የሞ ፋራህ ደብል ጎልድ ማሸነፍ በጣም የሚደነቅ እንደሆነ ግልጽ ነው . በፊት በኢትዮጵያውያን ዶሚኔትድ የሆነን ስፖርት ባብዛኛው ከመሬት አቀማመጥም ጭምር ሊሆን ይችላል በኢትዮጵያና ኬኒያ የአፍሪካ ተራሮች አከባቢ ከመጡ የሀገራችን አትሌቶች እና ኬንያውያን በስተቀር ማንም ማሸነፍ አይችልም በሚባልበት የ 5000 እና የ 10,000 km ርቀት በሚገርም ሁኔታ ማሸነፉ ምን ያህል ሊከብድ እንደሚችል ሲጠየቅ የመለሰው መልስ ምን ነበር መሰላቹ ይህን የ 5 እና የ 10ሺው ርቀት ማሸነፍ የጥንት ህልሜ ነበር ነገር ግን ይህ ርቀት በኢትዮጵያውያን እና በኬንያውያን ብቻ እንዴት ሊወሰድ ይችላል ብዬ ሳስብ ምን አልባት እዛው ሀገራቸው ድረስ ሄጄ በነሱ አየር ትሬኒንግ እየሰራው ለተወሰነ ግዜ መኖር እንዳለብኝ ስለተሰማኝ ኬንያ ድረስ በመጉዋዝ እዛ ተራራማ አከባቢ ትሬኒንግ እያረኩ ከከራረምኩ ቡሀላ በይበልጥ ርቀቱን ላሻሽል ችያለው ብሏል . ይህ እንግዲ ለፍቶ ማግኘትን እና ምን ያህል ሰው የፈለገውን ነገር ለማግኘት መጉዋዝ ያለበትን ርቀት ሁላ ስጉዋዝ እንዲሁም ኮሚትድ ሲሆን የሚገኝ ውጤት እንደሆነ ለብዙ ሰዎች ያስመሰከረበት ስራ ነው . እኛ ካላሸነፍን ተከትሎ የገባው አሜሪካዊው ነጫጭባ ከሚወስደው አፍሪካዊው ተወላጅ ሞ የጥረቱን ፍሬ በማግኘቱ ደስተኛ ነኝ ለኛዎቹም አትሌቶች ጥሩ ምሳሌ መሆን የሚችል አትሌት ነው .
What makes Farah's achievement all the more laudable is not just his ability to get over the physical lows and emotional highs of that first victory, won in his home city at its home Olympics, but the backstory that brought him to this point.
እንክዋን ደስ አለህ ሞ !!