ቄሮዎች የሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ማውጫ የሆነ የመብራት እና ውሐ መስመር በመሉ ቆረጡ

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ቄሮዎች የሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ማውጫ የሆነ የመብራት እና ውሐ መስመር በመሉ ቆረጡ

Postby ኳስሜዳ » Wed May 09, 2018 2:38 pm

Image
በጉጂ ዞን ቄሮዎች የሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ማውጫ መጠቀሚያ የሆነ የመብራት እና ውሐ መስመር መሉ በመሉ ቆርጠዋል።

መንገድ መሉ በሙሉ ዘግተዋል። በአሁን ሰዓት ወደ ማዕድን ቦታ በሺዎች የሚቆጠሩ ቄሮዎች ቦታውን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር እየገሰገሱ ነው።

በህጋዊ መልኩ ጥያቄ ጠይቀን መልሱ ግድያ ከሆነ የማዕድን ቦታ ሄደን ተቆጣጥረን እዛው ላይ እንሞታለን ግድያ እና እስር ማስፈራራያ እኛን አያቆመንም። የሚል መፎከር እያሰሙ በሞራል መንገድ በመዝጋት ውሐና መብራት በማቋረጥ ወደ ማዕድኑ ማውጫ ዘምተዋል ።

በኦሮሚያ ክልል የጉጂ ዞን ህዝብ የሚድሮክ የወርቅ ማዕድን ኩብኒያ እያደረሰ ያለውን የጤና ጉዳት በመቃወም ከ 20 አመታት በኋል ያበቃለት ኮንትራት እንዳይታደስ የተቃውሞ ሰልፎች እይደረገ መሆኑ ይታወቃል። ግዢው ፓርቲ የህዝቡን ጩኸት ሰምቶ እርምት ከማድረግ ይልቅ በወታደሮቹ በኩል በሰላማዊ ሰልፍኞች ላይ ተኩስ በመክፈት ህይወት መቅጥፍን እና አካልን ማቁሰልን መርጧል።
Image
በዛሬው እልት እንኳን ሻኪሶ ጉታ የተባለን ነጋዴ መኪና እየነዳ ወደ አዶላ ከተማ እየተጓዘ ሳል ወታድሮች የተኩስ እሩምታ አውርደውበት በግፍ ገድለውታል። ህዝቡም ቁጣው እያየለ በመምጣት ወደ ማዕድኑ የሚያገባውን የኤሌክትሪክ ምሰሶ በመገንደስ የማዕድን ፍብሪካው ስራ እንዲያቆም አስገዶዶታል። መንግስት በአፋጣኝ የሜድሮክን ኮንትራት ካልሰረዘ ይህተቃውሞው ወደ ሁሉም የኦሮሚያ ዞኖች መስፋፋቱ አይቀሬ ነው።
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2149
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 4 guests