ክቡራን wrote:ቁምቢ ፍቅር ተነተነውና እንዲህ ል ጠየቀኝ...: ለመሆኑ አፍቅረህ ነው ተፈቅረህ ትርጉም ፍለጋ የምትባዝነው
_________________
አሪፍ ጥያቄ ናት.. :D ሁለቱንም ሆኘ ነው..:: :D ትንትናህ ግሩም ነው ተመችቶኛል..!
ፍቅር ማጣት እኮ ግን በራሱ ገኅነም ነው...የእጊዚአብሄርን ፕርዘንስ ስታጣ እዛ ጋ ሲኦል ይጀምራል:: ሌላ እሳት ለምን ይጨመራል...? እስኪ አስፋፋውና ሂድበት ይሄን ሀሳብ...
ሪቾ ..ሬቾ....የኔ ከረፈፍ ...የሚኒልክ ዘፈን ለኔ ነው የተመረጠው እያልሽ አስረኛ ፎቅ ላይ ተቀምጠሽ ሸልዪ...እሺ...የኔ ባለ ቴክስ ኮፍያ.. :D እኛ ፈርስት ፍሎር ላይ ስራችንን እየሰራን ነው...ይሄን ዝግጅት ደሞ አዳምጭውና ለኔ የተመረጠ ሙዚቃ ነው በይ እሺ... ጠቅ አድርጊው ማታ ማታ ቢፎር ዩ ጎ ቱ ቤድ.. :D
እቺን ጠቅ..
ወይ ፍቅር አለ መሀሙድ......ፍቅር ማጣት ትንሽ ይከብድ ይሆናል ይሁን እንጂ የፍቅረኛ ፍቅር ስላጣህ አትሞትም ወገን ዘመድ ምንም የሌለው የመንገድ አዳሪ ምናልባት አብሮት የሚዞር አንድ ውሻ አያጣም እሱም እኮ ፍቅር ነው....ሞጭሟጫ አይኖቹን እያቅለሰለሰ ጭራውን ከግራ ወደ ቀኝ እያማታ ሲተሻሸው ሰውየው በፍቅር አይን እያየ ያሻሸዋል............በአለም ላይ ፍቅር የሌለበት ቦታ የለም......
ግን ፍቅርን ሲሰጡት መቀበል የማይችል እንከፍ ደግሞ ሞልቷል..........አንድ ታሪክ ላጫውትህ..........ድሮ ከአንድ የሰፈሬ ልጅ ጋር በጓደኝነት ጀምረን ከዛ ቅልጥ ያለ ፍቅር ውስጥ ገባን....ታዲይ ሲበዛ ወረተኛ ነኝ......ለግዜው በቃ አስረሽ ምችው አልኩና ልጅቷ በንፁ ልቧ ስትወደኝ መኩራት አመጣው.......አንዳንድ ፍሬንዶች ደግሞ አንተና እሷኮ አትሄዱም.....ከዚች የተሻለች ስንት ቺክ መያዝ ስትችል ይቺን ይዘን ለምን ትጃጃላለህ.....ምናምን እያሉ....ልቤን አሳበጡት....ሞከረች ሞከረች ሲያቅታት አልቅሳ ተለያየን............ከምንም አልቆጠርኳትም ያኔ.......የመጨረሻ ቀን አገሬን ለቅቄ ልወጣ የሆነ ቦታ ላይ አይቻት እንዳላየ አለፍኳት.......ነገሩን ስለሰማች በአይኗ ሸኝችኝ......ስደት ክፉ ብዙ ነገር አሳየኝ....ማግኝት ማጣት...መውደድ መጥላት.......እኔም ታዲያ በተራዬ አሜሪካ ከመጣው በxላ አንዲት ቆንጆ ወድጄ ፍዳዬን ፈተፈትኩኝ...........ልጅቷ እንደኔ አይነት መጤና ያልተቋቋመ ሰው እንደማትፈልግና ለወደፊት ኑሮዋ የሚበጃትን እንደምትፈልግ ጠቆመችኝ..........ብለምን ባስለምን ጆሮ ዳባ ልበስ ብላ አንዱን ባለ ብር አገባች........ለካ ልብ ሲሰበር እንደዚ ነው.......ለካ ወዶ ማጣት ይሄን ይመስላል.............ያቺን አገር ቤት ያስቀየምኳት ልጅ ባይኔ ላይ አሁንም አሁንም ድቅን ትላለች..........ስራ ጀምሬ ኑሮ ተስተካክሎ ሁለት አመታት አለፉ..........አሁንም ግን ልቤ እሷን ከማሰብ አልባዘነም.........አንድ ቀን ታዲያ የመጣው ይምጣ ብዬ የሞባይሏን ስልክ ፈልጌ ደወልኩላት......ሀሎ! ሄሎ! ማን ልበል!.........ትንፋሽ አጥሮኝ ትንሽ ዝም አልኩና ማንነቴን ነገርኳት..........ዝም ብላ ትንሽ ቆይታ.........እንዴት ደወልክ አለችኝ......በቃ ያሁሉ ኩራት የለ ያ ሁሉ ጥጋብ የለ......የልቤን ነገርኳት አለምን ዞርኩኝ አንቺን የመሰለች የደጎችና የየዋሆች ንግስት ግን ላገኝ አልቻልኩም አልኳት.........አሁንም በዝምታ ተዋጠችና ይቅርታዬን እንደምትቀበል ነግራኝ አሁን ግን የምትወደው ጓደኛ እንዳላትና.......በመጨው ጥር ሊጋቡ ማሰባቸውን አረዳችኝ..........እኔም በተራዬ አልቅሸ......ተሰናበትኳት.......
አሁን ታዲያ ፍቅር ክቡርና ሰማያዊ መሆኑን ተረዳው......የፍቅርም ጡር እንዳለው በከባዱ ተማርኩኝ.....አሁን አግብታ የአንድ ልጅ እናት ሆናለች አውርተን አናውቅም ግን በማላውቀው ባሏ ስቀና እኖራለው...........ፍቅር ይሄን ይመስላል ዛሬ የማገኛቸውን ቀበጦች ሁሉ እንደሷ ቢሆንሉኝ እየተመኝው በምኞት ብቻ ቀረው......