በፊደላችን ላይ የተቃጣ ዘመቻ...

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

በፊደላችን ላይ የተቃጣ ዘመቻ...

Postby ዳግማዊ ቅዥቢው » Tue Dec 04, 2012 12:09 pm

ወርቅ ነው ፤ወርቅ ነው የግዕዝ ፊደል፣
ሰባት እጅ የጠራ በሰባት ባሕል
አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ 1926

አራሚ
ነቃይና አራሚ ድሮም ዛሬም አሉ
ከሐበሻ ምድር መቼ ይጠፋሉ።
አሉ! አሉ! አሉ!
ጥንትም ዛሬም አሉ
ባ’ረም አመኻኝተው ሰብል የሚነቅሉ።
ይስምዕከ ወርቁ

በወንዛዊ፣ጎጣዊና ዘውጋዊ ልክፍት የተለከፉ የአምሐራና አምሐርኛ ታሪካዊ ጠላቶች በእጹብ ድንቁ ፊደላችን ላይ ከ85 ዓመት በፊት የአወጁትን ጦርነት ሰሞኑን የአምሐርኛ ሞክሼ ፊደላት ይወገዱልን በሚል መፈክር ስር በአዲስ መልክ ጀምረዋል::የሰሞኑ ዘመቻ የጦር አበጋዝ በድሉ ዋቅጅራ የተባለ ኦሮሞ ነው::ይህ ገመድ አፍ አጥንተ ሰባራ 180 ፊደላት ለአንድ ቋንቋ ይበዛሉ ይለናል::"አልሰሜን ግባ በለው" አለ አበበ በለው::የአምሐርኛ ፊደላት 563 መድረሳቸውን አልሰማም የአያ ሰጠኝ መርቆ ልጅ::"ወይ ነዶ!" አለ ሮናልዶ::
እኔ 'ኮ ማይገባኝ ምደረ ጉዴላና ጋላን ምን በደልናቸው?ቓ ሹሉቃ፣ ፊጣ ፣ጝኛሞ፣ ጫልቱ፣ ቔራሮ፣ ቜቡሼ፣ ቛዱጬ ምንትሴ ቅብጥርሴ ለተሰኙ ዘግናኝ ስሞቻቸው ፊደል ቀርጸን አዘጋጀን::ይህ ወንጀል ነው እንዴ?ምስጋናው ቢቀር ስድቡን ምን አመጣው::ኤዲያ ዱሮም ባሪያ አንገት የለውም...
እነ ቓ ሹሉቃ፣ ፊጣ፣ ጝኛሞ፣ ጫልቱ ፣ቔራሮ፣ ቜቡሼ ፣ቛዱጬ ምንትሴ ቅብጥርሴ ሆይ አምሐርኛ የቴክኖሎዢ ቋንቋነቱ ያስመሰከረ ብቸኛ አፍሪካዊ ቋንቋ ከሆነ ሰነበተ::አምሐርኛን ያለመጠቀም መብታችሁ የተጠበቀ ነው::ስትጠቀሙ ግን ደምብና ስርዓቱንም ልብ እያላችሁ..."በፊደሎቻችን ላይ ሦስት ሀ - ሐ - ኀ፣ ሁለት አ - ዐ -፣ ሁለት ሠ - ሰ ሁለት፣ ጸ - ፀ አሉ፡፡ እነዚህ ፊደሎች የራሳቸው የሆነ የስም አጠራርም አላቸው፤ ሀሌታው ሀ፣ ሐመሩ ሐ፣ ብዙኃን ኀ፣ ንጉሡ ሠ፣ እሳቱ ሰ፣ ጸሎት ጸ፣ ፀሐዩ ፀ ይባላሉ፡፡ በጽሑፍ የሚገቡበትን ተገቢ (ተስማሚ) ቦታም አላቸው፡፡ ለምሳሌ በሁለት ፊደሎች መጠቀም ይቻላል፡፡ ሀገር አገር ይህ ትክክለኛ አጻጻፍ ሲሆን፤ ነገር ግን ከዚህ ውጪ ሐገር፣ ኀገር ብሎ መጻፍ ግን ስሕተት ይሆናል፤ የሚከተሉትን ደግሞ እንመልከት፤
ሕገ መንግሥት፣ ሕገ ወጥ፣ ሕዝብ፣ ሕብረት፣ ዓቃቤ ሕግ፣ ወዘተ. የመሳሰሉት አጻጻፋቸው ትክክል ነው፡፡ ከዚህ ልማዳዊ አሠራር ውጪ ህገ መንግሥት፤ ህገወጥ፤ ህዝብ፤ ህብረት፤ አቃቤ ህግ ስሕተታዊ አጻጻፍ ይሆናል፤ ሌላ ማስረጃ ቢፈለግ፤ ኃይለሥላሴ የሚለው ስም ሦስት የተለያዩ ፊደሎች ይዟል፡፡ የመጀመርያው ፊደል ብዙኀን - ኃ - ሲሆን፣ ከንጉሡ -ሥ- ሳድስ፣ ከእሳቱ -ስ- ሃምስን በመጻፍ እንዲካተት ተደርጓል፡፡ ሀይለ ስላሴ ብሎ ቢጻፍ ግን የፊደሎቻችን የአጻጻፍ ሥርዓት ማፋለስ ይሆናል፤ በአቦ ሰጡኝ ፊደሎቻችን አለቦታቸው መግባትም፣ መጻፍም የለባቸውም፡፡ "
መሪ ጌታ ቅዥቢው ዘ-ብሔረ አምሐራ
ዳግማዊ ቅዥቢው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 117
Joined: Mon Nov 26, 2012 1:08 am

ፊደል...

Postby ዳግማዊ ቅዥቢው » Tue Dec 04, 2012 3:59 pm

‹‹ስለፊደል ቅነሳ የተደረጉ ጥናቶች ኢትዮጵያውያንን ከነባሩ ታሪካቸውና ሥነ ጽሑፋቸው ነጥሎ የማስቀረት ዓላማ ያነገቡ ናቸው›› አቶ ፋንታሁን እንግዳ
ኅዳር 2003
በኢትዮጵያ ፊደል ገበታ በተለይም ስለፊደል ቅነሣ የተደረጉ ጥናቶች ኢትዮጵያውያንን ከነባሩ ታሪካቸውና ሥነ ጽሑፋቸው ነጥሎ የማስቀረት ዓላማ ያነገቡ መሆናቸውን አንድ ሙዳዬ ቃላት ጠቆመ፡፡
በቅርቡ የሕትመት ብርሃን ያየው የአቶ ፋንታሁን እንግዳ ‹‹ሥነ ጽሑፋዊ ሙዳዬ - ቃላት ከነማብራሪያቸው›› በተሰኘ መጽሐፍ ደራሲው እንደጠቆሙት፣ ‹‹እስካሁን የተደረጉ ጥናቶች በአጠቃላይ የሚያሳዩት ከፊደል ቅነሳና ከቃላት መጥበቅ -መላላት ጋር በተያያዘ በቋንቋ ፖለቲከኞች የሚቀነቀኑ ጉዳዮች ሁሉ ኢትዮጵያውያኑን ከነባሩ ታሪካቸውና ሥነ ጽሑፋቸው ነጥሎ የማስቀረት ዓላማ ያነገቡ መሆናቸው ነው፡፡
ከሥነ ቃል፣ ልብወለድ፣ ግጥም፣ ወግ፣ ተውኔት፣ ሒሳዊ ምልከታ እና ከአተራረክ ስልት ጋር የተያያዙ ዘውጎች፣ አላባዎችና ጽንሰ ሐሳቦች የተካተቱበት ሙዳዬ ቃላት፣ በአማርኛው የፊደል ገበያ ከሀ እስከ ፐ ቅደም ተከተል በምዝግብነት (ኢንትሪስ) የቀረቡበት ነው፡፡
‹‹የኢትዮጵያ ፊደል›› በሚለው ምዝግብ ውስጥ አቶ ፋንታሁን እንዳመለከቱት፣
የኢትዮጵያ ፊደል ከሌሎች አገሮች ፊደላት ለምሳሌ ከእንግሊዘኛና ከላቲን ፊደላት ከሚለይባቸው ነገሮች አንደኛው የተለዩ ድምፆችን የሚያወጡ ፊደላትን ማካተቱ ነው፡፡ ቀ፣ ኘ፣ ጠ፣ ጨ፣ ጰ እና ፀ ፊደላት ለዚህ አባባል ዓይነተኛ ማስረጃዎች ናቸው፡፡
የተለየ ድምፅ ያላቸውን ማካተቱ ብቻ ሳይሆን፣ የኢትዮጵያ ፊደል አናባቢንና ተነባቢን በአንድነት ተሸክሞ መገኘቱና አንዳችም ችግር ሳይፈጠር የምንናገረውን ለመጻፍ፤ የምንጽፈውን ደግሞ ለመናገር ስለሚያስችለን ከተጠቀሱት የሌሎች አገሮች ፊደሎች የበለጠ ጥንካሬ እንዳለውም እስካሁን የተደረጉ ጥናቶች ያስገነዝባሉ፡፡
የኢትዮጵያ ፊደል የሥልጣኔአችን መገለጫ በመሆን አገልግሎት እየሰጠ በሺሕ የሚቆጠሩ ዓመታትን የዘለቀ ቢሆንም ‹‹ቁጥሩ በዝቷልና መቀነስ አለበት›› እና ‹‹የሚጠብቁና የሚላሉ ቃላት ችግር ፈጥረውብናልና መላ ይፈለግላቸው›› የሚሉ ጥያቄዎችን እያነሡ በሌለ ችግር ላይ ትውልዱን ጠብ ውስጥ አስገብተው ለማቆራቆስ የሚፈልጉ የቋንቋ ፖለቲከኞች በአንዳንድ ታዋቂ ደራሲያን ጀርባ ተከልለው በ1950ዎቹ አንሥቶ ግፊት ሲያደርጉ መቆየታቸውን አቶ ፋንታሁን አስታውሰዋል፡፡
የቋንቋ ፖለቲከኞች ድብቅ አጀንዳ አቀንቃኝ ከነበሩት ደራስያን ብለው የጠቀሷቸው ደግሞ አቶ ሐዲስ ዓለማየሁን ነው፡፡ ፍቅር እስከ መቃብር የተባለውን ልብወለድ በሚያሳትሙበት ጊዜ የኢትዮጵያ ፊደል ቁጥሩ ስለበዛ ‹‹ሐ፣ ሠ፣ ኀ፣ ዐ፣ ፀ›› የተባሉትን አምስት የግእዝ ፊደሎችን የማንንም ውሳኔ ሳይጠብቁ በግል ሥልጣናቸው ተነሣሥተው መጣላቸውን እንዲያውጁ አድርጓቸዋል፡፡
በወቅቱ በአቶ ሐዲስ ዓለማየሁ የተሰጠው የፊደል ቅነሳ ምክንያት ‹‹... የፊደሎቻችን ያለመጠን መብዛት ትምህርታችንንም ሆነ ሥራችንን ሳያስፈልግ አስቸጋሪ አድርጐብናል›› የሚል ነበር፡፡
ከአቶ ሐዲስ ዓለማየሁ በመቀጠል ደግሞ ይህን ፊደል የመቀነስ አመለካከት በመደገፍ በረዥሙ የሥነ ጽሑፍ ታሪካችን ትልቅ የባለቤትነት ድርሻ ያላቸውን ተቋማት እንኳን ሳያማክር የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቋንቋዎች ጥናትና ምርምር ማዕከል ድብቁን የፖለቲካ አስተሳሰብ የሚያሳካ ሥራ መሥራቱንም አቶ ፋንታሁን በሙዳዬ ቃላቱ አመልክተዋል፡፡ አቶ ሐዲስ ከሰረዟቸው በተጨማሪ ‹‹ኸ›› የተባለውን ፊደል እስከነእርባታው በመቀነስ አማርኛ መዝገበ ቃላት እና ክብረ ነገስት ግእዝና አማርኛ የተባሉትን መጻሕፍት በ1993 እና በ1994 ዓ.ም. አሳትሞ አውጥቷል፡፡
እንዲህ ያሉትን ድርጊቶች ተከትለው የተደረጉ የተቃውሞ ጥናቶች የሚያሳዩት ግን የፊደል ቅነሳው በመጠን ሊገለጹ የማይችሉ ውድመቶችን እንዲያስከትል ታስቦ የተፈጠረ ችግር ነው፡፡
ደራሲው፣ ይህን መሰሉ ፊደል የመቀነስ ተግባር በዋናነት ግእዝ የኢትዮጵያ መንግሥት የሥራ ቋንቋ ከነበረበት ጊዜ አንሥቶ ላለፉት 2000 ዓመታት የተጻፉትን የታሪክ እና የሥነ ጽሑፍ ክምችቶች ቆርጦ በመጣል ከአሁኑ ትውልድ ጋር ለያይቶ ለማስቀረት የታሰበ ፖለቲካ ነው የሚል እምነትም አላቸው፡፡
ይህንን የፊደል ቅነሳ በይፋ ከተቃወሙ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት አንዱ ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል መሆናቸው በአቶ ፋንታሁን ሙዳዬ ቃላት ውስጥ ተብራርቶ ተጽፏል፡፡
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቋንቋዎች ጥናትና ምርምር ማዕከል እየሠራ ያለውን ታሪካዊ ስህተት በጽኑ የነቀፉት ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል የፊደላትን መቀናነስ አስመልክተው በሰጡት ማብራሪያ ሁለት መሠረታዊ ነጥቦችን አንሥተዋል፡፡
አንደኛ የፊደላቱ ቁጥር ይቀነስ የሚሉት ወገኖች ሐሳባቸው ሞልቶ የተወሰኑ ፊደላት እንዲጠፉ ቢደረግ፣ በቀዳሚነት የትርጉም መፋለስ ያመጣል፡፡ ሊቀ ካህናት ጉዳዩን በምሳሌ አስረግጠው ሲያቀርቡትም በሀሌታው ‹‹ሀ››፣ በሐመሩ ‹‹ሐ›› እና በብዙኃኑ ‹‹ኀ›› የሚጀምርን አንድን ቃል በማቅረብ ቃሉ ተመሳሳይ አነባበብ ቢኖረውም ትርጉሙ ፍጹም የተለየ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ እነዚህ ፊደላት ቢቀነሱ ትልቅ ጉዳት እንደሚከሠት አሳይተዋል፡፡
ሁለተኛውና ዐቢዩ ጉዳት ደግሞ እንደተባለው ፊደላቱ ቢቀነሱ መጪው ትውልድ ባለፉት ሺሕ ዓመታት የተጻፉትን መንፈሳዊም ሆነ ዓለማዊ ይዘት ያላቸውን መዛግብት አንበቦ ሊረዳቸው አይቻለውም፡፡ ይህም በመሆኑ በቀደሙት አባቶችና በዛሬው ትውልድ መካከል የነበረው ድልድይ ሙሉ በሙሉ ሊፈርስ እንደሚችል አብራርተዋል፡፡
ሊቀ ካህናት እንዳሉት፣ እስካሁን የተጻፉትን መጻሕፍት አዲሱ ትውልድ እንዲያውቃቸው ቢፈለግ እንኳን የትርጉም ሥራ ሊጠይቁ ነው፡፡ የትርጉም ሥራ ይሠራ ከተባለ ደግሞ ከሚታሰበውም በላይ የገንዘብ፣ የጉልበትና የጊዜ ኪሣራን የሚጠይቅ በመሆኑ ከማይወጡት ችግር ውስጥ የሚከት ነው፡፡
ለምሳሌ በጦርነትና በልዩ ልዩ አደጋዎች የወደሙትንና የተዘረፉትን ሳይጨምር፣ በዓይነታቸው ብቻ (ቅጅዎችን ሳይጨምር) ከ12,000 በላይ የሆኑ በግእዝ ቋንቋ ተጽፈው የሚገኙ መጻሕፍት አሉ ከሚል ያልተጣራ ግምት እንነሣ፡፡ በአማርኛ እና በሌሎች ቋንቋዎች የተጻፉት ደግሞ በግእዝ ከተጻፉት በእጅጉ እንደሚበልጡ ጨምረን እንገምት፡፡ በዚያ ላይ ጋዜጦች፣ መጽሔቶችና ልዩ ልዩ ሰነዶችም አሉ፡፡
አምስትና ስድስት ፊደሎችን ከነዕርባታቸው እንሰርዝ ከተባለ እንግዲህ በነዚህ መጻሕፍት፣ ጋዜጦች፣ መጽሔቶችና ሌሎች ሰነዶች የሚገኙትን ተቀናሽ ፊደላት በሙሉ አስተካክሎና እንደገና አሳትሞ ማውጣት የግድ ይለናል ማለት ነው፡፡ ያንን ተግባር ለመፈጸም ደግሞ ከላይ እንደተገለጸው የሚጠይቀው ገንዘብ፣ ጉልበትና ጊዜ ሲታሰብ ፖለቲከኞች አለ የሚሉትን የፊደል መብዛት ችግር ለመፍታት የሚቀመጠው መፍትሔ በሚሊዮን አባዝቶ የሚከተል ውስብስብ ችግር እንዲፈጠር የሚያደርግ ነው፡፡
ይህንን ሁሉ ችግር በሚገባ የተመለከቱት ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል ‹‹ለመሆኑ የትኞቹ የፈረንጅ ፊደላት ሲቀነሱ አይተው ነው የእኛን የተስተካከሉና በወግ የተሰናዱ ፊደላት የሚቀንሱት?›› ሲሉ ከጠየቁ በኋላ ዩኒቨርሲቲው ቋንቋን የመቆነፃፀልና በአማርኛም ሆነ በግእዝ ከፍተኛ አገልግሎት ያበረከቱትን ፊደላት የማውደም ሥልጣኑ እንዳልሆነ አጽንኦት ሰጥተው አስረድተዋል፡፡
ሌሎች አስተያየት ሰጭዎች ባቀረቡት የመከራከርያ ነጥብ፣ እንዲሁም ሥልጣኔውን በመምራት ላይ ካሉ የአውሮፓ አገሮች አንዷ የሆነችው እንግሊዝ ትልቁ ፊደል፣ ትንሹ ፊደልና ቅጥልጥሉ ፊደል የሚባሉ ሦስት ዓይነት ፊደሎች እንዳሏት ያወሱና ‹‹በእርግጥ የፊደል ቁጥር መብዛት ሥልጣኔን ይጐትታል ከተባለ ለምን እስካሁን እነሱ ሁለቱን የፊደል ዓይነቶች ሳይቀንሱ ቀሩ? ሥልጣኔአቸውስ እንዴት አልተጐተተም?›› ሲሉ በመጠየቅ የእኛን ነባር ፊደላት ለመቀነስ የተነሡ ወገኖች በጎ ነገር አስበው ያልፈጸሙት መሆኑን ያስረዳሉ፡፡
የኢትዮጵያ ፊደል የሚገነባቸውን በማጥበቅና በማላላት የምንረዳቸውን ቃላት በተመለከተ የቀረበውም ችግር እንዲሁ ሰው ሠራሽና መሠረት የሌለው ነው፡፡
እንደፊደል ቅነሳው ሁሉ የመጥበቅ የመላላቱን ሐሳብ እያነሡ የቋንቋ ፖለቲከኞች ለመሟገት የሚፈልጉት ‹‹ታዋቂው የልብ ወለድ ደራሲ ሐዲስ ዓለማየሁ ሐቁን ተናግረዋል›› የሚል ማሳመኛ የሚሉትን ነጥብ እያቀረቡ መሆኑ ታውቋል፡፡
ቃላትን የማጥበቅ የማላላቱን ጉዳይ በተመለከተ ሐዲስ ዓለማየሁ፣ በፍቅር እስከመቃብር መጽሐፍ መቅድም ላይ ያሰፈሩት፣ ‹‹በላቲን አጻጻፍ ለማጥበቅ የሚፈለገው ቀለም ሁለት ሆኖ ይጻፋል፡፡ በእኛ አጻጻፍ ግን ሁለት ሆኖ የተጻፈ አንድ ቀለም ሁለት ጊዜ ለየብቻ ይነበባል እንጂ አይጠብቅም›› በማለት በኢትዮጵያና በላቲን ፊደላት የሚገነቡትን ቃላት የማይገባ ንጽጽር በማድረግ ለማሳየት ሞክረዋል፡፡
በመጀመርያ ሁለቱ ፊደላት የየራሳቸው የአጻጻፍ ሥርዓት እንዳላቸው አልተገነዘቡም፡፡ ሁለተኛ ደግሞ በማጥበቅና በማላላት የሚነገሩ ወይም የሚነበቡ ቃላት በግእዝ፣ በአማርኛና በሌሎችም ቋንቋዎች የአጻጻፍ ሥርዓታችን አካል እንደሆኑ አልተረዱም፡፡
በዝርውም ይጻፍ በግጥም፣ ወይም በቅኔ እየጠበቁ እና እየላሉ የሚነበቡ ቃላት ወይም የሚረቡት ግሦች መጥበቅ መላላታቸውም ሆነ ትርጉማቸው የሚታወቀው በአገባባቸው ነው፡፡ አገባብ ሲባል ደግሞ ደቂቅ አገባብ፣ ዐቢይ አገባብና ንኡስ አገባብ እየተባሉ የሚጠሩትን ያካትታል፡፡ ስለዚህም ነው በማጥበቅ በማላላት የሚነገሩ ቃላት የእኛ የቋንቋ ሥርዓታችን አካላት ናቸው የሚባለው፡፡ ይህም ማለት የተለየ የአረባብና የአጠቃቀም ሥርዓት ካለው ከላቲን ፊደል ጋር ተነጻጽረው የሚወገዙበት ነገር የላቸውም ማለት ነው፡፡
አቶ ፋንታሁን እንግዳ አጽንዖት እንደሰጡበት፣ እስካሁን የተደረጉ ጥናቶች በአጠቃላይ የሚያሳዩት ከፊደል ቅነሳና ከቃላት መጥበቅ-መላላት ጋር በተያያዘ በቋንቋ ፖለቲከኞች የሚቀነቀኑ ጉዳዮች ሁሉ ኢትዮጵያውያንን ከነባሩ ታሪካቸውና ሥነ ጽሑፋቸው ነጥሎ የማስቀረት ዓላማ ያነገቡ መሆናቸውን ነው፡፡
ዳግማዊ ቅዥቢው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 117
Joined: Mon Nov 26, 2012 1:08 am

Re: በፊደላችን ላይ የተቃጣ ዘመቻ...

Postby ዲጎኔ » Tue Dec 04, 2012 4:11 pm

ሰላም ለሁላችን ይሁን ድጋሚ ቅዥብ ለሚልባቸው ሁሉ
ወገን ዳግማዊ ቅዥቤው ምንም እንኩዋን የብሄር ንቀት ቫይረሱ ቢኖርብህ አልፏልፎ በሎጅክህ ትመቸኛለህ::እስኪ ኦሮሞ ያልተጠመቀ ወይም ያልተባረከ የሚበላ የሚል ኢሰባዊ ፊውዳላዊ ትርጉም ያለውን ትተህ በቅን መንገድ ኦሮሞ እያልክ ተወያይ::ከዚህ በተረፈ እኔ በሳባው/ግእዙ ፊደል መጠቀማችን ይቀጥል ከሚሉ በአምቦና በሰላሌ አካባቢ ካሉ ወገኖቼ ጋር ስሆን በላቲን መጠቀም የሚወዱ ወገኖቼን መብትም አከብራለሁ::እባክህ እንደሰለጠነ 21ኛ ክፍለዘመን ሰው ሀሳብህን በትህትና በጨዋነት አቅርብና እንወያይ::በነገራችን ላይ አንድ ጎንደሬ አርታኢ በእነዚህ ሆሄያት አጠቃቀም ገና በጅማሬ ስነጽሁፌ ዘመን አሳር ያሳዩኝን አልረሳም::ጉራጌው የደራሲያን ማህበር መስራች አማረ ማሞም እንዲሁ ለሆሄያቱ ያላቸው ተሞጋችነትና ችሎታ አደንቃለሁ::ነገር ግን አማርኛን በሚገባ በመጠቀም አማራ ያልሆኑ የመጀመሪያው የአማርኛ መጽሀፍ ቅዱስ ከተረጎሙ እንግሊዛዊው ቄስ ማንስል ኮሊንና ባለቤታቸው ያህል አማርኛ/Ethiopicያስከበረ የለም ዶ/ላጲሶን ጭምር::
ከውጭ ትወላጆችም ከጥቂት የአፍሪካ ብሸኛ ፊደላት አንዱ አምርኛ መሆኑን የሚያደንቁ የጁባው የት/ቤት ጉዋደኛዬ ጭምር በአፍሪካዊ ቅርስነቱ አምሀርኛን አከብራለሁ::

ዳግማዊ ቅዥቢው wrote:ወርቅ ነው ፤ወርቅ ነው የግዕዝ ፊደል፣
ሰባት እጅ የጠራ በሰባት ባሕል
አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ 1926

አራሚ
ነቃይና አራሚ ድሮም ዛሬም አሉ
ከሐበሻ ምድር መቼ ይጠፋሉ።
አሉ! አሉ! አሉ!
ጥንትም ዛሬም አሉ
ባ’ረም አመኻኝተው ሰብል የሚነቅሉ።
ይስምዕከ ወርቁ

በወንዛዊ፣ጎጣዊና ዘውጋዊ ልክፍት የተለከፉ የአምሐራና አምሐርኛ ታሪካዊ ጠላቶች በእጹብ ድንቁ ፊደላችን ላይ ከ85 ዓመት በፊት የአወጁትን ጦርነት ሰሞኑን የአምሐርኛ ሞክሼ ፊደላት ይወገዱልን በሚል መፈክር ስር በአዲስ መልክ ጀምረዋል::የሰሞኑ ዘመቻ የጦር አበጋዝ በድሉ ዋቅጅራ የተባለ ኦሮሞ ነው::ይህ ገመድ አፍ አጥንተ ሰባራ 180 ፊደላት ለአንድ ቋንቋ ይበዛሉ ይለናል::"አልሰሜን ግባ በለው" አለ አበበ በለው::የአምሐርኛ ፊደላት 563 መድረሳቸውን አልሰማም የአያ ሰጠኝ መርቆ ልጅ::"ወይ ነዶ!" አለ ሮናልዶ::
እኔ 'ኮ ማይገባኝ ምደረ ጉዴላና ጋላን ምን በደልናቸው?ቓ ሹሉቃ፣ ፊጣ ፣ጝኛሞ፣ ጫልቱ፣ ቔራሮ፣ ቜቡሼ፣ ቛዱጬ ምንትሴ ቅብጥርሴ ለተሰኙ ዘግናኝ ስሞቻቸው ፊደል ቀርጸን አዘጋጀን::ይህ ወንጀል ነው እንዴ?ምስጋናው ቢቀር ስድቡን ምን አመጣው::ኤዲያ ዱሮም ባሪያ አንገት የለውም...
እነ ቓ ሹሉቃ፣ ፊጣ፣ ጝኛሞ፣ ጫልቱ ፣ቔራሮ፣ ቜቡሼ ፣ቛዱጬ ምንትሴ ቅብጥርሴ ሆይ አምሐርኛ የቴክኖሎዢ ቋንቋነቱ ያስመሰከረ ብቸኛ አፍሪካዊ ቋንቋ ከሆነ ሰነበተ::አምሐርኛን ያለመጠቀም መብታችሁ የተጠበቀ ነው::ስትጠቀሙ ግን ደምብና ስርዓቱንም ልብ እያላችሁ..."በፊደሎቻችን ላይ ሦስት ሀ - ሐ - ኀ፣ ሁለት አ - ዐ -፣ ሁለት ሠ - ሰ ሁለት፣ ጸ - ፀ አሉ፡፡ እነዚህ ፊደሎች የራሳቸው የሆነ የስም አጠራርም አላቸው፤ ሀሌታው ሀ፣ ሐመሩ ሐ፣ ብዙኃን ኀ፣ ንጉሡ ሠ፣ እሳቱ ሰ፣ ጸሎት ጸ፣ ፀሐዩ ፀ ይባላሉ፡፡ በጽሑፍ የሚገቡበትን ተገቢ (ተስማሚ) ቦታም አላቸው፡፡ ለምሳሌ በሁለት ፊደሎች መጠቀም ይቻላል፡፡ ሀገር አገር ይህ ትክክለኛ አጻጻፍ ሲሆን፤ ነገር ግን ከዚህ ውጪ ሐገር፣ ኀገር ብሎ መጻፍ ግን ስሕተት ይሆናል፤ የሚከተሉትን ደግሞ እንመልከት፤
ሕገ መንግሥት፣ ሕገ ወጥ፣ ሕዝብ፣ ሕብረት፣ ዓቃቤ ሕግ፣ ወዘተ. የመሳሰሉት አጻጻፋቸው ትክክል ነው፡፡ ከዚህ ልማዳዊ አሠራር ውጪ ህገ መንግሥት፤ ህገወጥ፤ ህዝብ፤ ህብረት፤ አቃቤ ህግ ስሕተታዊ አጻጻፍ ይሆናል፤ ሌላ ማስረጃ ቢፈለግ፤ ኃይለሥላሴ የሚለው ስም ሦስት የተለያዩ ፊደሎች ይዟል፡፡ የመጀመርያው ፊደል ብዙኀን - ኃ - ሲሆን፣ ከንጉሡ -ሥ- ሳድስ፣ ከእሳቱ -ስ- ሃምስን በመጻፍ እንዲካተት ተደርጓል፡፡ ሀይለ ስላሴ ብሎ ቢጻፍ ግን የፊደሎቻችን የአጻጻፍ ሥርዓት ማፋለስ ይሆናል፤ በአቦ ሰጡኝ ፊደሎቻችን አለቦታቸው መግባትም፣ መጻፍም የለባቸውም፡፡ "
መሪ ጌታ ቅዥቢው ዘ-ብሔረ አምሐራ
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

ተናግረህ...

Postby ዳግማዊ ቅዥቢው » Tue Dec 04, 2012 4:23 pm

ዲጎኔ ተናግረህ አታናግረኝ::ዋርካ ዉስጥ ከማከብራቸው ሐበሾች አንዱ አንተ ነህ::እናም ተወኝ...ዛሬ በበረዶ ምክኒያት ከቤቴ አልወጣሁም ድብን ብየ ተጠናቅቄያለሁ...እንደፈልግኩ የመሳደብ ስካራዊ መብቴ ነው::
ዳግማዊ ቅዥቢው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 117
Joined: Mon Nov 26, 2012 1:08 am

Re: ተናግረህ...

Postby እንሰት » Tue Dec 04, 2012 10:22 pm

መሪ ጌታ ቅዥቢው
እንዲህ ወዝ ያለው ጨዋታ ጀምረህ እንደ አስር አለቃ ደበላማ መሳደብ አያምርብህም::

ዲጎኔንም አታስፈራራው ያሰበውን ያመነውን የሚያውቀውን ይናገር::

የፋንታሁን እንግዳን ጽሁፍ ዘርዘር አድርገህ አቅርበሀል የዶ/ር በድሉ ዋቅጅራንም ጽሁፉን ማግኘት ባይቻል ምንጩን ቦታውን ብትነግረን ለመነጋገር ይመቻል::

እኔ ሳውቅ ዶ/ር በድሉ ገጣሚ እንዲየውም በቅርቡ ሁለተኛውን መጽሀፍ አሳትሞዋል ማህበራዊ ጉዳይ አሳቢም በመሆን የተለያዩ ጽሁፎች በፍትህ ጋዜጣ አስነብቦናል::

ይህን ሁሉ ያነሳሁልህ ያነበብከውን ወይ የሰማህበትን ብትጠቁመን ብዬ ነው::

አክባሪህ
ያልሰከረው ለመሳደብም መብት የሌለው እንሰት

ዳግማዊ ቅዥቢው wrote:ዲጎኔ ተናግረህ አታናግረኝ::ዋርካ ዉስጥ ከማከብራቸው ሐበሾች አንዱ አንተ ነህ::እናም ተወኝ...ዛሬ በበረዶ ምክኒያት ከቤቴ አልወጣሁም ድብን ብየ ተጠናቅቄያለሁ...እንደፈልግኩ የመሳደብ ስካራዊ መብቴ ነው::
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

ፊደል...

Postby ዳግማዊ ቅዥቢው » Tue Dec 04, 2012 10:51 pm

ሰላም እንሰት
የበድሉ ዋቅጅራን ጦማር አሁን በቅርቡ በታገደችው የፍትሕ ጋዜጣ የመጨረሻ እትሞች በአንዱ ላይ ያገኙታል::ለግንዛቤ ይረዳዎ ዘንድ ሰሞኑን ሰለሞን ተሰማ ጂ."የፊደል ጣጣና የአምስት ትውልድ ውዝግብ"በሚል ርዕስ ኢትዮጵያ ዛሬ ላይ ዱቅ ያደረጋትን ጦማር ይመንጥሩ::
ዳግማዊ ቅዥቢው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 117
Joined: Mon Nov 26, 2012 1:08 am

Re: ተናግረህ...

Postby እንሰት » Tue Dec 04, 2012 10:53 pm

ጥያቄዬ አልተመለሰም መሪ ጌታ ቅዥቢው አሁንም ዝርዝር እንጠብቃለን::

የተሻለ መረጃ ከ ኢትዮጵያ ዛሬ አገኘሁና አመጣሁላችሁ::
ሙሉ ጽሁፉን እዚያ ማየት ይቻላል::

የፊደል ጣጣና የአምስቱ ትውልድ ውዝግብ!
http://www.ethiopiazare.com/history/his ... -existance
ሰሎሞን ተሰማ ጂ.
ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፣ “መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ” (1948) በታተመው መጽሐፋቸው ውስጥ እንደበየኑት፣ “ፊደል ማለት ቀለም፤ ምልክት፤ የድምፅና የቃል መልክ፤ ሥዕል፤ መግለጫ ማስታወቂያ፤” ነው (ገጽ 616)። ደስታ ተክለ ወልድም በበኩላቸው፣ በ1962 ዓ.ም. ባሳተሙት “ዐዲስ ያማርኛ መዝገበ ቃላት” መጽሐፋቸው እንደገለጹት፣ “ፊደል ማለት የነገር፣ የቃል ምልክት፣ የድምፅ ሥዕል፣ ማጉሊያ፤ መግለጫ ነው፤” (ገጽ 988)። በሁለቱም ሊቃውንት አተያይ ውስጥ ፊደል የድምፅና የቃል ምልክት መሆኑን በአጽንዖት ተገልጧል።

ስለሆነም፣ እንደማንኛውም የሰው ልጆች ፈጠራና ቅርስ ከጊዜ ጋር ሊለወጥና ሊሻሻልም መቻሉን ጠቋሚ ሁናቴ በትርጓሜው ውስጥ አለ።

የዚህ ጽሑፍ መነሻ የሆነን፣ ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ በአዲስ ታይምስ መጽሔት (ቅጽ 1፣ ቁጥር 6) ላይ ያወጡት “የአጻጻፍ ሥርዓታችንን ስለማሻሻል” የሚለውን ጽሑፋቸውን ካነበብን በኋላ ነው (ገጽ 14-15ና 26 ላይ ይመልከቱ)። ጽሑፉ በርካታ ቁምነገሮችን ይዟል። ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ፣ ስለፊደልና ስለአጻጻፍ ሥርዓታችን ጉዳይ ደግመው በዚህ ዘመን ላለውም አንባቢ ስላነሡትና የአንባቢያንን አስተውህሎትም ለመቆስቆስ ስለሞከሩ ምስጋና ሊቸራቸው ይገባል። በተጨማሪም፣ የሃሳቡን ማጠንጠኛ እንዝርትና ቀሰም በወጉ ስላቀረቡልንና የትኛውንም የሃሳብ ጎራ እንደሚደግፉም በአደባባይ ወጥተው ስለገለጹልን ላቅ ያለ ሥራ ሰርተዋል።

ዶ/ር በድሉ በጽሑፋቸው ውስጥ የሃሳብ ጎራቸውን ከመለየታቸውም በተጨማሪ፣ ሁለቱን “እምነቶቻቸውን” በጠራ ቋንቋ ገልጠውልናል። የመጀመሪያው እምነታቸው፣ ስለሞክሼ ፊደላት ጉዳይ ሲሆን፣ “አንድን ድምጽ ለመወከል ሲባል ሁለትና ከዚያም በላይ የሆኑ ሞክሼ ፊደላት መደጋገማቸው አስፈላጊ አይደለም፤” የሚል ነው። በሁለተኛ ደረጃም የጠቀሱት መከራከሪያቸው፣ “ጽሕፈትን/ፊደልን ለማሻሻል የሚገባው፣ ቋንቋ ከጊዜ ጋር እየተለወጠ የሚሄድ አኃዝ ስለሆነ ነው፤” ሲሉ ያቀርባሉ። በመጨረሻም፣ “የአንድን ቋንቋ የአጻጻፍ ሥርዓት ለማሻሻል ሲነሱ ሁለት ደረጃዎች አስፈላጊ ናቸው። እነርሱም፣ በመጀመሪያ የአጻጻፍ ሥርዓቱ ችግር አለበት ወይ ወይንስ “ብቁ” ነው በሚለው ላይ እንነጋገርበት፤” ሲሉ አንባቢያኑን ይጋብዛሉ። በማስከተልም፣ “በሁለተኛው ደረጃ ላይ ደግሞ፣ ፊደላችንና የአጻጻፍ ሥርዓታችን “ችግሮች አሉበት” የምንል ከሆነ፣ ችግሮቹ እንደምን ይስተካከሉ” የሚለው ነጥብ ላይ ኋላ እንመለስበታለን” የሚል ገንቢ ጥያቄ ነው ያነሱት።

የዶ/ር በድሉ ጽሑፍ ስለፊደላት ጉዳይ ሲያወሱ በአመዛኙ የሀገራችንን የፊደላት ክርክር ታሪክ ትተው፣ በውጭው (ማለትም በቱርክና በጃፓኖች) የፊደላት ለውጥ ጉዳይ ላይ አተኩረዋል። በተጨማሪም፣ በርካታ የፊደላትነ ለውጥ የሚደግፉ ንድፈ ሃሳቦችን በሰፊው አቅርበዋል። ይበል የሚያሰኝ ነው። ነገር ግን፣ የእኛን ጓዳም በተመለከተ በዝርዝር ስላልከለሱልን (ሙያቸው ነውና በቅጡ ያውቁታል)፣ ይህንን ጽሑፍ ለአንባቢያን እዝነ ሕሊና ይበጃል ስንል ጽፈነዋል። ስለፊደላችን ጉዳይም ጠቅለል ያለ መረጃ ለአንባቢያን ይሰጣል ብለን እናምናለን።

እንሰት wrote:መሪ ጌታ ቅዥቢው
እንዲህ ወዝ ያለው ጨዋታ ጀምረህ እንደ አስር አለቃ ደበላማ መሳደብ አያምርብህም::

ዲጎኔንም አታስፈራራው ያሰበውን ያመነውን የሚያውቀውን ይናገር::

የፋንታሁን እንግዳን ጽሁፍ ዘርዘር አድርገህ አቅርበሀል የዶ/ር በድሉ ዋቅጅራንም ጽሁፉን ማግኘት ባይቻል ምንጩን ቦታውን ብትነግረን ለመነጋገር ይመቻል::

እኔ ሳውቅ ዶ/ር በድሉ ገጣሚ እንዲየውም በቅርቡ ሁለተኛውን መጽሀፍ አሳትሞዋል ማህበራዊ ጉዳይ አሳቢም በመሆን የተለያዩ ጽሁፎች በፍትህ ጋዜጣ አስነብቦናል::

ይህን ሁሉ ያነሳሁልህ ያነበብከውን ወይ የሰማህበትን ብትጠቁመን ብዬ ነው::

አክባሪህ
ያልሰከረው ለመሳደብም መብት የሌለው እንሰት

ዳግማዊ ቅዥቢው wrote:ዲጎኔ ተናግረህ አታናግረኝ::ዋርካ ዉስጥ ከማከብራቸው ሐበሾች አንዱ አንተ ነህ::እናም ተወኝ...ዛሬ በበረዶ ምክኒያት ከቤቴ አልወጣሁም ድብን ብየ ተጠናቅቄያለሁ...እንደፈልግኩ የመሳደብ ስካራዊ መብቴ ነው::
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby እንሰት » Tue Dec 04, 2012 11:21 pm

ዳግማዊ ቅዥቢ ባነሳው ምክንያት ዋና ጽሁፍ ፍለጋ አሰሳ ሄደን በለስ ቀንቶን ተመልሰናል::
ኢትዮጵያ ዛሬ ድረ ገጽ አዲስ ታይምስን በ ፒዲ ኤፍ ገጹ ማህደር ውስጥ አኑሮታል::

የዶ/ር በድሉን ጽሁፍ አንብበን አስተያያተችንን መቀጠል ነው::

http://www.ethiopiazare.com/images/doc/ ... -no-06.pdf
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

ፊደል...

Postby ዳግማዊ ቅዥቢው » Wed Dec 05, 2012 12:03 am

ፍረዱኝ...
"ያላዋቂ ሳሚ ንፍጥ ይለቀልቃል"አለች ሕፃን አማረች:: :lol:
የኦቦ ዋቅጅራ ልጅ እንደ ግመል አንገት የረዘመ ጦማረ እንቶፍንቶ ዉስጥ እንደ መከራከሪያ ሆነው የቀረቡት አንኳር ነጥቦች ከዚህ በታች ያሉት ናቸው:-
"ለመሆኑ የአማርኛ አፃፃፍ ችግር አለበት? ካለበትስ ችግሩ ምንድ ነው? በተደጋጋሚ እንደሚነሳው የአማርኛ አፃፃፍ ችግር አለበት፤ ችግሩ ደግሞ የሞክሼ ፊደላት መኖርና ጠብቀውና ላልተው የሚነበቡ ድምጾችን አለመለየቱ ነው፡፡ እዚህ ላይ ሊጤን የሚገባው አፃፃፉ ከጽህፈት ስርዓት መመዘኛዎች አንፃር ችግሩ አለበት ተባለ እንጂ፣ በዚህ ችግር የተነሳ የአማርኛ ጽህፈት መልእክት ማስተላለፍ ተሳነው አለመባሉን ነው፡፡
የአማርኛ አፃፃፍ በሚጠቀምበት የፊደል ገበታ ላይ አንድ ድምጽ ከአንድ በላይ ምልክት ተሰጥቶታል፡፡ እነዚህ ከአንድ በላይ ምልክት የተሰጣቸው ድምጾች ሀ፣ ጽ፣ አ እና ሰ ናቸው፡፡ በዚህም የተነሳ አማርኛ መደበኛ የሆነ የአፃፃፍ ስርዓት እንዳይኖረው ሆኗል፡፡ አንዱ በሰበሰ ሲል ሌላው በሠበሠ ብሎ ይጽፋል፡፡ ውሃ፣ ውሀ፣ ውኃ፣ ውሐ የሚሉት የአንድ ንግግር ቃል ወካይ አራት የአፃፃፍ መንገዶች ናቸው፡፡ ብዙዎች ለዚህ ሀሳብ የሚያቀርቡት መቃወሚያ አይ አይሆንም፤ ይህኛው አፃፃፍ አልተለመደም ወይም በግዕዝ ቋንቋ እንዲህ አይፃፍም የሚል ነው፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ግዕዝና አማርኛ ሁለት ቋንቋዎች ናቸው፡፡ በየትኛውም መንገድ ግዕዝን እያሰብን አማርኛን መፃፍና ማንበብ ተቀባይነት ሊኖረው አይገባም፡፡ “አልተለመደም” የሚለውን በተመለከተ ግን ብዙ ትክክለኛ አማራጮች አስቀምጦ “የተለመደውን ብቻ ምረጥ” ከማለት ለምንድነው አንዱን መርጠን የማናስቀምጠው? እውቃለሁ “ውሐ” ብሎ መፃፍ አልተለመደም፤ ግን ትክክል ነው፡፡ ሁለቱ ፊደላት ተገጣጥመው ሲነበቡ “ውኃ” የሚለው ቅንብር የሚሰጠውን ትርጉም ይሰጣሉ፡፡ ጽህፈት የድምፅ ውክልና እስከሆነ ድረስ አራቱም አፃፃፍ ትክክል ናቸው...
ዳግማዊ ቅዥቢው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 117
Joined: Mon Nov 26, 2012 1:08 am

Re: ፊደል...

Postby እንሰት » Thu Dec 06, 2012 3:27 am

ዋርካውያን ዳግማዊ ፍረዱኝ ብሎዋል ወይ ፍረዱለት ወይ ፍረዱበት በሀሳቡ ማለቴ ነው::

በነገራችን ላይ እንደ አባይ (አባይ አሁን እንኩዋን ፖልቲካ ሆኖዋል) ሁሉ ፊደልም ሀይማኖትም ሴክሲ ርእሶች እየሆኑ መታወቅ የሚፈልጉ ሰዎች ሲያነሱ ሲጥሉት ይታያል::

መሪጌታ ምስጋና ይገባህል:: የኔንም ሀሳብ አቀርባለሁ:: ባጭሩ ግን ፊደላት አይቀነሱ ባይ ነኝ::

ዳግማዊ ቅዥቢው wrote:ፍረዱኝ...
"ያላዋቂ ሳሚ ንፍጥ ይለቀልቃል"አለች ሕፃን አማረች:: :lol:
የኦቦ ዋቅጅራ ልጅ እንደ ግመል አንገት የረዘመ ጦማረ እንቶፍንቶ ዉስጥ እንደ መከራከሪያ ሆነው የቀረቡት አንኳር ነጥቦች ከዚህ በታች ያሉት ናቸው:-
"ለመሆኑ የአማርኛ አፃፃፍ ችግር አለበት? ካለበትስ ችግሩ ምንድ ነው? በተደጋጋሚ እንደሚነሳው የአማርኛ አፃፃፍ ችግር አለበት፤ ችግሩ ደግሞ የሞክሼ ፊደላት መኖርና ጠብቀውና ላልተው የሚነበቡ ድምጾችን አለመለየቱ ነው፡፡ እዚህ ላይ ሊጤን የሚገባው አፃፃፉ ከጽህፈት ስርዓት መመዘኛዎች አንፃር ችግሩ አለበት ተባለ እንጂ፣ በዚህ ችግር የተነሳ የአማርኛ ጽህፈት መልእክት ማስተላለፍ ተሳነው አለመባሉን ነው፡፡
የአማርኛ አፃፃፍ በሚጠቀምበት የፊደል ገበታ ላይ አንድ ድምጽ ከአንድ በላይ ምልክት ተሰጥቶታል፡፡ እነዚህ ከአንድ በላይ ምልክት የተሰጣቸው ድምጾች ሀ፣ ጽ፣ አ እና ሰ ናቸው፡፡ በዚህም የተነሳ አማርኛ መደበኛ የሆነ የአፃፃፍ ስርዓት እንዳይኖረው ሆኗል፡፡ አንዱ በሰበሰ ሲል ሌላው በሠበሠ ብሎ ይጽፋል፡፡ ውሃ፣ ውሀ፣ ውኃ፣ ውሐ የሚሉት የአንድ ንግግር ቃል ወካይ አራት የአፃፃፍ መንገዶች ናቸው፡፡ ብዙዎች ለዚህ ሀሳብ የሚያቀርቡት መቃወሚያ አይ አይሆንም፤ ይህኛው አፃፃፍ አልተለመደም ወይም በግዕዝ ቋንቋ እንዲህ አይፃፍም የሚል ነው፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ግዕዝና አማርኛ ሁለት ቋንቋዎች ናቸው፡፡ በየትኛውም መንገድ ግዕዝን እያሰብን አማርኛን መፃፍና ማንበብ ተቀባይነት ሊኖረው አይገባም፡፡ “አልተለመደም” የሚለውን በተመለከተ ግን ብዙ ትክክለኛ አማራጮች አስቀምጦ “የተለመደውን ብቻ ምረጥ” ከማለት ለምንድነው አንዱን መርጠን የማናስቀምጠው? እውቃለሁ “ውሐ” ብሎ መፃፍ አልተለመደም፤ ግን ትክክል ነው፡፡ ሁለቱ ፊደላት ተገጣጥመው ሲነበቡ “ውኃ” የሚለው ቅንብር የሚሰጠውን ትርጉም ይሰጣሉ፡፡ ጽህፈት የድምፅ ውክልና እስከሆነ ድረስ አራቱም አፃፃፍ ትክክል ናቸው...
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

ፊደል...

Postby ዳግማዊ ቅዥቢው » Thu Dec 06, 2012 3:43 am

ፊደላችንን የነካ እንደኔ አዕምሮው ይነካ...አፉን ሽንኩርት ቂጡን ዋሽንት ያድርገው ብዬ ረግሜዋለሁ!
ዳግማዊ ቅዥቢው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 117
Joined: Mon Nov 26, 2012 1:08 am

Postby Asir Aleqa Dabala » Thu Dec 06, 2012 5:12 am

አማራን ያየ አማሪኛን አይፅፍም አይናገርም

የእኮኖሚ ሁነታህ የቁቆህን የወደፍት እድል ይወስናል

አሁን እየታየ ያለው አፋን ኦሮሞ በኦሮሚያ እኮኖሚ እየታገዘ ወደፍት መምጣቱ ነው

ሻይ ለማዘዝ ኦሮሚኛ መኮላተፍ ያስፈልጋል ዛረ በኦሮሚያ ውስጥ

እስቲ ልኩራራ ብለህ አማሪኛ ከጀመርክ ለብቻህ ኢንዳበድ ሰው ታወራለህ እንጂ የሚሰማህ የለም
Asir Aleqa Dabala
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 114
Joined: Mon Dec 03, 2012 12:01 am

Postby እንሰት » Thu Dec 06, 2012 5:51 am

ስለ አማርኛ ሲወራ ውቡ ኦሮሚኛን አምጥቶ ድንቅር ምንድን ነው?

Asir Aleqa Dabala wrote:አማራን ያየ አማሪኛን አይፅፍም አይናገርም
...
እስቲ ልኩራራ ብለህ አማሪኛ ከጀመርክ ለብቻህ ኢንዳበድ ሰው ታወራለህ እንጂ የሚሰማህ የለም

እንግዲህ ፍርድ ከራስ አይደል የሚጀምረው ኦቦ ደበላ
ከስምህ ሶስቱ ቃላት ሁለቱ አማርኛ ናቸው አስር አለቃ...
አንድ ቃል ኦሮሞኛ ደበላ እና ምን እንበልህ አንተን?
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Re: ፊደል...

Postby እንሰት » Fri Dec 07, 2012 7:22 am

መሪ ጌታ ይህንን መጠቆሚያ እኔ ዋርካ ላይ ስጽፍ አልነበረም ወይም አላየሁትም::

ስለ ፈጣኑ ምላሽሕ ላመሰግን ነው ብቅ ያልኩት::

ዳግማዊ ቅዥቢው wrote:ሰላም እንሰት
የበድሉ ዋቅጅራን ጦማር አሁን በቅርቡ በታገደችው የፍትሕ ጋዜጣ የመጨረሻ እትሞች በአንዱ ላይ ያገኙታል::ለግንዛቤ ይረዳዎ ዘንድ ሰሞኑን ሰለሞን ተሰማ ጂ."የፊደል ጣጣና የአምስት ትውልድ ውዝግብ"በሚል ርዕስ ኢትዮጵያ ዛሬ ላይ ዱቅ ያደረጋትን ጦማር ይመንጥሩ::
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

ፊደል...

Postby ዳግማዊ ቅዥቢው » Fri Dec 07, 2012 9:36 pm

ምስጋናውን ተቀብለናል እንሰት::ባጋጣሚ ሁለታችንም በሁለት ደቂቃ ልዩነት ፖስት ስላደረግን ነው ክፍተቱ የተፈጠረው::በተመሳሳይ ሰዓት ላይ ስንገናኝ ቻት ማድረግ አይከፋም::እርግጥ ነው ዋርካ ላይ ዱቅ 'ምለው ጨብ ብዬ ስለሆነ ስድብ እንደ ዝናብ አዘንብብዎት ይሆናል ቢሆንም...ቢሆንም....መቻል ነው...በመቻል ነው መቻቻል 'ሚቻለው::በቬራ ዉብ ቃላቶች ቀደዳዬን ልግታ:-
“Each letter of the alphabet is a steadfast loyal soldier in a great army of words, sentences, paragraphs, and stories. One letter falls, and the entire language falters.”Vera Nazarian, The Perpetual Calendar of Inspiration
ዳግማዊ ቅዥቢው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 117
Joined: Mon Nov 26, 2012 1:08 am

Next

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests

cron