ኢትዮጲያ የሚል ሁሉ የኢትዮጲያዊነት ተሃድሶን ይደግፍ

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ኢትዮጲያ የሚል ሁሉ የኢትዮጲያዊነት ተሃድሶን ይደግፍ

Postby እሰፋ ማሩ » Fri May 04, 2018 12:21 pm

የዶ/ር አብይ ቀናኢነትና የአንድነት ኃይሉ ማፈግፈግ; ስለአንዳርጋቸው መጮህና ምፀቱ! (በመሃመድ አሊ )
May 4, 2018
(በመሃመድ አሊ )
የአል-በሽር ምላሽና አንደምታው;

የዶ/ር አብይ ቀናኢነትና የአንድነት ኃይሉ ማፈግፈግ;

ስለአንዳርጋቸው መጮህና ምፀቱ!“የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን እስረኞች እንዲለቀቁ ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት የሃገሪቱ ፕሬዝዳንት ኦማር ሃሰን አልበሽር ኢትዮጵያዊያኑ እንዲፈቱ ወሰኑ”

ይህ ዜና በሁሉም ብዙሃን መገናኛዎች እየናኘ ሲሆን ድብቅልቅ ያለ ስሜት ፈጥሮብኛል። በአንድ በኩል ከቤተሰብና ከዘመድ ርቀው በሰው አገር እሥር ቤት ሲማቅቁ የነበሩ ወገኖቻችን በመፈታታቸው ተደስቻለሁ። ዶ/ር አብይ አህመድም ከተለመደው ዲፕሎማሲያዊ የቃላት ጨዋታ ባለፈ በእሥር ላይ ለነበሩ ወገኖቻችን ትኩረት ሰጥተው ጥያቄውን ማቅረባቸው; እንዲሁም የሱዳኑ ፕሬዝዴንት ሀሰን ዑመር አልበሽር ጥያቄውን ተቀብለው አፋጣኝ ውሳኔ መስጠታቸው አስደምሞኛል።

በርግጥ የሱዳን መንግሥት ቀደም ብሎ በሀገሩ ያሠራቸውን የፖለቲካ እስረኞች ሙሉ በሙሉ መፍታቱን ሰምተናል። በአንፃሩ የኢትዮጵያው ገዥ ፓርቲ ኢህአዴግ የፖለቲካ እስረኞችን ሙሉ ለሙሉ ለመፍታት መወሰኑን ቢያበስረንም የነፃነት ታጋዩን አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ጨምሮ በርካታ የፖለቲካ እስረኞች እስካሁን ድረስ በእሥር ቤት እየማቀቁ ነው።

እዚህ ላይ አነጋጋሪው (ironic) ጉዳይ ዶ/ር አብይ የኢትዮጵያ መሪ ሆነው አገራቸው ላይ መፈፀም ያልቻሉትን የጎረቤት አገር መሪ ተማፅነው ማስፈፀም መቻላቸው ነው። ከዚህ ተነስተን ዶ/ር አብይ እንደ አንዳርጋቸው ፅጌ ያሉ አገር ወዳድ ዜጎች የበቀል ፖለቲካ ሰለባ መሆናቸው ሳያሳስባቸው ቀርቶ ነው? ወይስ እንደ ሱዳኑ መሪ የመወሰን ሥልጣን የላቸውም? የሚል ጥያቄ ለማንሳት እንገደዳለን።

ሰሞኑን ከቤተ-መንግሥት አካባቢ እንደተናፈሰው ወሬ ከሆነ ዶ/ር አብይ ራሳቸው የበቀል ፖለቲካው ሰለባ ከመሆን ለትንሽ ነው የተረፉት። ስለሆነም ሀገርን መውደድና ከሥርዓቱ የተለዬ አቋም መያዝ ምን ያህን ዋጋ እንደሚያስከፍል ከዶ/ር አብይ በላይ ማን ምስክር ሊሆን ይችላል? ሀቁ ይኸ ከሆነ የዶ/ር አብይ መንግሥት እነ አንዳርጋቸው ፅጌን የማይፈታው ለምንድነው? ምንስ እስከሚሆን ነው የሚጠበቀው?

ከዚሁ በተጓዳኝ ዶ/ር አብይ ኢትዮጵያዊነትን ለመስበክና በዚህ ዙሪያ ገዥ አስተሳሰብ ለመፍጠር የሚያደርጉትን ጉዞ ቀጥለው አሶሳ ላይ ህዝብን ሲያወያዩ በሌላ በኩል የአማራ ተወላጅ የሆኑ ዜጎች ከቤኒሻንጉል ክልል እንዲወጡ እየተደረገ ነው። ዶ/ር አብይ የኢትዮጵያዊነትን አስተሳሰብ ከላይ ለመደረብ ሲታገሉ ጠባብ ብሔርተኞች ከሥር እርቃኑን እያስቀሩት ነው። የነዶ/ር አብይን ተነሳሽነት አፈር ለማልበስ እርምጃቸውን እየተከተሉ ከሥር ከሥር ጉድጓዳ የሚምሱትና አካፋና ዶማ የሚያቀብሉት እነማን ናቸው?

በዚህ ሁኔታ TeamLemaና ዶ/ር አብይ የሚያቀነቅኑት ኢትዮጵያዊነት ዕጣ ፈንታው ምን ይሆናል? በተለምዶ የአንድነት ኃይል ሲባል የነበረው የማህበረሰብ ክፍል የነለማን ቅን ተነሳሽነትና ገንቢ ትርክት (constructive rhetoric) በወጉ ማስተጋባትና ማበረታታት ለምንና እንዴት አቃተው? ወይስ አጥብቆ ያልያዘውን የአንድነት አስተሳሰብ እንደዋዛ ተነጠቀ?

በሌላ በኩል የትግራዩ ጠባብ ብሔርተኛና መሰሎቹ ይዘውት የተነሱት አስተሳሰብ አሸናፊ ሆኖ እየወጣ ይሆን? የሚል ጥያቄ ማንሳትም ምክንያታዊ ነው። ሁሉም የየራሱን ሰበብ (excuse) በማበጀት ጠባብ ብሔርተኞች በቀደዱት ቦይ የሚፈስ ከሆነ ወደፊት ህወሓትንና የአስተሳሰቡን አቀንቃኞች መክሰስና መውቀስ የሚቻልበት መነሻ (ground) አይኖርም።

በዚህ መሐል የአያት ቅድመ-አያቶቻችንን ውለታ አፈር በላው። ወይም ደግሞ ትውልዱ የአያት ቅድመ-አያቶቹን “አደራ እየበላ ነው” ማለት ይቻላል። ይህች ሀገርኮ በጀግኖች አያት ቅድመ-አያቶቻችን አጥንትና ደም የተገነባች ናት። ለዚች አገር አንድነትና ነፃነት ሲባልኮ ብዙ ደም ፈስሷል; አጥንት ተከስክሷል። ዛሬ ላይ በጠባብ ብሔርተኝነት ስሜት ተሸብበን በአያት ቅድመ-አያቶቻችን መቃብር ላይ ሽምጥ እየጋለብን ነው። ግን የጆግኖቻችንን አፅም እየረገጥን እንዴት ነው የምንዘክራቸው?

ባይሰማን እንጅ ደማቸው ይጮህ; ነፍሶቻቸው ይጣሩና አጥንታቸውም ይወቅሰን ይሆናል። ለእኛ ግን ዛሬ ላይ ይኸ ሁላ ምናችንም አይደል! እነሱ የገነቡትን ማፍረስና ህልምና ራዕያቸውን ማጨንገፍ የቁልቁለት መንገድ ነው። እስቲ የሩቁን እንተወውና ኢትዮጵያን አንድ ለማድረግ የተነሳው ቴወድሮስ ህልሙ ምን ነበር? ዮሃንስ መተማ ላይ አንገቱን የሰጠው ለምን ነበር? እምዬ ምኒልክ ዕድሜውን ሙሉ የኳተነው ለምን ነበር? የነራስ አሉላ; ባልቻ አባነፍሶ; በላይ ዘለቀ. .. ህልምና ምኞት ምን ነበር?

ከዚያስ ወዲህ ስንቱ ጀግና ጎበዝ “ኢትዮጵያ ወይም ሞት” ብሎ; ፎክሮና አንጎራጉሮ ክንዱን ተንተራሰ? ስንቱ ቤቱን ዘግቶ እንደወጣ ቀረ? በምሥራቅ; በምዕራብ; በደቡብ; በሰሜን ስንት ደም ፈሰሰ? ዛሬም ቢሆን ብዙዎች የሀገር ፍቅር ዋጋ እየከፈሉ ነው።

እስቲ አንዳርጋቸው ፅጌን እናስበው? አንዳርጋቸው ዕድሉን ቢያገኝ “አደራው” ምን ሊሆን ይችላል? ለምንድነው ይህን ሁሉ መከራና ስቃይ የሚቀበለው? ጊዜው ሲደርስ ራሱ ይነግረናል።

“ላንች ነው ኢትዮጵያ” እያለ ይዘምርልናል።

አንዳርጋቸውን ከቆመለት ክቡር ዓላማ ለይቶ መውደድ አይቻልም። የአንዳርጋቸውን አደራ ደጋግመን ብንጠይቀው “ኢትዮጵያን. ..” የሚል ይመስለኛል። የአንዳርጋቸውን አደራ ቅርጥፍ አድርጎ በልቶ ስለአንዳርጋቸው መጮህ አጉል ምፀት ነው።

ይሁንና አንዳርጋቸውን ፍቱት!!!
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1530
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm

Re: ኢትዮጲያ የሚል ሁሉ የኢትዮጲያዊነት ተሃድሶን ይደግፍ

Postby ቢተወደድ1 » Fri May 04, 2018 1:57 pm

የእንዳርጋቸው ጉዳይ እንተ በምታይበት እይን እይደለም የሚታየው፡፡ ለማንኛውም በሰፊው ለመነጋገር በአንድ ወቅት ምን ነበር ያለው?
ኢትዮጵያ ውስጥ የምንመሰርተም መንግስት የመለስ ሬሳ ከተቀበረበት አውጥተን መንገድ ላይ ነው የምንጎትተው ማለቱ የትናንት ትውስታችን ነው፡፡ ከማንስ ጋር ነበር ሲያብር የነበረው? በጭፍን ባትነዳ ይበጅሃል፡፡ ለማንኛውም በተጀመረው አዲስ ጅማሬ የሚታይ ነው፡፡ ለሰላም ጥረት የሚታገል ከሆነ እሱም ቢሆን የማይፈተበት ምክንያት እይታየኝም፡፡
ለትውስታ፤ ከኢሓዴግ ጋር እብሮ በሚሰራበት ወቅት ስንት ሰው ያሰቃይ እንደነበረ እናንተ ማስታወስ እትፈልጉም፡፡ ኤርትራ ላይ በሁለት የግም ቦት አባሎች ለምን ይሆን የተደበደበው?
አይ የናንተ ሂሮ!!!
ቢተወደድ1
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 221
Joined: Thu Sep 01, 2016 8:48 am
Location: Bisheftu

Re: ኢትዮጲያ የሚል ሁሉ የኢትዮጲያዊነት ተሃድሶን ይደግፍ

Postby እንድሪያስ » Thu May 17, 2018 12:48 pm

የአህያ ባል ከጅብ አያስጥል አይነት ነው የአንድነት ኃይል ተብየው ነገር። መጀመሪያ አካባቢ የእንግሊዝ ዜጋ ነው ድፍረት ነው በአስቸኳይ መፈታት አለበት ተባለ ስሚ አልተገኘም ምክንያቱም የእንግሊዝ ዜጋ ሆኖ ኤርትራ ውስጥ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ የሆነ ሽምቅ ተዋጊ ሃይል መሪ ሆኖ መገኘት ለህወሓት ምቹ ሁናቴን የፈጠረ ነውና። ሁለተኛ መለስን ከመቃብር አውጥቼ አደባባይ ላይ እጥለዋለሁ ብሎ ተናግሮ ብዙ ሳይቆይ እጃቸው ላይ ወደቀ....እግዜር ይርዳው።
እንድሪያስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1784
Joined: Fri Mar 19, 2004 10:55 pm
Location: *****

Re: ኢትዮጲያ የሚል ሁሉ የኢትዮጲያዊነት ተሃድሶን ይደግፍ

Postby ኳስሜዳ » Thu May 17, 2018 1:43 pm

የህዝብን ትግል የሚቋቋም ምንም ሓይል የለም፣ ወደድክም ጠላህም ወያኔ፡ አንዳርጋቸውን ሳይወድ በግዱ ይፈታዋል፣ እንዳለውም መለስን ከመቃብር አውጥቶ አደባባይ ይጥለዋል፣ የሽምቅ ውግያውም ፍሬ ያፈራል፡፡
እንድሪያስ wrote:የአህያ ባል ከጅብ አያስጥል አይነት ነው የአንድነት ኃይል ተብየው ነገር። መጀመሪያ አካባቢ የእንግሊዝ ዜጋ ነው ድፍረት ነው በአስቸኳይ መፈታት አለበት ተባለ ስሚ አልተገኘም ምክንያቱም የእንግሊዝ ዜጋ ሆኖ ኤርትራ ውስጥ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ የሆነ ሽምቅ ተዋጊ ሃይል መሪ ሆኖ መገኘት ለህወሓት ምቹ ሁናቴን የፈጠረ ነውና። ሁለተኛ መለስን ከመቃብር አውጥቼ አደባባይ ላይ እጥለዋለሁ ብሎ ተናግሮ ብዙ ሳይቆይ እጃቸው ላይ ወደቀ....እግዜር ይርዳው።
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2149
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Re: ኢትዮጲያ የሚል ሁሉ የኢትዮጲያዊነት ተሃድሶን ይደግፍ

Postby እሰፋ ማሩ » Thu May 17, 2018 2:18 pm

ወገኖች በቅርቡ የሃገር ቤት ታጋዮቻችን የተፈቱት በፈጣሪ ጣልቃ ገብነት በህዝባችን በተለይ በቄሮዎችና ፋኖውች ትግል ነው፡፡አንዳርጋቸው ልክ እንደዶ/ር አብይ ወያኔን በትግል ተቀላቅሎ የሚሰሩትን ግፍ በማየት የተለየና የትጥቅ ትግል የጀመረ ሲሆን ዶ/ር አብይ ግን አብሮ ቆይቶ በዘዴ በውስጣዊ ትግል ለውጦችን ለህዝባችን በማሳየት ላይ ያለ ነው፡፡በዶ/ር አብይ አመራር አንዳርጋቸው ሊፈታ የሚችለው በግንቦት ሰባት ትግል ያለመሆኑን ማንም ይመስክራል፡፡ ያኔ ከቅንጅቱ ብዙሃን ተነጥሎ ፋይዳ ለማይሰጥ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባነት ልግባ ያለው ዶር ብርሃኑ ትግሉ በግንቦት ሰባት ነው ያለውን መቀበል ያስቸግራል፡፡ስለዚህ ከውጭ ሆነነ ተጨማሪ ወጣት የሚያልቅበትን ቅስቀሳ አቁመን በተጀመረው ወያኔ ሳይወድ በህዝቡ ትግል የተቀበለውን ለውጥ ተጠቅመን የወያኔን ግፍ ስርአተ ቀብር እናፍጥን፡፡

ኳስሜዳ wrote:የህዝብን ትግል የሚቋቋም ምንም ሓይል የለም፣ ወደድክም ጠላህም ወያኔ፡ አንዳርጋቸውን ሳይወድ በግዱ ይፈታዋል፣ እንዳለውም መለስን ከመቃብር አውጥቶ አደባባይ ይጥለዋል፣ የሽምቅ ውግያውም ፍሬ ያፈራል፡፡
እንድሪያስ wrote:የአህያ ባል ከጅብ አያስጥል አይነት ነው የአንድነት ኃይል ተብየው ነገር። መጀመሪያ አካባቢ የእንግሊዝ ዜጋ ነው ድፍረት ነው በአስቸኳይ መፈታት አለበት ተባለ ስሚ አልተገኘም ምክንያቱም የእንግሊዝ ዜጋ ሆኖ ኤርትራ ውስጥ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ የሆነ ሽምቅ ተዋጊ ሃይል መሪ ሆኖ መገኘት ለህወሓት ምቹ ሁናቴን የፈጠረ ነውና። ሁለተኛ መለስን ከመቃብር አውጥቼ አደባባይ ላይ እጥለዋለሁ ብሎ ተናግሮ ብዙ ሳይቆይ እጃቸው ላይ ወደቀ....እግዜር ይርዳው።
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1530
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests