የግጥም ጥግ የጆሲ ወግ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby Jossy1 » Sun Nov 24, 2013 3:50 pm

ህይወት ስትፈተን ልትቆም ስትዋትት
መከራ እየገፋት ሊጥላት ሲባትት
ጥንካሬ ሲልም ጥቃቱ ሲበዛ
ደስታ ጭራሽ ጠፍቶ ጭቆና ሲንዛዛ
በጣጥሰህ ምትጥለው የፈተናን መረብ
በተስፋ ብቻ ነው ጥንካሬ ሚያብብ::

ተስፋም የሚታሰብ ተስፋ ሲፈተን ነው
በደስተኞች አለም ተስፋ የሌለ ነው::
Freewill
Jossy1
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 215
Joined: Sun Aug 28, 2005 6:37 am
Location: qatar

Postby ሳምራውው33 » Sun Nov 24, 2013 3:56 pm

መራራ

አልሞተም ወርቅሰው አልሞተም ቃኘው:
ይሄው በዲጎኔ አይኔ እያየው::
ሞቷል አትበሉኝ ወርቅሰው አልሞተም:
ሄዷል አትበሉኝ ወርቅሰው አልሄደም:
አራምባ እና ቆቦን ሁሌም እንዳንረሳ:
ዛሬም በ ዋርካችን ተቀምጧልሳ::
ሀ-ግስ እና ለ-ግስ እረ እነ ሁካይ:
ይህን ግጥም አይተው በህይወት አሉ ወይ? :lol: :lol:
የ ድንቅነሽ ወዳጅ የ ላርዲ ጓደኛ:
የ ሶስት ሺ ዘመን ቃኚ ዘለሰኛ:
ከ ወዲያኛው ማዶ ሁሌም ነኝ የሚለንን:
ግጥም እንድትደፈር ሁሌም ያኑርልን:: :lol: :lol: :lol:አቤት አገጣጠም የቃላት ድርደራ
ላካስ ገጣሚነዎት ልእልት መራራ :!:

ተመልከት ዲጎኔ የግጥም አጻጻፍ
የቤት አመታትን የቃላት አሰካክ
ያንተን ግጥም እኔ ስመለከታቸው
አጥር ማፍረስ እንጂ ፋይዳም የላቸው :roll: :roll:
ግጥም ካልጣፈጠ ሚስጥርን ካልያዘ
አፍዞ አደንግዞ ልብን ካልመሰጠ
በአእምሮ ሰሌዳ ምስሉ ካልታየ
ከስድ ንባብ ጋር በምንስ ተለየ :?: :?: :?:
The love of money is the root of all evil.

ሳምራውው 33 የግጥም አርበኛ
ስንኝ ቋጣሪ በውብ አማርኛ ::
_________________
ሳምራውው33
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 530
Joined: Thu Jun 21, 2007 12:23 am

Postby ክቡራን » Sun Nov 24, 2013 7:34 pm

ወንድሜ ዲጊኔ የምቀኞችን ወሬ አትስማ!! ጥበብ እንደሆነ አንዴ ጠርተሀለች:: ጥሪዋን አትመልሰውም:: ጥበብ እንደሰጠችህ ና የግጥም መንፈስ በገለጸልህ መጠን ጥበብን ተጠበብባት::
ከቡዙ አድናቆት ጋር::
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8259
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ክቡራን » Sun Nov 24, 2013 8:38 pm

ጥበብ እኮ ታምራት ገለታንም ጠርታለች:: ዚቁ ያለው ግን ጥሪውን በመልካም ተግባር ላይ ማዋሉ ላይ ነው:: ""ያልቦካ ጸሎት ከመከራ አያድንም "" ዲሞጥሮስ የሚባለው አስተማሪዬ እኮ ነው::

እነሆ ጠቢባን ሆይ ተጠበቡ... ያላወቁቹ ደሞ እወቁ ወይም ደሞ ጠበብ መስሏቹ የዋጣችሁትን ቴትራ ሳይክሊን አስታውኩት :::: :D

መተሬ= ውርስ ትርጉም= ስናይፕር ተኴሽ :D

http://www.youtube.com/watch?v=t4iGx1z5gls
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8259
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby መራራ » Mon Nov 25, 2013 10:35 am

ሰለሞን ጠቢቡ የ ሳባ አማላይ:
ታምራት ጠቢብ ነው ባዮችን ብታይ:
የጥበብን ሚስጥር ምጡቅነቷን:
ላለማወቃቸው ሰም እና ወርቋን:
ታዝላቸው ነበር ""ጥበብ"" የሸማኔውን:: :lol: :lol: :lol:

ተጻፈ በ ልእልት መራራ:: መታሰቢያነቷ ለ ሳምራውው33 ትሁንልኝ:: :lol: :lol: ዱላነቷ ደግሞ ለ ካርቦንዬ :lol: :lol: :lol:

ክቡራን wrote:ጥበብ እኮ ታምራት ገለታንም ጠርታለች:: ዚቁ ያለው ግን ጥሪውን በመልካም ተግባር ላይ ማዋሉ ላይ ነው:: ""ያልቦካ ጸሎት ከመከራ አያድንም "" ዲሞጥሮስ የሚባለው አስተማሪዬ እኮ ነው::

እነሆ ጠቢባን ሆይ ተጠበቡ... ያላወቁቹ ደሞ እወቁ ወይም ደሞ ጠበብ መስሏቹ የዋጣችሁትን ቴትራ ሳይክሊን አስታውኩት :::: :D

መተሬ= ውርስ ትርጉም= ስናይፕር ተኴሽ :D

http://www.youtube.com/watch?v=t4iGx1z5gls
መራራ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 753
Joined: Sat Sep 25, 2004 9:58 am
Location: united states

Postby ክቡራን » Mon Nov 25, 2013 3:41 pm

ሀማል መራራ:- ለማስተካከል ያህል ነው ግጥም ብለህ የጫርከውን ..ነገር....
ሰለሞን ጠቢቡ የሳባ አማላይ..
ታምራት ጠቢብ ነው ባዮችን ቢያይ..

ነው የሚባለው ብታይ...አይባልም:: አንተ የጾታ ዲሲኦሬንትሽን ስላለብህ ሰለሞንም አለበት ማለት አይደለም:: ማን መሆንህን ለማሳየት ያህል ብቻ ነው:: ሰላሙን::

በልዕልት መራራ ስም የገባው ሀማል wrote:ሰለሞን ጠቢቡ የ ሳባ አማላይ:
ታምራት ጠቢብ ነው ባዮችን ብታይ:
የጥበብን ሚስጥር ምጡቅነቷን:
ላለማወቃቸው ሰም እና ወርቋን:
ታዝላቸው ነበር ""ጥበብ"" የሸማኔውን:: :lol: :lol: :lol:

ተጻፈ በ ልእልት መራራ:: መታሰቢያነቷ ለ ሳምራውው33 ትሁንልኝ:: :lol: :lol: ዱላነቷ ደግሞ ለ ካርቦንዬ :lol: :lol: :lol:

ክቡራን wrote:ጥበብ እኮ ታምራት ገለታንም ጠርታለች:: ዚቁ ያለው ግን ጥሪውን በመልካም ተግባር ላይ ማዋሉ ላይ ነው:: ""ያልቦካ ጸሎት ከመከራ አያድንም "" ዲሞጥሮስ የሚባለው አስተማሪዬ እኮ ነው::

እነሆ ጠቢባን ሆይ ተጠበቡ... ያላወቁቹ ደሞ እወቁ ወይም ደሞ ጠበብ መስሏቹ የዋጣችሁትን ቴትራ ሳይክሊን አስታውኩት :::: :D

መተሬ= ውርስ ትርጉም= ስናይፕር ተኴሽ :D

http://www.youtube.com/watch?v=t4iGx1z5gls
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8259
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ቦቹ » Mon Nov 25, 2013 5:57 pm

መራራ wrote:ሰለሞን ጠቢቡ የ ሳባ አማላይ:
ታምራት ጠቢብ ነው ባዮችን ብታይ:
የጥበብን ሚስጥር ምጡቅነቷን:
ላለማወቃቸው ሰም እና ወርቋን:
ታዝላቸው ነበር ""ጥበብ"" የሸማኔውን:: :lol: :lol: :lol:

ተጻፈ በ ልእልት መራራ:: መታሰቢያነቷ ለ ሳምራውው33 ትሁንልኝ:: :lol: :lol: ዱላነቷ ደግሞ ለ ካርቦንዬ :lol: :lol: :lol:
እንዴ እንዴ ወይዘሮ በላይነሽ ሰላም ብለናል ቅቅቅቅቅ :lol: :lol: ለካ ጥሩ ገጣሚ ሆነዋል እንደዚህ አይ ጥሩ ነው:: እኔ የምለው ግን ዘንድሮ ምነው ገጣሚ በዛሳ :wink: :wink: ያም ተነስቶ ሆዴ ዴ ዴ ዴ ቻ ቻ ቻ ዋ ዋ ዋ: :lol: :lol: ቅቅቅቅቅ ይሁን ዋርካ ላይ ካልተለማመድን የት ልንለማመድ ነው:: ይቺ ድሮ ውቤ በረሃ ቡጊ እያስነኩ በነበረበት ዘመን ላይ የተገጠምች ግጥም ነች:: የግጥሙ ባለቤት እርሶና ባለቤቶት አቶ ብርሌ እንደሆኑ ብዙ ሰዎች ይናገራሉ...... :lol:

ትምሕርት ቤት ሆነን የጠየከኝን
እንጦጦ አፋፉ ላይ የሰጠውክን
ፋዘር ተቆጥቷል መልስ ድንግሌን

ፋዘርሽ ቢቆጡ ቢፈርጡ እንደንቧይ
የፈሰሰ ውሃ ይታፈሳል ወይ
የፈሰሰ ውሃ ከታፈሰላቸው
አባትሽ ለናትሽ ይመልሱላቸው
እንኳን ያንቺ ድንግል የትናትናው
ያባይ ድልድል ፈርሷል ጣልያን የሰራው......... :D :D
ቦቹ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 357
Joined: Fri Dec 31, 2004 1:26 am

Postby ዲጎኔ » Tue Nov 26, 2013 1:53 am

ሰላም/አሻማ
ወገን ቦቹ ድሮ ለአዲስ አመት ይቀርቡ የነበሩ ዜማዎችን አስታወስከኝ:-
አስኮበለልኩዋት ያችን ልጅ
አባትዋ ከሰው ታሰርኩ እንጂ
እኔም ወድጄ እሷም ወድዳ
ብቻየን አየሁ የቁም ፍዳ
የሻማ እያሉ መንጋዱራ
በቃሪያ ጥፊ ፊቴ በራ
በከያኒ ጌጡ አየለ

አውሮፕላን መጣ እየገሰገሰ
በዘፈን አንደኛ ጥላሁን ገሰሰ

ከከያኒ ጥላሁን ዜማና ግጥሞች ግብረገብ ያለው እነሆ:-
የእውነትን መንገድ ተሳስቼ
ተቀጣሁ በውሸት ተመርቼ
እውነት ማሪኝ ብያለሁ
ይቅርታ እጠይቃለሁ
በሀሰት ለለወጧት እውነትን ባፋቸው
የቁምነገር አምላክ ይቅር ይበላቸው
የትግልና የከሴ/ከርቼሌ ጉዋዳችን ከያኒ ቶማስ አበበ እንዲህ ብሎ ነበር:-
አበባ ምንጣፉ የእኔም ድሪቶዬ
የገንዘቡ ካዝና የእኔም ስልቻዬ
እበላው እጠጣው እቀምሰው የለለኝ
ከርታታው ምስኪኑ ጭቁኑ ቶማስ ነኝ

ቦቹ wrote:

ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby ቦቹ » Tue Nov 26, 2013 5:43 am

ዲጎኔ wrote:ሰላም/አሻማ

ሰላም ዲጎኔ ዋርካን በግጥም ድባብ መተሀታል ግን ደስ ይላል:: ልብን ይመስጣሉ ግጥሞችህ ጭቁኑ ቶማስ ደግሞ ያሳዝናል ይቺ መከረኛ አገር መቼም ስንቱ ስንት ነገር አይቶባታል:: ለማንኛውም እኔ የግጥም የማንበብ ፍቅር እንጂ የመጻፍ ችሎታው የለኝምና ከተጻፉት መካከል አንደኛውን ለትዝታ መዝዤ ልጋብዝህ..........እንሆ በረከት

ሃ ገ ሬ
{ሰአሊና ገጣሚ ገብረ ክርስቶስ ደስታ}

አገሬ ውበት ነው፣

ለምለምና ነፋስ የሚጫወትበት፣

ፀሃይ የሞላበት፣ ቀለም የሞላበት።

አገሬ ቆላ ነው፣ ደጋ ወይና ደጋ፣

እዚያ ብርሃን አለ ሌሊቱ እስኪነጋ።

አገሬ ተራራ ሸለቆ ረባዳ፣

አገሬ ጅረት ነው ገደልና ሜዳ፣

ውበት ነው በበጋ ፀሃይ አትፋጅም፣

ክረምቱም አይበርድም፣

አይበርድም፣ አይበርድም።

አገሬ ጫካ ነው፣

እንሰሳት አራዊት የሚፈነጩበት፣

በወጥመድ ሳይገቡ ሳይነካቸው ጠላት።

እዚያ አለ ነፃነት፣

በሃገር መመካት፣

በተወላጅነት፣

በባለቤትነት፣

እዚያ አለ ነፃነት።

አገሬ ሃብት ነው፤

ጎመኑ ስብ ጮማ፣ ቆሎ ክትፎ ስጋ፣

ድርቆሹ ፍትፍት ነው፣ ቃሪያው ሙክት ሠንጋ፣

ጠጁ ነው ወለላ፣

ከኮኛክ ያስንቃል የመንደሩ ጠላ።

እህሉ ጣእም አለው እንጀራው ያጠግባል፣

ከቢራ ከሻምፓኝ ውሃው ይጣፍጣል፣

በዓሉ ይደምቃል፣

ሙዚቃው ያረካል፣

ጭፈራው ዘፈኑ ችግርን ያስረሳል።

እዚያ ዘመድ አለ፣

ሁሉም የናት ልጅ ነው፣

ሁሉም ያባት ልጅ ነው፣

ጠላትም አንዳንዴ ይመጣል መቃብር፣

ባለጋራም ቸር ነው “ያገር ልጅ ሲቸገር” ፤

ገነት ነው አገሬ።

ምነው ምን ሲደረግ ?

ምነው ለምን እንዴት ?

ዘራፊ ቀማኛ ምቀኛ ወንበዴ፣

ጥርኝ አፈር በጁ ስንዝር ወሰን አልፎ፣

የተቀደሰውን ያፍሪቃ ላይ ደሴት፣

ባያገኝ ለማርከስ ጠላት ይመኝ እንዴት።

እምቢኝ አሻፈረኝ፣

አሻፈረኝ እምቢ፣

መቅደስ ነው አገሬ፣

አድባር ነው አገሬ፣

እናትና አባት ድኸው ያደጉበት፣

ካያት ከቅደም አያት የተረካከቡት፣

አፈር የፈጩበት፣

ጥርስ የነቀሉበት።

አገሬ ዓርማ ነው፣ የነጻነት ዋንጫ፣

በቀይ የተጌጠ ባረንጓዴ ቢጫ።

እሾህ ነው አገሬ፣

በጀግናው ልጅ አጥንት የተከሰከሰ፣

ጠላት ያሳፈረ አጥቂን የመለሰ።

አገሬ ታቦት ነው ፣ መቅደስ የሃይማኖት፣

ዘመን የፈተነው በጠበል በጸሎት።

ለምለም ነው አገሬ፣

ውበት ነው አገሬ፣

ብሞት እሄዳለሁ ከመሬት ብገባ፣

እዚያ ነው አፈሩ፣ የማማ ያባባ።

ስሳብ እሔዳለሁ ቢሰበርም እግሬ፣

አለብኝ ቀጠሮ ከትውልድ አገሬ።

አለብኝ ቀጠሮ

ከትውልድ አገሬ፣

ካሳደገኝ ጓሮ።
ቦቹ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 357
Joined: Fri Dec 31, 2004 1:26 am

Postby መራራ » Tue Nov 26, 2013 7:38 am

ዱላነቷ ላንቺ ትሁንልኝ ብዬ የሰደድኳት ፖስታ:
ኢላማውን መታች እንደ ኪሮስ ቴስታ:: :lol: :lol:
ያልሞተውን ጠቢብ ሁሌም ህያውን:
ግደይው የምባል ፌዴራል አልሆን:
ዳኘው ያስተማረሽ ሀ-ግስ እና ለ-ግስ:
አላርጂክ ሆኖብሽ: ሆነሻል ግብስብስ::
ንግስቷን ለማረም እንከን ለማውጣት:
ይቅደም! የ አበጀ ጎሹን ፊደሎች መብላት:: :lol: :lol:
ግዜ ተጋሩ እና እነ አይጋ ፎረም:
ይቀልሽ ይሆናል ስህተት ለ ማረም::
የ አንቺ በ ሆነው ድክ ድክ ባልሽበት:
በ ""ቦንቢ"" ጀምረሽ ""ጠጠው"" ባከልሽበት:
በዛው በጺልኛሽ ተንተባተቢበት:: :lol: :lol: :lol:

ተጻፈ: ቢያይ ነው የሚባለው እንጂ ብታይ አይባልም ብላ ልታርመኝ ለ ሞከረችው ሰማያዊ በጌ ክቡዬ ካርቦኔ:: :lol: :lol: :lol:

ከ: ንግስት መራራ::
ክቡራን wrote:ሀማል መራራ:- ለማስተካከል ያህል ነው ግጥም ብለህ የጫርከውን ..ነገር....
ሰለሞን ጠቢቡ የሳባ አማላይ..
ታምራት ጠቢብ ነው ባዮችን ቢያይ..

ነው የሚባለው ብታይ...አይባልም:: አንተ የጾታ ዲሲኦሬንትሽን ስላለብህ ሰለሞንም አለበት ማለት አይደለም:: ማን መሆንህን ለማሳየት ያህል ብቻ ነው:: ሰላሙን::

በልዕልት መራራ ስም የገባው ሀማል wrote:ሰለሞን ጠቢቡ የ ሳባ አማላይ:
ታምራት ጠቢብ ነው ባዮችን ብታይ:
የጥበብን ሚስጥር ምጡቅነቷን:
ላለማወቃቸው ሰም እና ወርቋን:
ታዝላቸው ነበር ""ጥበብ"" የሸማኔውን:: :lol: :lol: :lol:

ተጻፈ በ ልእልት መራራ:: መታሰቢያነቷ ለ ሳምራውው33 ትሁንልኝ:: :lol: :lol: ዱላነቷ ደግሞ ለ ካርቦንዬ :lol: :lol: :lol:

ክቡራን wrote:ጥበብ እኮ ታምራት ገለታንም ጠርታለች:: ዚቁ ያለው ግን ጥሪውን በመልካም ተግባር ላይ ማዋሉ ላይ ነው:: ""ያልቦካ ጸሎት ከመከራ አያድንም "" ዲሞጥሮስ የሚባለው አስተማሪዬ እኮ ነው::

እነሆ ጠቢባን ሆይ ተጠበቡ... ያላወቁቹ ደሞ እወቁ ወይም ደሞ ጠበብ መስሏቹ የዋጣችሁትን ቴትራ ሳይክሊን አስታውኩት :::: :D

መተሬ= ውርስ ትርጉም= ስናይፕር ተኴሽ :D

http://www.youtube.com/watch?v=t4iGx1z5gls
መራራ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 753
Joined: Sat Sep 25, 2004 9:58 am
Location: united states

Postby ዲጎኔ » Tue Nov 26, 2013 1:26 pm

ሰላም /አሻማ
ወገኔ ቦቹ ይህ ሀገራዊ ግጥም ድንቅ ነው::እስኪ እኔ ደግሞ ድሮ ክፍል ውስጥ የሰማሁት ሀገርኛ ግጥምን በራሴ አባባል ላስቀምጠው:-
ተናገር ሀውልት አክሱም ላይ ያለህው
እስከዛሬ ድረስ ብዙ ጉድ ያየህው
ግፈኛ ገዥዎች ሁሌ የታዘብከው
የህዝቦች ጥበብ ውጤት የሆንከው
እኒያ ህዝቦች ግን መች ተዘከሩ
ቡዳዎች ተብለው እየተወገሩ
ቀጥቃጭ ቆዳ ፋቂ እየተማረሩ
በጥበብ ስራቸው መቸ ተከበሩ
ይባስ ብሎ ያክፉ ወያኔ ሲልጠን
ሀውልቱ ለደቡቡ ምኑ ነው ሲለን
ለከፋፍል ለያባላን ሲጀነጅነን
እኛስ ማን ነን በጊዜ ነቄ አልን

እስኪ ደሞ ጥበብን በስእል እናናግር
የቢሾቱን ሜትር ለማ ጉያን እናክብር
ያኔ ለገባሮች ከትቦ ተሰቃይቶ ነበር
ጆሲ ፍቀድልኝ ጥበብ ለትግል ያብር
http://quatero.net/archives/26095

ቦቹ wrote:
ዲጎኔ wrote:ሰላም/አሻማ
ወገን ቦቹ ድሮ ለአዲስ አመት ይቀርቡ የነበሩ ዜማዎችን አስታወስከኝ:-
አስኮበለልኩዋት ያችን ልጅ
አባትዋ ከሰው ታሰርኩ እንጂ
እኔም ወድጄ እሷም ወድዳ
ብቻየን አየሁ የቁም ፍዳ
የሻማ እያሉ መንጋዱራ
በቃሪያ ጥፊ ፊቴ በራ
በከያኒ ጌጡ አየለ

አውሮፕላን መጣ እየገሰገሰ
በዘፈን አንደኛ ጥላሁን ገሰሰ

ከከያኒ ጥላሁን ዜማና ግጥሞች ግብረገብ ያለው እነሆ:-
የእውነትን መንገድ ተሳስቼ
ተቀጣሁ በውሸት ተመርቼ
እውነት ማሪኝ ብያለሁ
ይቅርታ እጠይቃለሁ
በሀሰት ለለወጧት እውነትን ባፋቸው
የቁምነገር አምላክ ይቅር ይበላቸው
የትግልና የከሴ/ከርቼሌ ጉዋዳችን ከያኒ ቶማስ አበበ እንዲህ ብሎ ነበር:-
አበባ ምንጣፉ የእኔም ድሪቶዬ
የገንዘቡ ካዝና የእኔም ስልቻዬ
እበላው እጠጣው እቀምሰው የለለኝ
ከርታታው ምስኪኑ ጭቁኑ ቶማስ ነኝ

ሰላም ዲጎኔ ዋርካን በግጥም ድባብ መተሀታል ግን ደስ ይላል:: ልብን ይመስጣሉ ግጥሞችህ ጭቁኑ ቶማስ ደግሞ ያሳዝናል ይቺ መከረኛ አገር መቼም ስንቱ ስንት ነገር አይቶባታል:: ለማንኛውም እኔ የግጥም የማንበብ ፍቅር እንጂ የመጻፍ ችሎታው የለኝምና ከተጻፉት መካከል አንደኛውን ለትዝታ መዝዤ ልጋብዝህ..........እንሆ በረከት

ሃ ገ ሬ
{ሰአሊና ገጣሚ ገብረ ክርስቶስ ደስታ}

አገሬ ውበት ነው፣

ለምለምና ነፋስ የሚጫወትበት፣

ፀሃይ የሞላበት፣ ቀለም የሞላበት።

አገሬ ቆላ ነው፣ ደጋ ወይና ደጋ፣

እዚያ ብርሃን አለ ሌሊቱ እስኪነጋ።

አገሬ ተራራ ሸለቆ ረባዳ፣

አገሬ ጅረት ነው ገደልና ሜዳ፣

ውበት ነው በበጋ ፀሃይ አትፋጅም፣

ክረምቱም አይበርድም፣

አይበርድም፣ አይበርድም።

አገሬ ጫካ ነው፣

እንሰሳት አራዊት የሚፈነጩበት፣

በወጥመድ ሳይገቡ ሳይነካቸው ጠላት።

እዚያ አለ ነፃነት፣

በሃገር መመካት፣

በተወላጅነት፣

በባለቤትነት፣

እዚያ አለ ነፃነት።

አገሬ ሃብት ነው፤

ጎመኑ ስብ ጮማ፣ ቆሎ ክትፎ ስጋ፣

ድርቆሹ ፍትፍት ነው፣ ቃሪያው ሙክት ሠንጋ፣

ጠጁ ነው ወለላ፣

ከኮኛክ ያስንቃል የመንደሩ ጠላ።

እህሉ ጣእም አለው እንጀራው ያጠግባል፣

ከቢራ ከሻምፓኝ ውሃው ይጣፍጣል፣

በዓሉ ይደምቃል፣

ሙዚቃው ያረካል፣

ጭፈራው ዘፈኑ ችግርን ያስረሳል።

እዚያ ዘመድ አለ፣

ሁሉም የናት ልጅ ነው፣

ሁሉም ያባት ልጅ ነው፣

ጠላትም አንዳንዴ ይመጣል መቃብር፣

ባለጋራም ቸር ነው “ያገር ልጅ ሲቸገር” ፤

ገነት ነው አገሬ።

ምነው ምን ሲደረግ ?

ምነው ለምን እንዴት ?

ዘራፊ ቀማኛ ምቀኛ ወንበዴ፣

ጥርኝ አፈር በጁ ስንዝር ወሰን አልፎ፣

የተቀደሰውን ያፍሪቃ ላይ ደሴት፣

ባያገኝ ለማርከስ ጠላት ይመኝ እንዴት።

እምቢኝ አሻፈረኝ፣

አሻፈረኝ እምቢ፣

መቅደስ ነው አገሬ፣

አድባር ነው አገሬ፣

እናትና አባት ድኸው ያደጉበት፣

ካያት ከቅደም አያት የተረካከቡት፣

አፈር የፈጩበት፣

ጥርስ የነቀሉበት።

አገሬ ዓርማ ነው፣ የነጻነት ዋንጫ፣

በቀይ የተጌጠ ባረንጓዴ ቢጫ።

እሾህ ነው አገሬ፣

በጀግናው ልጅ አጥንት የተከሰከሰ፣

ጠላት ያሳፈረ አጥቂን የመለሰ።

አገሬ ታቦት ነው ፣ መቅደስ የሃይማኖት፣

ዘመን የፈተነው በጠበል በጸሎት።

ለምለም ነው አገሬ፣

ውበት ነው አገሬ፣

ብሞት እሄዳለሁ ከመሬት ብገባ፣

እዚያ ነው አፈሩ፣ የማማ ያባባ።

ስሳብ እሔዳለሁ ቢሰበርም እግሬ፣

አለብኝ ቀጠሮ ከትውልድ አገሬ።

አለብኝ ቀጠሮ

ከትውልድ አገሬ፣

ካሳደገኝ ጓሮ።
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby ምክክር » Wed Dec 25, 2013 9:10 am

ሀገር

ክብሬ መመኪያዬ የቆዳዬ ቀለም:
መልኬ መለያዬ የተናኘ በደም::
ኢትዮጵያ ሀገሬ ሥሜ መጠሪያዬ:
ድጋፍ አለኝታዬ:
ምርኩዝ ከዘራዬ::

ልዩ ምልክቴ:
የኔ ማንነቴ:
እትብት ውልደቴ
ልጅነት ልደቴ:
ዞሮ መግቢያ ቤቴ::

ባዕድ አገር ሁኜ
በዕምባ ከማምባራቅ:
ጥሪኝ ወደ ምስራቅ:
እኔም እንደ ጸሐይ
ፏ ብዬ ልፈንጥቅ::

የስሜ መጠሪያ:
ዋሴ ነሽ ኢትዮጵያ::

ለሀገር ናፋቂዎች...ለሀገር ወዳዶች::
ምክክር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 326
Joined: Thu Jun 26, 2008 10:10 am
Location: Super Earth

Postby ዲጎኔ » Wed Dec 25, 2013 10:17 am

ሰላም ለጦቢያ እንመኝላት
የጋራ ሀገር የተፈጠርንባት
ምክክር ወገናችን የተቀኘላት
ምንም ብንርቃት በአካል
በክፉ ገዥዎችዋ ብንጣል
ሀገራችን ድጋፍ ያሻታል
የህዝቡ ጉዳይ ያገባናል
መጻኢ እድሏ እንዲሰምር
የነገ ትውልድ እንዲያምር
እስኪ ለበጎ ነገር እንጣር

ምክክር wrote:ሀገር
ክብሬ መመኪያዬ የቆዳዬ ቀለም:
መልኬ መለያዬ የተናኘ በደም::
ኢትዮጵያ ሀገሬ ሥሜ መጠሪያዬ:
ድጋፍ አለኝታዬ:
ምርኩዝ ከዘራዬ::

ልዩ ምልክቴ:
የኔ ማንነቴ:
እትብት ውልደቴ
ልጅነት ልደቴ:
ዞሮ መግቢያ ቤቴ::

ባዕድ አገር ሁኜ
በዕምባ ከማምባራቅ:
ጥሪኝ ወደ ምስራቅ:
እኔም እንደ ጸሐይ
ፏ ብዬ ልፈንጥቅ::

የስሜ መጠሪያ:
ዋሴ ነሽ ኢትዮጵያ::

ለሀገር ናፋቂዎች...ለሀገር ወዳዶች::
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby ምክክር » Sat Dec 28, 2013 7:57 amእንደ ንብ ሊቀስም ከሁሉም አበባ:
ዐይን ይንከራተታል ዉበትን ፈለጋ:
ከዉበቷ ጉያም በጭራሽ አይረጋ:
ሲዋልል ይወላል ከዚችም ከዚያች ጋ::

እምቡጥ ጽጌረዳ ጠምበለል ሸበላ:
ደምግባት ቁመና ማርሸት ወላል:
ሸጋ አገኘሁ ብሎ ዐይናችን አይሞላ:
እንዴት ነው 'ምንቀጣው አትይ ብለን ሌላ::

እውነቱን ልንገርህ ብትወድም ብጠላም:
ከአፈር በስተቀር ዐይንህን አይሞላም::

ዐይንዬ....
ምክክር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 326
Joined: Thu Jun 26, 2008 10:10 am
Location: Super Earth

Postby ዛቲ » Mon Dec 30, 2013 1:18 pm

የዋርካ ገጣሚያን እንደምን አላቹ
አዲስ ሰው እንግዳ ትቀበላላቹ
ስትገጣጥሙት ደስ ትላላቹ
ይመቻት ይመቻት ይመቻት ብዕራቹ
ድፍረት አትቁጠሩት ገጠምኩኝ ብላቹ
ከቻልኩት ብዬ ነው ጀባ ልበላቹ

ባለዋሽንቱ(ከቀያቸው ወጥተው ላልተመለሱት ትሁን[/u]

የዋሁ እረኛ ደጉ ባለ ዋሽንት
ከብቶቹን ኣማትሮ ከተራራው አናት
በዋሽንቱ ቃና እንዲያ ያንቆረቆረው
ከዳገት ቁልቁለት ከገደል ሸለቆው
እንሰማት ነበር ዋሽንቱ ስታዜም
አሁን ግን አጣነው ካፋፉ ላይ የለም
ማልደን ወጥተን ነበር ከሰማነው ብለን
በሃሴት ልንቀልጥ ከታዛው ስር ሆነን
በለምለም እንግጫ አክርማ ተነጥፈን
ከንጹህ ምንጭ ውሃ ቀድተን ተጎንጭተን
ዋ! ቀረን በምኞት አፋችን አፋሽጎ
የዋሽንቱን ቃና ሲያጣ እንዲያ ፈልጎ
ምን ቀረን እንበል ያላሰስነው መሬት
ወዴት ሄደ በሉ ደጉ ባለ ዋሽንት?
ዛቲ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 13
Joined: Thu Oct 03, 2013 12:59 pm

Previous

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 0 guests