሁ' የሚል አምድህ የተከፈተው ከ7አመት በፊት ሲሆን ዛሬ ዶ/ር አብይ የሃገራችንን ህዝቦች ያለአንዳች የሃይማኖት የዘር የፖለቲካ ልዩነት በሚያስማማበት ወቅት የቆየ የከረመ የሃገሪቱን ችግር 'የጎንዮሽ' ብለህ ከዶ/ር አብይ ጋር ማያያዝ የጥላቻህ መሽፈኛ ነው፡፡ይህ በትግራይ ላይ ሆነ በሌላው ላይ ያለ የዘር ጥላቻ በሀገራችን የቆየ የክፉ የጥላቻ ባህል እንጂ በዶ/ር አብይ አስገራሚ ድንቅ ስራዎች የተከሰተ አይደለም፡፡ዶ/ር አብይ ደጋግሞ ተናግሮ ነበር መስማት የማትፈልግ ስለሆነና በጭፍን ጥላቻ ስለተሞላህ እንጂ 'ድርጅትን ከህዝብ ለዩ' የሚል ወርቃማ መመሪያ ዶ/ር አብይ ሰጥቶናል፡፡ ህዝቡ ኦሮሞ ጉደላ ኡመቴ ቡዳ ትግሬ አንበጣ በሊታ ጋላና ገለባ ጉራጌና ምስጥ ወዘተ በሚል ክፉ ባህል የተበከለ በአስተሳሰብ መታደስ መለወጥ አለበት፡፡ዶ/ር አብይ ለኢትዮጲያ ቀርቶ የተባበሩት አፍሪካ ፕሬዚዳንት መሆን የሚችል ነው ፡፡አንተ ግን ኮልኔሉ በማለት ማለቃቀስህን ቀጥል፡፡ ህዝቡ ግን ከዶ/ር አብይ ጋር ወደፊት በማለት በኢትዮጲያ ተሃድሶ ይራመዳል፡፡የሃገራችን ሰው ቀርቶ የአለም ምሁራን ሚዲያ ስላደነቀው በዶ/ር አብይ ስለሚካሄደው በጎ ለውጥ ምንም ያልተነፈስህ ዶ/ር አብይን ለመተቸት የማትፈነቅለው ድንጋይ የሌለህ ሰው ዶ/ር አብይ በቅንነት የጠራው ፈጣሪ ይማርህ!
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1530
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm

Re: ትግሬ እጠላለሁ !ዘረኛ ግን አይደለሁም::

Postby ቆራሌ » Sun Jul 08, 2018 11:46 pm

እበላ ባዩ እሰፋ ማሩ ፡ እስኪ ተረጋጋ። ኣቶ ዘርኣይ እቅጩን ነው የተናገረው። ዋርካን ጨምሮ፡ ከሞላ ጎደል ሁሉም የዲያስፖራ መደረኮች ላይ የትግራይ ህዝብ ላይ ያነጣጥረ ዘመቻ ነበር የተካሄደው። እንደው ኢሃዴግ ኣስተዋይ ሰለሆነ ነው እንጂ- እንደእናንተ ቢሆን ኖሮ ኢትዮጵያ እንደ ሩዋንዳ ነበር የምትሆነው...
ቆራሌ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 44
Joined: Wed Oct 05, 2016 12:58 am

Re: ትግሬ እጠላለሁ !ዘረኛ ግን አይደለሁም::

Postby ኮኮቴ » Mon Jul 09, 2018 12:02 am

ሰላም ነው እዚህ ቤት?????
እኔ ድሮ ዋርካ ውስጥ የማውቀው ዘራይደረስ አስተዋይ ... የነገሮችን ግራና ቀኝ ሳያይ ለፍረጃ የማይቸኩል ... ታሪክ እና ባህሉን አክባሪ ነበር፡፡ ሰሞኑን ዋርካ ልይ ብቅ ስል የማያቸው አንዳንድ ፖስቶቹ ትንሽ ግር አሰኝተውኛል፡፡ በተለይ በጠ/ሚስትሩ ላይ ያለው ምክንያታዊ ያልሆነ ጥላቻ ... "ይህ ሰው እውነት የድሮው ዘራይ ደረስ" ነው አሰኝተውኛል፡፡ ከጠ/ሚንስትርነቱ ወይም ተምሮ ካገኘው የፒኤችዲ ድግሪው ይበልጥ ለዘራይ ደረስ የሚታየው ኮለንኔለቱ ነው ፡፡ አብይ የትግራይን ህዝብ ጨምሮ ኢትዮጵያውያንን ሁሉ በፍቅር በታጀቡ ቃላት በአደባባይ ሲያሞጋግስ እያየ ... ኤርትራ ድረስ ሄዶ እንኳን "እባካቹ የትግራይን እና የአፋርን ህዝብ በፍቅር አይን እዩአቸው" እያለ በአደባባይ ሲማጠን እየሰማ ሰምቶ እንዳልሰማ ማለፍ ያስተዛዝባል፡፡ በስልጣናቸው እና በሌብነታቸው የመጣባቸው ባለስልጣኖች አብይን ቢተቹ አይገርመንም፡፡ ወይም ደግሞ ጭፍን ዘረኝነት የተጠናወታቸው እና ከኔ ዘር እና ሃይማኖት ተከታይ ውጪ ማንም ስልጣን ላይ መውጣት የለበትም ብለው የሚያስቡ ሰዎችም ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ አስተዋይ ነው ብዬ ከማስበው በዘራይ ደረስ ፖስቶች ላይ የማያቸው ነገሮች ኝ በፍጡም አልተዋጡልኝም፡፡ ይህ ማለቴ ግን... አብይ በማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፖሊሲዎቹ አይተች ማለቴ አይደለም፡፡ ለማለት የፈለኩት ትችቱ ምክኛታዊ ይሁን ነው!
ለገ፟፟፟፟ ኮኮቴ ዘብሄረ ኢትዮጵያ
o-o-o-o-o-o-o-o-o-o-o-o
".... Indeed, we Ethiopians are a beautiful multi-lingual and multi-cultural people who in a flower vase called Ethiopia decorate the great continent of Africa", Professor Ephraim Isaac
ኮኮቴ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1289
Joined: Wed Nov 04, 2009 2:07 am

Re: ትግሬ እጠላለሁ !ዘረኛ ግን አይደለሁም::

Postby ለማ12 » Mon Jul 09, 2018 4:36 pm

እኔ ክቡ ተባለ የሚለውን አልሰማሁም ቢባል ግን አያስገርመኝም ምክንያቱም ህዝቡን እነ ክቡና አለቆቹ ማንነቱን አጥበውታል ስለዚህ
የሚነገረውን በደብ ማየት ብቻም ሳይሆን ለምን ማለትም ተገቢ ነው ባይ ነኝ፡፡
ሰትዮይቱ እለች የምትሉት ለኔ
ቆማጣን ቆማጣ ማለት ተገቢ ነው ብላ ያሰበች ይመስለኛል በደብ ተረዱት
ይህን የነክቡንም ዘፈን ተከታተሉ
እንድታዩት ነው ኮፒ የማደርግላችሁ፡፡
Back to Front Page


Share This Article!ግልጽ ደብዳቤ ለትግራይ ክልል ምክትል ፕሬዚደንት

አቶ ደብረጺዮን ገብረሚካኤልአብርሃም ከአዲስ አበባ፣ 07-09-18

ክቡር ምክትል ፕሬዚደንት፣ይህን መልዕክት እንድጽፍልዎ ያነሳሳኝ ለህወሓት ያለኝ አክብሮት እና አድናቆት ነው፡፡ የህወሓት ትግል በኢትዮጵያ ታሪክ ከተመዘገቡ የነጻነት እና የእኩልነት ትግሎች ምን አልባት ታላቁ ወይም ከታላላቆቹ አንዱ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ የህወሓት ትግል ለመላው ኢትዮጵያዊ የነጻነት እና የእኩልነት ፈር ቀዳጅ ነበር፡፡ ኢሕአዴግ አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ በኋላ፣ በየመጽሔቱ እና ጋዜጣው፡- “ህወሓት ወይም ወያኔ አገር ሊበጣጥስ ነው፣ አገር ሊያፈርስ ነው፣ የአገሪቱን ሃብት ሊዘርፍ ነው” ወዘተ… ይባል ነበር፡፡ ህወሓት የትኛውን አገር እንደበጣጠሰ እና እንደዘረፈ እኔ አላውቅም፡፡ በእውነቱ ኢህአዴግ አዲስ አበባን ሲቆጣጠር የሚዘረፍ ሃብት ነበር? የአገሪቱ ካዝና በጦርነት የተራቆተ አልነበረም? እንዴትስ ለእንደዚህ ዓይነቱ እኩይ ተግባር አንድ ድርጅት እና ታጋዮቹ መቼ እንደሚያባራ በማያውቁት ጦርነት ራሳቸውንም፣ ሕዝባቸውንም ይማግዳሉ? የህወሓት ዓላማ ግልጽ ነበር፤ ሕዝብን ማስቀደም፡፡ እንደ ግለሰብ እጅግ ከማደንቃቸው እና ሚያስቀኑኝም ነገሮች መካከል የህወሓት ትግል ዋናው ነው፤ በህወሓት የትጥቅ ትግል ውስጥ ጽናት ነበር፣ ዓላማ ነበር፤ መስዋዕትነት ነበር፤ ከሁሉ በላይ ደግሞ ሕዝባዊነት ነበር፡፡አሁን አሁን በአገሪቱ ያለው ሁኔታ ወደ መልካም አቅጣጫ ይወስዳል ወይስ አይወስድም ለሚለው ጥያቄ እንደ እኔ ጊዜ የሚመልሰው ነው፡፡ መልካም ጅምሮች አሉ፡፡ መስመር የሳቱ የሚመስሉም ነገሮች አሉ፡፡ የአገሪቱ አንጡራ ሃብቶች በውጭ ዜጎች መያዝ የለባቸውም፤ ያ ከሆነ ሃብት አይኖረንም፣ አገራችን በሌሎች ቁጥጥር ስር ትወድቃለች የሚል አቋም ሕዝባዊ እና ጸረ ሕዝብ አቋም ነው ብዬ ለማሰብ ይከብደኛል፡፡ አንጡራ ሃብታችንን ለራሳችን እናቆይ የሚል መሪ፣ እነዚህን ሃብቶች ለባዕድ አገር ባለገንዘቦች መሸጥ ገንዘብ እንደሚያስገኝ ጠፍቶት ወይም ሳያውቅ ቀርቶ ነው አልልም፡፡ እኔ አሁን ይህን መልዕክት ለመጻፍ የፈለግሁት፣ ህወሓት በመላ አገሪቱ ላለው ችግር መንስኤ እና ተጠያቂ ተደርጎ የሚነገረውን በማስመልከት ነው፡፡ አሁን እየሆነ ካለው ስሜት የተቀላቀለበት ሁኔታ ጋር በማነጻጸር ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ለሕዝብ ቅርብ አልነበሩም፡፡ ነገር ግን ሊሆኑ ይችሉ ነበር፤ ምን አልባት ቀረብ ያላሉት አገሪቱ ጠንካራ መንግሥት ያስፈልጋታል፣ አመራሩም ጠንከር፣ ኮስተር ያለ መሆን አለበት ብለው ስላመኑ ሊሆን ይችላል፡፡ እንዲህ ዓይነቱ አመራር ያስፈለገበት ምክንያት ደግሞ የአገሪቱ ስር የሰደደ እና የበዛ ችግር ሳይሆን አይቀርም ብዬ እገምታለሁ፡፡ አቶ መለስ በስቴዲየም እና በአደባባይ ሕዝብ ሰብስበው ስሜት የሚኮረኩሩ ንግግሮች ማድረግ የሚያቅታቸው አልነበረም፤ ችግር ፈቺ አድርገው ስላላዩት ይሆናል እንጂ፡፡ ይህ ማለት ግን ያንን ያህል ሩቅ ሆነው መቆየታቸው ሊተች አይገባም ለማለት አይደለም፡፡
Videos From Around The Worldበእርግጥ አንድ እጅግ ያሳዘነኝ ነገር አለ፡፡ እርሱም በመገናኛ ብዙሃን እየተነገረ ያለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ጉዳይ ነው፡፡ መቼስ ይህ ሁሉ አቶ መለስ ወይም አቶ ኃይለማሪያም ወይም በጠቅላላው የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራር እያወቀው የተደረገ ከነበረ እጅግ በጣም ያሳዝናል፡፡ ደርግ ሰው የሚበላ የሕዝብ ጠላት መንግሥት ነበር የሚባለው እንዲህ ዓይነቱን ሰይጣናዊ ተግባር ከቤተ መንግሥት እስከ ቀበሌ በተደራጀ መዋቅር ይፈጽም ስለነበር አይደለም? ፈጻሚው ደርግ ሆነ ኢህአዴግ የሚመራው መንግሥት ሆነ ለውጥ ያመጣል?ክቡር ምክትል ፕሬዚደንት፣ እኔ የትግራይ ተወላጅ አይደለሁም፡፡ ስለዚህ ህወሓት መለወጥ አለበት ብል ድፍረት አድርገው አይውሰዱብኝ፡፡ እኔ እስከማውቀው እና እንደማምነውም ህወሓት ትናንት የሕዝብ ግምባር-ቀደም ተሟጋችና ታጋይ ነበር፤ አሁን ደግሞ ወደ ቀድሞ ማንነቱ መመለስ አለበት፡፡ አዳዲስ መሪዎችን ወደ ፊት ማምጣት አለበት፡፡ ነባር መሪዎች ለአዲስ ትውልድ መሪዎች ቦታ መልቀቅ አለባቸው፡፡ ህወሓት ብቻውን ሊጠየቅበት የሚገባ ነገር አለ ባልልም፣ ተራ ዜጋ ነኝና እኔ የማላውቀው ነገር ግን ህወሓት ብቻውን የሚጠየቅበት ነገር ካለ ኃላፊነት ወስዶ፣ የትግራይን እና የኢትዮጵያን ሕዝቦች ይቅርታ ጠይቆ ቀድሞ ወደ ነበረው የሕዝብ አለኝታነት አቋም መመለስ አለበት፡፡ ወደ ቀድሞ አቋሙ ስል የጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታ በህወሓት አባል መያዝ አለበት ማለቴ አይደለም፡፡ ያ ፓርቲው የሚወስነው እና በዴሞክራሲያዊ መንገድ ብቻ ሊሆን የሚገባው እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ህወሓት ድንቅ ታሪክ ያለው ድርጅት ነው፤ በቀጣይ ትውልዶች ድርጅቱ መታወስ ያለበት በዚህ አስደናቂ ታሪኩ ነው፡፡ እኔ እንደማውቀው ህወሓት ለሕዝብ ታግሏል፣ ዋጋ ከፍሏል፤ ይህ ሆኖ እያለ ግን አሁን ስሙ ጠልሽቷል፡፡ ለስሙ መጠልሸት ምክንያት የሆኑትን በመለየትና በማስተካከል የድሮውን አቋም መልሶ መያዝ አለበት፡፡ ወገቡን አስሮ ለነጻነት የታገለ፣ የተዋደቀ፣ የቆሰለና የተሰዋ የትግራይ ሕዝብ ካሣ ያስፈልገዋል፡፡ ካሣ ስል ገንዘብ ነክ ካሣ አይደለም፡፡ ካሣ ሊሆነው የሚችለው የመሪ ድርጅቱ ህወሓት መቃናት እና ወደ ቀድሞ ሕዝባዊነቱ መመለስ ነው፡፡ ህወሓት በእውነት እና በሃቅ ላይ የተመሠረቱ አቋሞች ይዞ ተጉዟል ብዬ አምናለሁ፡፡ አሁንም መታደስ ያለበትን፣ መለወጥ ያለበትን፣ መቀየር ያለበትን ለይቶ አዲስ ህወሓት ሆኖ መውጣት ይችላል፡፡ ክቡር ምክትል ፕሬዚደንት፣ ህወሓት የማይቻል የሚመስለውን ግብ በግምባር ቀደምትነት ያሳካ ድርጅት ነው፡፡ ህወሓት በእርስዎ አመራር ታሪኩ ሁሉ ተረስቶ ወደ መገፋት የሚሄድበት ዘመን መሆን የለበትም፡፡ ሕዝባዊነቱን መልሶ ማምጣት ከቻለ፣ ለሕዝብ ጥቅም ሲል መከለስ የሚገባውን መከለስ አይከብደውም፡፡ ክቡር ምክትል ፕሬዚደንት ዛሬ እንደሚባለው ህወሓት ጸረ ሕዝብ ሳይሆን የሕዝብ አለኝታ መሆኑን በተግባር ሊያሳይ ይገባዋል፡፡ከአክብሮት ሰላምታ ጋር፣

አብርሃም
Back to Front Page
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1107
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Re: ትግሬ እጠላለሁ !ዘረኛ ግን አይደለሁም::

Postby ዘርዐይ ደረስ » Mon Jul 09, 2018 7:43 pm

እሰፋ ማሩ፦አንተ መቼም ሐሳብን በሐሳብ መሞገት አይመችህም።ምናልባት ሐሳቤን ግልጽ አላደረግሁ ይሆናል።ኰሎኔሉ ትግሬ ይጠላል ለማለት ፈልጌ ሳይሆን ትግራይ ውስጥ በባድሜ ምክንያት ተቃውሞ ስለ ገጠመውና እንደ ሌሎቹ ክልሎች ደማቅ የድጋፍ ሰልፍ ስላልተደረገለት በተለይ ደግሞ በአዲስ አበባው ሰልፍ ላይ በፈነዳው ቦምብ ሰበብ በሌላው ክልል ህዝብ ዘንድ ትግሬን በጥርጣሬና በጥላቻ የማየት አዝማሚያ እንዳለ መቼም የሚክድ ያለ አይመስለኝም።ይህንን ክስተት ነው የጎንዮሽ ጉዳት ያልኩት።
ኮኮቴ፦ዋርካ ከመዘጋቷ በፊት የነበረውን ኮኮቴ የማስታውሰው በቀልድ በተዋዛ ስልቱ የሥርዐቱን ደጋፊዎች መሳለቂያ ሲያደርጋቸው ነው።የፖለቲካ አቋምህንም በአብዛኛው እጋራ ነበር።የውይይት ሥነ ምግባርህም ለአብዛኛው ታዳሚ የሚመች እንደነበር የታወቀ ነው።ዋርካ በድጋሚ ከተከፈተች ወዲህ ግን በመሰላቸት ይሁን በሌላ ምክንያት የጎላ ተሳትፎ ስታደርግ አላየሁም።አሁን በተለያየ ጎራ መሰለፋችን የአገራችን ፖለቲካ ተለዋዋጭ ባህርይ ውጤት ነውና አይገርመኝም።አንተ ተደምረሃል።እኔ ደግሞ የመደመርም የመቀነስም ፍላጎት የለኝም።በዚህ አመለካከቴ በአሁኑ ወቅት ከብዙሃኑ ጎራእንዳልሆንኩ ግልጽ ከሆነልኝ ሰንብቼአለሁ።በተረፈ ማስተዋል የሚጎድላቸውን ሐሳቦቼን ብትጠቁመኝ ደስ ይለኛል።
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1092
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: ትግሬ እጠላለሁ !ዘረኛ ግን አይደለሁም::

Postby ኮኮቴ » Tue Jul 10, 2018 1:42 am

ሰላም ዘራይደረስ ... ያው "ጀማሪ እረኛ ከብታ አያስተኛ" የሚባል ተረት አለ መሰለኝ ... እኔም በዶ/ር አብይ ወደ ስልጣን መምጣት ምክንያት ተካ (ተስፈኛ ካድሬ) ሆኜ ... እብይን ሲነኩት እንደ እነ ክቡ ቶሎ ግንፍል ይልብኝ ጀምሯል ፡)
በነገራችን ላይ ሙሉ በሙሉ ተቃውሞም ሆነ ሙሉ ለሙሉ ድጋፍ ጤነኛ እንዳልሆነ አምናለሁ፡፡ መሪዎች የሚሰሩትን ግድፈት ነቅሶ እያወጣ የሚያሳይ ተቀናቃኝ ሊኖር የግድ ነው፡፡ አንተ ከአብይ አስተሳሰብ ጋር ባለመደመርህ በጭራሽ ቅር አያሰኝም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ እኔ ዋርካ ውስጥ የማውቀው ዘራይደረስ ኢትዮጵያን የሚወድ እና ለአገሩ ቅን የሚመኝ ሰው እንደሆነ ስለምገምት ነው፡፡ ምናልባትም እኛ በሰፊው መንገድ ተጋፍተን ስንደግፍ ያልታዩን ጉድለቶች ... ላንተ ታይተውህ ሊሆን ይችላል ስለዚህ የተለየ እቋምህን እከብራለሁ፡፡

የቅርብ ግዜ እቀራረብህን ከተቃውምኩባቸው ነገሮች እንደኛው ሃሳብ ውስጥ፡ የኰሎኔሉ ስልጣን መያዝ ካመጣቸው የጎንዮሽ ጉዳቶች አንዱ በትግራይ ህዝብ ላይ ከተለያዩ አቅጣጫዎች እየተካሄደ ያለው የጥላቻ ዘመቻ ነው።በአንድ በኩል ከኤርትራ ህዝብ ጋር እንቀራረብ እየተባለ በሌላ በኩል ደግሞ ኢትዮዮጵያዊውን የትግራይ ህዝብ ማራቅ ምን የሚሉት ፖለቲካ ነው? ከሚለው ፖስትህ እንነሳ፡፟፟
1) ጠ/ሚ/ር አብይ ... አንተ እንደገለጽከው ... በጦሩ ውስጥ ኮሎኔልነት ማእረግ ነበረው ... በመንግስት ስልጣን ውስጥ ሚንስትር ሆኖ ነበር ... በትምህርት ደረጃውም የፒኤች ዲ ዲግሪ አግኝቷል፡፡ አሁንም ደግሞ በኢህአዴግ መራሹ መንግስት ጠ/ሚ/ር ሆኗል፡፡ እንግዲህ እነዚህን ሁሉ ነገሮች ያገኘው በኢህአዴግ ጥላ ስር ሆኖ ነው፡፡ ታዲያ ኢህአዴግ በሰጠውን የኮሎኔልነት ማእረግ ተቀብለህ በሱ ለመጥራት ከተስማማህ ... ጠ/ሚ/ር ብሎ ለመጥራት ለምን አልደፈርክም ... ወይም ደግሞ ... እሱ ካልተስማማህ ደግሞ ዶ/ር አብይ ብትለውስ ምን የሚጎዳ ነገር አለው፡፡ ዶ/ር አብይ የተጠማቸው ቃላት ህዝብን በህዝብ ላይ እያነሳሱ ነው ብለህ ከሰጋህና ... ቃላቶች የሚፈጥሩት አሉታዊ አንደምታ ስጋት ውስጥ የሚከትህ ከሆነ ... አሁን በሲቪል ስራ ላይ የተሰማራውን ሰው ደጋግሞ የሚሊታሪ ባክግራውንዱን ሪፈር እያደረጉ መጥራት አሉታዊ አንደምታ የለውም ብለህ ታስባለህ? ኮሎኔልነቱ በአሁኑ ስራ ላይ ያሳደረው ተጽእኖ አለው ብለህ ታስባለህ?
2) በህዝብ ዘንድ ተሰሚነት ያላቸው ሰዎች በሚጠቀሙባቸው ቃላት ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው በሚገባ አምናለሁ፡፡ በተለይም የ"ቀን ጅብ" እና "ጸጉረ ልውጥ" የሚሉት አባባሎች ... በጎሰኝነት ፖለራይዝ በተደረገው ፖለቲካችን ውስጥ የተሳሳተ ፍቺ ተሰጥቶት ያልታሰበ ነገር ሊያስከትል ይችላል ብሎ መስጋት ተገቢ ነው፡፡ ካሁን በኋላ ጠ/ሚ/ሩ በቃላት አጠቃቀም ረገድ ጥንቃቄ ያደርጋል ብዬ አስባለሁ፡፡ ለኔ ይህ የጠቅላይ ሚ/ሩ honest mistake እንንጂ ሆነ ብሎ በህዝብ መሃል ጥርጣሬን ለመፍጠር ያደረገው ነገር ነው ብዬ እላስብም፡፡ ይሄ ደሞ ሰውየው በየግዜው በሚያሳየው ትህትና በግልጽ ይታያል፡፡ ደግሞስ ከትግራይ ህዝብ የኤርትራን ህዝብ አብልጦ ለማቅረብ የሞከረው መቼ ነው፡፡ ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ... አስመራ ላይ ሳይቀር የትግራይን ህዝብ በአደባባይ ዲፌንድ ሲያደርግ ታይቷል፡፡ የዶ/ር አብይ ጠብ ከህዝባቸው ይልቅ የግል ጥቅማቸው መቅረት ካሳሰባቸው ጥቂት ፖለቲከኞች ጋር ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች ደግሞ ለጥቅማቸው ሲሉ ... ሃውዜን ላይ እንዳደረጉት ... በትግራይ ህዝብ ውስጥ ተሸሽገው ህዝቡን ለጭዳ ከማቅረብ አይመለሱም፡፡ ባይሆን ህዝቡ ከስግብገብ ወያኔዎች እራሱን እንዲለይ መምከር እንጂ ፟ ... ከቀደምቱ መሪዎች የተሻለ ለውጥ ለማምጣት የሚጥረውን ሰው ማደናቀፍ ለኢትዮጵያ ይበጃታል ብለህ ታስባለህ???

ለገ፟፟፟፟፟ ኮኮቴ
o-o-o-o-o-o-o-o-o-o-o-o
".... Indeed, we Ethiopians are a beautiful multi-lingual and multi-cultural people who in a flower vase called Ethiopia decorate the great continent of Africa", Professor Ephraim Isaac
ኮኮቴ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1289
Joined: Wed Nov 04, 2009 2:07 am

Re: ትግሬ እጠላለሁ !ዘረኛ ግን አይደለሁም::

Postby ለማ12 » Wed Jul 11, 2018 5:02 pm

Back to Front Page


Share This Article!


 
ግልፅ ደብዳቤ ለክቡር ጠ/ሚኒስተር ዶ/ር አብይ አሕመድና ለኢትዮጵያ ህዝብ
ዋስይሁን ከአዲስ አበባ
07-11-18
 
የኢትዮጵያ ህዝቦች በደማቸውና አጥንታቸው የገነቡት ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ፣ ወደውና ተፋቅረው ያፀደቁት የሉዓላዊነታቸው መገለጫ የሆነው ህገ መንግስት በጠራራ ፀሀይ ያለምንም ስጋት ሲጣስና ሲቀደድ ማየት፣ አንዱን ህዝብ በሌላውን ህዝብ እንዲነሳሳ እና ግጭት ውስጥ እንዲገባ የሚያደርግ አፍራሽ ተግባሮች መፈፀም የመጨረሻው ውጤት ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት ለእርስዎ ይከብዳል የሚል እምነት የለንም፡፡
·       ላለፉት ሁለትና ሦስት ዓመታት እንደዚህ በመሰለ አፍራሽና ፀረ ህዝብ ተግባር በተለያዩ አካባቢዎች ስንት ወገኖች እንዳለቁና እንደተጎዱ ከመኖሪያ ቦታቸውና ከንብረታቸው እንደተፈናቀሉና እንደተዘረፉ ፣ ለእርስዎ የተሰወረ ነገር አልነበረም፡፡ አሁን መቋጫ እያገኘ ነው መባል በተጀመረበት ወቅት ደግሞ ትላንትና አውሮፕላን ይዘው ሲጨፈጭፉ የነበሩ ወገኖችና ሀይሎችም ተጨምረውበት ብቀላ በሚመስል መልኩ ብሄርን ያነጣጠረ ጥቃት ቀጣይነት እንዲኖረው የሚያደርግ ስራ መስራትና ለዚህም በግልፅ የተፈቀደ በሚመስል መልኩ የህዝብ ሉዓላዊነትና ህዝባዊ አንድነት ባረጋገጠ ህገ መንግስት ላይ ጥሰት ሲካሄድ ዝም ብሎ ማለፍና ማየት ለሁላችን ወገኖች ስጋት ላይ እንዲጥል ምክንያት ሆነዋል፡፡
·       ሉዓላዊነታችን ባረጋገጠ ህገ መንግስት ላይ ጥቃት መፈፀምና ግዝአታዊ አንድነትን የሚያስቀድም መፈክር ወደፊት አምጥቶ ቀሮሮ ማሰማት ትላንትናም ለአገሪቷ አልጠቀመም ነገም አይጠቅምም፡፡ ስለ ሰላምና ስለ ፍቅር እየተዘመረ ስለ ህዝቦች አንድነትና ሀይማኖታዊ እኩልነት እየተነገረ ባለበት ሰዓት የእኩልነታቸውና አንድነታቸው መገለጫ የሆነውንና በህገ መንግስታችን ያረጋገጥነውን ባንዴራ እያቃጠሉና እየረገጡ ግዛታዊ አንድነትን የሚገልፅ ባንዴራ እያውለበለቡ ቀረሮ ማሰማት በኢትዮጵያ ህዝቦችና ብሔር ብሔረሰቦች ላይ ያላቸውን ንቀት በግልፅ ያስመሰክራል፣
·       የኤርትራ መንግስትና የግብፅ መንግስት የፌዴራል ስርዓቱ ዋና ሀይል ወያነና የትግራይ ህዝብ ነው በዚሁ ሀይል ላይ ጥቃት ከፈፀምን ፌዴራል ስርዓትና ኢትዮጵያ የምትባል አገር ትበተናለች፣ ህዳሴ ግድቡም ይቆማል፣ የሚል የተሳሳተ እስትራቴጂ ተነድፎ ስራ ላይ መዋል ከጀመረና ሰፊ ዘመቻ መካሄድ ከጀመረበት 5 ዓመት አስቆጥረዋል፡፡ ይህንን የውጭ የጠላቶች ሴራ የራስን እቅድ በማድረግ ለተግባራዊነቱም ላይና ታች እያለ ያለውን የስርዓቱ አመራርና ሀይል አወቀም አላወቀም እቆምልሃለህ ፣ እሞትልሃለህ እያለው ላለው ህዝብም ፍፁም እንደማይጠቅመው ገሀድ ሆኖ ይታያል፡፡
·       ትላንትና በትግራይ ህዝብና በቅማንት ህዝብ ላይ ፍፁም አስቀያሚ ጭፍጨፋና ግፍ የፈፀመ አመራር በፈፀመው ግፍና ጭፍጨፋ ላይ ተጠያቂነት የማይታይበትና ጠያቂ የሌለው ስርዓት በማግኘቱ ተኩራርቶ ራሱን ለቀጣይ ጭፍጨፋና የህዝቦች መተላለቅ እያቅራራ ያለው አመራርና የጠላቶች መሳሪያ የሆነውን ሀይል፣ አገሪቷ ወዴት ሊወስዳት እንደሚችልና ለሁላችን እያንዣበበ ያለውን አደጋ ለእርስዎም ከፍተኛ ስጋት ሊሆን እንደሚችል ሳይገነዘቡት ይቀራል የሚል እምነት የለንም፡፡
·       የግዛት አንድነት አራማጅ ሀይል ስለ ኢትዮጵያ ህዝቦች አንድነት ፣ እኩልነትና ተፈቃቅሮ መኖር ደንታው እንዳልሆነ በግልፅ እያየን ነው፡፡ ቤተ አማራ በሚል የግዛት አንድነት ካርታው እንደተመለከትነው ከሆነ ስለ ኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሶችና ህዝቦች ያላቸውን ንቀት በግልፅ ገሀድ ሆኖ እናየዋለን፡፡ ቤተ አማራ ብሎ ሲያስብ አሁን ካለችው የትግራይ ክልል ከግማሽ በላይ ወደ ቤተ አማራ ያካተተ፣ ሙሉ ዓፋር በቁጥጥሩ ስር ያደረገ፣ ምፅዋዕና ዓሰብን ይዞ ሸዋ ክ/ሀገር ሲባል የነበረ በሙሉ አካቶ በምስራቅ እስከ ድሬዳዋ ፣ በደቡብ እስከ አዋሳ ፣ በደቡብ ምዕራብ ደግሞ እስከ አምቦና ቤንሻንጉል ጉምዝ የሚባለው ክልል ሙሉ በሙሉ በግዛት አንድነቱ የማጠቃለል ፍላጎት እንዳለው ገሀድ አድርገዋል፡፡
·       ሌላው ቀርቶ እርስዎ በአሁን ሰዓት የጀመሩትን መሰረታዊ ለውጦች ህዝቡ ከጎንዎ መሆኑ በሚገልፅበትና ከጎንዎ መሆኑ በሚያረጋግጥበት ወቅት ትላንትና በአደባባይ የህዝቦች ህይወት እንደቅጠል ሲቀጥፉ ከነበረው የፋሽሽት ስርዓት መሪ መንግስቱ ኃይለማርያም ጎን ጋር ፎቶግራፍዎ ዘርግተው ድጋፋችን እየገለፅንልዎት ነን ሲልዎት ፀረ ህዝብ ሀይሎች ፤ በመፈቃቀድ ወደንና ተማምነን የገነባነውን ፌዴራላዊ ስርዓት ለማፍረስ ምን ያህል ቆርጠው እንደተነሱ በግልፅ የምናይበት ሁኔታ እንዳለን ገሃድ አድርጎልናል፡፡
·       ድህነትን ለመቅረፍ አባይ የሚል ግድብ በመስራቱ የስርዓቱ ዋና ሀይል ወያነና የትግራይ ህዝብ እንደ ዋና ጠላት ተወስዶ በሻዕቢያ መሀንዲስነትና በግብፅ ፋይናንሳዊ ድጋፍ ሲካሄድ የነበረ ዘመቻና አገርን የማፈራረስ ሂደት አሁንም በተጠናከረ መልኩ ለማስቀጠል የቦርደር ጉዳይ አሁን አጀንዳ መሆን የለበትም በሚል የሻዕቢያ (የማነ ገብረአብ እና ፕ/ኢሳያስ አፈወርቂ) ስትራቴጂ አፍራሽና በታች ሀይሉ አዲስ አበባ ኮማንድ ፖስት መስርቶ ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ያቀደው ስትራቴጂ ዞሮ ዞሮ የህዝቦች መተላለቅ ሊያስከትል እንደሚችልና በዓለም ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ ጥፋት ሊያመጣ እንደሚችል እርስዎም ከአሁኑ ጀምሮ በአግባቡ መረዳት ያለብዎት ይመስለናል፡፡
·       በተለያዩ መድረኮችና የህዝብ ውይይቶች ሊያደርጉት የነበረ ንግግር ሁሉ ስናየው ለአገሪቷ ጥሩ እሳቤ ፣ ሰላም፣ ፍቅር፣ የሚያሰፍን ለሁሉም ህዝቦች እኩል የሚመለከት፣ ጥላቻና መቃቃርን የሚያስወግድ መፈቃቀርና መዋደድን የሚያሰፍን ንግግር እንደሆነና በዚሁ ልክም የእርስዎ እሳቤ ልባዊ እሳቤ እንደሆነ አድርገን እንመለከተዋለን፡፡
·       ይህ እንዳለ ብንወስደውም የህግን የበላይነት ከማረጋገጥና ከማስፈን አንፃር ግን የራሱ ክፍተት እንዳለው አድርገን እናየዋለን፡፡ በመሆኑም ነፃነት ማለት ህገ መንግስትን መጣስ ፣ የህዝቦች እኩልነትና አንድነት ያረጋገጠውን ህገ መንግስት በጠራራ ፀሀይ መርገጥ፣ አንዱን ህዝብ በሌላው ህዝብ እንዲነሳና ጥቃት እንዲፈፅምበት ማድረግ አድርጎ የተገነዘበ ሀይል ለሌላው የኢትዮጵያ ህዝብም ከፍተኛ ስጋት ሆኖ እንዳለ እርስዎም በአፅንኦት ማየት ያለብዎት ይመስለናል፡፡
ስለሆነም ክቡር ጠ/ሚኒስተር
1.      ለለውጥ መነሳትዎ ለፍቅር ለአንድነት መቆምዎ፣ ጥላቻና ቂም በቀልን ማስወገድዎ፣ ሁሉም ወገኖች በአገራቸው በህዝባቸው ጉዳይ ላይ በሰላማዊ መንገድ ያገባናል ብለው እንዲያስቡ እንዲታገሉ በሰላማዊ መንገድ እንዲወዳደሩ ማድረግዎ እጅግ የሚበረታታና የሚደገፍ ነው፡፡ ለዚሁም ከምንም በላይ ከጎንዎ እንቆማለን፡፡
2.      ለውጥ በንግግር ብቻ አይመሰረትም፡፡ ለውጥ በእቅድና በፕሮጀክት ፣ ለውጥ በመርሀ ግብር በትራንስፎርሜሽን ፣ ተመስርቶ ይካሄዳል፡፡ ይህ ሲሆንም በተደራጀ መልኩና ህዝብን ያሳተፈ ለውጥ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ ስለሆነም ጥሩ እሳቤዎና ፍላጎትዎ የተደራጀና ህዝብን ያሳተፈ ለውጥ እንዲሆን በእቅድ የተመሰረተ፣ ነባራዊ ሁኔታውን ያገናዘበና ተጨባጭ ለውጥን የሚያመጣ ከምፅአታዊ ለውጥ የፀዳ ለውጥ እንዲሆን አድርገው ቢመሩት ውጤታማ ለውጥ እንዲሆን ያደርገዋል አንላለን፡፡
3.      መምጣት ያለበት ለውጥ መነሻና መድረሻ ያለው ለውጥ ቢሆን ህዝቦች በሂደቱና አካሄዱ ያለውና ሊኖረው የሚችል አመለካከት የተስተካከለ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡
·       ይህ ማለት የለውጡ መነሻ ፌደራል ስርዓቱና ህገ መንግስቱ ሆኖ መድረሻው ደግሞ አስተማማኝ ሰላም፣ አስተማማኝ የህዝቦች እኩልነት ፣ አንድነትና ነፃነት፣ የጋራ ተጠቃሚነትና ልማት፣ ከአድልዎ ስርቆትና ሌብነት የፀዳ ፈጣን የህዝብ አገልግሎት የሚያረጋግጥ ስርዓት፣ ፍቅር ፣ አንድነትና ውህደት የሰፈነባት ኢትዮጵያ ፣ ጥላቻ፣ መቃቃር፣ ቅናት ፣ የማይታይባት ኢትዮጵያ፣ በሆነ ይሁን ጊዜ የህግ የበላይነት የሰፈነባት ሰላማዊት አገር ፣ ዜጎች በየትም ቦታ በሰላም ሰርተው የሚኖሩባት ኢትዮጵያ፣ ከውጭ ጣልቃ ገብነት የፀዳች ሉዓላዊነት አገር የመመስረት መዳረሻ ሊኖርዎት ይገባል፡፡ ይህንን ሲሆን ደግሞ ከአገሪቷ አራቱ ማዕዝኖች ድጋፍዎ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚችል ልናረጋግጥልዎት እንወዳለን፡፡      
4.      የአመራርዎ እምብርት ግልፅ መደባዊ ይዘት ያለው አመራር እንዲሆን በአፅንኦት ይጠበቃል፡፡ እስካሁን ባለው አካሄድ ሁሉም ለማስደሰት ታሳቢ ያደረገ እንቅስቃሴ ብቻ ተመልክተናል፡፡ በአንድ ፖለቲካዊ ስርዓት ውስጥ ሁሉም ማስደሰት ቢፈለግና ቢታሰብም ዞሮ ዞሮ ግን መደባዊ ይዘት ያለው ሂደት መሆኑ ፍፁም የማይቀየር ነው፡፡ የፕረዚዳንት ትራምፕ አመራር ዋና መደባዊ ይዘቱ ካፒታሊስቱን በዋናነት መጥቀም ነው፡፡ ለዚህ ሲሉ ያላቸውና የሌላቸው ሀይልና አቅም በሙሉ አሟጠው ሲጠቀሙ ይታያል፡፡ ኢህአዴግ ደግሞ ካፒታሊዝም የመገንባት እቅድ ፍላጎት ቢኖረውም ዋና ይዘቱ ነፃ ኢኮኖሚ በመገንባት ሰፊውን ህዝብ ተጠቃሚ እያደረገ የሚገነባ ካፒታሊዝም የመገንባት እቅድ እንደነበረው በግልፅ ያስቀምጣል፡፡ የእርስዎ አካሄድም ሁሉም ለማስደሰት አስበው ቢሰሩም እምብርት ያለው አካሄድ እንዲሆን ግን በግድ ይፈለጋል፡፡
5.      እርስዎ እርቅና ሰላም ለመፍጠር፣ ፍቅርና አንድነት ለማስፈን፣ ጥላቻና ቂም በቀልን ለማስወገድ አስበው የሚሰሩት ስራ እጅግ በጣም የሚደገፍና የሚበረታታ ቢሆንም በዚህ መፈክር በዙርያዎ እርስዎን መጠቀምያ ለማድረግ የሚያንዣብብ ፣ የውሸት ወሬ የሚረጩ፣ ያልተደረገ፣ ያልተወራ፣ ያልታሰበ ነገር እንደታሰበ፣ እንደተደረገ እንደተወራ አድርገው የሚያስወሩ፤ ጥላቻን የሚጭሩ፣ እርስዎ በተሳሳተ መንገድ የሚመሩ፣ እርስዎን መጠቀሚያ የሚያደርጉት ጥገኞች በዙርያዎ እንዳያንዣብቡና ገና የለውጥ ሂደቱን እሳት እንዳያስገቡበት ፣ ያሰቡትና ያቀዱት ገና ሳይጀመር ጥላሸት እንዳይቀቡት ከጅምሩ ሁሉም ስራዎችዎ በጥንቃቄና በተደራጀ መንገድ እንዲመሩት ከሁሉም በላይ በህዝብ ተሳትፎና ግሩፕ ስራ ትልቅ ቦታ እንዲሰጡት ከአደራ ጭምር እናሳስብዎታለን፡፡ ከአሁኑ ጀምሮ አማካሪ ነኝ ፣ ፕሮጀክት አሰጥሀለህ ፣ ሚኒስተር አስደርግልሀለህ እየተባለ በጠራራ ፀሀይ እየተዘረፈ ያለውን ገንዘብ ለእርስዎም መረጃው ሳይደርስ ይቀራል የሚል እምነት የለንም፡፡
6.      እርቅና ሰላምን ለማውረድ ጥላቻና ቂም በቀልን ለማስወገድ ሲሉ ትላንትና በመስቀል አደባባይ በሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖች የቀጠፈ የደርግ ባለስልጣኖችም ምህረት አስገብቷል፡፡ ሰላም፣ ፍቅር ለቀጣይ ህዝባዊ አንድነት ሲባል ሁሉ ሰው እየደገፈ ነው፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ የኔ ተቀናቃኝ ናቸው ስለኔ እንዲህ ብሎ አውርቷል ወዘተ ብለው ወደ ቂም በቀል የሚወስድ እርምጃ እየሄዱ እንደሆነ እያየን ነው፡፡ የተናገሩትን ንግግር ቀለሙ ሳይቀር ወደ እንደነዚ እርምጃ መሄድ አያስፈልግም ነበር በኛ እምነት በጀመሩት አካሄድ ቢቀጥሉ ይመረጣል እንጂ እርስ በእርሱ የሚጣረስ ተግባር መፈፀም ለእርስዎም ግምት ውስጥ ይከታል እንላለን፡፡
7.      ከሁሉ በላይ በአፅንኦት ልንመክርዎት የምንፈልገው ነገር ቢኖር በአሁኑ ሰዓት ለዚህ ህዝብና ለዚች አገር ጦርነት ፍፁም አያስፈልገውም፡፡ ማን ያሸንፋል ማን ድል ያስገኛል የሞኞች እሳቤ ነው፡፡ በአሁኑ ሰዓት እያንዳንዷ እንቅስቃሴዎ እንደ ጀመሩት ፍቅርን ሰላምን የሚያሰፍን ጦርነትን የሚያስርቅ እንጂ ህዝቦች ወደ ጦርነትና ግጭት የሚያስገባ እንዳይሆን ጥንቃቄ ይጠይቆታል፡፡ እያንዳንዷ እንቅስቃሴዎ ደግሞ ከሁሉም ህዝቦች ብቃትና ህዝባዊ ውግንና ያላቸው አማካሪዎች ቢያደርጉ እሳቤዎና ምኞትዎ ይቃናል፣ ይሳካልም ብለን እናምናለን፡፡
8.      በኛ እምነት በአሁኑ ሰዓት እርስዎን የሚያግዙና ራእይዎ በማሳካት ከጎንዎ የሚቆሙ ሰዎች ነገሮች በነቀፌታ ዓይን የሚያዩ ሰዎች ቢሆኑና እርስዎም እንደዚህ የመሰሉ ሰዎች ቢመርጡ ለውጤትዎ አጋዥ ይሆናሉ የሚል እምነት አለን፡፡ ለእርስዎ ጥሩ እየመሰሉ ከበስተጀርባዎ ደግሞ ሌላ ስራ የሚሰሩ ሰዎች መምረጥ ኢህአዴግም ለውድቀት የዳረጉት እንደዚህ ዓይነት “Yes Men” ሰዎችና ወረበሎች ናቸው፡፡ ከማንም ጊዜ በላይ አደራ የምንልዎት ከነዚህ የመሰሉ አስመሳዮች ምንም ዓይነት ስብእና የሌላቸው ወሬኞችና ወረበሎች መራቅ ነው፡፡
9.      አጀማመርዎ ለህዝቦች እያስደሰተ ነው፡፡ አጀማመርዎ ፍቅር ነው፣ ሰላም ነው፣ መዋደድ ነው፣ ይቅር ይቅር መባባል ነው፡፡ ኢኮኖሚውም በዚህ ልክ ቢሆን ፤ የተራበ እንዲበላ ቢደረግ፤ ስራ ያጣ ስራ እንዲያገኝ ቢደረግ፤ የኑሮ ውድነቱ መልክ ቢይዝ፤ አጀማመርዎ እንዳማረ ሁሉ አጨራረስዎ ያማረ እንዲሆን እያንዳንዷን እንቅስቃሴ በጥናቃቄ ቢመራ ያምራል እንላለን፡፡ አለበለዚያ እዩኝ እዩኝ እንደተባለ ሁሉ ነገ ደግሞ ሰውሩኝ ሰውሩኝ እንዳይሆን፡፡              
ክቡር ጠ/ሚኒስተር
·       ሌላውን ህዝብ የሚንቅና የሚያንቋሽሽ አመራር የራሱን ህዝብ ሊጠቅምም ፍፁም አይችልም፡፡ እንደ ትላንትናው የደርግ መፈክር “እፍኝ”  የማይሞሉ የሚል የተሳሳተ የሰነፎችና ደካሞች አባባል ያነገቡና በትምክህት የተወጠረ አመለካከት ያለው ሀይል ለውጡ ሳይጀመር ሌላ እሳት እንዳይጭርብን ለ27 ዓመት ያገኘነውን ሰላም ሌላ ጦርነት ውስጥ እንዳይከተን ነገሮች በጥንቃቄና በበቂ ችሎታ ልንመራውና ልንከታተለው ይገባል፡፡ በዛም በዚህም ከአሁኑ ብቅ ብቅ እያሉ ያሉ አካሄዶችና አመለካከቶች ምልክታቸው አደገኛና ትላንትናም ለከፍተኛ ፍጅት የዳረገን አመለካከት ነው፡፡ እርስዎን በመደገፍ ስም ህገ መንግስቱን በጠራራ ፀሀይ የሚንድ አካሄድ መሄድ፣ ህዝቦችን የሚንቅ አመለካከት ፣ የግዛት አንድነትን ለማስመለስ የሚቋምጥ አካሄድ በሆነ ይሁን መለኪያ ነገና ከነገ ወዲያ የእርስዎ ስልጣን ለመንጠቅ ያሴራ ሀይል እንጂ እርስዎ ላነገቡት ለውጥ ፍፁም ሊደግፍ አይችልም፡፡ ስለሆነም ስንዴውና እንክርዳዱ ተደበላልቆ አደጋ ውስጥ እንዳያስገባን በጥንቃቄ እንዲያዩትና እንዲመሩት በአፅንኦት ምክራችን እንለግሳለን፡፡
የተከበራችሁ የፌደራል ስርዓቱ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት
·       የፌደራል ስራአቱ ሉዓላዊነት የኢትዮጲያ ብሄሮችና ብሄረሰቦች ህዝቦች የኢትዮጲያ ሉአላዊ ስልጣን ባለቤቶች ናቸው፡፡ ህገ መንግስቱ ደግሞ የሉዓላዊነታቸው መገለጫ ነው፡፡ ሉዓላዊነታቸው የሚገለጸው ደግሞ በዚህ ህገ መንግስት መሰረት በሚመርጧቸው ተወካዮችና በቀጥታ በሚያደርጉት ዴሞክራሲያዊ ተሳትፎ አማካይነት ነው፡፡ ህገ መንግስቱ ደግሞ የአገሪቷ የበላይ ህግ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ማንኛውም የአገሪቷ ዜጋ፣ የመንግስት አካላት፣ የፖለቲካ ድርጅቶች ፣ሲቪክ ማህበራት ፣ማንኛውም ባለስልጣን  ህገ መንግስቱን የማስከበርና ለህገ መንግስቱ ተገዥ መሆን እንዳለበት ህጉን ይደነግላል፡፡
·       ስርዓቱና ህጉ ግልፅ በሆነበት አገር ላይ የህዝብ ሃላፊነትና ስልጣን የያዙ ሃይሎችና አመራሮች ህገ መንግስቱ በግልፅ  ሲንዱትና ሲጥሱት ዝም ብሎ መመልከት ለናንተ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላትም የሞራልና የህሊና ቁስል ነው፡፡ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ተገዥነታችሁ ለህገ መንግስቱ ለህዝቡና ለህሊናችሁ በሆነበት ወቅት ህገ መንግስቱ ሲጣስና የህዝብ ሉዓላዊነት ሲናድ ዝም ብሎ ማየትና መስማት አገሪቷ ዋስትና ወደ ሌለው መንገድ እየሄደች እንደሆነ ፤ አነሰም በዛም ወደ ሌላ የእርስ በርስ ጦርነት እየተመራች እንደሆነ ማወቁና መረዳቱ የግድ ይላል፡፡
 
ስለሆነም የያዛችሁት የህዝብ ውክልና ተጠቅማችሁ ህገ መንግስቱ እንዲከበር ፣ የህዝብ ሊዓላዊነት እንዲከበር ፣ ህገ መንግስቱና ስርዓቱ ሲጣስ ህገመንግስቱን የጣሱ ሃይሎች ፣ አመራሮች፣ ባለስልጣኖች በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ፣ ህዝቦች በአገራቸው ላይ ሰብአዊና ፖለቲካዊ መብታቸው እንዲከበር፣ በማንኛውም የአገሪቷ ክልል ተዘዋውረው የመስራት መብታቸው እንዲጠበቅ፣ አገራችን የጀመረችው የሰላም፣ የልማትና የዴሞክራሲያው አንድነት መንገድ እንዲጠበቅ፤ እናንተም በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባልነታችሁ በህሊናችሁ ለመረጣችሁ ህዝብ ስትሉ ዘብ እንድትቆሙ፣ ከአደራ ጭምር ትጠየቃላችሁ፡፡
መላ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ህዝቦች፡
·       ትላንትና በደማችሁ እና በአጥንታችሁ አስከፊውን የደርግ ስርዓት በማስወገድ ወዳችሁና ተፈቃቅራችሁ ፌዴራላዊት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ መስርታችኋል፡፡ መብታችሁና ጥቅማችሁ ሉዓላዊነታችሁ አንድነታችሁና ነፃነታችሁ የምታረጋግጡበት ህገ መንግስት መስርታችኋል፡፡ በሆነ ይሁን ጊዜ ይህ ህገ መንግስት የሁላችን ህዝቦች ዋስትና ነው፡፡ ማስተካከልና ማሻሻል ካስፈለገም በገዛ ፍቃዳችንና እምነታችን እንጂ በማንም ሀይል አስገዳጅ ፍፁም ሊቀየር አይችልም፡፡ ስለሆነም ይህንን ህገ መንግስት የሁላችን ህዝቦች ዋስትና እንደመሆኑ መጠን ከማንም ጥቃትና አፍራሽ እንቅስቃሴ በንቃት በተደራጀና በተዋሃደ መልኩ ልንጠብቀው ይገባል፡፡ የግዛት አንድነት አራማጆች ሽንፈታቸውን ባለመቀበል የድሮ ስርዓታቸውን ለማስመለስ እየቋመጡብን መሆናቸው በአመክሮ ልንመለከተው ይገባል፡፡ በሆነ ይሁን ጊዜ ደግሞ ቅንጣት ታክልም ለግዛት አንድነት አመለካከታቸውና ተግባራቸው እድል ልንሰጥ አይገባም፡፡
የተከበራችሁ የኢህአዴግ አመራሮች   
·        አገራችን ከአስከፊው የደርግ ስርዓት ተላቃ የህዝቦች እኩልነት፣ ነፃነት፣ አንድነትና የጋራ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ከጀመረች 27 ዓመት አስቆጥራለች፡፡ እንዲህ በሆነበት ወቅት ከህዝቡ ጥቅም በፊት የራሱን ጥቅም ማስቀደም የመረጠውን አመራር ራሱን ወደ ገዢ መደብ በመቀየር የህዝቦችን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብት በመርገጥ፣ የያዘውን ስልጣን ለኢፍትሃዊ አድላዊ አካሄድ፣ ለስርቆትና ለቅጥፈት ሲጠቀምበት ቆይቷል፡፡ ይህንን የበሰበሰ አካሄድ ራሳችሁም አምናችሁም የተቀበላችሁት መሆኑ የሚታይ ቢሆንም በውስጣችሁ ያለው የገማ አካሄድ የመጨረሻው ውጤት ወደ ህዝቦች መተላለቅና ፍጅት እየመራችሁት መሆኑ በግልፅ እየታየ ነው፡፡ ህዝቦች በውስጣቸው ምንም አይነት ቅራኔ የለም፡፡ በየትም ጊዜም ኖሮ አያውቅም፡፡ ተፈቃቅሮ ተከባብሮ አንድነቱን ጠብቆ ሲኖር የነበረ ህዝብ በኋላ ቀር አመለካከትና ዘርአዊ ቅስቀሳ ህዝቦችን ለማፋጀት እየቋመጣችሁ መሆናችሁ እየታየ ነው፡፡ ይህንን የተሳሳተ አካሄድ ፍጅቱ በህዝቦች ብቻ የሚቆም ሊሆን አይችልም፡፡ እናንተንም ጭምር የሚያቃጥላችሁ ፍጅት ሊሆን እንደሚቻል ከአሁኑ ጀምራችሁ ልትገነዘቡት ይገባል፡፡ ቢሆን ቢሆን ለስልጣን ብላችሁ ህዝቡን ከምታፋጁት በገዛ ፍቃዳችሁ ስልጣኑን ለህዝብ አስረክባችሁ የህዝቡን ሰላምና የልማት ጉዞ እንዲቀጥል ብታደርጉት ለናንተና ለቤተሰባችሁም ተጠቃሚ እንደሚያደርጋችሁ የሚጠፋችሁ አይመስለንም፡፡ ስለሆነ ከማፋጀት ሰላም ብትመርጡ፣ ለግላችሁና ለሆዳችሁ ከምታስቡ ለህዝብና ለአገር ብታስቡ፣ ከመቃቃርና ጥላቻ መቻቻልና በጋራ መስራት ብታስቀድሙ ፣ ወንጀለኞች በህግ ተጠያቂ ብታደርጉ፣ መጥፎ መስራት ለአገርና ለህዝብ ጥፋት ካልሆነ በስተቀር የሚያተርፈው ነገር እንደሌለ ተረድታቹ፤ ጥሩ በመስራት ስማችሁና ክብራችሁ አስጠብቃችሁ በህዝባችሁም ተከብራችሁ ብትኖሩ ይመረጣል እንላለን፡፡
የተከበራችሁ የትግራይ ህዝብ ሆይ
·       በአስር ሺዎች የሚቆጠር መስዋእት ከፍለህ የህዝቦች እኩልነት፣ አንድነትና ነፃነት የጋራ ተጠቃሚነት ያለው ስርዓት መመስረትህ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ያውቁታል፡፡ ሁሌም ለመስዋእትህና ለከፈልከው ዋጋና ክብር ይሰጡታል፡፡
·       በመስዋእትህ የተገነባውን ስርዓት ለማፍረስና የከፈልከውን መስዋእት ዋጋ ቢስ ለማድረግ አንተም አበሳጭተው ወደ አልተፈለገ ግጭት ሊያስገቡህ ላለፉት ሁለት ሦስት ዓመታት ያልተፈለገ መስዋእት ዳግም እንድትከፍል እያደረጉህ እንደሆነ በግልፅ ታይቷል፡፡
·       እጅግ በጣም የሚገርመው ግን በነሱ ሴራና ጥላቻ ሳትበገር የከፈልከውን መስዋእት ታሳቢ በማድረግ ያሳየኸውን አስተዋይነት፣ ቻይነትና ታጋሽነት የታላቅነትህ ምስክር መሆኑ ገሀድ የሚያደርገው ነው፡፡
·       ጠላቶችህ ማንነትህና የማድረግ ችሎታህ በአግባቡ ጠንቅቀው ያውቁታል፡፡ አሁን በደካማ አስተሳሰባቸውና ቀቢፀ ተስፋ እምነታቸው የማይጫር ነገር ቢጭሩ እንደወትሮህ ታጋሽነትህ ፣ ቻይነትህ፣ ታላቅነትህ አሳያቸው፡፡ ይህንን ስታደርግም ራስህን አደራጅተህ ፣ ውስጣዊ አንድነትህን ጠብቀህ ፣ እያንዳንዷን እንቅስቃሴ በጥንቃቅ በአፅንኦት እየተመለከትክ ፣ ከሌላው ወንድምህ ኢትዮጵያዊ እየተደጋገፍክ ፣ ለሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ መፍትሄ ቅድሚያ ሰጥተህ ፣ ታጋይነትህና ጀግንነትህ ግን እንደወትረው ጠብቀህ የግዛት አንድነት ሀይሎች ከሁሉም ኢትዮጵያውያን በጋራ ሆነህ መክታቸው፡፡
የተከበራችሁ የኤርትራ ህዝብ ሆይ
·       አስከፊው የደርግ ስርዓት ከወንድምህ የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በጋራ ሆነህ ከገረሰስከው በኋላ ከወንድምህ የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በመተባበር ሰላምና የጋራ እድገት ይመጣል ተብሎ በሚጠበቅበት ጊዜ እብሪትና ጦርነት የሚናፍቃቸው አመራሮች ከወንድምህ የኢትዮጵያ ህዝብ በቦርደር ስም ወድ ጦርነት ማግደውህ ከሁሉም ህዝቦች በአስር ሺዎች የሚቆጠር ወጣት አልቀዋል፡፡ ላለፉት 20 ዓመታት ደግሞ ሰላምና ጦርነት የሌላቸው አገሮች እንደሆኑ አድርገውሃል፡፡
·       ሰላም፣ ወንድማማችነት፣ የጋራ ተጠቃሚነትና ወንድማዊ መደጋገፍ ለሁላችን ህዝቦች ይጠቅማል፡፡ ከማንም ግዜ በላይ ደግሞ አሁን ያስፈልገናል፡፡
·       ይህንን ፍላጎት የተረዱ የተወሰኑ አመራሮችህ የህዝባቸውን ፍላጎት በማስቀደም በአሁን ወቅት ከኢትዮጵያ ህዝብ በተለይ ደግሞ ከትግራይ ህዝብ ትክክለኛ እርቅ ያስፈልገናል ሲሉ ይሰማል፡፡ ይህንን ፍላጎት የሌላቸው እንደነ ፕረዚዳንት ኢሳያስ እና የማነ ገብረአብ የመሰሉ ግን ከትክክለኛውና የህዝብ እርቅ ወጥተው ከግዛት አንድነት ሀይሎች በሚስጥር እየደለቱና እየተማከሩ የትግራይ ህዝብን ከጫወታ ውጭ በማድረግ ቁማር እየተጫወቱ መሆናቸውን በግልፅ እየተመለከትን ነው፡፡ ይህንን የተሳሳተ አመለካከት ግን ላንተው ይሁን ለወንድምህ የኢትዮጵያ ህዝብ አንዳች ጥቅም የለውም፤ ፍፁምም አይኖረውም፡፡
·       ስለሆነም ትክክለኛው እርቅ እየተመኙ ያሉ አመራሮችህን እየደገፍክ ከወንድምህና የቅርብ ቤተሰብህ ሰላምህን ፈጥረህ አፍራሽ ሴራና እንቅስቃሴ እያደረጉ ያሉ ሰይጣን አመራሮችህ እየተቃወምክ መልካም ጉርብትናህን ወንድምነትህን ወደ ድሮ ቦታው መልስ፡፡ ወንድምህና መልካም ጉርብትናህ የሚመኘው የኢትዮጵያ ህዝብም እንደወትረው እጁ ዘርግቶ እየጠበቀህ ይገኛል፡፡
በስተመጨረሻ ኢትዮጵያ አገራችን በአሁኑ ወቅት ከሰላምና ልማት መንገድ ውጭ ሌላ ምርጫ ሊኖራት አይገባም፡፡ ጦርነት ለህዝባችንና ለአገራችን ያለው ፋይዳ በአግባቡ ጠንቅቀን የምናውቅና የተረዳን ህዝቦች ነን፡፡ ከዴሞክራሲያዊ አንድነት፣ ከሀይማኖታዊ ብሄር ብሄረሰብ ነፃነት ውጭ ሌላ ምርጫ ይኖረናል ብሎ ማሰብ ከንቱ ምርጫ ነው፡፡ በሆነ ይሁን ጊዜ ፍፁም ተቀባይነት የማይኖረው ምርጫ ነው፡፡ እንኳን አሁን ድሮም ቢሆን ከከፍተኛ ኪሳራ ውጭ የፈየደ ነገር የለም፡፡
ስለሆነም ህዝቦች በሀይል ገዝቶና አንበርክኮ መኖር ፍፁም እንደማይቻል ማወቅና መረዳት የግድ ይላል፡፡ በመሆኑም በስልጣን ያላችሁና ለስልጣን የምትቋምጡ ወገኖች ሀይሎች በሙሉ ዘመን ያለፈበት ሴራ አንግባችሁ ሌላ ሽንፈት ከመከናነብ ትክክለኛውን የህዝብ ምርጫ ይዛችሁ ሰላምና ልማቱ ብታስቀጥሉ ለናንተም ጠቃሚ ምርጫ ነው ልንላችሁ እንወዳለን፡፡ ይህንን ሳይሆን ሲቀር ግን ሊያስከትለው የሚችል አደጋ ቀላል ሊሆን እንደማይችል በአፅንኦት ለመግለፅ እንወዳለን፡፡   
 
ሀገራችን ኢትዮጵያ ሰላምዋን ያብዛልን!
 
Back to Front Page
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1107
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Re: ትግሬ እጠላለሁ !ዘረኛ ግን አይደለሁም::

Postby ለማ12 » Sat Jul 14, 2018 11:38 am

Back to Front Page


Share This Article!

የድንበር ጉዳዮች

ዕረፍት ይነሳሉ፤ማሰብ ይፈልጋሉ

ክፍል ሁለት

አሜን ተፈሪ 07-11-18

ባለፈው ሣምንት በሰሜን ምዕራብ እና በደቡብ ኢትዮጵያ በሚገኙ ሁለት የጠረፍ ከተሞች በተለያዩ መነሾዎች የተከሰቱት ጠንከር ያሉ ግጭቶች በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት ማስከተላቸው ሰምተናል፡፡ እነዚህ ግጭቶች የተከሰቱት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የተዘጋጀው የጠረፍ ከተሞችን ችግሮች የመዳሰስ እና የፖሊሲ ምክረ ሐሳቦችን የመቀመር ዓላማ ይዞ የተካሄደው አውደ ጥናት በተጠናቀቀ ማግስት ነበር፡፡

ኢትዮጵያ ሞያሌ፣ ቋራ እና መተማን ከመሳሰሰሉ የጠረፍ ከተሞች የመጡ ሰዎች ተሳታፊዎች በዚሁ ጉባዔው ተሳታፊ እንደነበሩ እና ከአዲስ አበባ ወደ መጡበት በመመለስ ሳይ ሳሉ ነበር ግጭቶቹ ተከሰቱት -- የመተማው ግጭት ሰኔ 27 2010 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሞያሌው ደግሞ በማግስቱ ሰኔ 28 2010 ዓ.ም፡፡ በቋራ እና መተማ አካባቢ የተከሰተው ግጭት በመከላከያ ኃይል ጣልቃ ገብነት ቢቆምም፣ ግጭቱን ለዘለቄታው ለመፍታት እንዲያስችል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር)፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ለሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር ሐሰን አል በሽር የላኩትን መልዕክት መላካቸው ታውቋል፡፡

ከቋራ እና መተማው ግጭት አንድ ቀን ቀደም ብሎ ውጥረት ተለይቷት በማታውቀው የኢትዮጵያ ሞያሌ ከተማ የተከሰተው ጎሣን መሠረት ያደረገ ግጭት መሆኑን እና የመተማው ደግሞ ከእርሻ መሬት ጋር የተያያዘ እንደሆነ የተለያዩ መገናኛ ብዙሃን የጠቀሱ ሲሆን፤ ከሁለቱ ከተሞች የመጡት የጉባዔው ተሳታፊዎች በስብሰባው ላይ ከሰጡት አስተያየት መረዳት እንደሚቻለው ግጭቶች በተደጋጋሚ ይከሰታሉ፡፡

በኢትዮጵያ ሞያሌ ከተማ ከሁለት ወር በፊት ሚያዚያ 28/2010 ዓም ተፈጥሮ በነበረ የጎሣ ግጭትበርካታ ሰዎችን ለጉዳት የዳረገ እና ንብረትም ያወደመ ግጭት መከሰቱን የሚታወስ ሲሆን፤ ከትናንት በስቲያ ሐሙስ ሰኔ 28/2010 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ዳግም ባገረሸው ጎሣን መሠረት ባደረገ ግጭት ከሁለቱም ወገን ሰዎች መሞታቸውን እና ከመሐል ሐገር ወደ ሞያሌ የሄዱ ዘጠኝ የጭነት መኪኖችም መጋየታቸውንም አመልክተዋል፡፡

በሞያሌ በሚገኘው የፌደራል ገቢዎች እና ጉምሩክ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት ላይ ጉዳት መድረሱን የጠቀሱት ምንጮቻችን፤ በገሪ እና ቦረና ጎሣ አባላት መካከል የተከሰተውን ይህን ግጭት ለማብረድ የጸጥታ ኃይሎች ጥረት ማድረጋቸውን ጠቅሰው፤ ግጭቱ በዘመናዊ መሣሪያ የተደገፈ በመሆኑ ጉዳቱን ከፍ እንደሚያደርገው እና የጸጥታ ኃይሎች ግጭቱን ለመቆጣጠር የሚያደርጉትን ጥረት አስቸጋሪ እንደሚያደርገውም በዚሁ ስብሰባ ያገኘኋቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸውልኛል፡፡

በኦሮሚያ እና በኢትዮ-ሶማሌ ክልል ለሥር ለሚተዳደሩ ሁለት ወረዳዎች መቀመጫ በመሆን በምታገለገልው እና የአንዳንድ የፌዴራል መስሪያ ቤቶች መቀመጫ በሆነችው የሞያሌ ከተማ፤ ከሁለት ወራት በፊት ከአስፋልት ግራ እና ቀኝ በመሆን በተካሄደ የተኩስ ልውውጥ በርካታ የከተማው ነዋሪዎች ለአካል ጉዳት እና ለሞት መዳረጋቸውን እንዲሁም ንብረት መውደሙን ያስታወሱት እነዚሁ ምንጮች፤ ከተማዋ ዘወትር በውጥረት የምትኖር እና ባልረባ ምክንያት ግጭት እንደሚቀሰቀስ፤ የሁለቱ ጎሣ አባላት በመበቃቀል መንፈስ እንደሚጠቃቁ፤ የከብት ዝርፊያ እንደሚካሄድ እና በከተማው በሰፊው በሚታዩ የሞተር ሳይክሎች የታገዘ የሰዎች ጠለፋ አንደሚፈጸም ተናግረዋል፡፡

በአንድ የአስፋልት መንገድ ግራ እና ቀኝ የተለያይተው የሚገኙት የሁለቱ መስተዳድሮች የሚታዘዙ የጸጥታ ኃይሎች በግጭቱ ተሳታፊ እንደሚሆኑ የሚጠቅሱት ምንጮቻችን፤ የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል እና የኦሮሚያ ክልል አድማ በታኝ ኃይል አባላት እንዲሁም የቀበሌ መስተዳድር ሚሊሻዎችን በስም ይጠቅሳሉ፡፡ ሰኔ 28 በገሪ ጎሣ አባላት (ሶማሌ) እና በቦረና ጎሣ አባላት (አሮሞ) በተከሰተው ግጭት ከሁለቱም ወገን ሰዎች ለህልፈተ ህይወት መዳረጋቸውን አመልክተዋል፡፡

በሌላ በኩል፤ ሱዳንን ከኢትዮጵያ በሚያዋስነው የምዕራብ ጎንደር ዞን፣ መተማ አካባቢ በሚገኝ የእርሻ መሬት ይገባኛል ጥያቄ ለግጭቱ ምክንያት መሆኑን የጠቀሱት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘላለም ልጃለም ‹‹ሱዳኖች በኢትዮጵያ መሬት ላይ የሚያነሱት የይገባኛል ትክክል አይደለም›› ማለታቸውን የአማራ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል፡፡

‹‹የእርሻ ስራ በሚያከውኑ የአካባቢው የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች ላይ ትንኮሳ በመፈጸማቸው ምክንያት ግጭቱ ተከስቷል›› ያሉት ኃላፊው፤ የአካባቢው አርሶ አሮችም የመከላከል አጸፋ መውሰዳቸውን እና አሁን የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በቋራ እና መተማ ጥበቃ እያደረገ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ የዞኑ አስተዳዳሪ እና አርሶ አደሮች እንደተናገሩት አሁን ላይ ግጭቱ የተረጋጋ ቢመስልም፤ በሱዳን ወታደሮች ትንኮሳ ምክንያት በአካባቢው ባሉ ሌሎቹ የኢትዮጵያ መሬቶች ላይ የእርሻ ስራ ማከናወን አልተቻለም ብለዋል፡፡
Videos From Around The World

ከአማራ ብዙሃን መገናኛ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክት፤ በግጭቱ ምክንያት በመተማ ደለሎ በኩል ከሚገኝ የሱዳን ጦር አንድ የሱዳን ሻለቃ አመራር ህይወቱ አልፏል፡፡ በቋራ ነፍስ ገበያ በኩል በተፈጠረው ግጭትም 7 የሱዳን ወታደሮች መሞታቸውን እና 2 መኪናዎችን እና 7 የጦር መሳሪያዎችም መማረካቸውን አቶ ዘላለም ተናግረዋል ያለው የአማራ መገናኛ ብዙሃን፤ ሶስት የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች እና ሁለት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ህይወታቸው ማለፉን፤ 6 ሰዎች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸው ሆስፒታል መግባታቸውን አመልክቷል፡፡ ከነዚህም መካከል ሁለቱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ናቸው፡፡ ለጣምራ የጸጥታ ቁጥጥር በሚል በአካባቢው የሰፈረው የሱዳን ጦር በተለያዩ ጊዜያት ትንኮሳ እንደሚፈጽም የአካባቢው ነዋሪዎች እና ዋና አስተዳሪው አስረድተዋል፡፡ በተደጋጋሚ በሰላማዊ መንገድ ቦታውን ለቀው እንዲወጡ ጥረት ቢደረግም ፈቃደኛ አለመሆናቸውንም አመለክተዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ በሁለቱ አገሮች ድንበር አካባቢ የሚነሱ ግጭቶችን በዘላቂነት ለመቅረፍ ትኩረት ሰጥቶ መሰራት እንደሚያስፈልግ የሚገልጽ መልዕክት የያዘ ደብዳቤ ከኢትዮጵያው ጠ/ሚ ሚኒስትር ደረሳቸው፤ የሱዳን ፕሬዚዳንት አማር ሀሰን አል በሽር እንዲህ ዓይነት ግጭት የሁለቱን አገሮች ስትራቴጂካዊ ግንኙነት እንደማይጎዳው እና ሰዳን የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ለማጠናከር አገራቸው እንደምትሠራ መናገራቸው ተሰምቷል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ በበኩላቸው፤ ሰሞኑን በኢትዮጵያ እና በሱዳን ድንበር አከባቢ በአርሶ አደሮች የተፈጠረው ግጭት አዲስ እንዳልሆነ እና ክረምት፤ በመጣ ቁጥር የሚከሰት በመሆኑ፤ ይህን ችግር ለመፍታት ሁለቱ አገሮች ይበልጥ መሥራት እንዳለባቸው የገለጹ ሲሆን፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ከሱዳኑ አቻቸው አል ዲርዲሪ መሐመድ አህመድ ጋር ተገናኝተው በተወያዩ ጊዜ፣ በሁለቱ አገሮች ድንበር አካባቢ የሚነሱ ግጭቶችን በዘላቂነት ለመቅረፍ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሠሩ አስታውቀዋል፡፡

ሰኔ 23 እና 24/2010 ዓ.ም የተካሄደው እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የተዘጋጀው ገባዔ እንዲህ ባሉ ድንበር አካባቢ ችግሮች ነው፡፡ በቅርቡ ጠ/ሚ አቢይ አህመድ ለፓርላማ እንደተናገሩት የአፍሪካ ሐገራት ድንበሮች እቲፊሻል እና የተወሳሰበ ችግር የሚታይባቸው ናቸው፡፡ ስለዚህ በጠረፍ አካባቢ ያሉ መንደሮች እና ማህበረሰቦች ከፍተኛ ጫና የሚፈጥር የተጠላለፈ ህይወት የሚመሩ ናቸው፡፡ አንድ ቀን በዓይኑ አይቶት ወይም በእግሩ ረግጦት የማያውቀውን አካባቢ በእርሳስ እያሰመረ እንደ ፈቀደው ካርታ እየሰራ ቅኝ ገዢ በፈጠረው ድንበር ለመኖር የተገደዱ ናቸው፡፡ ይህም ካርታ የአፍሪካ ሐገራት ድንበር ሆኖ ጸና፡፡ ስለዚህ የአፍሪካ ሐገራት ድንበሮች፤ በወታደራዊ ቁርቋሶዎች፤ በከብት ዘረፋ፤ በሽብርተኝነት፤ በመገንጠል እንቅስቃሴ፤ ኮንትሮባንድ ንግድ፤ በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር፤ ግዛት በማስፋፋት ጥረት እና በገበሬዎች የአመጽ እንቅስቃሴ የሚታመስ አካባቢ ነው፡፡

ከፍ ሲል የተጠቀሱት ችግሮች በአፍሪካ የድንበር አካባቢዎች ዘወትር የሚስተዋሉ ናቸው፡፡ ሆኖም የድንበር ችግር በአፍሪካ ሐገሮች የተወሰነ አይደለም፡፡ የሩሲያ እና የዩክሬን ሁኔታ ለዚህ ማስረጃ ነው፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚወሳሰብ ችግር የሚታይባቸው የአፍሪካ ድንበሮች፤ በጥበብ ካልተያዙ በቀር፤ ጊዜ ጠብቆ ሊፈነዳ የሚችል ችግር የታቀፉ ናቸው፡፡

የአፍሪካ አህጉር መንግስታት ከቅኝ ግዛት ዘመን በፊት ድንበራቸውን ለመወሰን ባደረጉት ጥረት ከሞላ ጎደል ትክክለኛ ድንበር ወይም የታወቀ ወሰን ፈጥረው ነበር፡፡ ሆኖም ‹‹ከበርሊን ኮንፈረንስ›› በኋላ ሁኔታዎች በእጅጉ ተለወጡ፡፡ ቅኝ ገዢዎችም ድንበሩን እንዳሻቸው አደረጉት፡፡

የበርሊን ኮንፈረንስ የአፍሪካን ድንበር ለመወሰን ጥረት የተደረገበት አይደለም፡፡ ድንበሩም በዘፈቀደ ሲሰመር የነበረ ነው፡፡ በመሆኑም በአሁኑ ጊዜ በርካታ የአፍሪካ ሐገራት በድንበር ጉዳይ ተፋጥጠው ይገኛሉ፡፡ በአህጉሪቱ ወደ መቶ ገደማ የሚሆኑ የድንበር ይገባኛል ውዝግቦች አሉ፡፡ ከእነዚህ ድንበሮች አንደ በኢትዮ-ኤርትራ መካከል ያለው እና በሺዎች ለሚቆጠሩ የሁለቱ ሐገራት ዜጎች ህይወት መጥፋት መንስዔ የሆነው የባድመ ውዝግብ አንዱ ነው፡፡ ለምሳሌ ኬንያ፤ ከሰሜን ሱዳን፣ ከደቡብ ሱዳን እንዲሁም ከዩጋንዳ ጋር የድንበር ውዝግብ አላት፡፡ በደቡብ፣ በሰሜን፣ በምሥራቅ፣ በምዕራብ ተመሳሳይ ችግር አለ፡፡ ይህን ችግር በመረዳት የአፍሪካ መንግስታት በአፍሪካ አንድነት ድርጅት (አአድ) በኩል የቅኝ አገዛዝ ድንበር እንዲጸና ውሳኔ አሳለፉ፡፡ ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት ባትገዛም ከጎበረቤቶቿ ጋር ያላት ድንበር በቅኝ ግዛት ኃይሎች የተወሰነ ነው፡፡ ይህም ውስብስብ የድንበር አካባቢ ‹ዳይናሚክስ›› እንዲፈጠር አድርጓል፡፡
Back to Front Page
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1107
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Re: ትግሬ እጠላለሁ !ዘረኛ ግን አይደለሁም::

Postby ዘርዐይ ደረስ » Tue Jul 31, 2018 8:30 am

በጣና በለስ ትላንት በተፈጠረው ግጭት የሶስት ትግሬዎች ህይወት አልፏል።
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1092
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

PreviousNext

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 5 guests