ጣጥፈናል ተናግረናል ፡ ለማስረዳት ሞክረናል ፡ ከድጡ ወደ ማጡም እንዳይሆን መክረናል፡፡

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

Re: ጣጥፈናል ተናግረናል ፡ ለማስረዳት ሞክረናል ፡ ከድጡ ወደ ማጡም እንዳይሆን መክረናል፡፡

Postby ቆቁ » Wed Apr 04, 2018 12:26 pm

የ ጠቅላይ ሚንስትሩን ንግግር

እንደዚህ ዓይነት ንግግር የት ነው የሰማሁት ብዬ ሳስብ፡ ሳልም ፡ሳውጠነጥን ፡ዛሬ በድንገት ብልጭ ነው ያለብኝ

እናቴ ማህጸን ውስጥ ሆኜ ነበር ለካ ይህንን ነገር የሰማሁት !!!

አንድነታችን ልዩነታችን ነው ልዩነታችን አንድነታችን ነው ብዬ ነበር መሰለኝ እኔ ፈላስፋው ያን ጊዜ ሳልወለድ እናቴ ማህጸን ውስጥ ሆኜ!!


ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3854
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: ጣጥፈናል ተናግረናል ፡ ለማስረዳት ሞክረናል ፡ ከድጡ ወደ ማጡም እንዳይሆን መክረናል፡፡

Postby ቆቁ » Sat Apr 07, 2018 6:31 pm

ችግራችን ሶስት ነው ብሎ ነበር ፈላስፋው
1. የሚዲያ እርማጌዶን
2. የመሪዎቻችን የበስተሁዋላ ጣጣ
3. የተቃዋሚዎች መፍትሄ አልባ መንግስት

የሁለተኛውን ጣጣ ፈላስፋው ሲመረምረው ፡፡
መርዎች ወደ እርጅና ሲሄዱ ወይም ከስራቸው ሲፈናቀሉ ወዴት ይሄዳሉ የሚለው ጉዳይ ነው ፈላስፋው ያልገባው
እስከ ዛሬ ድረስ
ሐይለስላሴ ተገደሉ
መንግስቱ ተባረሮ ዚምባብውዌ ገባ
ጠቅላይ ሚንስቴር ታምራት በሙስና
ጠቅላይ ሚንስቴር መለሰ ዜናዊ ነፍሱን ይማረውና
አቶ ሐይለማርያም ስልጣናቸውን ለቀቁ
እንደዚህ እያለ ጉዞው ይቀጥላል
ሌሎችስ የድርጅት መሪዎች ወይም ሹማምንቶች ለምን ወደ ጡረታ አይሄዱም ?
የጡረታ አበላቸውን ተቀብለው መኖሪያ ቤት ተቀብለው ወደ ጡረታ ፡
በጡረታ አለም ብዙ የሚሰሩ ሕዝባዊ ነገሮች አሉ እኮ
ወደ ጡረታ መሄድ ትልቅ ነገር ነው
ለተከታዩ ትውልድ ቦታ መስጠት ነው የስራ እድል መክፈት ነው ፡ አዲስ ሐሳብ ማብቀል ነው ፡፡
ወደ ጡረታ !
አንድነታችን ልዩነታችን ነው ልዩነታችን አንድነታችን ነው
ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3854
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: ጣጥፈናል ተናግረናል ፡ ለማስረዳት ሞክረናል ፡ ከድጡ ወደ ማጡም እንዳይሆን መክረናል፡፡

Postby ቆቁ » Sat Apr 21, 2018 2:13 pm

ማመልከቻ
1. በፈቃዳችሁ ወደ ጡረታ ለመሄድ ያሰባችሁ መሪዎቻችቻን እንዲህም የድርጅት መሪዎችችንና አባላቶች
2. በመንግስት ወደ ጡረታ እንድትጉዋዙ የተደረጋችሁ መሪዎቻችን እንዲሁም የድርጅት መሪዎችና አባላቶች
3. እሁን በስራ ላይ የምትገኙ የመንግስት ተወካዮችና የድርጅት አባላት
4. በተለይ ለዶክተር ዓቢይ

አንደኛ ፡ እስከ ዛሬ ድረስ እንደተመለከትነው የጎሳ ፖለቲካ ለኢትዮጵያ ሐገራችን መፍትሄ አልሆነም
ቁዋንቁዋ ለማዳበር ባህል ለማዳበር የጎሳ ፖላቲካ መፍትሄ አይደለም ፡፡
ይህንን ለመሞከር ሌላ 30 ዓመት ላቦራቶሪ አያስፈልግነም፡፡
ወይም ቁዋንቁዋ ፡ ባህል በጌቶ ወይም ዓለም በቃኝ መታፈን የለበትም

ሁለተኛው ፡ በመድበለ ፓርቲ ቁዋንቁዋ ይዳብራል ፡
ባህል ይዳብራል፡
ተከባብሮ መኖር ብቻ ነው የሚያስፈልገው
የትግራዩ ተወላጅ ኦሮምኛ እንዲማር ፡
የኦሮሞው ትግሪኛ ፤
ወይም የአፋሩ አማርኛ
የወላይታው ጉራጌኛ እንዲማርና እንዲናገር ፍቅር ዝምድና የሚያመጣ የፖለቲካ መሰረት ነው

ሶስተኛ በመድበለ ፓርቲ ፡ አንድነታችን ልዩነታቻን ነው ልዩነታቻን አንድነታችን ነው የሚለው ትልቁ ኢትዮጵያዊነት የሚተረጉመበት የፖለቲካ መሰረት ነው

ምን አጠፋሁ ?
ፈላስፋው ቆቁ
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3854
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: ጣጥፈናል ተናግረናል ፡ ለማስረዳት ሞክረናል ፡ ከድጡ ወደ ማጡም እንዳይሆን መክረናል፡፡

Postby ቆቁ » Tue Jun 12, 2018 7:13 pm

ጮኸን ነበር
እሪ ብለን ነበር
እረ ተዉ ታሪክ አታበላሹ ብለንም ነበር
ባልሆነ ነገር ቢሰበሰቡት ፡ ቢነታረኩት የትም የሚያደርስ ነገር የለም ብለንም ነበር
ታዝበንም ነበር ፡ አስተያየትም ሰጥተን ነበር
አታውቁም ተብለን ያልተጻፈ ታሪክ እንድናነብ ተደርገንም ነበር
ስለ ኢትዮጵያዊነታችንም ሊያስረዱን ሊያስተምሩን ሞክረው ነበር ፡
ስለ ሐይማኖታችን ሊነግሩን ሊሰብኩንም ተንጠራርተው ነበር
ለማንነታችን መታወቂያ ሰጥተውን ነበር
ከድጡ ወደ ማጡ እንዳይሆን ተናግረን ነበር ?????
የኢትዮጵያ አንድነትና ልዩነት ለዘላለም ይኑር
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3854
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Previous

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests