ከዶ/ር አብይ መሾም በኋላ የሀገራችን ፖለቲካ በ2 ምክንያቶች በጣም ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚሻው ነው

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ከዶ/ር አብይ መሾም በኋላ የሀገራችን ፖለቲካ በ2 ምክንያቶች በጣም ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚሻው ነው

Postby ኳስሜዳ » Tue May 22, 2018 1:40 pm

ፕሮፌሰር ብርሐኑ ነጋ!!!
አንደኛ ፡ ዶክተር አብይ በቃላት ደረጃ ለማድረግ እፈልጋለሁ የሚሏቸው ነገሮች አብዛኛዎቹ እኛም የምንፈልጋቸው እና እስከ ዛሬ የታገልንላቸው አላማዎቻችን ስለሆኑ የሚሉት የምራቸውን ከሆነ እንዲሳካላቸው ከልብ መመኘት ብቻ ሳይሆን በተቻለን መጠን ልናግዛቸው እንፈልጋለን። እኛ እነኚህን ውጤቶች ነው እንጂ የምንሻው የግድ እኛ ካላመጣናቸው አንልም። እንደ ድርጅት እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲመጣ የማገዝ እንጂ ስልጣን የመያዝ ፍላጎት ኖሮን አያውቅም። በርግጥም ይህን የሚጠራጠሩና መጠራጠርን ብቻ በራሱ ትልቅ የፖለቲካ እውቀት አድርገው የሚያዩ ሀይሎች እንዳሉ እናውቃለን። እነሱ ተጠራጠሩም አልተጠራጠሩም ግን በድርጅታችን ውስጥ ስር የሰደደውና በፍጹም የማያወላውለው ዕምነታችን ይኸው ነው።

በሌላ በኩል ፡ ግን አሁን ያለውን የፖለቲካ ኃይል አሰላለፍ ከስሜት በወጣ መንገድ ካየነው ከመጀመሪያው ቢሆንስ (እውነተኛ የዴሞክራሲያዊ ሽግግር) ይልቅ የሁለተኛው ቢሆንስ (ጥገናዊ ለውጥ)እውን የመሆን እድሉ ከፍተኛ ነው። ዶክተር አብይ ወደ ጥገናዊ ለውጥ እያመሩ ላለመሆኑ ማረጋገጫ ማግኘት እንሻለን። ጥገናዊ ለውጥ ውሎ አድሮ ወደ ትርምስ እና እልቂት ይወስደናል እና ይህንን መፍቀድ አንችልም።

እነኚህ ሁለት ሁኔታዎች ተቃራኒዎች በመሆናቸው በከፍተኛ ጥንቃቄ መራመድ ይኖርብናል።
https://www.youtube.com/watch?time_cont ... lXl35RMqok
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2155
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Re: ከዶ/ር አብይ መሾም በኋላ የሀገራችን ፖለቲካ በ2 ምክንያቶች በጣም ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚሻ

Postby አባዊርቱ » Fri Jun 01, 2018 5:29 pm

ይህ ሙከራ ነው. እላችሁ ወገኖች???
አባዊርቱ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 800
Joined: Mon Feb 23, 2004 4:11 am

Postby እንድሪያስ » Mon Jun 11, 2018 9:10 pm

አባዊርቱ የጥዋቱ የጥንቱ......
ዋርካዎች እንደምን አላችሁ ?
እንድሪያስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1784
Joined: Fri Mar 19, 2004 10:55 pm
Location: *****

Re: ከዶ/ር አብይ መሾም በኋላ የሀገራችን ፖለቲካ በ2 ምክንያቶች በጣም ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚሻ

Postby አባዊርቱ » Thu Jun 14, 2018 6:34 pm

ሰላም ወገኖቼ እንደገና!!
እንዴት ነህ እንድርያስ የጥንቱ አርበኛ
ምህረትን የማታቅ የብ እር ጀብደኛ!
ሄሄሄ
ልብህ እያወቀ ተያይዘህ እልህ
እንዲያ ስታደብነው ሞቶ አረፈልህ
መቸስ ወርቅነህን ታስታውሰዋለህ።፧

ይህን ካልኩኝማ ይድረስህ ሰላምታ
አምላክ ይጠብቅህ ባለህበት ቦታ!!
እንደው ቂም ይዤብህ እንዴት ነህ ማለቱ
ከብዶኝ ነው እንድርያስ ይቅርታ በውነቱ።

ይድረስ ሰላምታዬ ለሁሉ ካንጀቴ
ቴዲ ሳልሳዊ ዋቆና ኮኮቴ
አንቺሆዬ ቆቁ መንጌና ዳሞቴ
ጀግናው አባፈርዳ ወይንም ናፍቆቴ!!!

አቤት የዛን ጊዜ ያቦካነው ሁላ
አወይ የድሜ ነገር ወጣልን አውላላ።

የዛሬው “ጫወታ” አለው አንድ ነገር
“እብረት ያ ቶኩማ” ብለንም አልነበር?!!!
ሰሚ አጣን እንጂ እነ “ወይኔ” መንደር።
እናማ እንድረያስ ጤናውን ሁንልኝ
አስቀይሜ እንደሆን ይቅርታም አርግልኝ
ሰሞኑን ብቅ ብዬ የምልህ አንድ አለኝ።
እናም!
መለዮ ክፍ አርገው ሚሰናበቱቱ
የጥንቱ አርበኛ፣ ዛሬም ብርቱ ናቸው ኤታማዦር ዊርቱ!!!፡)
አባዊርቱ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 800
Joined: Mon Feb 23, 2004 4:11 am

Re: ከዶ/ር አብይ መሾም በኋላ የሀገራችን ፖለቲካ በ2 ምክንያቶች በጣም ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚሻ

Postby አባዊርቱ » Sat Jun 16, 2018 12:54 am

ወገኖቼ!!

የሰሞኑ የአገራችን ሁኔታ በጣም የሚያሳስብ በተለይም ይህ አርስት ወቅታዊና ተገቢም መነጋገሪያ የሆነበት ነው ብዬ አስባለሁ። ዶር አቢይ መልካም ስራ እየሰሩ የሚገኙ ግለሰብ ሆነው ነገሩ ግን ልቦናዬ ከምንጊዜም በላይ ደጀን የሚፈልጉበት ወቅት አሁን መሆኑ ይሰማኛል። በዚህ አጋጣሚ እንደኔው ቆባችሁን ሰቅላችሁ የተቀመጣችሁ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ጊዜው የደረሰ ስለሆነ በተጠንቀቅ እንድትቀመጡ በትህትና ላሳስብ እወዳለሁ። ዶር አብይ በጅቦች ተከቦ ያለ ሰው መሆኑን ተረድታችሁ አገራችንን ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንድትታደጉ በየዋሁ ህዝባችን ስም ጥሪዬን አቀርባለሁ። የኔው አይነት አባት አርበኛ በ አለማማጅነትና ካውንስሊንግ፤ እንደነ ካፒቴን ተሾመ ተንኮሉ አይነት ደግሞ ካስፈለገ በአብራሪነት እንኩዋ የሚሳተፉ እንደሚኖሩ እገምታለሁ። የምድር ጦሩ ባብዛኛው በአስተማሪነት፣ ካልሆነም በተዋጊነትና ደንብ አስጠባቂነት የሚተባበሩ ብዙ ናቸው። ጥሪው ብቻ ይድረሳቸው በይፋ!!. ህዝቡ በነቂስ ከኒህ እግዜር ቀብቶ ወደ ኢትዮጵያ ምድር ከላካቸው ሰው ጋር መሆን ይገባዋል። የ 27 አመቱን መከራ ያየ ጊዜው ሰውዬውን የማሽሙዋጠጫ ጊዜ አለመሆኑን ተረድቶ አካሄዱን ማሳመር የግድ ይላል። እንግዲህ ይህ ጥሪ አክራሪ ወያኔዎችን እንደማይመለከት ግልጽ ሲሆን፣ መቼውንስ ከመሃላቸው ጥቂት አገር ወዳድ መኖራቸውን ሳልዘነጋ ነው!!
ውድ ኦሮሞ ወገኖቼ!

ወያኔ የደነገጠ ድኩላ መሆኑን ተረድታችሁ ከመካከላችሁ በፍርፋሪ ቀፈታቸው እንደትግራዋይ ወያኔዎች የተቀፈደደ ኦሮሞ ወንድሞቻችሁ መኖራቸውን እንደማይጠፋችሁ በደንብ ታቃላችሁ። ዬትኞቹ ሆዳቸውና የሚቀመጡበት መኪና ሳይቀር ወደ ምድር የወደቀው ከርሳሞች የዋሁን ያገሬን ሰው ከሌላው ብሄር በተለይም ከአማራው ብሄር ለማናከስ ከ አለቃቸው ከወያኔ አሁንም እንደጥንቱ ያውም አብይ ጮራ ፈንጥቆ እያለ ደፋ ቀና ማለታቸውና ትግሉን ለማደናቀፍ መሞከራቸው አልቀረም! መቼስ መሞከር ከግብ ማድረስ አይደለምና ሙከራቸው የነ ለምዬን ትግል ትንሽም ቢሆን መጎተቱ አይቀሬ ነው። ይህ እንዳይሆን ኦሮሞው ወገኔ ነቅተሕ ደጅህን ጠብቅ። ታቃቸዋለህ እነዚህን ሆድ አደር አሳማዎች። ደግነቱ ቁጥራቸው በጣም ትንሽ ነው። ዛሬም እንደጥንቱ በዚህች ዋርካ መስኮት ለመናገር ላይ ታች የምለው፣ ኦሮሞና አማራ አንድ የሆነ ለታ ወያኔ አበቃለትን ነበር። ይህው እየታየም ነው። ገና ግን አላበቃለትም። አከርካሪው ግን ተሰብሮአል። ቅቅቅቅቅ
ማሳሰቢያ!
ጀግናው የኦሮሞ ቄሮ ሆይ! መቼስ ቄሮን ሳስብ ጄኔራል ጃገማ በልጅነታቸው ሌላው ቢቀር ፎቶአቸውና ገድላቸውን ያልሰማ አይኖሮም። ቄሮ ሆይ፣ አዲስ ከተቁዋቁዋመው የፋኖዎች ደጀን የብሄረ አማራ ንቅናቄ ጋር አንድነትህን አጥብቅ;። ድሮም ዛሬም በክፉም በደጉም፣ በመከራም በደስታም፣ በአምቻም በጋብቻም ከጎንህ የኖረውና የተዋለደው አማራው ወንድምህ መሆኑን አትዘንጋ። ዛሬ ወያኔ እንዲህ መላወሻ አጥታ ጭራሽ ለኢሃዴግ አቤቱታ ድረስ የበቃችው በዚሁ አስፈሪ ክስተት መሆኑን ለሰከንድ ያህል አትዘንጋ። የትግራይ ህዝብም ወገንህ ነው ምንም እንኩዋ መኖሩም አንዳንዴ ቢያጠራጥርህ። ከፍራቻ ነጻ የወጣ ለታ የልቡን ይነግረሃል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። እስከዛ ትግሬን በጅምላ ለመጥላት አትዘናጋ። ሁሉ ትግሬ ወያኔ አይዶለምና። እነዚህ የሰይጣን ውላጆች የሚፈልጉት (የወያኔን አመራር ማለቴ ነው) ይህንኑ ነውና። እንደው ምናለ የበሉትን መቼስ ትፉ ያለ የለም ተኝተው ዝም ብለው በለመዱት ጫታቸው ቢያወራርዱት?!! መቼስ እንዲህ የሚያቅነዘንዛቸው የሰሩት ሃጢያት እኮ ነው! ጉድ ያስብላል። ለምን ተቀፍደን ወህኒ አልወረድንም ይሆን እላለሁ አንዳንዴ። ሰውዬው ስራውን እንዳይሰራ ይህ ሁሉ ሳቦታጅ ምን የሚሉት ነው ወገኖቼ? እንደው በጣም የሚገርም ነው የሰው ልጅ ክፋት!!
ቄሮ ሆይ!
ሌላው የዚህች አብዲ ኢሌ የሚሉዋት ሰውዬ ጉዳይ እልባት ያስፈልገዋል። ወገናችን እስከመቼ በዚህች ሰውዬ ታምሶ እንደሚዘልቅ አይገባኝም። ለነቲም ለማ ደጀንነትህን በቃልም በተግባርም ላስቸኩዋይ ጥሪ ተዘጋጅ። ነሚቲን ባዬ ኑሚቴ ጂርቲ። አማዮሚቲ ሰሙኬኛራቲ ቴሴ ኑቲሮሪፍቲ? ኢቲያዲ ያ ቄሮቶ!!
ወድ ያገራችን መለዮ ለባሾችና አገር ወዳዶች!
የተጋረጠብን አደጋ ቀላል አለመሆኑን ትገነዘባላችሁ። ወያኔ ለ 27 አመታት ምንም እንኩዋ ስራዊታችንን አዋርዶና ስብናቸውን ገፎ ሁሉን ነገር ወደ አንድ ክልል ቢያተኩርም (ለዛውም የጠቀመው ይመስል ያንን ክልል)፣ አሁንም የቀድሞው ሰራዊት አባላት ገላችንና ቆዳችን ትንሽ ቢገረጣም፣ ወኔአችን እንዳለች ነችና፣በተለይም ለናት አገር በኢትዮጵያ አገራችን ስም ለሰላምም ይሁን ለሚያስፈልገው ማንኛውም መስዋእትነት ለመክፈል በተጠንቀቅ ተዘጋጁ። ዶር አብይም ይህንን ጥሪ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ያስተላልፉ። መቼውንስ ማስተላለፊያው ዘዴ ይጠፋዎታል ብዬ አልገምትም፣ በተልይም እርስዎን የመሰለ ኢንሳን የመሰለ መዋቅር ውስጥ ያለፈ ሰው ቀርቶ ማንም ይረዳዋልና። እንደው ደጀን ለመሆን ያህል እንጂ ህዝቡን እንደሆነ በፍቅር እያንበረከኩት ነው። የዛሬ ስንት አመት ህዝቡን በፍቅር ማንበርከክ ይቻላል፣ አዎ፣ ልበቀና ወያኔዎችንም ጭምር ብዬ በነበረበት ወቅት ተስቆብኝ ነበር እዚሁ ቤት። እድሜ መስታወት ነውና እየሆነም ያለው በዶር አብይ ዪህው ነው። ቅቅቅ ፈጣሪ ምስጋና ይግባውና። የሰይጣን ሃይላትን ግን መናቅ ሞኝነት ነውና፣ ወገን ጠንቀቅ በል። አላስፈላጊ ትችትን ወደሁዋላ በማቆየት ሰውዬውን እንዴት እንደምንረዳ ማሰብና ማወራረድ አለብን። ሰዎቹ የአገራችንን ካዝና ማራቆታቸውን ያወኩት በተጨባጭ ዛሬ ነው። 3 ቢልዮን ዶላር ቀላል ባይሆንም 1 ቢልዮኑ ለአስቤዛ 2 ቢሊዮኑ ደግሞ ለመውተርተሪያ ከ ኤሚሬቱ አልጋወራሽ በደስታ ሲቀበሉ ሥሰማ ምን እንደሚሰማችሁ ለመገመት አያዳግትም። እግዜርም ይታደጋቸው ኤሚሬቶችን። ጉዳዩ ግን ላስተዋለው እጅጉን ያሳዝናል። ወያኔው የዘረፈውና ያዘረፈው ከዛ በላይ ነውና። ኤፈርት ጉያ ስር ያለው ጊዜው ሲደርስ እንደሚመለስ ልቦናዬ ቢነግረኝም፣ ዶር አብይ ያሉበትን ሁኔታ መገመት ግን አስቸጋሪ አይሆንም። ፈጣሪ ይጨመርበት እንጂ ያገራችን ፈተና ገና ብዙ ነው።
አባዊርቱ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 800
Joined: Mon Feb 23, 2004 4:11 am

Re: ከዶ/ር አብይ መሾም በኋላ የሀገራችን ፖለቲካ በ2 ምክንያቶች በጣም ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚሻ

Postby እሰፋ ማሩ » Sat Jun 16, 2018 4:00 am

አባ ዊርቱ ሃርካ ፉኔ
ድሮም ታላቆቹ ሁለቱን ብሄሮች ሰረገኛነት በዶ/ር አብይ ሳይነገረን በፊት የተነበይክ መሆንህን አስታውሳለሁ፡፡ሰሞኑን የወይኔ ርዝራዦች ህዝባችንን የማባላት ተንኮላቸውን ያጋለጠ መጣጥፍ ቀጥሎ ይነበባል፡፡ይህን ማባላት የወያኔው መሪ 'ኦሮሞና አማራ ከተስማማ ወያኔ ያልቅለታል' ያለው ተግባራዊ ሆኖ ወያኔ በመቀበር ላይ ነው ጌታ ያፍጥንልን፡፡
--------------------------=====================================----------------------------------------
ጠ/ሚ አብይ “ሊያባሉንና ሊያጫርሱን ለተዘጋጁት የቀን ጅቦች እድል ልንሰጣቸው አይገባም" ማለታቸውን በመጥቀስ "#እነማን_ናቸው_ጅቦቹ?" የሚል ጥያቄ ሳይ ሞባይሌን ወርውሬ ለመስበር ትንሽ ይቀረኛል፡፡ በዚህ ሰዓት ፈርቶ እንዲህ በኮድ የሚያወራ ሰው መኖሩን ሳስብ ቅጥል ያደርገኛል፡፡ ቆይ እዚህ ሀገር ስንት #ሰው_በላ ጅቦች አሉ?? በስም #ህወሓቶች ይባላሉ! በዝርዝር አያጅቦ እና ግልገል ጅቦች ይባላሉ! (ግልገል ጅቦች የአያጅቦን ትርፍራፊ የሚለቃቅሙ ውጫጮች ናቸው!!)
አያ_ጅቦ1: ጌታቸው አሰፋ
አያ_ጅቦ2: ስብሃት ነጋ
አያ_ጅቦ3: አባይ ፀሓዬ
አያ_ጅቦ4: ስዩም መስፍን
አያ_ጅቦ5: ደብረፂዮን ገ/ሚካሄል

…ይቀጥላል!

ግልገል ጅብ1: ዳንኤል ብርሃኔ፣
ግልገል ጅብ2: ፍፁም ብረሃኔ
ግልገል ጅብ3: ሰናይት መብርሃቱ
ግልገል ጅብ4: ዳዊት ከበደ
ግልገል ጅብ5: ሚሚ ስብሃቱ
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1550
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm

Re: ከዶ/ር አብይ መሾም በኋላ የሀገራችን ፖለቲካ በ2 ምክንያቶች በጣም ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚሻ

Postby አባዊርቱ » Mon Jun 18, 2018 10:07 pm

ሃርካፉኔካ ኦቦሌቻኮ!! ኡልፋዱ ለሚቶ!
አዎ የኔ ወንድም ብዙ ብለንም ደክመንም ነበር በውነቱ። የኒህ አብይ ሰውዬ ጉዳይ እጅግ በጣም የሚገርምና እውነትም ኢትዮጵያ መከራዋ ያበቃ መስሎ ይታየኛል። ተመልከት ወንድሜ፣ ጅቦች መሃል ሆኖ ጅብን ጅብ የሚል ደፋር መሪ፣ ያውም ዝምታ ወርቅ ሆኖ እንጂ ብዙ ግልገል ጅቦችም መኖራችሁ አልጠፋኝም የሚል ጀግና!!! አይኔን እስኪያመኝ ድረስ የዛሬውን የፓርላማ ንግግር ከአንዴም ሁለቴ በዩቱብ መስኮት ሰማሁት! አጃኢባ ረቢ ያሰኛል በውነቱ! እንደው የወለዱት እናቱና በመፈጠሩ የታደለችው የኢትዮጵያ አምላክ ከክፉ አይን ይጠብቀው አቦ! እንዲህ አይነቱን አይምሮ ለመሪነት ህይወቴ ሳያልፍ ማየቴ ምነኛ እድለኛ መሆኔን እገምታለሁ! እንዴት አይነቱ አንጀት አርስ ሰው ነው እባካችሁ!!!! አንዲት የወያኔ ሴትወይዘሮ የፓርላማ አባል(በገጽታቸው እንደማየው፣ ከይቅርታ ጋር) እንደው አወኩ ብለው ከባድ ጥያቄ የጠየቁት መስሎዋቸው ደህና አድርጎ እሳቸውን ተገን አድርጎ ጅቦቹን ደቁሶአቸው አንጀቴን አራሰው!! ቅቅቅቅቅ
ሌላው የድንበር አልባነት ጉዳይ ነው ። ይገርማል፡ ቪዝነሪ ይሉሃል ይህ ነው። እኔ ተቃዋሚ ብሆን ጥሪም አልፈልግም። በተለይ በሙያው አለም ብዙ ልምድ ያካበትን ወገኖች እንደው በኢትዮጵያ አምላክ አገራችንን አሁን ነው መታደግ የምንችለው። ብዙ ጡረተኞች አለን ምንም ሳንፈልግ ከአገሪቱ በሙያ ብቻ በበጎአድራጎትነት መሳተፍ የምንችል ወገኖች። ይቺን ቀን ነበር ለማየት አምላኬን ሌት ተቀን የምለምነው ለብዙ አስርተ አመታት። ይህንን ብርቅዬ ሰው ሁሉ ሰው እንደኪሱ ሞባየል መንከባከብ የግድ ነው።
ወያኔዎች ሆይ!
አበቃ ወገኖቼ! ኦሮሞን ከአማራው በማባላት ብቻ ነበር እስካሁን የሰነበታችሁት። ሌላ ተክናችሁት የተለየ ሳይንስ ከጫካ ይዛችሁት የመጣችሁት ነገር የለም ወገኖቼ!! ያ ጊዜ አከተመ! እናሳ? እባካችሁ አደብ ገዝታችሁ ተባበሩት። ወይንም አፋችሁን ዘግታችሁ፣ መሰሪነታችሁን ትታችሁ ታዘቡት እስቲ። ባለፈው ፓርላማ እንዳስተማራችሁ ሁሉ። ጉደኛ መሪ እኮ ነው ያገኘነው። አለበለዚያ ከምኑም ሳትሆኑ ብኩን ሆናችሁ ትቀራላችሁ። በተለይ የዛሬውን ስለትግራይ ዶክተሩ የተናገረውን የሰማ ትግራዋይ፣ ድሮም ድሮ ነው፣ ዛሬማ የየጅብ ጅራታችሁን ይዞ ለአቢይ ያስረክባችሁዋል እንኩዋንስ እንቁላሉዋን ታቅፋ እንደምታሞቅ ዶሮ ሊያቅፋችሁ ቀርቶ። አብይ ደግሞ ወደ ታስሮ የወጣ ህዝብ እንዳይጥላችሁ ነው ስጋቴ እንጂ እሱ እንኩዋ የበቀል አንጀት የለውም!! ዋ!!! አጉል እብሪታችሁ እናም የየብሄራት ትንኮሳችሁን አቁሙ!! እስቲ ለጥቂት ጊዜም ቢሆን የበላችሁትን አወራርዱት!! የስኩዋሩም፣ ኩላሊቱም፣ ጉበቱም ህመም እኮ በቅጡ የሚስተናገደው አገር ሰላም ሲሆንና ውጭ የተቀመጠውም ገንዘብ ሴፍቲ ሲኖረው ነው። ሰውዬው ከባድና በጣም ብልህ ነው። የኢትዮጵያ አምላክ የህዝቡን በደል ሁሉ አይቶ አጥንቶ ፈርዶና ወስኖ ነው ስውዬውን የላካቸው። ሞኝ አትሁኑ! የኛ ሰው ቶሎ ይረሳል። ያውም በዚያ ሙዚቃችሁ እመር እመር ብትሉበት ልቡን አማላችሁ ያደረሳችሁበትን ስቃይ ረስቶ ቁጭ ብሎ እናንተው ያደረሰባችሁትን በደል ለናንተው እዬዬ የሚል ህዝብ እኮ ነው ያለን ወገኖቼ! ግፍም ልክ አለው። የናንተው እንደምትረግጡት አመድ (ጅቦችም ናችሁና) የወረደ ነው። ይታሰብበት ወገኖቼ!
ትግራይ ኦንላይን ሆይ!
መቼስ አሜሪካ እየኖራችሁ ፊደል ቆጥራችሁዋል ብዬ አስባለሁ። ድሮስ የጥቅሚቲ ጉዳይም አለና ተመላልሶ መቀራመቱም ነበርና ይቸግር ይሆናል። እንደው ግን ሃቁን ላለማየት ነው እንዲህ መከራ የምትበሉት ወይስ ያጨለመባችሁ ነገር አለ?? ያ ጀዋር ባለፈው መቼስ እንደው በጣም ነው የነገራችሁ። ጃዋር በኢትዮጵያ አቁዋሙ አይጥመኝም ነበር ሲጀምር አካባቢ። አሁን ግን የኦሮሞ ችግር ምን እንደሆነ በደንብ የገባው ይመስለኛል። ጀባዱ ጃዋር። ትግራይ ኦንላይን እድምተኞች ግን ታዘብኩዋችሁ። ለትግራይ ነው ወይስ ለጅቦቹ ነው የምትፋለሙት? እረ ተው፣ ተመለሱ ወደ ገራገሩ ትግራዋይ! ባለፈው አቶ አንዳርጋቸውም ትግራዋይን ሲገልጣቸው ማን ያላለቀሰ ወገን አለ?? ያሳዝናል የናንተ እንዲህ መራወጥ። ያሳፍራልም። ለጅቦቹ ጥብቅና መቆማችሁ ነው ያሳዘነኝ በስመ ትግራይ ህዝብ። አሁንም አልነጋም ወደህሊና ለመመለስ!!! ተመለሱ ወገኖቼ!!!!
ትንብያ!
ዶር አቢይ በቅርቡ ከኤርትራው መሪ የወንድማማችነት ጥሪ ይደርሰውና አስመራ ደማቅ አቀባበል ይደረግለታል! እኔ ጅቦቹን ብሆን፣ እሰጋለሁ። መሄጃ የለም ጅቦች ወገኖቼ! አካሄዳችሁን በፍጥነት አስተካክሉ! ቶሎ ለፍቅር እጅ ስጡ!


ለኤርትራውያን!
ሰውዬው ምንድነው የሚጠብቁት?? መካሪ የለም እንዴ?? አብይ ጊዜና ትግስት የላቸውም! ሃይ በሉዋቸው እንጂ!! ሶማሌ ሂደው ሲተቃቀፉ ኤርትራ ምንድነው የምትጠብቀው?? ወገኖች እኮ ነን! አይ ሃቭ ኤ ድሪም አሉ ማርቲን!! ይታየኛል መልካም ነገር!! አምላክ ይጨመርበት እንጂ!! እዚህ ላይ አቶ ኢሳያስ ቆፍጠን ያሉ መስሎዋቸው ከሆነ ከአብይና ለማ ወድያ ቆፍጣና ላሳር ነውና ይልቅዬ የተዘረጋውን ቆንጅዬ እጅ ቶሎ ለቀም ማድረጉ ብልህነት መሰለኝ!!
ኤታማዦር ዊርቱ!፣ የጥንት የጠዋቱ!!
አባዊርቱ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 800
Joined: Mon Feb 23, 2004 4:11 am

Re: ከዶ/ር አብይ መሾም በኋላ የሀገራችን ፖለቲካ በ2 ምክንያቶች በጣም ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚሻ

Postby እንድሪያስ » Wed Jun 20, 2018 9:23 am

የዶ/ር አብይ የፓርላማ ውሎ - አጭር ቅኝት;
Summary,

"የህዝብን የለውጥ ጥያቄ በፌዴራል ሥርዓቱ ላይ የተቃጣ ጥቃት ነው የሚሉ የአገዛዙ ሰዎች አሉ" መሐመድ ቦልኮኦ; ከአፋር ክልል የተመረጡ የፓርላማ አባል።

"አፍሪካ ውስጥ ለመንቀሳቀስ ቪዛ ይቅር እያልን; ከክልሌ ውጡ የሚለው ማነው? አዋሳ ላይ ወላይታው በነፃነት በማይንቀሳቀስበት አገር እንዴት ነው ሌላው አፍሪካዊ እዚህ አገር መጥቶ ገንዘቡን የሚያፈስሰው?" ዶ/ር አብይ አህመድ

"የባድመን ጉዳይ ለፖለቲካ ፍጆታ የሚያራግብ ኃይል ምን ያህል የሞራል ልዕልና እንዳለው አላውቅም"

"በባድመ ላይ አልተወያዬንም የሚባለው; በአሰብ ጉዳይ ላይ ተወያይተናል እንዴ?"

"ባድመ ላይ ብዙ ወንድሞቻችን ሞተዋል ይባላል። እውነት ነው ብዙ ሰው ሞቷል። ግን ፋላሲ አለው። አሰብ ላይ የሞተው ኢትዮጵያዊ አይደለም እንዴ?"

"የፀረ ሽብር; የፀረ ሙስና እና የወንጀል ህጎች ተጥሰዋል። በሽብርተኝነት; በሙስና እና ሰው በመግዴል የተከሰሱና የታሰሩ ሰዎች ከህግ አግባብ ውጭ ተፈትተዋል" ከትግራይ የተመረጡ የፓርላማ አባል።

"ይልቁንስ የደህንነት;የመከላከያና የፖሊስ ኃይሉ ዜጎችን በጨለማ ቤት በማሰር; በመግረፍና በማሰቃየት የሽብር ተግባር ፈፅሟል።

"ሁሉም አገሩን ይወዳል; ለአገሩ ይቆረቆራል። እኛ ብቻ አይደለንም የምንቆረቆረው። የኛ ድርሻ ሁሉንም ሊያሳትፍ በሚችል መልኩ ሜዳውን ማስፋት ነው።

"ሙስናን እንዋጋለን ስንል ከሥር ከሥር እያቆጠቆጠ ነው። ምክንያቱም እኛ ግንዱን ትተን ቅርንጫፉ ላይ እየተረባረብን ነው። ከምንጩ ነው ማድረቅ ያለብን።

"የመንግሥት ሥልጣን ይዞ ሀብታም መሆን አይቻልም። ሀብታም መሆን ከፈለገ ሥልጣኑን መልቀቅ አለበት። አለዚያ ግን እጃችሁን መሰብሰብ አለባችሁ።

"እስራኤል ፓርላማ ውስጥ የሀገሪቱን ጥቅም የሚቃረንና የግዛት ሉኣላዊነቷን ጥያቄ ውስጥ የሚያስገቡ ቡድኖች ጥግ ጥጋቸውን ይዘው ይከራከራሉ።

"ኢትዮጵያም ውስጥ ያለውን እውነት መካድ አይቻልም። ቢያንስ የማንፈልገውን ሀሳብ መስማት አለብን። ከዚያም በድምፅ ብልጫ ውድቅ ይደረግ።

"ህወሓት የትግራይ ህዝብ አይደለም። የትግራይ ህዝብ መደገፍ ያለበት ድሀ ህዝብ ነው።

"አሁን ህዝብ የሚፈናቀልበት ችግር መንስኤ ጥላቻ ነው። ይሁንና ኪሳራው ለተባራሪው ብቻ ሳይሆን ለአባራሪውም ጭምር ነው። ይህ አዝማሚያ ለማንም አይበጅም።

"እኛ ስንዋደድ; እኛ አንድ ስንሆን ዓለም ያከብረናል" ዶ/ር አብይ

"ህዝብን በማፈናቀል ከሚፈጠረው ቀውስ ፖለቲካዊ ትርፍ እናገኛለን በሚል ችግሩን ከኋላ በሚቆሰቁሱና በሚያባብሱ ኃይሎች ላይ ምን እርምጃ ይወሰዳል?" ወ/ሮ አሚናት የተባሉ የፓርላማ አባል

"የኢትዮጵያ ሀብት ተዘርፎ በውጭ ሀገራት ተከማችቷል። ሌቦቹ ያልታወቀባቸው መስሏቸው ሌላ ሴራ ሲሸርቡ እያዬን ነው። ነገር ግን ውጭ አገር ስላከማቹት ሀብት ተጨባጭ መረጃ አሰባስበን ለፍትህ እናቀርባቸዋለን።

"የፍትህ ሥርዓቱ ከፍተኛ ችግር ያለበት ነው።

"ጎረቤት አገሮች ላይ የጦር ሰፈር መገንባታቸው አይገርምም። የሚገርመው ሐረርና ጅጅጋ ላይ አለመገንባታቸው ነው። እኛ የሚያሳስበን የክልል ድንበር ጉዳይ ነው። የአፍሪካ ቀንድ ቀጠና ጉዳይ አያሳስበንም" ዶ/ር አብይ

ሰውዬው ያ "መለስ" የዘራውን አቀንጭራ አረም እየነቃቀለ ነው። አንዳንዱ አረም ግን እጅ ላይ እያሙለጨለጬ ለመንቀል እያስቸገረው ይመስላል። እንግዲህ አላህ ብርታቱን ይስጠው!
እንድሪያስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1784
Joined: Fri Mar 19, 2004 10:55 pm
Location: *****

Re: ከዶ/ር አብይ መሾም በኋላ የሀገራችን ፖለቲካ በ2 ምክንያቶች በጣም ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚሻ

Postby አባዊርቱ » Wed Jun 20, 2018 5:01 pm

ወንድሜ እንድርያስ! አይገርምህም የዚህ ጀግና ሰውዬ ስራ?? ማን አሰበው እንደው በዚህ ትውልድ እነዚህ ሰዎች እንዲህ ይሆናሉ ብሎ የጠበቀ? የኔ ምኞት ምን እንደሆነ ታቃለህ? ኤርትራና ኢትዮጵያ ህዝባዊ አንድነት ፈጥረው (አገራዊ ልዩነታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ፣ እንደኔ አንድ ሆነን በእንደራሴ ቢተዳደሩ ማንነታቸው ተጠብቆላቸው ደስታዬ ወሰን የለውም) ሁላችንም እንደልባችን አስመራና አዲሳባ እየተመላለስን እንድንኖር ነው። አቶ ኢሳያስ ዘገዩ ብዬ ነበር፣ ዛሬ ግን መልካም መልስ ሰጥተዋል። አላወቁትም እንጂ ህዝቡን እንዴት እንደምናፈቅረው ቢያውቁት እስካሁንም ባልቆዩ ነበር። ወያኔ ቢሆንለት ከምናመልከውም አምላክ ያለያየን ነበር እንኩዋንስ ከህዝብ። ለነገሩም ቢያለያየንም ነው የጫት ገራባ ጥርቅም ያደረገው አገራችንን። እረ እነሱንስ ክፉ ሳይነካቸው ፍቅር ምን እንደሆነ፣ ወገን ሲፋቀር ምን መስራት እንደሚችል ባይናቸው ሳያዩ አይግደላቸው አቦ። የምመኝላቸው ነገር ቢኖር፣ መቼውንስ ክፉ የስራውን አያጣምና፤ በስኩዋር፣ ኩላሊት፣ ጉበት ሲሰቃዩ የኢትዮጵያ ደጋግ ነርሶችን ፍቅርና እንክብካቤ ባይናቸው አይተው እስከወዲያኛው እየተቃጠሉ ቢሰናብቱ ደስታውን አልችለውም!! ከምሬ ነው የኔ ወንድም! የሰው መከራ እንኩዋ ማየት አይመቸኝም እንደው ቅጣት ቢሆን ብዬ ነው ከሚታሰሩና ከሚገረፉ። እንኩዋን ደስ አለን የኔ ወንድም!
ኤታማዦሩ ነኝ
አባዊርቱ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 800
Joined: Mon Feb 23, 2004 4:11 am


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests