ባንድ ሃገር ሁለት መንግስት!

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ባንድ ሃገር ሁለት መንግስት!

Postby ኳስሜዳ » Wed May 09, 2018 3:36 am

Image
የዐቢይ ያለህ ፤! የመሪያችን ያለህ ፣! የጠቅላይ የጦር አዛዦች ያለህ፤! ኧረ አለቅን የትግሬ ማፊያ ቡድን ጨረሰን ።

የስቃይ ማማ በሆነው ማዕከላዊ እንዲሁም በሌሎች የወያኔ ማሰቃያ ቤቶች ጥፍር ይነቀላል ወንዶች ብልት ላይ ሃይላንድ ይንጠለጠላል ሴቶች ይደፈራሉ ልብሳቸውን እንዲያወልቁ ይደረጋሉ ለመስማት እሚሰቀጥጥ ብዙ ስቃዮች በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ነው ስንል በተደጋጋሚ ውሸት ነው ሲል መንግስት ነኝ ብሎ ራሱን እሚጠራው አካል ሲያስተባብል ኖሯል፣

ይኸው ዛሬ የመንግስት ልሳን በሆኑት ዳኞች ይህ ተረጋግጧል "በቂሊንጦ እሳት የተከሰሱት 38ቱ ተከሳሾች በተደጋጋሚ ጊዜ ኢሰብአዊ ድርጊት እየደረሰብን ነው ብለው ለፍ/ቤቱ ባቀረቡት አቤቱታ ምክንያት ለማጣራት እንደሞከርነው ጥፍራቸው የተነቀለ በሚስማር የተበሱ የተለያዩ ድብደባ የደረሰባቸው በዛም ምክንያት የተሰበሩ የተጎዱ ሰዎች እንዳሉ አረጋግጠናል" ብለው ለችሎቱ አሳውቀዋል፣

ይሄንስ ምን ብላችሁ ማስተባበያ ትሰጡበት ይሆን?? መቼም ዛሬም አንባገነኑ ደርግ ምናምን እያላችሁ እንደለመዳችሁት አትቀልዱብንም፣

በዚህ መልኩ የተጀመረው ችሎት አጨራረሱ ግን አሰቃቂ ነበር የጎንደሩ አንጋውና የአየር ሃይሉ ሰይፈን ጨምሮ 8 ልጆች በነፃ የተሰናበቱ ሲሆን ፍቅረማርያም ማስረሻ ዶ/ር ፍቅሩ እንዲሁም አግባውን ጨምሮ 26 እሚሆኑት አንቀፃቸው ከሽብር ወጥቶ ወንጀል ላይ ገብቷል፣

በጣም አሳዛኙ ከፖለቲካ ውጭ ያሉትን በሌላ ወንጀል የተከሰሱትን ልጆች በከባድ ነፍስ ማጥፋት ወንጀል እንዲከላከሉ ተወስኖባቸዋል፣

እንግዲህ እስከዛሬዋ ቀን ድረስ በዚህ ክስ በዋነኝነት ተጠያቂ የነበሩት የኞዎቹ ሽብርተኛ ጓደኞቻችን ነበሩ ሆኖም በዛሬዋ ቀን ጓደኞቻችንን እንዲሁም ዶ/ር ፍቅሩን ከከባድ ሽብር ወንጀል አውጥተው በእስር ቤት ውስጥ የማምለጥ የማደራጀት ሙከራ ውስጥ ከተዋቸዋል ምክንያቱም አነሰም በዛ እነዚህ ልጆች እሚጮህላቸው ሰው ስላለ በነፍስ ማጥፋቱ ወንጀል እነዚህን ለመክሰስ አልተመቻቸውም፣

አሁን እዳውን ሁሉ ያስረከቧቸው ልጆች ግን ከቤተሰቦቻቸው ውጪ ማንም ጠያቂ የላቸውምና ይህን በሀሰት የተቀነባበረ ክስ መጨረሻ ላይ እነዚህ ምስኪኖች ላይ አርፏል፣

ከነዚህ መሃል አንዱ ተነስቶ ነው እንግዲህ ስሜቱን መቆጣጠር አቅቶት እናንተ አቃጥላችሁ በቀበራችሁት ለዛውም የሰፈሬ ልጅ አብሮ አደግ ወንድሜን ገደለ ብላችሁ ተከላከል እምትሉኝ ህሊና የላችሁም እያለ ፍትህን ሲለምን ሱስ አይለቅም እና የለመደ እጅ የመሳርያውን ቃታ ለመሳብ ያቀባበለው፣

በጣም በፍጥነት ፌደራል እና አዲስ አበባ ፖሊስ ችሉቱን ሞልተው በመሳሪያ ማቀባበል ድምፅ ችሎቱን በሽብር አናወጡት ወዲያው ትርምስ እና ግፊያ ሆነ፣

ፖሊሶቹ የተቀባበለ መሳሪያቸውን እስረኞቹ ላይ ደግነው ዱላ ጀመሩ ይህን ሲያይ ቤተሰብ ስሜቱን መቆጣጠር አልቻለም እና ብዙ እናቶች እና እህቶች ራሳቸውን ሳቱ የቀረነው በእንባ እየተራጨን ከችሎት እየተገፈተርን እንድንወጣ ተገደደን፡፡

ዳኞቹም ችሎቱን እንኳን ሳይዘጉ በድንጋጤ ወደውስጥ ዘልቀዋል!!!!!
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2149
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 3 guests