ዳግማዊ አፄ ምኒሊክ(፲፰፻፴፮‐፲፱፻፮)(፲፰፻፹፩—፲፱፻፮)

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

Re: ዳግማዊ አፄ ምኒሊክ(፲፰፻፴፮‐፲፱፻፮)(፲፰፻፹፩—፲፱፻፮)

Postby ዘርዐይ ደረስ » Fri Mar 02, 2018 10:36 pm

ዛሬ የዓድዋ ድል መታሰቢያ 122ኛ ዓመት ተከብሮ ውሏል።መቼም ይህ አኩሪ ታሪክ ሲነሳ የአፄ ምኒልክ ሥም ጎልቶ መውጣቱ አይቀርም።የአፄ ምኒልክ አስተዋይነትና ብልሃት የተሞላበት አመራር ባይኖር ኖሮ በጀግንነት ብቻ ድሉ ይገኝ ነበር ለማለት አያስደፍርም።ሆኖም ግን ባለፉት 27 ዓመታት የተለያዩ አጀንዳዎች በሚያራምዱ ክፍሎች በአፄው ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መጠነ ሰፊ የጥላቻ ዘመቻ ሲካሄድ ቆይቷል።እዚህ ዋርካ ላይ ራሱ ሦስት ዓይነት አመለካከቶች አጋጥመውኛል።
፩ኛ)አፄ ምኒልክን በግልፅ የሚቃወሙና በጠላትነት የፈረጁ
፪ኛ)አፄ ምኒልክን በሚመለከት የሚነሱ ርእሶች ላይ ምንም ዓይነት አስተያየት ባለመስጠት አቋማቸው ግልፅ እንዲሆን የማይፈልጉ
፫ኛ)ድጋፋቸውን በግልፅ የሚያሳዩ
የዘንድሮው በዓል በአገር አቀፍ ደረጃ የተከበረው እንደተለመደው በአዲስ አበባ ሳይሆን በዓድዋ ከተማ ነበር።የዓድዋን ድል በሚመለከት በየጊዜው በሚደረጉ ንግግሮችና ዘገባዎች ላይ ተደጋጋሚ ስህተቶች ይሠራሉ።የዘንድሮውም ከዚህ የተለየ አልነበረም፤ ለምሳሌም የጥንታዊት ኢትዮጵያ አርበኞች ማኅበር ፕሬዝደንት ልጅ ዳንዔል ጆቴ መስፍን በዓሉ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ሁለቱን ጦርነቶች (ዓድዋና ከ1928—33 የተደረገውን ዳግማዊ ወረራ) ሲያምታቱ ተስተውለዋል።ፕሬዝደንቱ ስለ ዓድዋ ጦርነት ሲናገሩ ፋሽስት ጣልያን ባደረገብን ወረራ ብለዋል እንደሚታወቀው በዓድዋ ጦርነት ጊዜ ጣልያን በንጉሥ የምትተዳደር እንጂ ፋሽዝም አልነበረም።ፋሽዝም የመጣው ከአድዋ ጦርነት 25 ዓመት በኋላ ነበር።በርግጥ ያኔም ቢሆን ንጉሣዊ አገዛዝ ቢኖርም ለይምሰል ነው እንጂ አገሪቱን በአምባገነንነት ይገዛ የነበረው በሙሶሊኒ የሚመራው ፋሽስት ፓርቲ ነበር።በሌላ በኩል ደግሞ ጣልያን በአየርና በመሬት ወረረችን ብለዋል በዓድዋው ጦርነት ጊዜ የጦር አውሮፕላን ጥቅም ላይ ሊውል ቀርቶ የተሠራው ራሱ ከ10 ዓመት በኋላ ነበር።
በነገራችን ላይ አራዳ ጊዮርጊስ የሚገኘው የአፄ ምኒልክ ሐውልት ከጊዜ ብዛትና በሁለተኛው የጣልያን ወረራ በደረሰበት ጉዳት ከዚህ በፊት ታድሶ የነበረ ቢሆንም አስተማማኝ ሁኔታ ላይ አይገኝም።በዚህም ምክንያት ከሳምንታት በፊት ተከልሎ በእድሳት ላይ ይገኛል።አንዳንድ ባለሙያዎች እንደሚሉት ከሆነ ሥራውን ተረክበው እየሰሩ ያሉት ግለሰቦች ብቃት ስለሌላቸው ሐውልቱ ላይ ተጨማሪ ጉዳት እንዳይደርስ ያሰጋል።
ሌላው ከ115 በላይ ያልተደረገና ዘንድሮ ለአምስተኛ ጊዜ የተካሄደው ጉዞ ዓድዋ ነው።በጥቂት ወጣቶች አነሳሽነት በ፳፼፮ ዓ∙ም∙ የተጀመረው ይህ ጉዞ መነሻውን ጣይቱ ሆቴል አድርጎ በእግር ዓድዋ ድረስ (ከ1000 ኪ∙ሜ በላይ) መጓዝ ነው።ተጓዦቹ በቀን ከ25 እስከ 40ኪ∙ሜ እንደሚጓዙ ይነገራል።
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1096
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: ዳግማዊ አፄ ምኒሊክ(፲፰፻፴፮‐፲፱፻፮)(፲፰፻፹፩—፲፱፻፮)

Postby ዘርዐይ ደረስ » Tue Apr 03, 2018 10:14 pm

ህወሓት/ኢህአዴግ ሲጨንቀውና ምድር ሰማዩ ሲዞርበት ከካርታዎቹ መካከል እየቀፈፈውም ቢሆን ኢትዮጵያዊነትን ከመዘዘ ከራርሟል፡፡ይህ ግን የተቃዋሚዎች እንጂ የሥርዐቱ ድል እይደለም፡፡ሌ/ኮ አቢይ ሥርዐቱን ለማዳን በህወሃት አለቆቻቸው የተቀነባበረውን ድራማ የእገሪቱን ተዋንያን በሚያስንቅ ሁኔታ ለመድረክ አበቁት፡፡
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1096
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: ዳግማዊ አፄ ምኒሊክ(፲፰፻፴፮‐፲፱፻፮)(፲፰፻፹፩—፲፱፻፮)

Postby ዘርዐይ ደረስ » Sun Aug 19, 2018 8:19 pm

የአፄ ምኒልክ ፩፻፸፬ኛ የልደት በዓል ከዚህ በፊት ከነበሩት በተሻለ ሁኔታ የሚዲያ ሽፋን ተሰጥቶት አልፏል።
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1096
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: ዳግማዊ አፄ ምኒሊክ(፲፰፻፴፮‐፲፱፻፮)(፲፰፻፹፩—፲፱፻፮)

Postby ዘርዐይ ደረስ » Tue Feb 12, 2019 4:43 pm

የልደት በዓላቸው በተከበረ ማግስት ጸረ ምኒልክ ቅስቀሳ አሁንም አገርሽቷል።
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1096
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Previous

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Majestic-12 [Bot] and 5 guests